Asrat Atsedeweyn

Asrat Atsedeweyn 5th President of the University of Gondar. Committed to institutional excellence, global partnerships, and the advancement of higher education in Ethiopia.

Bridging tradition with innovation for a brighter future.

ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በዩኒቨርሲቲያችን ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የህጻናት የልብ ቀዶ ህክምና (Open Heart Surgery) ዘመቻ ከዛሬ ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ጀም...
21/05/2026

ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በዩኒቨርሲቲያችን ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የህጻናት የልብ ቀዶ ህክምና (Open Heart Surgery) ዘመቻ ከዛሬ ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ ተጀምሯል!

ይህ በሦስት ቀናት ውስጥ የሚከናወነው የህጻናት የልብ ቀዶ ህክምና ዘመቻ፣ ለበርካታ ህጻናት አዲስ ህይወትንና ተስፋን የሚሰጥ፣ ለሆስፒታላችንም ትልቅ የዕድገት ምዕራፍ ነው።

ይህ ታላቅና ታሪካዊ ስኬት ያለ አጋሮቻችን ቀና ትብብርና ድጋፍ እውን ሊሆን አይችልም ነበር። በመሆኑም ለዚህ በጎ ተግባር መሳካት ከጎናችን ለቆሙት ለኢትዮ-ስታምቡል አጠቃላይ ሆስፒታል፣ Heart-to-Heart Children Aid የተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት፣ ለኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር፣ ጣሊያን አገር ለሚገኘው Padre Pio የተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት እንዲሁም ሌሊትና ቀን ሳይሰለቹ ለዚህ ታሪካዊ ስራ መሳካት እየደከሙ ለሚገኙት ለዩኒቨርሲቲያችን የህክምና ባለሙያዎች፣ አስተዳደር ሰራተኞችና ለበጎ ፍቃደኛ የህክምና ቡድኖች በሙሉ በዩኒቨርሲቲያችን ስም የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

የህጻናትን ልብ መፈወስ፣ የነገዋን ኢትዮጵያን መገንባት ነው!

ፈጣሪ የጀመርነውን የህክምና ዘመቻ በድል እንዲያጠናቅቅልን እየተመኘን፣ ለታካሚ ህጻናት በሙሉ ፈጣን ማገገምንና ሙሉ ጤንነትን እንመኛለን!
፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥
ግንቦት 13 ቀን 2018ዓ.ም

Historic Pediatric Open-Heart Surgery Campaign Launches!

​In collaboration with various partner organizations, the pediatric open-heart surgery campaign has officially launched today, May 21, 2026, for the very first time in our university's history!

​This pediatric open-heart surgery campaign, which will be conducted over the course of three days, will grant new life and hope to many children, marking a major milestone in our hospital's development.

​This grand and historic achievement would not have been possible without the genuine cooperation and support of our partners.

Therefore, on behalf of the University of Gondar, we extend our highest gratitude to those who stood by us for the success of this noble cause: Ethio-Istanbul General Hospital, the non-governmental organization Heart-to-Heart Children's Aid, the FDRE Ministry of Health,Ethiopia, the Italy-based NGO Padre Pio, as well as our university's medical professionals, administrative staff, and volunteer medical teams who have been working tirelessly day and night to make this historic endeavor a reality.

​Healing a child's heart is building the Ethiopia of tomorrow!

​Wishing that the Almighty helps us conclude this medical campaign in victory, we wish all the pediatric patients a speedy recovery and full health!
፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥
​May 21, 2026
Ministry of Education Ethiopia Medical Information Ministry of Education Ethiopia Lijalem Gashaw Aynishet Adane Hakim Afework Kassu Binyam C. Tilahun Ethiopian Medical Association Ethiopian health today

I was honored to lead a delegation from the University of Gondar to the University of Leicester recently to officially r...
20/05/2026

I was honored to lead a delegation from the University of Gondar to the University of Leicester recently to officially renew our Memorandum of Understanding.

​For nearly three decades, our institutions have shared a steadfast partnership rooted in mutual growth, healthcare advancement, and academic excellence. From the early days of the Health Action Leicester for Ethiopia (HALE) charity to current initiatives strengthening research management and academic capacity, this collaboration continues to yield impactful results for our communities.

​We look forward to this next chapter of joint research, leadership mentorship, and expanded impact across the region.

Thank you to Sir Nishan Canagarajah, President and Vice Chancellor, and Professor Richard Thomas, Pro Vice Chancellor Research and Enterprise, and the entire team at Leicester for their warm welcome and enduring commitment.

​Read more about our renewed landmark partnership here:
https://le.ac.uk/news/2026/may/gondar-leicester-university-ethiopia-delegation?dm_i=I8Y,97VN0,1G5HVP,12OF9C,1,0,0,0
፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥
May 20, 2026

Lijalem Gashaw Ministry of Education Ethiopia Ministry of Health,Ethiopia Medical Information Ministry of Education Ethiopia Ethiopian Public Health Institute Ethiopian Medical Association Aynishet Adane Binyam C. Tilahun Afework Kassu Hakim

University of Leicester has renewed its landmark partnership with the University of Gondar, building on nearly three decades of collaboration in research, education and capacity building.

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ዓጼ ቴዎድሮስና ማራኪ ግቢዎች ተዟዙረን ስንመለከት ካጋጠመን ማራኪ እይታ ጥቂቱን። ይህ ካምፓስ ለዕውቀት መገብያ ብቻ ሳይሆን ለአይንና ለልብም ማረፊያ ነው።፥፥፥፥፥፥፥፥፥...
19/05/2026

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ዓጼ ቴዎድሮስና ማራኪ ግቢዎች ተዟዙረን ስንመለከት ካጋጠመን ማራኪ እይታ ጥቂቱን። ይህ ካምፓስ ለዕውቀት መገብያ ብቻ ሳይሆን ለአይንና ለልብም ማረፊያ ነው።
፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥
ግንቦት 11 ቀን 2018ዓ.ም

A few of the captivating sights we encountered while touring the Atse Tewodros and Maraki campuses of the University of Gondar. This campus is not only a marketplace for knowledge, but also a resting place for the eyes and the heart.
፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥
May 19, 2026
​ Lijalem Gashaw Aynishet Adane

የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ራስ-ገዝነት (Autonomy) ሽግግር ዝግጁነትን ለመገምገም በትምህርት ሚኒስቴር የተመደበው ባለሙያ ቡድን ዛሬ በዩኒቨርሲቲያችን ሥራውን ጀምሯል።​በዛሬው ዕለት ከቡድ...
18/05/2026

የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ራስ-ገዝነት (Autonomy) ሽግግር ዝግጁነትን ለመገምገም በትምህርት ሚኒስቴር የተመደበው ባለሙያ ቡድን ዛሬ በዩኒቨርሲቲያችን ሥራውን ጀምሯል።

​በዛሬው ዕለት ከቡድኑ ጋር የመግቢያና የትውውቅ መርሐግብር የተካሄደ ሲሆን፣ በመቀጠልም በአጼ ቴዎድሮስ ግቢ የሚገኙትን የልማት ሥራዎች (የእንስሳት እርባታና የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት መስኮችን) ቡድኑ በቦታው በመገኘት ተመልክቷል።

​ይህ የዝግጁነት ግምገማ ዩኒቨርሲቲያችን ወደ ሙሉ ራስ-ገዝነት ለሚያደርገው ታሪካዊ ሽግግር እጅግ ወሳኝ ምዕራፍ ነው።

ለገምጋሚ ቡድኑ መልካም የሥራ ጊዜ እንመኛለን!
፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥
ግንቦት 10 ቀን 2018ዓ.ም

A team of experts assigned by the Ministry of Education Ethiopia to assess the readiness of public universities for the transition to autonomy commenced its work at our university today.

​Today, an introductory and orientation program was held with the team. Following this, the team conducted an on site visit to the development projects located at the Atse Tewodros Campus, specifically looking into the livestock farming and the fruit and vegetable cultivation fields.

​This readiness assessment marks a crucial milestone in the University of Gondar's historic transition toward full autonomy.

We wish the evaluation team a highly productive and successful stay!
፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥
May 18, 2026
Medical Information Binyam C. Tilahun Lijalem Gashaw Aynishet Adane Ministry of Education Ethiopia

​ ​ ​ ​

በሕዝብ ልብና አእምሮ ውስጥ የኖሩት ሊቅ፡- ዶ/ር ዘኪ አብዱራህማን!በጎንደር ሕዝብና በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ልብ ውስጥ የማይረሳ አሻራ ያኖሩ፤ እርሳቸውም ጎንደርን በልባቸው ያተሙ፤ ታዋቂውና ተ...
17/05/2026

በሕዝብ ልብና አእምሮ ውስጥ የኖሩት ሊቅ፡- ዶ/ር ዘኪ አብዱራህማን!

በጎንደር ሕዝብና በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ልብ ውስጥ የማይረሳ አሻራ ያኖሩ፤ እርሳቸውም ጎንደርን በልባቸው ያተሙ፤ ታዋቂውና ተወዳጁ የጉበት፣ የቆሽትና የሀሞት ቀዶ ሕክምና ሰብ-ስፔሻሊስት ናቸው ዶክተር ዘኪ አብዱራህማን። አገራቸውንና ወገናቸውን ከልብ የሚያፈቅሩ፥ በትምህርታቸው የተመሰከረላቸው እና በተማሪዎቻቸው በእጅጉ የሚወደዱ ምሁር ናቸው። የሀገር ሀብት!

ከተማሪነት እስከ መምህርነትና ስመ-ጥር ሐኪምነት ወደቀሰሙበትና በቅንነት ወዳገለገሉበት ቀደመ ቤታቸው እንኳን በደህና መጡ። መምጣትዎ ለዩኒቨርሲቲያችን ማኅበረሰብ ታላቅ ደስታና ኩራት ነው። በጎንደር ሕዝብ እቅፍ ሆነው የወጣትነት ጊዜያቸውን ያሳለፉ ሁሉ ሁልጊዜም ከጎንደር አይለዩም!

እንደ ዶ/ር ዘኪ ዓይነት ለአገርና ለወገን የሚተርፉ እና ለተተኪ ትውልድ አርአያ የሚሆኑ ሊቃውንትን ማፍራት በመቻሉ ጎንደር ዩኒቨርስቲ ኩራትና ክብር ይሰማዋል!!!
፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥
ግንቦት 9 ቀን 2018ዓ.ም

መንገዱ ፈታኝ፤ ተመራቂዎቹ ለፈተና የማይበገሩ!​ዛሬ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ታሪክ ውስጥ ልዩ ስፍራ የሚይዘው የ41ኛው ዙር የሕክምና ሳይንስ ተማሪዎቻችን የምረቃ በ...
16/05/2026

መንገዱ ፈታኝ፤ ተመራቂዎቹ ለፈተና የማይበገሩ!

​ዛሬ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ታሪክ ውስጥ ልዩ ስፍራ የሚይዘው የ41ኛው ዙር የሕክምና ሳይንስ ተማሪዎቻችን የምረቃ በዓል ነው።

​በ6 ዓመታት መጠናቀቅ የነበረበት የትምህርት ጉዞ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና በተለያዩ አስገዳጅ ወቅታዊ ሁኔታዎች ምክንያት 8 ዓመታትን ወስዷል። ነገር ግን እነዚህ ውድ ልጆቻችን ተስፋ ሳይቆርጡ፣ ሳይበገሩና ከሙሉነታቸው ሳይጎድሉ ሁሉንም ፈተናዎች ወደ ጥንካሬ ቀይረው ለዚህ ታላቅ ቀን በቅተዋል። ምሩቆቻችን በትምህርትም ሆነ በሥነ-ምግባር ደምቃችሁ የታያችሁ የሁላችንም ኩራቶች ናችሁ!

በተለይ በዛሬው ዕለት፣ በጎንደር ሕዝብና በዩኒቨርሲቲያችን ልብ ውስጥ ልዩ ቦታ ያላቸው፣ የመልካም አገልጋይነት፣ የላቀ ሙያዊ ሥነ-ምግባር እና የፍጹም ታካሚዎች ፍቅር ተምሳሌት የሆኑት ዶ/ር ዘኪ አብዱራህማን በመካከላችን መገኘታቸው ለበዓላችን የተለየ ድምቀትና ትልቅ ክብር ሆኖታል።

​ውድ ተመራቂዎቻችን፤
ከዚህ ታላቅ የሕክምና ሊቅ የካበተ ጥበብንና ርኅራኄን እንደ ስንቅ ትወስዱ ዘንድ አደራ እላለሁ። የእስካሁኑ ተግባራችሁ የሚያረጋግጠው ለአገራችሁና ለወገናችሁ ያላችሁን ፍቅር፣ የሚያስቀናውን የእርስ በርስ ትብብርና መደጋገፍ እንዲሁም ለሙያችሁ ያላችሁን ልዩ አክብሮት ነው። እነዚህን አኩሪ እሴቶች አጠናክራችሁ እንደምትቀጥሉ ባለሙሉ ተስፋ ነኝ።
​የሕዝቡን ስቃይና ፍላጎት በቅርብ የተመለከታችሁ እንደመሆናችሁ፣ አሁን ዕውቀታችሁን ለወገናችሁ ፈውስና ተስፋ የምትለግሱበት ጊዜ ላይ ደርሳችኋል።

​የዛሬዎቹ ተመራቂዎች፣ አስተማሪዎችና የጤና ባለሙያዎች፤ እንዲሁም ውድ ወላጆችና መላው የዩኒቨርሲቲያችን ማኅበረሰብ እንኳን ደስ አላችሁ፣ እንኳን ደስ አለን!

​የታሪካዊቷ እና የእናት ተቋማችሁ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሁልጊዜም ኩሩ አምባሳደሮች እንደምትሆኑ ሙሉ እምነት አለኝ። በቀጣዩ የሥራ ዘመናችሁ የኃላፊነትን ዘውድ በታማኝነትና በትጋት በመሸከም ለወገናችሁ የፈውስ እጆች እንድትሆኑ እመኛለሁ።
​የምረቃ በዓላችን ፍፁም ደስታ የተሞላበት ይሁን!

​ደስታችሁ ደስታችን ነው። ኮርተንባችኋል!!!
​፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥
ግንቦት 8 ቀን፣ 2018 ዓ.ም

The Journey Was Challenging; The Graduates Are Unconquerable!

​Today marks a special milestone in the history of the College of Medicine and Health Sciences at the University of Gondar, the graduation ceremony of our 41st batch of medical science students.

​An academic journey that should have been completed in 6 years instead took 8 years, extended by the COVID-19 pandemic and various compelling current circumstances. However, these dear children of ours never lost hope; they remained unyielding and steadfast, turning every challenge into a source of strength to triumphantly reach this great day. Our graduates, you have shone brightly in both your education and your ethics, and you are the pride of us all!

​Our celebration is uniquely brightened and deeply honored today by the presence of Dr. Zeki Abdurahman, a man who holds a special place in the hearts of the people of Gondar and our university, serving as an epitome of dedicated public service, exceptional professional ethics, and absolute love for patients.

​To our dear graduates:
I urge you to carry forward the rich wisdom and profound compassion of this great medical authority as your guiding light. Your actions thus far clearly demonstrate your love for your country and your people, your admirable mutual cooperation and support, and your exceptional respect for your profession. I am filled with hope that you will continue to strengthen these noble values.

​Having closely witnessed the suffering and needs of the public, the time has now come for you to dedicate your knowledge to bringing healing and hope to your people.

​Congratulations to today’s graduates, instructors, and health professionals, as well as to the dear parents and our entire university community—congratulations to us all!

​I've full confidence that you will always be proud ambassadors of your historic mother institution, the University of Gondar. In your upcoming professional careers, I wish for you to wear the crown of responsibility with integrity and diligence, becoming hands of healing for your people.

​May our graduation ceremony be filled with absolute joy!

​Your joy is our joy. We are proud of you!!!
​፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥
May 16, 2026

Hakim Ministry of Health,Ethiopia Ethiopian Public Health Institute Medical Information Ethiopian Medical Association Ministry of Education Ethiopia Ministry of Education Ethiopia Lijalem Gashaw Aynishet Adane Binyam C. Tilahun Afework Kassu Solomon Abrha

ታሪካዊ ትስስርን ማጠናከር፦ ከሌስተር ዩኒቨርሲቲ ጋር የተደረገ የመግባቢያ ሰነድ እድሳትበጎንደር ዩኒቨርሲቲ እና በሌስተር ዩኒቨርሲቲ መካከል ያለውን የመግባቢያ ሰነድ ዛሬ ግንቦት 6 ቀን 20...
14/05/2026

ታሪካዊ ትስስርን ማጠናከር፦ ከሌስተር ዩኒቨርሲቲ ጋር የተደረገ የመግባቢያ ሰነድ እድሳት

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ እና በሌስተር ዩኒቨርሲቲ መካከል ያለውን የመግባቢያ ሰነድ ዛሬ ግንቦት 6 ቀን 2018ዓ.ም በሀገረ-እንግሊዝ በሚገኘው ሌስተር ዩኒቨርሲቲ ተገኝተን በይፋ ማደሳችንን ስገልጽ በታላቅ ደስታ ነው።

የፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ከሌስተር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እና ምክትል ቻንስለር ሰር ኒሻን ካናጋራጃ ጋር የተከናወነ ሲሆን፣ ይህም ለበርካታ አስርት ዓመታት የዘለቀው ጉዟችን ሌላኛው ምዕራፍ ነው።

በ1990ዎቹ በጤና ጥበቃ እና በትምህርት ዘርፍ የጋራ ራዕይን ሰንቆ የተጀመረው አጋርነታችን፣ ዛሬ በዓለም አቀፍ ደረጃ ካሉን እጅግ ዘላቂ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ አጋሮቻችን አንዱ ለመሆን በቅቷል። ሌስተር ዩኒቨርሲቲ ለዩኒቨርሲቲያችን ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ለሀገራችን ኢትዮጵያም የማይለወጥ ደጋፊ ሆኖ ቆይቷል። የጋራ ስኬቶቻችን በጥቂቱ፦

1. በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አምስት ወሳኝ የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ማለትም አንስቴዥያ፣ ፊዚዮቴራፒ፣ ነርሲንግ፣ ሚድዋይፈሪ እና ክሊኒካል ላቦራቶሪ እንዲጀመሩ ሌስተር ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ድጋፍ አድርጓል። በነዚህ ዘርፎች የራሳችንን ባለሙያዎች እስክናፈራ ድረስም መምህራኖቻቸውን እየላኩ የማስተማር እና የማማከር ሥራዎችን ሠርተዋል።

2. የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንታችንን ዶ/ር ካሳሁን ተገኘን ጨምሮ በርካታ የመምህራን አባላት የዶክትሬት ዲግሪ (PhD) ትምህርታቸውን በሌስተር ዩኒቨርሲቲ አጠናቅቀዋል።

3. ተከታታይነት ያለው የአመራር እና የመምህራን ልውውጥ በማድረግ የልምድ ልውውጥን እና የተቋማዊ እድገት ባህልን አሳድገናል።

4. የሥነ-አእምሮ ህክምና (Psychiatry) ትምህርት ክፍላችን በሠራተኞች አቅም ግንባታ እና በቁሳቁስ ድጋፍ የተጠናከረ ሲሆን፣ በአማራ ክልል ለሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች የሥነ-አእምሮ ህክምና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የሚያግዝ የተሽከርካሪ ድጋፍንም ያካትታል።

5. የሌስተር ዩኒቨርሲቲ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጪዎች በዩኒቨርሲቲያችን የማህበረሰብ ትምህርት ቤት የእንግሊዝኛ ቋንቋ በማስተማር፣ መጽሐፍትን እና ለልጆች መጫወቻና የመማሪያ ቁሳቁሶችን በመለገስ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ አበርክተዋል።

6. በአሁኑ ወቅት በብሪቲሽ አካዳሚ የሚደገፈውን "በምስራቅ አፍሪካ እና በዩናይትድ ኪንግደም የምርምር አስተዳደር እና የአመራር አቅምን ማጠናከር" የተሰኘውን ፕሮጀክት ጨምሮ በተለያዩ ከፍተኛ የጋራ ምርምሮች ላይ በንቃት እየሠራን እንገኛለን።

ይህ የእድሳት ስምምነት በምርምር፣ በትምህርት እና በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ያለንን የላቀ ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋገጠ ነው።

ለክቡር ሰር ኒሻን ካናጋራጃ (የሌስተር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እና ምክትል ቻንስለር) እንዲሁም ለፕሮፌሰር ሪቻርድ ቶማስ (የምርምርና ኢንተርፕራይዝ ፕሮ-ቫይስ ቻንስለር) ላደረጉልን ሞቅ ያለ አቀባበልና ፍሬያማ ውይይት ላቅ ያለ ምስጋናዬን ማቅረብ እወዳለሁ። የእርስዎ አመራር እና ለዚህ አጋርነት ያለዎት የማይነጥፍ ቁርጠኝነት እጅግ የሚያነቃቃ ከመሆኑም በላይ በተቋሞቻችን መካከል ያለውን ትስስር እያጠናከረ ይቀጥላል።

ድንበሮችን በመሻገርና አጋርነትን በማጠናከር ህይወትን እንለውጣለን! 🇪🇹 🇬🇧
፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥
ግንቦት 6 ቀን 2018ዓ.ም

Strengthening a Legacy: MoU Renewal with the University of Leicester

I'm honored to announce that we have officially signed the renewal of our Memorandum of Understanding between the University of Gondar and the University of Leicester May 14, 2026 at the University of Leicester, UK.

The signing ceremony took place with Sir Nishan Canagarajah, President and Vice-Chancellor of the University of Leicester, marking another milestone in our decades-long journey.

Our partnership, which began in the 1990s with a shared vision for healthcare and education, has grown into one of our most sustainable and impactful global alliances.

The University of Leicester has been a steadfast supporter not only of our University but of Ethiopia at large.

Reflecting on our shared achievements:
1. University of Leicester was instrumental in launching five vital MSc programs at University of Gondar: Anesthesia, Physiotherapy, Nursing, Midwifery, and Clinical Laboratory. Their staff taught and mentored ours until we achieved institutional self-sufficiency in these fields.

2 Numerous faculty members, including our Academic Vice President, Dr. Kassahun Tegegne and others, have completed their PhD programs at University of Leicester.

3. We've seen a continuous exchange of leadership and faculty, fostering a culture of shared experience and institutional growth.

4. Our Psychiatry department has been transformed through staff capacity building and material support, including vehicles that facilitate essential mental health outreach across the Amhara region.

5. University of Leicester volunteers have enriched our University Community School through English language teaching, book donations, and plying and educational materials for our children.

6. We continue to collaborate on high level projects, including our current British Academy funded initiative: "Strengthening Research Governance and Research Management Capacity in East Africa and the UK."

As we look toward the future, this renewal reaffirms our commitment to excellence in research, education, and community service.

I wish to extend my deepest gratitude to Sir Nishan Canagarajah, President and Vice-Chancellor of the University of Leicester, and Professor Richard Thomas, Pro-Vice-Chancellor for Research and Enterprise, for their warm hospitality and our productive discussions. Your leadership and unwavering commitment to this alliance are truly inspiring and continue to strengthen the bond between our institutions.

Together, we're bridging borders and transforming lives. 🇪🇹 🇬🇧
፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥
May 14, 2026

British Embassy, Addis Ababa - UK in Ethiopia The British Academy Embassy of Ethiopia, London Ministry of Education Ethiopia Ministry of Education Ethiopia The Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia Medical Information Ethiopian Medical Association Ministry of Health,Ethiopia Ethiopian Public Health Institute Afework Kassu Aynishet Adane Lijalem Gashaw Binyam C. Tilahun

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ብሔራዊ የጤና ሽልማት 2018 (2025/26)፦ የዕጩዎች ጥቆማ ጥሪ​የጎንደር ዩኒቨርሲቲን 70ኛ ዓመት እና የማስተማሪያ ሆስፒታሉን 100ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በማስመል...
13/05/2026

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ብሔራዊ የጤና ሽልማት 2018 (2025/26)፦ የዕጩዎች ጥቆማ ጥሪ

​የጎንደር ዩኒቨርሲቲን 70ኛ ዓመት እና የማስተማሪያ ሆስፒታሉን 100ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በማስመልከት የተዘጋጀው ታላቁ "ብሔራዊ የጤና ሽልማት" የዕጩዎች ጥቆማ መቀበል ላይ መሆኑን ያውቃሉ?

​በኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ ላይ ጉልህ አሻራ ያረፉ ግለሰቦችን፣ ቡድኖችን ወይም ተቋማትን በሚከተሉት ዘርፎች በመጠቆም የክብሩ ተካፋይ ያድርጓቸው፦

​✅ የዕድሜ ልክ የጤና አገልግሎት፣

✅ የማህበረሰብ ጤና ተሟጋች/አሸናፊ፣

✅ የጤና ምርምር የላቀ ውጤት፣ እና

✅ የጤና ትምህርት እና መካሪነት።

​📍 ጥቆማው ለማን ክፍት ነው?
ለማንኛውም ሰው!

📍 እጩዎች፦
በዘርፉ ተፅዕኖ የፈጠሩ ኢትዮጵያውያንና ዓለም አቀፍ ተቋማት/ግለሰቦች።

​🔗 ጥቆማዎን በዚህ ሊንክ ያድርሱ፦
https://survey.uog.edu.et/surveys/national-health-award-ethiopia

​📅 የጥቆማ ጊዜው የሚያበቃው፦
ግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ነው።
​ልዩነት የፈጠሩትን በጋራ እናክብር!
፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥
ግንቦት 5 ቀን 2018ዓ.ም

University of Gondar National Health Award 2018 (2025/26): Call for Nominations

​Did you know that the "National Health Award", one of the landmark projects launched to mark the 70th Anniversary of the University of Gondar and the Centenary of our Teaching Hospital, is currently accepting nominations?

​Help us recognize the excellence of individuals, groups, or institutions that have left a significant mark on Ethiopia's health sector in the following categories:
​✅ Lifetime Health Service Award;
✅ Community Health Advocate/Champion;
✅ Excellence in Health Research; and
✅ Excellence in Health Education and Mentorship

​📍 Who can nominate? Anyone!

📍 Who is eligible? Ethiopian and international individuals/institutions who have created a lasting impact in the Ethiopian health sector.

​🔗 Submit your nomination here:
https://survey.uog.edu.et/surveys/national-health-award-ethiopia

​📅 Nomination Deadline: May 20, 2026

​Let’s honor those who have made a difference!
፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥
​May 13, 2026

​ Ministry of Health,Ethiopia Ethiopian Public Health Institute Ministry of Education Ethiopia Ethiopian Medical Association Ministry of Education Ethiopia Medical Information Dr Mekdes Daba, Minister of Health Binyam C. Tilahun Aynishet Adane Lijalem Gashaw Afework Kassu

የጤና ሚኒስቴር ከጤናው መረጃ ሥርዓት አጋሮች ጋር በመተባበር ለአምስተኛ ጊዜ በሚያከብረው "ሀገር አቀፍ የጤና መረጃና ዲጂታል ሳምንት" ላይ እንድንገኝና ላበረከትነው የላቀ አስተዋጽኦ እውቅና...
11/05/2026

የጤና ሚኒስቴር ከጤናው መረጃ ሥርዓት አጋሮች ጋር በመተባበር ለአምስተኛ ጊዜ በሚያከብረው "ሀገር አቀፍ የጤና መረጃና ዲጂታል ሳምንት" ላይ እንድንገኝና ላበረከትነው የላቀ አስተዋጽኦ እውቅና እንድንቀበል በመጋበዛችን ትልቅ ኩራት ይሰማናል።

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በአገር አቀፍ ደረጃ የ Capacity Building and Mentorship Program (CBMP) አባል ዩኒቨርሲቲዎችን (አዲስ አበባ፣ መቀሌ፣ ሐሮማያ፣ ጅማ እና ሐዋሳ) በማስተባበር በጤና መረጃ አያያዝ፣ ጥራትና አጠቃቀም ላይ ላለፉት ስምንት ዓመታት በቁርጠኝነት ሲሠራ ቆይቷል።

ዩኒቨርሲቲያችን በዚህ ዘርፍ ካከናወናቸው አበይት ተግባራት መካከል ጥቂቶቹ፡-
1. ፈር-ቀዳጅነት፦
በአገራችን የመጀመሪያውን የጤና መረጃ አያያዝ ፕሮግራም (BSc, MPH and PhD in Health Informatics) የከፈተ መሆኑ።

2. የሰው ኃይል ልማት፦
በአሁኑ ሰዓት እስከ ሦስተኛ ዲግሪ (PhD) እና ፖስትዶክተራል ፕሮግራም በማሰልጠን ለአገራችን የጤና መረጃ ሥርዓት የሚፈለገውን የሰው ኃይል በማፍራትና በምርምር ዘርፍ ጉልህ ሚና መጫወቱ።

3. ተግባራዊ ተፅዕኖ፦
የጤና መረጃ አብዮት (Information Revolution) ሞዴል የሆኑ ጤና ጣቢያዎችንና ሆስፒታሎችን በማፍራት ረገድ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑ።

4. ተሞክሮ ማጋራት፦
ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመርና በማጋራት በጤና ሥርዓቱ ውስጥ የአካዳሚክ ባለሙያዎችን ተሳትፎ በማጠናከር የላቀ ውጤት ማስመዝገቡ እና ሌሎች ተግባራት ይገኙበታል።

እነዚህን ሁሉ ሥራወች ዩኒቨርሲቲያችን የድጅታል ጤና እና አተገባባር ሳይንስ (Center for Digital Health and Implementation Science- CDHI) የተባለ የልህቀት ማዕከል በመክፈት በሀገር አቀፍ፣ በአፍሪካ እንዲሁም በዓለምአቀፍ ደረጃ ትልልቅ ሥራዎችን በመሥራት ላይ እንገኛለን።

ይህ እውቅና የዚህ ማዕከልና የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ የጋራ ጥረት ውጤት ነው። የጤና ሚኒስቴር ለሥራችን እያደረገልን ላለው ያልተቋረጠ እገዛና ዛሬ ከኢፌዴሪ ጤና ሚንስቴር ሚንስትር ክብርት ዶ/ር መቅደስ ዳባ በግልና በተቋም ደረጃ ለሰጠን እውቅና በራሴና በዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ ስም ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ።

እንዲሁም ዛሬ ሞዴል በመሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ እውቅና ለተሰጣቸው 11 ተቋማትና በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርስቲያችን ቀጥታ ድጋፍ ያደረገላቸው የጎንደር እና ባህርዳር ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያዎች እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እወዳለሁ።

በቀጣይም በጤናው ዘርፍ የሚታዩ ችግሮችን በዲጂታል ቴክኖሎጂና በመረጃ በመደገፍ የበለጸገች ሀገር ለመገንባት በበኩላችን የምናደርገውን ጥረት አጠናክረን እንቀጥላለን!

የጤና መረጃ ለተሻለ ውሳኔ፣ ዲጂታል ጤና ለላቀ አገልግሎት!

ከታሪክ ማህደር፡-
የዩኒቨርሲቲያችን መሠረት የሆነው የጎንደር ሕብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ኮሌጅና ማሰልጠኛ ተቋም መስከረም 24 ቀን 1947 ዓ.ም ሲመሠረት ተጠሪነቱ በአገር ግዛት ሚኒስቴር ሥር ነበር። ይሁን እንጂ በ1948 ዓ.ም ማንኛውም የጤና ነክ ትምህርት በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ስር እንዲተዳደር በመወሰኑ፣ ተቋማችን እስከ 1953 ዓ.ም ድረስ ለስድስት ዓመታት ያህል በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሲተዳደር የነበረ የረጅም ዘመን የጋራ ታሪክና ትስስር ያለው ነው።
፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥
ግንቦት 3 ቀን 2018ዓ.ም

We're immensely proud to be invited to the 5th National Health Information and Digital Week, organized by the Ministry of Health,Ethiopia in collaboration with health information system partners, and to receive recognition for our outstanding contributions.

​For the past eight years, the University of Gondar has worked with steadfast commitment on health information management, quality, and utilization. We've led this effort by coordinating member universities of the national Capacity Building and Mentorship Program (CBMP), including Addis Ababa University, Mekelle University, Haramaya University, Jimma University, and Hawassa University.

​Key milestones achieved by our university in this sector include:
1. ​Pioneering Leadership:
Establishing the country’s first health information management programs (BSc, MPH, and PhD in Health Informatics).

2. ​Human Resource Development:
Playing a vital role in research and producing the necessary skilled workforce for the national health information system by training professionals up to the PhD and Postdoctoral levels.

3. ​Practical Impact:
Contributing to the development of health centers and hospitals that serve as models for the Information Revolution.

4. ​Knowledge Sharing:
Achieving excellence by synthesizing and sharing best practices and strengthening the involvement of academic professionals within the health system.

​To spearhead these initiatives, our university established a center of excellence, the Center for Digital Health and Implementation Science (CDHI). Through this center, we are executing significant projects at national, continental, and international levels.

​This recognition is a result of the collective efforts of the CDHI and the entire university community.

On behalf of myself and the University of Gondar, I would like to express my deepest gratitude to the Ministry of Health for its continuous support and to Her Excellency Dr Mekdes Daba, Minister of Health, Ministry of Health of the FDRE, for the recognition bestowed upon me personally and our institution today.

​Furthermore, I wish to congratulate the 11 institutions recognized nationally as models, as well as the Health Departments of Gondar and Bahir Dar City Administrations, which received direct support from our university within the Amhara Region.

​Moving forward, we will strengthen our efforts to support the health sector through digital technology and data driven insights to contribute our part toward building a prosperous nation!

​Health Information for Better Decisions, Digital Health for Superior Service!

​From the Archives:
​The Public Health College and Training Center, the foundation of our university, was established on October 4, 1954 under the Ministry of Interior. However, in 1955, it was decided that all health related education should be administered by the Ministry of Public Health. Consequently, our institution was managed by the Ministry for six years until 1961, marking a long history of partnership and connection.
፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥
​May 11, 2026

Ministry of Education Ethiopia Ethiopian Public Health Institute Ethiopian Medical Association Ministry of Education Ethiopia Medical Information Binyam C. Tilahun Lijalem Gashaw Aynishet Adane

ዩኒቨርሲቲያችንን ወደ "ኢንተርፕርነሪያል ዩኒቨርሲቲ" (Entrepreneurial University) ለመለወጥ በምናደርገው ጉዞ ውስጥ የአመራሩ ሚና ቁልፍ ነው።​ዩኒቨርሲቲያችን ከኢትዮጵያ ኢን...
09/05/2026

ዩኒቨርሲቲያችንን ወደ "ኢንተርፕርነሪያል ዩኒቨርሲቲ" (Entrepreneurial University) ለመለወጥ በምናደርገው ጉዞ ውስጥ የአመራሩ ሚና ቁልፍ ነው።

​ዩኒቨርሲቲያችን ከኢትዮጵያ ኢንተርፕርነርሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት (Ethiopian Entrepreneurship Development Institute - Ethiopia - EDI) ጋር በመተባበር፣ ከዛሬ ግንቦት 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለሦስት ቀናት የሚቆይ የስልጠና መርሃ-ግብር በይፋ ጀምሯል። የኮሌጅ ዲኖችና ሥራ አስፈጻሚዎች የሚሳተፉበት ይህ ስልጠና፤ ተቋማችንን የፈጠራ እና የኢንተርፕርነርሽፕ ማዕከል ለማድረግ የሚያስችሉ መሠረታዊ እውቀቶችን የሚያስጨብጥ ነው።

​ይህ ስልጠና፤ በተቋማችን ውስጥ የሕዝብ ኢንተርፕርነርሽፕ እና የፈጠራ ስነ-ምህዳር ግንባታን (Public Entrepreneurship and Innovation Ecosystem Building) ለማጠናከር፤ አመራሩ የፈጠራ ሥራዎችን ለመደገፍና ወደ ተግባር ለመቀየር የሚያስችል ክህሎትና አመለካከት እንዲያዳብር፤ እንዲሁም ዩኒቨርሲቲያችን ለማኅበረሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት በፈጠራ የታገዘ እንዲሆን ለማስቻል ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል።

​ይህ መድረክ የንድፈ-ሀሳብ ብቻ ሳይሆን ዩኒቨርሲቲያችንን እንዴት የፈጠራ ማዕከል እንደምናደርግ የምንመክርበት ጭምር ነው። ዩኒቨርሲቲያችን ወደ ራስ-ገዝ (Autonomous) ተቋምነት በሚያደርገው የሽግግር ጉዞ ውስጥ የኢንተርፕርነርሽፕ አስተሳሰብን መላበስ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። ይህም ማለት ምርምሮቻችን ወደ ተግባርና ወደ ገበያ የሚወጡበት፤ ተማሪዎቻችን የሥራ ፈላጊ ሳይሆን የሥራ ፈጣሪነት መንፈስ የሚላበሱበት፤ እንዲሁም ተቋማችን የራሱን ገቢ እያመነጨ ለሀገር ዕድገት ትልቅ አሻራ የሚያሳርፍበት ሥርዓት መገንባት ነው።

​የዓለማችን ታላላቅ ዩኒቨርሲቲዎች ለሀገራቸው ብልጽግና መሠረት የሆኑት በዚህ መንገድ ነው፦

ስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ (Stanford University) - አሜሪካ፡ ለሲሊከን ቫሊ (Silicon Valley) መፈጠር ምክንያት የሆነና በሺዎች የሚቆጠሩ ኩባንያዎች እንዲመሠረቱ በማድረግ ግንባር ቀደም ተምሳሌት ነው።

ሙኒክ የቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ (Technical University of Munich - TUM) - ጀርመን፡ 'The Entrepreneurial University' በሚል መሪ ቃል ትምህርትን፣ ምርምርን እና የንግድ ሥራ ፈጠራን በማቀናጀት በአውሮፓ ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ሽግግር ውጤት እያመጣ ይገኛል።

ናንያንግ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (Nanyang Technological University - NTU) - ሲንጋፖር፡ የምርምር ውጤቶችን ወደ ገበያ በማውጣትና ከኢንዱስትሪ ጋር ያለውን ትስስር በማጠናከር ለሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት ዕድገት ትልቅ ድርሻ አበርክቷል።

​እነዚህ ተቋማት ያሳዩን ትልቁ ቁምነገር፣ ዩኒቨርሲቲ የእውቀት ማከማቻ ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ሞተር መሆን እንደሚችል ነው። እኛም ዛሬ ከEDI ጋር በመሆን የጀመርነው ስልጠና፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲን በዚህ የለውጥ ጎዳና ላይ ለማሰለፍ የምንወስደው ትልቅ እርምጃ ነው።

​ወደ ኢንተርፕሪነሪያል ዩኒቨርሲቲ ለምናደርገው ታላቅ ጉዞ ከፍተኛ አሻራ እያሳረፈ ላለው ለኢትዮጵያ ኢንተርፕርነርሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት (EDI) ምስጋናዬ የላቀ ነው።

​ዩኒቨርሲቲ የእውቀት ማከማቻ ብቻ ሳይሆን የሀገር ኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ሞተር መሆን አለበት!
፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥
ግንቦት 1 ቀን 2018 ዓ.ም

The role of leadership is pivotal in our journey toward transforming our university into an "Entrepreneurial University."

​In collaboration with the Entrepreneurship Development Institute (EDI) - Ethiopia, our university has officially launched a three-day training program starting today, May 9, 2026.

Attended by college deans and executive officers, this program is designed to equip our leadership with the fundamental insights necessary to establish our institution as a hub for innovation and entrepreneurship.

​This training will play a significant role in:
​Strengthening Public Entrepreneurship and Innovation Ecosystem Building within our institution; ​Empowering leadership with the skills and mindset required to support creative works and translate them into practical ventures; and
​Enhancing the university’s community services through innovation-driven approaches.

​This forum is more than just a theoretical exercise; it is a platform where we deliberate on how to practically transform our university into a center of excellence for innovation. As we transition toward becoming an Autonomous institution, embracing an entrepreneurial mindset is no longer an option but a necessity. This means building a system where:
​Our research is translated into practical applications and enters the market; ​Our students adopt a "job creator" rather than a "job seeker" spirit; and ​Our institution generates its own internal revenue while leaving a significant footprint on national development.

​This is precisely how the world’s leading universities became the bedrock of their nations' prosperity:
Stanford University(USA): A primary catalyst for the creation of Silicon Valley, serving as a leading model for an entrepreneurial university by facilitating the birth of thousands of companies.

Technical University of Munich (TUM) (Germany): Under the motto "The Entrepreneurial University," it achieves high-level technology transfer in Europe by integrating education, research, and business creation.

Nanyang Technological University, Singapore (NTU) (Singapore): Within just a few decades, it has contributed immensely to the country’s economic growth by commercializing research results and strengthening industry ties.

​The key lesson from these institutions is that a university should be an engine of the economy, not just a warehouse of knowledge. The training we launched today with EDI is a major step toward aligning the University of Gondar with this transformative path.

​I extend my deepest gratitude to the Entrepreneurship Development Institute (EDI) for their significant contribution to our grand journey toward becoming an Entrepreneurial University.

​A university must be an engine for the national economy, not just a storehouse of knowledge!
፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥
May 9, 2026

Address

Maraki
Gondar
P.O.BOX196

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00

Telephone

+251581141231

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Asrat Atsedeweyn posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Asrat Atsedeweyn:

Share