West Gondar Police

West Gondar Police Peace For All

በመተማ ወረዳ ዘውዴ ባድማ ንዑስ ቀበሌ የአካባቢውን ሰላም አስጠብቆ ለማስቀጠል ከኗራዎች ጋር ውይይት ተካሄደ።መተማ ሐምሌ:21፣2015 ዓ.ም በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ዘወዴ ባድማ ን...
28/07/2023

በመተማ ወረዳ ዘውዴ ባድማ ንዑስ ቀበሌ የአካባቢውን ሰላም አስጠብቆ ለማስቀጠል ከኗራዎች ጋር ውይይት ተካሄደ።

መተማ ሐምሌ:21፣2015 ዓ.ም በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ዘወዴ ባድማ ንዑስ ቀበሌ አካባቢውን ሰላም አስጠብቆ ለሞጠል ብሎም አጋች እና ሌባ በማስወገድ ህብረተሰቡ እንዴት በሰላም መኖር እንደሚችል ከኗሪዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል።

መድረኩ በአካባቢው የሚንቀሳቁ አጋችና ሌባ ለማስወገድ ህብረተሰቡ ተባባሪ እንዲሆን እና የአካባቢውን ሰላም ለማስፈን ያለመ ውይይት ነው።

ባለፉት አራት አመታት አካባቢያችን ብዙ ፈተናዎችን ያሳለፈ ሲሆን በወቅቱ ብዙ ዋጋ አስከፍሎና ከዚያ በኃላ አካባቢያችን ከህብረተሰባችን ጋር ተባብረን ሰላም ማድረግ ብንችልም አሁን ላይ ቀጠናችን ሰላም እንዳይሆን በሚፈልጉ አካላት እየተፈተነ እንደሚገኝ የመተማ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ ሞገስ አስረድተዋል።

ከዚህ በፊት ጠላቶቻችን አማራና ቅማንት የሚል የብሔር ሽፋን በመስጠት ህብረተሰቡን ለችግር እንዳጋለጡት ያነሱት አስተዳዳሪው የነበረው ችግር እንዲደገም የሚፈልጉ አካላት በዕገታ ስም የብሔር ግጭት እንዲፈጠር እየጣሩ ይገኛሉ ብለዋል።

ሌባ እና ሽፍታ ብሔር የለውም ጥቅም ፈላጊ እንጂ ያሉት አስተዳዳሪው ህዝባችን ሊነቃ ይገባል፣ እርስ በእርስ ሊያበላሉን የተነሱትን ሀይሎች ላይ በጋራ ማፅዳት አለብን ብለዋል።

አካባቢያችን እንዴት ሰላም አድርገን አልምተን መጠቀም እንዳለብን የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶችና ወላጆች እንዲመክሩ የጠየቁት አቶ ደሳለኝ እኛ ለሰፊው ህዝብ ሲባል ከጥፋት ለሚመለሱ አካላት በራችን ክፍት ነው ብለዋል።

የምዕራብ ጎንደር ዞን ሰላምና ደህንነት መምሪያ ም/ኃላፊ አቶ ጋሻው አለማየሁ እንደገለፁት ችግሮችን ከምንጩ ማምከን ምንችለው ሁላችንም እኩል ስራ መስራት ስንችል መሆኑን ተረድተን አጋችንና ሌባን ከምንጭ ለማድረቅ መነሳት አለበት ብለዋል።

ህብረተሰባችን ሌባ ጠል ሊሆን ይገባል ያሉት ም/ኃላፊው አንዷ ጣታችን ከተጎዳች እጃችን እንደሚጎዳው ሁሉ ህብረተሰባችን በትንሽ ፅንፈኛ አካላት ወደ ከፋ ችግር እንዳይገባ ከውስጡ ያሉትን
አረሞችን ሊያፀዳ ይገባል ብለዋል።

በቀጠናችን ባለፈው ጊዜ በተፈጠረው ችግር የደረሰበትን መፈናቀልና ጉዳት ልንረሳው አይገባም ያሉት አቶ ጋሻው ለአጋች ምግብና መረጃ የምታቀብሉ እና ሌባን የምታስጠጉ አካላት ከድርጊታችሁ ተቆጥባችሁ ለአካባቢያችን ሰላም የበኩላችሁን ልትወጡ ይገባል ብለዋል።

አካባቢያችን እየተፈተነ ያለው በትንሽ ጥቅመኞች ፍላጎት እንደሆን የተናገሩት የመተማ ወረዳ ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መላኩ ሞላ ህብረተሰባችን በመናበብ አስፈላጊውን መረጃ በመያዝ ስርዓት የሚይዘውን አካል ስርዓት ለማስያዝ ተቆራርጠን እየሰራን ነው ብለዋል።

ገበሬው አርሶ መብላትና ሰርቶ ልጆቹን ማሳደግ ይፈልጋል ትንንሽ ሀሳብ ባላቸው አጋቾች አካባቢያችን ሰላሙ ሊደናቀፍ አይገባም ብለዋል።

የጠላት አላማው ህብረተሰቡን እርስ በእርሱ በማጋጨት
ሰላምን በማደፍረስ እና የልማት እንቅስቃሴዎችን ማደናቀፍ ነው ያሉት ኃላፊው አካባቢውን በጋራ መታደግ አለብን ብለዋል።

በመድረኩ የተገኙት ተሳታፊዎች መካከል ወጣት ስመኘው ጥጋቡ እኛ የምንፈልገው ሰላምና ልማት ነው፣ ሌባው የማን ቤተሰብ እንደሆነ ከማጋለጥ ባሻገር ከፀጥታ አካላት ጋር አስፈላጊውን ስምሪት በመወጣት አካባቢያችን እንጠብቃለን ብለዋል።

ሌላው የቀበሌው ነዋሪ አቶ ሻበል ጥጋቡ ነዋሪ እኛ ከመንግስት ጎን እንጅ ከሌባ ግንኙነት እንፈልግም ይኸን ሽፋን አድርጎ አማራ ቅማንት የሚል አንቀበልም ብለዋል።

በመጨረሻም በመድረኩ የተሳተፉት ነዋሪዎች አጋችና ሌባን ጨምሮ ተባባሪ፣ የመረጃና የስንቅ አቀባይ ናቸው ያሏቸውን አካላት አጋልጠዋል።

✅ መረጃው:የመተማ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ነው።

10/06/2023
የትዳር አጋሩን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ፖሊስ በ 20 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ!ተከሳሸ ረዳት ሳጅን መኳንንት ብርሃኑ በምዕራብ ጎንደር ዞን አዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት የፖሊስ አባ...
07/06/2023

የትዳር አጋሩን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ፖሊስ በ 20 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ!

ተከሳሸ ረዳት ሳጅን መኳንንት ብርሃኑ በምዕራብ ጎንደር ዞን አዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት የፖሊስ አባል ሲሆን ሚያዚያ 18 ቀን 2015 ዓም በግምት ከምሽቱ 2: 00 ሲሆን ነጋዴ ባህር ከተማ ከሚኖርበት ቤት የትዳር አጋሩ የሆነችውን ረ/ሳጅን ልክነሽ የትነበርክን በትዳራቸው በነበረ አለመግባባት ምክንያት በያዘው የጦር መሳሪያ በሰደፍ አንገቷን መትቶ እንድትወድቅ በማድረግ ጀርባውን በተደጋጋሚ በጥይት ተኩሶ በመምታት እንድትሞት አድርጓል።
የአዳኝ አገር ጫቆ ፖሊስም ምርመራውን አጣርቶ ለዞን ዐቃቤ ህግ የላከ ሲሆን ዐቃቤ ህግም የኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 539( 1-ሀ) በመጥቀስ በምዕራብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በከባድ የሰው ግድያ ወንጀል ክሰ በማቅረብ ሲከራከር ቆይቷል።

ተከሳሽም ወንጀሉን አልፈፀምኩም ብሎ የተከራከረ ቢሆንም ፍ/ቤቱ የዐቃቤ ህግን ማስረጃ ከሰማ በሗላ ዐቃቤ ህግ እንደክሱ ስላስረዳ ተከሳሹ የዐቃቤ ህግን ክስ እንዲከላከል እድል ቢሰጠውም የመከላከያ ምስክር የለኝም ስላለ ጥፋተኛ ተብሏል።

የምዕራብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትም የዐቃቤ ህግን እና የተከሳሹን የቅጣት አስተያየት ካዳመጠ በሗላ ዛሬ በቀን 30/ 09/2015 ዓም በዋለው ችሎት ተከሳሹንና ሌሎችን መሰል የወንጀል ድርጊት የሚፈፅሙ ግለሰቦችን ያስተምራል ያርማል ያለውን #የ20ዓመት #ፅኑ እስራት ቅጣት ወስኖበታል።

መረጃው የምዕራብ ጎንደር ዞን ፍትህ መምሪያ ነው
30/09/2015 ዓም

24/05/2023

"እናትነቴ ከፖሊስነቴ በለጠብኝ" ፖሊስነት ሰብአዊነት

መሬት ላይ ተጥሎ የተገኘን የአንድ ወር ህፃን ለማትረፍ የሞከረችው ረዳት ሳጅን
በድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 09 ገንደ-ገራዳ ድልድይ አንድ ነገር ተፈጠረ፡፡ ገና አንድ ወር የሆነው ህጻን ተጥሎ እሪታውን ቢያሰማም ሰሚ ያገኘው ግን ሰአቱ ገፍቶ ምሽት ላይ ነበር፡፡

በአካባቢው የህጻን ድምጽ የሰማችው የአካባቢው ነዋሪ ወ/ሮ ፋጡማ ድምጹን ፦ወደ ሰማችበት ድልድይ ስር ስትሄድ ያገኘችው ነገር እጅግ እንዳስደነገጣት ትናገራለች፡፡

አንድ ወር ገደማ የሚሆነው ህጻን በጨርቅ ተጠቅልሎ ድረሱልኝ እያለ እሪታውን ያሰማ ነበር ፡፡ የተጣለውን ህጻን እንዳየችው በእናትነት ፍቅር ከወደቀበት አንስታው ወደ ቤት ይዛው ትሄዳለች ነገር ግን ይዛው የሄደችው እናት የምትሰጠው ነገር አልነበራትም እናም ለሊቱን ያለምንም ጡት በቤቷ ያሳልፋል፡፡ ግለሰቧ ወድቆ ያገኘችውን ህጻን ለፖሊስ ለመስጠት በማለዳ ነበር የደረሰችው ፖሊስ ጣቢያ፡፡

የፖሊስ መሬት ፖሊስ ጣቢያ መርማሪ ረ/ሳ ቤተልሄም ምትኩ ግለሰቧ በመጣች ወቅት በስራ ገበታዋ ላይ ነበረች፡፡"ልጁን ሳየው ውስጤ ተረበሸ" የምትለው ረ/ሳ ቤተልሄም "በወቅቱ ህጻኑ ምንም ምግብ ባለመመገቡ ተዳክሞ ነበር" ትላለች። "እናም የሆነ ነገር እንዲሰጠው ብጠይቅም ይዛው የመጣችው ግለሰብ ምንም ነገር እንደሌላት፤ ለሊትም ምንም ጡት እንዳልጠባ ነገረችኝ" በማለት አክላ "ይሄ ልጅ አይናችን እያየ ህይወቱ ማለፍ የለበትም" ያለቸው ቤተልሄም "እናትነቴ ገፍቶኝ ለህጻኑ ጡት ማጥባት እንዳለበኝ አሰብኩኝ እናም አጠባሁት ወዲያው ልጁ ብርታት አግኝቶ ነቃ" ትላለች፡፡

የሁለት ዓመት ሴት ልጅ እንዳላት የምትናገረው ረ/ሳ ቤተልሄም ምትኩ ልጄን ጡት እያጠባኋት በመሆኑ ይሄ አጋጣሚ ሲከሰት ለህጻኑ ጡቷን ልታጠባው እንደቻለች ተናግራለች፡፡

በአሁኑ ወቅት የተገኘው ህጻን በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኝና ፖሊስ ጉዳዩን እያጣራ መሆኑ ከድሬዳዋ ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።
በጀግንነት መጠበቅ- በሰብአዊነት ማገልገል !!

ወላጆች የተሰረቀች ልጃቸውን በልመና ሥራ ላይ አገኙሕፃን ረድኤት ዘሩ የሦስት ዓመት እድሜ ታዳጊ ስትኾን በደሴ ከተማ ሆጤ ክፍለ ከተማ 07 ቀበሌ ከጓደኞቿ ጋር እየተጫወተች ባለበት ጊዜ ሰኔ ...
24/05/2023

ወላጆች የተሰረቀች ልጃቸውን በልመና ሥራ ላይ አገኙ

ሕፃን ረድኤት ዘሩ የሦስት ዓመት እድሜ ታዳጊ ስትኾን በደሴ ከተማ ሆጤ ክፍለ ከተማ 07 ቀበሌ ከጓደኞቿ ጋር እየተጫወተች ባለበት ጊዜ ሰኔ 12 ቀን 2014 ዓ.ም ነበር ባልታወቁ ሰዎች የተወሰደችው።

በደሴ ከተማ አስተዳደር 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ የሴቶችና ሕፃናት ክፍል ኀላፊ ምክትል ኮማንደር ማንጠግቦሽ ደሴ ከሥራ ሲመለሱ ነበር የልጃቸውን መጥፋት የሰሙት።

በሁኔታው የተደናገጡት የረድኤት ቤተሰቦች በጊዜው ፍለጋ ቢያደርጉም ሊያገኟት አልቻሉም ነበር። በቀጣይ ቀናቶች በራዲዮና በተለያዩ ማስታወቂያዎች የማፈላለጉን ሥራ ቢሠሩም ሕፃን ረድኤትን አየሁ የሚል ጠፋ። የአካባቢው የፀጥታ ኀይልና የአካባቢው ነዋሪ ፍለጋውን ቢያጠናክርም የሕፃኗ ጉዳይ የውኃ ሽታ ሁኖ ቀረ። ቀናት ቀናትን እየወለዱ ወራት በወራት እየተተኩ ለአስራ አንድ ወር ያክል ሳትገኝ ቀረች።

አባት ዘሩ ሰይድ እና እናት ምክትል ኮማንደር ማንጠግቦሽ ደሴ የልጃቸው ጉዳይ ተስፋ የሚሰጥ ባለመኾኑ ቅስማቸው ተሰብሮ በቤታቸው ተቀመጡ። ጉዳዩ በመጨረሻም በከንቲባው ጽሕፈት ቤት ከተያዘ በኋላ እንደ አማራጭ በማኅበራዊ ሚዲያ ዳግም ልጅቱን የማፈላለግ ሥራ መሥራት ተጀመረ። በዚህም በደሴ ከተማ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንና በደሴ ብልጽግና ፓርቲ ይፋዊ የፌስቡክ ገጾች የአፋልጉኝ ማስታወቂያ ከሕፃኗ ፎቶ ጋር ተያይዞ ተለጠፈ።

ጉዳዩን የተመለከቱ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ለበርካታ ሰዎች ማጋራታቸውን ተከትሎ ከአዲስ አበባ ግንቦት 12 ቀን 2015 ዓ.ም ልጅቱን አየሁ የሚል ጥቆማ ተሰማ። በእናት ማንጠግቦሽ ደሴ የተደወለ ስልክ ልጅቱ አዲስ አበባ እዳለችና በቦሌ ክፍለ ከተማ አካባቢ ለወራት ያክል ለልመና አንዲት ሴት እየተጠቀመችባት እንደኾነ ተነገራት። ይህ ጥቆማ ለወራት የልጃቸው መጥፋት ሀዘን ለገባቸው ቤተሰቦች ተስፋን የሰጠ ነበር።

የልጅቱም ቤተሰቦች አዲሰ አበባ ለሚያውቋቸው ሰዎች ስለጉዳዩ በማስረዳት ሕፃን ረድኤት ዘሩንና እየለመነችባት ነው የተባለችው ግለሰብ እንድትያዝ በስልክ ተናገሩ። ዳዩን ለአካባቢው ፖሊስ ካሳወቁ በኃላ ግለሰቧ በቁጥጥር ስር ዋለች። አዲስ አበባ የሚገኙ ቤተሰቦቻቸው የጠፋችው ትክክለኝ ልጃቸው መኾኗን ለማረጋገጥ የሕፃን ረድኤት ፎቶ ለወላጆቻቸው ይልካሉ። ስለ ሁኔታው ለአሚኮ የተናገሩት እናት ማንጠግቦሽ "የልጄን ፎቶ ስመለከት ጥርጣሬ ገብቶኝ ነበር" ብለዋል።

"ልጄ ለወራት ያክል በደረሰባት እንግልትና ስቃይ መቀየሯ ታውቆኛል" ሲሉ ተናግረዋል። ነገር ግን በአካል ሂደው ማየትና ማረጋገጥ የፈለጉት ወላጆቹ ወደ አዲስ አበባ ሄዱ። "ገና ከርቀት እንዳየኋት ራሴን መቆጣጠር አቃተኝ እንባዬም መፍሰስ ጀመረ" የሚለው ወላጅ አባት ዘሩ ሰይድ ፈጣሪ ዳግም እንደ ፈጠረኝ ነው የማምነው ሲል ነበር ስሜቱን የገለጸው።

ለወራት ከልጃቸው የተለዩት እኚህ ወላጆች ግንቦት 16 ቀን 2015 ዓ.ም ደሴ ከተማ ሲገቡ በደሴ ከተማ አሥተዳደር አመራሮች፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በጎረቤቶቻቸውና ስለ ጉዳዩ በሰሙ በከተማይቱ ነዋሪዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በቤታቸው ተገኝተው እንኳን ደስ ያላችሁ ያሉት የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ ማኅበራዊ ሚድያን በአግባቡ ከተጠቀምን እንዲህ ልጅን ከቤተሰብ ማገናኘት ይቻላል ብለዋል።

ወንጀለኞችን ለመከላከል ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል ኀላፊነቱን መወጣት አለበት ያሉት ከንቲባው ለወራት በልጃቸው መጥፋት ቅስማቸው ለተሰበረው ቤተሰብ ከተማ አሥተዳደሩ የቤት ስጦታ እዳዘጋጀላቸውና በፈለጉት ጊዜ መረከብ እደሚችሉ አስታውቀዋል። ከዚህ በተጨማሪም ከተማ አሥተዳደሩ ቤተሰቡ በሚያስፈልገው ሁሉ ለማገዝ ዝግጁ መኾኑን ነው አቶ ሳሙኤል የተናገሩት።

አሚኮ ከሕፃን ረድኤት ዘሩ ቤተሰቦች ባገኘው መረጃ መሰረት ጥቆማውን የተናገረችው ምታምር በለጠ እንደምትባል እና በአዲስ አበባ በሊስትሮ ሥራ ላይ የተሰማራች ስለመኾኗ ለመረዳት ተችሏል። ጥቆማውን ላደረሰችው የደሴ ከተማ አስተዳደር የ50 ሺህ ብር ሽልማት እደሚያደርግ ገልጿል። ሕፃን ረድኤት ዘሩን በመስረቅና ለልመና ስትጠቀምባት የነበረችው ወይንሽት መኮንን የተባለችው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውላ ምርመራ እየተደረገባት ይገኛል።

የሕፃን ረድኤት ወላጆች በጭንቅ ጊዜ አብረዋቸው ለተጨነቁ፣ በፍለጋ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ከጎናቸው ለነበሩ የ07 ቀበሌ ነዋሪዎችና ጎረቤቶቻቸው ፈጣሪ ውለታቸውን ይክፈልልን ብለዋል። ለልጃቸው መገኘት ምክንያት ለኾኑላቸው የደሴ ከተማ መንግሥት ኮምዩኒኬሽንና ለብልጽግና ፓርቲ ደሴ ቅርንጫፍ ከፍተኛ ምስጋናም አቅርበዋል።

ዘጋቢ፦ አሚኮ

ለሱዳን ስደተኞች ድጋፍ ለማድረግ የፌዴራል መንግስት ግብረ ኃይል አቋቁሞ እየሰራ ነው የሱዳን ጦርነትን ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ ስደተኞች ድጋፍ ለማድረግ በፌዴራል መንግስት ደረጃ ግብረኃ...
17/05/2023

ለሱዳን ስደተኞች ድጋፍ ለማድረግ የፌዴራል መንግስት ግብረ ኃይል አቋቁሞ እየሰራ ነው

የሱዳን ጦርነትን ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ ስደተኞች ድጋፍ ለማድረግ በፌዴራል መንግስት ደረጃ ግብረኃይል ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በሱዳን የተከሰተውን የእርስ በርስ ግጭት ተከትሎ ወደኢትዮጵያ ለሚመጡ ስደተኞች ድጋፍ ለማድረግ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስተባባሪነት ግብረሃይል ተቋቋሞ እየተሰራ ነው።

በግብረኃይሉ የኤሚግሬሽንና የስደተኞች ተቋም፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽንና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት ጋር መካተታቸውን አስታውቀዋል።

ግብረ ኃይሉ ስደተኞቹ የሚገኙባቸው ስፍራዎች ድረስ በመሄድ የተለያዩ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል ሲሉም ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል።

ከድጋፍ ስራው ባለፈ በተደራጀ ሁኔታ ከሱዳን ወደሀገራቸው ለመምጣት ፍቃደኛ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ወደሀገራቸው የሚመጡበትን ሁኔታ የማመቻቸት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም አመላክተዋል።

በሱዳን የሚገኙ ማህበራት ለጊዜው መቀመጫውን ከካርቱም ከቀየረው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ዜጎችን የመለየት ስራዎች እየተከናወነ ይገኛል፤ የዝግጅት ስራው እንደተጠናቀቀ ዜጎቹን ወደየአካባቢዎቻቸው የማድረስ ስራ ይሰራል ብለዋል።

በተለያየ መንገድ ከሱዳን የመጡ ኢትዮጵያውያንን በካምፕ ውስጥ ከማቆየት ወደ መዳረሻቸው መውሰዱ የተሻለ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ፤ ኢትዮጵያ የገቡ ዜጎች ወደየአካባቢዎቻቸው የማድረስ ስራ በተጓዳኝነት እየተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል።

ክልሎችም ከሱዳን ለሚመለሱ ዜጎቹ የስራ ዕድል የሚፈጥሩበት ሁኔታ ላይ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

ከግጭቱ ጋር ተያይዞ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት ዜጎች ወደኢትዮጵያ እየመጡ ሲሆን፤ በመተማና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በኩርሙክ በኩል ስደተኞች እየገቡ መሆኑን አስታውቀዋል።

ወደኢትዮጵያ ለሚገቡ ዜጎች የሚደረገው ድጋፍ በተደራጀ መልኩ እየተከናወነ ይገኛል ያሉት ኮሚሽነሩ፤ የሚመለከታቸው ተቋማት ከፀጥታ ተቋማት ጋር በመተባበር በየቀኑ የድጋፍና ቁጥጥር ስራዎች እየገመገሙ እንደሚያከናውኑ ገልጸዋል።

ዓለም አቀፍ ተቋማትም ለስደተኞቹ የተለያዩ ድጋፎችን እያደረጉ መሆኑን የጠቆሙት ኮሚሽነሩ፤ በስፍራው የሰላምና ፀጥታ፣ የኢሚግሬሽንና የሰነድ ማረጋገጫ አገልግሎቶች በተቀላጠፈ ሁኔታ እየቀረበ በመሆኑ ተገልጋዮች ደስተኛ መሆናቸውን አስረድተዋል።

በጊዜያዊነትም ደረቅ ምግቦች፣ የንፁህ ውሃ አቅርቦትና የሕክምና አገልግሎት ለስደተኞቹ በመቅረብ ላይ መሆኑን አስታውቀዋል።

የምዕራብ ጎንደር ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ቢሆነኝ በበኩላቸው እንደተናገሩት፤ በግጭቱ ምክንያት ወደኢትዮጵያ የገቡ ዜጎች ቁጥር ከ21ሺህ በላይ ደርሷል።

ከጤና ሚኒስትርና ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተውጣጡ 14 የጤና ባለሙያዎችና በአካባቢዎቹ የሚገኙ የሕክምና ባለሙያዎች አስፈላጊውን አገልግሎት እየሰጡ መሆኑንም ገልጸዋል።

ከስደተኞቹ መካከል የጤና ባለሙያ ክትትል የሚያስፈልጋቸው 466 ሰዎች አገልግሎቱን አግኝተዋል፤ የጤና አገልግሎቱን ካገኙ መካከል ወላዶች እንደሚገኙበት ጠቁመዋል።

እንደ ኃላፊው ገለፃ፤ ሪፈር ለሚያስፈልጋቸው ህሙማን ደግሞ ወደ መተማ እና ወደጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሎች ሄደው አገልግሎት እንዲያገኙ እየተደረገ ነው።

ከሰላምና ፀጥታ ጋር በተያያዘ የተፈጠረ ምንም ችግር የለም ያሉት አቶ ፋንታሁን የተቋቋመው ግብረ ሀይል አጠቃላይ ያለውን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለው ነው ብለዋል።

የተፈናቃዮች ቁጥር የሚቀጥል ከሆነ ተጨማሪ መጠለያ ጣቢያዎችን ለመገንባት ከሶስተኛ ወገን ነፃ የሆነ 84 ሄክታር መሬት ተዘጋጅቶ ግንባታ ለመጀመር በሂደት ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

(ኢፕድ)

በቋራ ወረዳ ከ80 በላይ የታጠቁ ኃይሎች ወደ ሰላማዊ ሕይዎት መመለሳቸውን የዞኑ ሰላምና ደኅንነት መምሪያ አስታወቀ። ገንዳ ውኃ፡ ሚያዝያ 29/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋ...
08/05/2023

በቋራ ወረዳ ከ80 በላይ የታጠቁ ኃይሎች ወደ ሰላማዊ ሕይዎት መመለሳቸውን የዞኑ ሰላምና ደኅንነት መምሪያ አስታወቀ።

ገንዳ ውኃ፡ ሚያዝያ 29/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ከህግ ሸሽተው የነበሩ ከ80 በላይ የታጠቁ ኃይሎች ወደ ሰላማዊ ህይወት መመለሳቸውን የዞኑ ሰላምና ደህንነት መምሪያ አስታውቋል።

በምዕራብ ጎንደር ዞን የሰላምና የጸጥታ ስጋት ከሚስተዋልባቸው አካባቢዎች አንዱ ቋራ ወረዳ ነው።

ለቋራ ወረዳ አዋሳኝ በኾነው የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ድንበር አካባቢ በኾኑት በተለይም አባይዳር፣ ባንባሆ እና ቀዝቀዝና በተባሉ ቀበሌዎች በተለያዩ ምክንያቶች ከህግ የሸሹ የታጠቁ ኃይሎች የሰላምና የጸጥታ ስጋቶች ኾነው መቆየታቸውን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ይርዳው ካሳሁን አንስተዋል።

ይሁን እንጅ አሁን ላይ እንዚህን የታጠቁ ኃይሎች በሃይማኖት አባቶች፣ በሀገር ሽማግሌዎችና በጸጥታ መዋቅሩ የተቀናጀ ተግባር ወደ ሰላማዊ ሕይዎት እንዲመለሱ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ በተለያዩ ምክንያቶች ከህግ ሸሽተው የነበሩ ከ88 በላይ የታጠቁ ኃይሎችን የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ሰላማዊ ሕይዎት መመለሳቸውን የዞኑ ሰላምና ደህንነት መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አሰፋ አሸቤ ገልጸዋል።

የዞኑን ሰላምና ደኅንነት በዘላቂነት ለማስጠበቅ ከሕዝቡ፣ ከጸጥታ መዋቅሩ፣ ከሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ጋር በቅንጅት እየተሠራ መኾኑንም ነው የተናገሩት።

በቋራ ወረዳ የቧንቧኾ ቀበሌ ነዋሪ የኾኑት አቶ ገብሬ አንተነህ እና አቶ ጓዴ አንጋዳው በአካባቢው አለመግባባቶችና ግጭቶች ሲፈጠሩ ችግሮችን በሀገሬው የሽምግልና ባህል ሲፈቱ መቆየታቸውን አስታውሰዋል።

ከአሁን በፊት በግድያ ወንጀል ብቻ ከ120 በላይ ግለሰቦችን በማስታረቅ ሃይማኖታዊና ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ መኾኑንም ተናግረዋል።

አሁንም የታጠቁ ኃይሎች በሰላማዊ መንገድ ወደ አካባቢያቸው ገብተው የሰላምና የልማት አንባሳደር እንዲኾኑ የበኹላቸውን ድርሻ እየተወጡ መኾናቸውንም ገልጸውልናል።

መንግስት በሰጠው የሰላም አማራጭ መሰረት ወደ ሰላማዊ ሕይዎት መመለሳቸውን የገለጹት ታጣቂዎቹ በቀጣይ ከመንግሥት እና ከሰላም ወዳዱ ሕዝብ ጎን በመኾ የአካባቢውን ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ ቁርጠኛ መኾናቸውን አረጋግጠዋል።

የ98ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ሌተናል ኮሌኔል አንተነህ ከፈለኝ በበኩላቸው፤ ታጣቂ ኃይሎች ከመንግሥት ጎን በመቆም የሰላም እና የልማት አንባሳደር እንዲኾኑ መግባባት ላይ መደረሱን ተናግረዋል።

ሕዝባዊ አንድነትና ሰላም ለማምጣት መተማመን ላይ የተመረኮዘ የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ ይገባል ያሉት አዛዡ በቀጣይም ከሕዝቡ ጋር በመሆን የአካባቢውን ሰላም ለማስጠበቅ እንሠራለን ብለዋል።

ዘጋቢ፦ ቴዎድሮስ ደሴ

አሚኮ

የሱዳን ስደተኞች በመተማ በኩል እየገቡ ነውበሀገረ ሱዳን የእርስ በእርስ ግጭት ምክንያት የተለያዩ ሀገር ዜጎች በመሸሽ በምእራብ ጎንደር ዞን መተማ ዮኋንስ ከተማ በኩል እየገቡ ነው።በሀገረ ሱ...
27/04/2023

የሱዳን ስደተኞች በመተማ በኩል እየገቡ ነው

በሀገረ ሱዳን የእርስ በእርስ ግጭት ምክንያት የተለያዩ ሀገር ዜጎች በመሸሽ በምእራብ ጎንደር ዞን መተማ ዮኋንስ ከተማ በኩል እየገቡ ነው።

በሀገረ ሱዳን የእርስ በእርስ ግጭት ምክንያት የተለያዩ ሀገር ዜጎች ከግጭቱ በመሸሽ በምእራብ ጎንደር ዞን መተማ ዮኋንስ ከተማ በኩል እየገቡ ነው።

የተፈጠረውን አለመረጋጋት ሸሽተው የሚመጡ የተለያዩ የውጭ ሀገር ዜጎችን የምእራብ ጎንደር ዞን መተማ ዮኋንስ ከተማ በሰላም እያስተናገደች ነው።

ሱዳን ላይ በተፈጠረው የውስጥ አለመረጋጋት ምክኒያት ጦርነቱን ሸሽተው ከካርቱም ወደ ጎረቤት ሀገር ኢትዩጵያ የሱዳን ዜጎችን ጨምሮ የ23 ሀገራት የተለያዪ ሃገራት ዜጎች እንደገቡና ወደ ሚፈልጉት አካባቢ እየሄዱ ይገኛሉ።

በዚህም የምዕራብ ጎንደሯ የፍቅር ከተማ መተማ ዮሃንስ ከተማ እንግዶቿን እያስተናገደች ሲሆን በቀን ከ15-20 የሚሆኑ መኪናዎች ወደ ጎንደር እየሄዱ ይገኛሉ ። በዚህ የጦርነት ስጋት ሺሽትም ህፃናት፣ ሴቶች እና አቅመ ደካሞች ይገኙበታል።

የመተማ ዮሃንስ ከተማ አስተዳደር፣ የዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ የሚመለከታቸው የፀጥታ አካላትም ዜጎች ያለምንም እንግልት ወደ ሚፈልጉት አካባቢ እንዲደርሱ ሰብአዊ ተግባራትን እየተከናወኑ ይገኛሉ

15/04/2023

"የስቅለትን በዓል ስናከብር ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሁሉ ቤዛ የኾነበትን በማሰብ መኾን አለበት" ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ

ወልድያ: ሚያዝያ 06/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ብጹዕነታቸው የስቅለት በዓልን አስመልክተው በሰጡት አስተምህሮ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጆችን ለማዳን ሲል በመስቀል ላይ የተሰቀለበት ፣ የሾኅ አክሊልም የደፋበት ፣እጅና እግሮቹን በምስማር የተቸነከረበት፣እርሱ ሞቶ አዳምን አድኖ ወደ ገነት ያስገባበት ፣የበደሉትን ሁሉ ይቅር በማለት ለፍጥረታት ሁሉ ፍቅሩን ያሳየበት እለት መሆኑን አስረድተዋል ፡፡

እኛ ግን ከክርስቶስ አስተምህሮ በተቃራኒ ምድር የሰጠችንን የተፈጥሮ ጸጋ በጋራ መጠቀምና አብሮ መኖር አቅቶን የራሳችን ጥቅም የምናስቀደም፤ በሰው መቃብር ላይ ቆመን እኛ የምንደሰት ሆነናል ያሉት ብጹዕነታቸው እለቱን ስናስብ ክርስቶስ ያስተማረንን ለሰዎች በጎ በማሰብ ፣ የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት ፣የታመሙትን በመጠየቅ እና ሌሎች በጎ ተግባሮችን በመፈጸም ሊኾን እንደሚገባ አሳስበዋል ፡፡
በተለይም ሕዝበ ክርስቲያኑ የትንሣዔን በዓል ሲያክብር ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው በተለያዩ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች ልብስና የእለት ጉርስ የሌላቸውን ወገኖችን በመጠየቅና በመርዳት እንድያሳለፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዘጋቢ:- ባለ ዓለምየ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://www.facebook.com/DiscoverAmharaAMECO
አሚኮ ስፖርት https://www.facebook.com/AMECOSport
አሚኮ እውነታ ማጣሪያ https://www.facebook.com/AMECOFactCheck

Address

Gondar
Gondar

Telephone

+251931311730

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when West Gondar Police posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share