West Gondar zone Labor and Training Office

West Gondar zone Labor and Training  Office government organazation

22/05/2025
በምዕራብ ጎንደር ዞን በገንዳዉሃ ከተማ አስተዳደር በኢንተርፕራይዝ ለተደራጁ ወጣቶች በከተማዉ ስራና ስልጠና ፅ/ቤት አማካኝነት ከ4.3 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጭ የድንጋይ መፍጫ ማሽን(ክሬ...
07/06/2023

በምዕራብ ጎንደር ዞን በገንዳዉሃ ከተማ አስተዳደር በኢንተርፕራይዝ ለተደራጁ ወጣቶች በከተማዉ ስራና ስልጠና ፅ/ቤት አማካኝነት ከ4.3 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጭ የድንጋይ መፍጫ ማሽን(ክሬሸር) ርክክብ ተካሄደ።

ፋሲካ፣ ሀብታሙና ጓደኞቻቸዉ የተሰኘዉ ኢንተርፕራይዝ ከአመት በፊት በቀበሌ ደረጃ በመመዝገብና አስፈላጊዉን ህጋዊ ሰዉነት በማሟላት ከቆዩ በኋላ በዛሬዉ እለት ማሽኑን ሊረከቡ ችለዋል።

የማህበሩ አባል የሆኑት ፋሲካዉ ጀጃዉና ፋሲካ አያሌዉ እንደገለፁት በዚህ ስራ ዉጤታማ የሆኑ ጓደኞቻችንንና ጎረቤቶቻችን በማዬትና እነሱን በማማከር እኛም ዉጤታማ እንሆናለን ብለን በማሰብ ወደዚህ ሰራ ለመሰማራት እንዳሰቡ ገልፀዋል።

ወጣቶቹ አያይዘዉም እዚህ ደረጃ እንድንደርስ እገዛ ላደረገልን የከተማ አስተዳደሩ ትልቅ ምስጋናቸዉን በማስቀደም ራሳችንን እስክንችልና ዉጤታማ እስከምንሆን ድረስ የተለያዩ እገዛዎችና ድጋፎች እንዳይለያቸዉ ሀሳባቸዉን ሰጥተዋል።


በርክክቡ ላይ ተገኝተዉ መልእታቸዉን ያስተላለፉት የገንዳዉሃ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ይግለጥ አበባዉ አንዳሉት አሁን ላይ በከተማችን ወጣቶች ዘንድ እየተንፀባረቀ ያለዉ ምንም እሴት በማይጨምሩ እንደ ''ድለላ'' ባሉ መስኮች መሰማራት እንጅ እንደዚህ ጉልበትን ተጠቅሞና ላብን ጠብ አድርጎ ዉጤት በሚያመጣ ስራ ለመስማራት አዳጋች እየሆነ መምጣቱን አስታዉሰዉ እናንተ ደግሞ ይህን የስራ ዘርፍ መምረጣችሁ የሚያስመሰግናችሁ መሆኑን እየገለፅኩ በሚገባ ዉጤታማ እስከምትሆኑ ድረስ የሚደረግ እገዛ ካለ የሚመለከተዉ አካል ትብብርና እገዛ የሚያደርግ መሆኑን አስረድተዋል።

በርክክብ ስነ ስርአቱ ላይ ከንቲባዉን ጨምሮ የገንዳዉሃ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ አብዱልከሪም መሀሙድ እንዲሁም የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት አቶ ሙሉጌታ መለሰ፣ የስራና ስልጠና ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ገዛኸኝ ሞገስና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል።

መረጃው፦የገንዳዉሃ ከተማ አስተዳደር መ/ኮሙኒኬሽን ነው።
ግንቦት 30/2015

27/05/2023
በምዕራብ ጎንደር ዞን የተሠጠንን የ5 ወር ልዩ እቅድ ጠቅላላ የወረዳ:የከተማና የዞን አመራሮች በተገኙበት እቅዱን ያቀረብን ሲሆን ለሁሉም ወረዳና ከተማ ስራናስልጠና ጽ/ቤት  የዞኑ አስተዳዳሪ...
27/05/2023

በምዕራብ ጎንደር ዞን የተሠጠንን የ5 ወር ልዩ እቅድ ጠቅላላ የወረዳ:የከተማና የዞን አመራሮች በተገኙበት እቅዱን ያቀረብን ሲሆን ለሁሉም ወረዳና ከተማ ስራናስልጠና ጽ/ቤት የዞኑ አስተዳዳሪና የዞኑ ብልጽግና በተገኙበት የዉል መፈራረም ተካሂዷል።

ቀን 19/09/15 ዓ/ም

በኢንተርፕራይዝ  የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸው እየሰሩ ለሚገኙ ወጣቶች በኢንተፕርነር ሽፕ እና የቢዝነስ ፕላን አዘገጃጀት ዙሪያ  ስልጠና ተሰጠ*********** ስልጠናው የቋራ ወረዳ ስራና ስልጠ...
15/05/2023

በኢንተርፕራይዝ የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸው እየሰሩ ለሚገኙ ወጣቶች በኢንተፕርነር ሽፕ እና የቢዝነስ ፕላን አዘገጃጀት ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ
***********
ስልጠናው የቋራ ወረዳ ስራና ስልጠና ጽ/ቤት እና የገለጉ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ አማካኝነት ለወጣቶች ስልጠና የተሰጠ መሆኑን ተገልፃል።

በስልጠናው የተገኙት የቋራ ወረዳ ስራና ስልጠና ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድማገኝ አበራ ስልጠናው ለወጣቶች ካሉበት የስራ ደረጃ ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲያሳድጉ እና እራሳቸውን በተለያዩ የስራ ዘርፎች ላይ አሰመርተው ማሳደግ እንዲችሉ የሚያደርግ መሆኑን ገልፃዋል።

አቶ ወንድማገኝ እንደገለፁት ወጣቶች የስራቸውን የቢዝነስ ብላን በማዘጋጀት ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በጋራ በመስራት በኢኮኖሚ እራሳቸውን ማሳደግ የሚችሉበትን ሁኔታ እንደሚፈጥርም ተናግረዋል።

ቋራ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት
ግንቦት 7/2015 ዓ/ም

የገንዳውኃ ከተማ አስተዳደር ቴክኒክና ሞያ ኮሌጅ የምዝገባ ጊዜውን እንዳራዘመ ገለፀ ።ኮሌጁ ከዚህ በፊት የምዝገባ ጊውን ማሳወቁ ይታወቃል። ይሁን እንጅ አሁንም ለተማሪዎች ሰፊ የምዝገባ ቀን ...
23/03/2023

የገንዳውኃ ከተማ አስተዳደር ቴክኒክና ሞያ ኮሌጅ የምዝገባ ጊዜውን እንዳራዘመ ገለፀ ።

ኮሌጁ ከዚህ በፊት የምዝገባ ጊውን ማሳወቁ ይታወቃል።
ይሁን እንጅ አሁንም ለተማሪዎች ሰፊ የምዝገባ ቀን ለመስጠትና ተማሪዎች የተሠጠውን የመማር እድል ግምት ውስጥ በማስገባት ከዚህ በታች መስፈርቱን የሚያሟሉ ተማሪዎችን ከመጋቢት13/2015 እስከ መጋቢት19/2015 ድረስ እንድትመዘገቡ ሲል ኮሌጁ መልክቱን አስተላልፏል ።

መማሳሰቢያ የሰልጣኝ ቅበላው በቀድሞው 10ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ተማሪዎችን ይጨምራል ።

ገንዳውኃ ከተማ ኮሙኒኬሽን
መጋቢት 14/2015 ዓ.ም

የገለጉ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመረቀመንግስት ትኩረት ከሰጣቸው ዘርፎች ውስጥ የስራና ስልጠና ዘርፍ ነው በመሆኑም ወቅቱንና ዘመኑን የዋጀ በዝቅተኛና በ...
18/03/2023

የገለጉ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመረቀ

መንግስት ትኩረት ከሰጣቸው ዘርፎች ውስጥ የስራና ስልጠና ዘርፍ ነው በመሆኑም ወቅቱንና ዘመኑን የዋጀ በዝቅተኛና በመካከለኛ ደረጃ የሰለጠነ ኃይል በማቅረብ የተሟላ የኢንዱስትሪ ኤክስቴሽን አገልግሎት ለመስጠት አዋጭ የሆነ የቴክኖሎጅ ሽግግር በማድረግ የበለፀገች ኢትዮጵያ ለመገንባት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ወሰኝ ናቸው ይህንን መነሻ ያደረገ የገለጉ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በ2011 የትምህርት ዘመን ትምህርት በመጀመር አሁን ላይ 19 ወንድና 57 ሴት በድምሩ 76 ተማሪዎችን ማስመረቁን የቋራ ወረዳ ኮሙኒኬሽን በምረቃ ፕሮግራም ተገኝቶ ዘግቧል።

በምርቃት ስነ ስርዓቱ የዞንና የወረዳ አመራሮች የኮሌጁ መምህራን ተመራቂ ተማሪዎችና የተመራቂ ቤተሰቦች በተገኙበት የምረቃ ስነ ስርዓቱ ተካሄዷል።

በምርቃ ስነ ስርዓቱ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ተወካይና ምክትል ዲን ኢንስትራክተር አለማየሁ ለምርቃት የበቁ የኮሌጁ ተማሪዎችንና ቤተሰቦቻቸውን እንኳን ደስ ያላችሁ እያሉ ኮሌጁ የነበሩትን በርካታ ችግሮች ተወጥቶ ባለው ማቴሪያልና መምህራን መሰረት ተማሪዎችን ለምርቃት ማብቃቱን ገልፃዋል።

ኮሌጁ በተለያዩ ዲፓርትመቶች መስረት አቅም ያላቸውን በተለያዩ የስራ ዘርፎች መስራት የሚችሉ ተማሪዎችን ያፈራ ኮሌጅ ሲሆን በቀጣይ የሚቀበላቸውን ተማሪዎች ውጤታማ ለማድረግ የሚመለከተው አካል ለኮሌጁ የሚያስፈልጉ ከመኪና እስከ የኮሌጅ የማስተማሪያ ማቴሪያሎች ድረስ መሟላት እንዳለበት ተናግረዋል።

የምዕራብ ጎንደር ዞን የስራና ስልጠና ምክትል መምሪያ ኃላፊ አቶ አስፋው በሪሁን በበኩላቸው ምሩቃን ተማሪዎችን እንኳን ደስ አለችሁ እያሉ ምሩቃን ተማሪዎች በተመረቃችሁበት የሙያ መስክ ስራ በመፍጠር እራሳቸውንና ሃገራቸውን የስራ ዕድል መፍጠሪያ ዘርፉን ማሳደግ እንዳለባቸው አንስተዋል።

የቋራ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደጃዝማች ካሳሁን ምርቃን ተማሪዎችን የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈው ኮሌጁ ተማሪዎችን ለማስመረቀ የሄደበትን እርቀት አድንቀው ሌሎች ተማሪዎችን በመቀበል ለሚደረጉ የመማር ማስተማር ወረዳው የበኩሉን ለኮሌጁ ድጋፍ እንደሚያደርግም ተናግረዋል።

በመጨረሻም ጥሩ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎችና በመመር ማስተማሩ ጥረት ሲያደርጉ ለነበሩ መምህራን እንዲሁም ለኮሌጁ ድጋፍ ላደረጉ ግለሰቦችና ሴክተር መስሪያ ቤቶች የምስገና የምስክር ወረቀት ተበርክቷል።

መጋቢት 9/2015 ዓ.ም
(ቋራ ኮሙኒኬሽን)

13/03/2023

ከገለጉ ቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጅ ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ የተላለፈ መልእክት

የገለጉ ቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ወስዳችሁ ለቴክኒክ ሙያ የመግቢያ ነጥብ ያመጣችሁ ሰልጣኞችን ተቀብሎ ከቀን 04/07/2015 ዓ.ም እስከ 22/07/2015 ዓ.ም ምዝገባ ስለሚካሄድ በአካል ኮሌጁ ድርስ በመምጣት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን የገለጉ ቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ መልእክቱን ያስተላልፋል፡፡

የሚሰጥባቸው የሙያ መስኮች
1ኛ. ዳታ ቤዝ አድሚኒስትሬሽን
2ኛ.ኮንስትራክሽን
3ኛ. አኒማል ፕሮዳክሽን( እንስሳት እርባታ)

የቅበላ መስፈርቶች፡-
የስልጠና ደረጃ ለማህበራዊ ሳይንስ ለተፈጥሮ ሳይንስ
ደረጃ 1 ደረጃ 2
ለወንዶች 148 እና ከዚያ በታች 157 እና ከዚያ በታች
ለወንዶች 148 እና ከዚያ በታች 157 እና ከዚያ በታችዚያ በታች
ለአካል ጉዳተኞች 130 እና ከዚያ በታች 130 እና ከዚያ በታች
ደረጃ 3 ደረጃ 4
ለወንዶች ከ149 እስከ 202 ከ158 እስከ 245
ለሴቶች ከ142 እስከ 170 ከ157 እስከ 217
ለአካል ጉዳተኞች ከ131 እስከ 148 ከ131 እስከ 148

ለመመዝገብ ስትመጡ የመመዝገቢያ 50 ብር እና የ2 ወር የወጭ መጋራት 300 ብር በድምሩ 350 ብር መክፈል ይኖርባችኋል፡፡

ማሳሰቢያ፡-የ10ኛ ክፍል ጨራሽ ተማሪዎችን ጭምር የምናስተናግድ ይሆናል፡፡

ቋራ፡- መጋቢት 04/2015 ዓ.ም ( ቋራ ኮሙኒኬሽን)

27/02/2023

Address

Gendwuha
Gonder

Telephone

+251991480992

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when West Gondar zone Labor and Training Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to West Gondar zone Labor and Training Office:

Share