Welkait Tegede Setit Humera Zone Disaster Risk Management Office

Welkait Tegede Setit Humera Zone Disaster Risk Management Office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Welkait Tegede Setit Humera Zone Disaster Risk Management Office, Government Organization, W/T/S/HUMERA ZONE, Gondar.

የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አደጋ ስጋት ስራ አመራር ተጠሪ ጽ/ቤት ኦፊሴላዊ የፌስቡክ ገጽ ነው። ገጹ ስለ አደጋ መከላከል፣ ቅድመ ማስጠንቀቂያ፣ ፈጣን ምላሽ፣ የእርዳታ ስራዎች፣ የግንዛቤ ማስፋፊያ መረጃዎች፣ የመስክ እንቅስቃሴዎች እና ሌሎች ከአደጋ ስጋት ጋር የተያያዙ ኦፊሴላዊ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ያቀርባል።

የጠገዴ ወረዳ በጎ አድራጎት ማህበር ለክረምት በጎ ፈቃድ ተግባር የሚውሉ ቁሳቁሶችን አስረከበ📍 ጠገዴ | ነሐሴ 28/2018 ዓ.ምበአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ...
04/09/2026

የጠገዴ ወረዳ በጎ አድራጎት ማህበር ለክረምት በጎ ፈቃድ ተግባር የሚውሉ ቁሳቁሶችን አስረከበ
📍 ጠገዴ | ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን የጠገዴ ወረዳ በጎ አድራጎት ማህበር፣ በተጠናከረ መንገድ እየተካሄደ ለሚገኘው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁሶችን አስረክቧል።
ማህበሩ ከበጎ አድራጊ ግለሰቦችና ድርጅቶች በሰበሰበው ሀብት የ42,090 ብር ግምት ያላቸው 45 ቆርቆሮዎች፣ 16 ደርዘን ደብተሮችና 3 ፓኮ እስክርቢቶዎችን ለጠገዴ ወረዳ ሴቶችና ወጣቶች ማህበራዊ ጽ/ቤት እና ለወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት አስረክቧል።
“በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል ለተጀመረው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተደረገው ይህ ድጋፍ፣ አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ለማቅረብ እንዲሁም ለአቅመ ደካሞችና አረጋውያን መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባትና ያረጁ ቤቶችን ለመጠገን እንደሚውል ተገልጿል።
በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ከመፍታት ባለፈ የእርስ በርስ ትስስርንና የመረዳዳት ባህልን የሚያጠናክር መልካም ተግባር በመሆኑ፣ ሌሎችም በመሳተፍ የወገን ደራሽነታቸውን እንዲያሳዩ ጥሪ ቀርቧል።
ምንጭ፡ ጠገዴ ወረዳ ኮሙኒኬሽን

04/09/2026
በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በቃብትያ ወረዳ አደባይ ቀበሌ በበረዶ የተቀላቀለ ከፍተኛ ዝናብ ጉዳት አደረሰበ26/12/2018 ዓ.ም በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን፣ በቃብትያ ወረዳ አ...
04/09/2026

በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በቃብትያ ወረዳ አደባይ ቀበሌ በበረዶ የተቀላቀለ ከፍተኛ ዝናብ ጉዳት አደረሰ
በ26/12/2018 ዓ.ም በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን፣ በቃብትያ ወረዳ አደባይ ቀበሌ በጣለው ከፍተኛ በረዶ የተቀላቀለ ዝናብ በቋሚና ጊዜያዊ ሰብሎች፣ በሰብል ልማት፣ በእንስሳትና በመኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት ደርሷል።
በአደጋው የተጎዱ ቋሚ ተክሎች ውስጥ 21.5 ሄክታር ሙዝ፣ 1 ሄክታር ፓፓያ፣ 92 የማንጎ ዛፎች፣ 80 የሎሚ ዛፎች፣ 30 የቡና ዛፎች፣ 20 የጌሾ ዛፎች እና 5 የአቮካዶ ዛፎች ይገኙበታል።
በጊዜያዊ ሰብሎች ደግሞ 35 ሄክታር ሽንኩርት፣ 1.5 ሄክታር ቃሪያ፣ 0.25 ሄክታር ባሚያ እና 1,000 እግር ኮድኮዴ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
በተጨማሪም በሰብል ልማት 70 ሄክታር ሰሊጥና 4 ሄክታር ጥጥ በድምሩ 74 ሄክታር የሰብል ማሳ በአደጋው ተጎድቷል።
ከዚህ በተጨማሪ በአደጋው 18 እንስሳት ሞተዋል፤ 4 የቆርቆሮ ቤቶችም ፈርሰዋል።
ዛሬ የዞን ህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች፣ የዞንና የወረዳ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ባለሙያዎች፣ የመስኖ ባለሙያ፣ የዞኑ ግብርና ኃላፊ እንዲሁም የተጎዱ ባለሀብቶች በመሆን ቦታው ድረስ በመሄድ የደረሰውን ጉዳት በአካል ተመልክተው ቅድመ ግምገማ አካሂደዋል።

04/09/2026

እየተጠናከረ የመጣው ኤል ኒኖ ከባድ የአየር ሁኔታ ስጋት እያሳደረ እንደሆነ ተገለጸ

የዓለም ሜትሮሎጂ ድርጅት እንደገለጸው አሁን ላይ እየተስተዋለ የሚገኘው የኤል ኒኖ ክስተት በ70 ዓመታት ውስጥ ከታዩት በጣም ኃይለኛ ክስተቶች አንዱ ሊሆን እንደሚችል ያስታወቀ ሲሆን፥ክስተቱም ቢያንስ እስከ የካቲት 2027 ሊቀጥል እንደሚችል ተገልጿል።

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ዓለም ከፍተኛ የአየር ሁኔታ አደጋ ወደሚበዛበት ደረጃ እየገባች መሆኑን አንስተው፥ኤል ኒኖ እየጠነከረ በመምጣቱ የድርቅ፣ የጎርፍ፣ የመሬት ናዳ እና የከፍተኛ ሙቀት አደጋዎች ሊባባሱ እንደሚችሉ ተናግረዋል።

በፓሲፊክ ውቅያኖስ ማዕከላዊና ምሥራቃዊ ክፍል የባሕር ሙቀት በቅርብ ወራት በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረ ሲሆን፥በተለይም የባሕር ወለል ሙቀት ከመደበኛው በ2 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል ።

የኤል ኒኖ ተጽዕኖ በሰው ልጅ ከሚመነጨው የረጅም ጊዜ የአየር ንብረት ሙቀት መጨመር ላይ ተደምሮ የከፋ የአየር ሁኔታ ሊያስከትል እንደሚችል ሳይንቲስቶች ገልጸዋል።

ባለሙያዎች በበኩላቸው የኤል ኒኖ ተጽዕኖ በሰዎች ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ ቅድመ ማስጠንቀቂያ፣ የሕክምና ድጋፍና የአደጋ ዝግጅት ሥርዓቶችን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

04/09/2026
04/09/2026

"የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ"

የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ ሚቴዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው የሆኑ የደቡብና ደቡብ ምሥራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ተገልጻል።

ኢንስቲትዩቱ ለጋዜጣ ፕላስ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በሚቀጥሉት አሥር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ።

በመጪዎቹ አሥር ቀናት ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና መካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ የጠቆመው ኢንስቲትዩቱ፤ በሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ መካከለኛውና ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር አመላክቷል።

በወሩ የመጨረሻ ሳምንት ዝናብ ሰጪ ክስተቶች እየተዳከሙ እንደሚመጡ በመግለጽ፤ አብዛኞቹ የሰሜን ምሥራቅ፣ መካከለኛውና ምሥራቅ አካባቢዎች በበጋው ደረቅ የአየር ጠባይ ተፅዕኖ ሥር መሆን እንደሚጀምሩ ተጠቅሷል።

በምዕራብ አማራ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና የኦሮሚያ ምዕራባዊ አጋማሽ ላይ የክረምቱ ዝናብ እስከ ወሩ መጨረሻ ድረስ እንደሚቀጥልም መግለጫው ያመላክታል።

የምሥራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች፣ የሶማሌ ማዕከላዊ እና ደቡባዊ ክፍል፣ ከኦሮሚያ ምዕራብና ምሥራቅ ሐረርጌ፣ አርሲ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምሥራቅ ባሌ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ የሲዳማና የአፋር ደቡባዊ ክፍል ቀላል መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል የደቡብ ኢትዮጵያ፣ ከደቡብ ኦሮሚያ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምሥራቅ ቦረና ዞኖች፣ እንዲሁም የደቡብ ሶማሌ አካባቢዎች ከወሩ አጋማሽ ጀምሮ ዝናብ እንደሚያገኙ ተመላክቷል።

03/09/2026

Address

W/T/S/HUMERA ZONE
Gondar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Welkait Tegede Setit Humera Zone Disaster Risk Management Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share