Posetivity is prefer To all things.

Posetivity is prefer To all things. ለሰውና ለሀገር የሚጠቅም ነገር ለመስራት ግዜ አያስፈልግም። ማህበራዊ ሚዲያ ግዜን በተገቢው ይፈልጋል። እውነት ለሀገር ግንባታ እንስራ ለዚህም ግዴታ አመራር መሆን አይጠበቅም። በዚህ ገጽ ትውልድ ስለ ሀገር ያለው ሚናና እውነተኛ መረጃ የሚለቀቅበት ነው።

ጠቃሚ ሀገራዊ ወቅታዊ መረጃዎች በገጹ መልቀቅ

21/08/2026
ኢትዮጵያ እየመከረች ነው!!የአጀንዳ ምክረሀሳቦች ለ4ሺ ጉባኤተኞች እየቀረቡ ነውከሀምሌ 8/2018 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ መጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሷል።...
21/08/2026

ኢትዮጵያ እየመከረች ነው!!

የአጀንዳ ምክረሀሳቦች ለ4ሺ ጉባኤተኞች እየቀረቡ ነው

ከሀምሌ 8/2018 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ መጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሷል።

በስምንት አጀንዳዎች ላይ ሲመክሩ የቆዩት 4ሺ ጉባኤተኞች በአሁኑ ሰዓት በእያንዳንዱ አጀንዳ ላይ የተጠናቀሩ የመጨረሻ የአጀንዳ ምክረሀሳቦችን በማዳመጥ ላይ ይገኛሉ።

የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሰላም፣የአብሮነትናየብልጽግና ተምሳሌት ነው።
18/08/2026

የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሰላም፣የአብሮነትናየብልጽግና ተምሳሌት ነው።

 #እኖርወረዳ የቀጣይነት ተምሳሌት የከዚህ በፊት አረንጓዷ አሻራ በከፊል
03/08/2026

#እኖርወረዳ የቀጣይነት ተምሳሌት የከዚህ በፊት አረንጓዷ አሻራ በከፊል

አረንጓዴ አሻራ የአብሮነትና የትውልድ ቀረጻ መገለጫ ነው። በርቱ
03/08/2026

አረንጓዴ አሻራ የአብሮነትና የትውልድ ቀረጻ መገለጫ ነው። በርቱ

ሀምሌ 27/2018 ዓ/ም
አረንጓዴ አሻራ በሀገራችን ለቀጣዩ ትውልድ የጋራ የሆነችና ውብ የማትለምን ሀገር ገንብቶ ለማስረከብ እየተደረገ ያለ የተሟላ እንቅስቃሴ ነው።
"ተስፋን እንትከል"በሚል መሪ ቃል ዛሬ በእኖር ወረዳ በአንድ ጀንበር 453,691 ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኝ ተከላ ተካሂዷል። በተከላው 53,206 የወረዳው የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ሆኖዋል።

የእኖር ወረዳ ዋና አስተዳደር የተከበሩ አቶ መብራቴ ተክሌ እና የእኖር ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊና ዋና የመንግስት ተጠሪ የተከበሩ አቶ ሞሸዲን አህመድ በጋራ የእንኳን ደስ አለን መልእክት አስተላልፏል።

#እኖርወረዳብልጽግናፓርቲ

“በአራት ዓመታት ውስጥ ከሃያ ቢልዮን በላይ ችግኞችን በመላ ኢትዮጵያ ለመትከል አልሞ የተነሣው የአረንጓዴ አሻራ ፕሮጄክት፤ ሀገራችን በየዘመናቱ የሚገጥማትን ድርቅ እስከ ወዲያኛው የማስቀረት ...
31/07/2026

“በአራት ዓመታት ውስጥ ከሃያ ቢልዮን በላይ ችግኞችን በመላ ኢትዮጵያ ለመትከል አልሞ የተነሣው የአረንጓዴ አሻራ ፕሮጄክት፤ ሀገራችን በየዘመናቱ የሚገጥማትን ድርቅ እስከ ወዲያኛው የማስቀረት ዐቅም እንዳለው ምንም ጥርጥር የለዉም”

#የመደመርመንገድ

ሃሳብን መሰረት ያደረገው የምክክሩ ስልታዊ ጉዞ አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘመናት የተከሰቱ የፖለቲካ አለመግባባቶች፣ የትጥቅ ግጭቶች እና የተሳሳቱ ...
29/07/2026

ሃሳብን መሰረት ያደረገው የምክክሩ ስልታዊ ጉዞ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘመናት የተከሰቱ የፖለቲካ አለመግባባቶች፣ የትጥቅ ግጭቶች እና የተሳሳቱ ትርክቶች ሲፈትኗት ቆይተዋል።

ይህንንም ተከትሎ የጋራ መፍትሔ ለማፈላለግ፣ መተማመንን ለመገንባት እና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ሀገራዊ ምክክር እያከናወነች ትገኛለች፡፡

የምክክር ኮሚሽኑም ከአራት ዓመታት አድካሚ ዝግጅት በኋላ ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ታሪካዊ የምክክር ጉባኤውን በአዲስ አበባ መጀመሩ ይታወሳል፡፡

የዚህ የምክክር ጉባኤ ልዩ ስነ ዘዴ እያንዳንዱ ዜጋና ተወካይ ያለምንም ፍርሃትና መገለል ሃሳቡ ሳይቀበር በነጻነት እንዲያቀርብ የሚያስችል እጅግ ጥንቁቅ አደረጃጀትን የተከተለ ነው።

በሂደት ላይ የሚገኘው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ዛሬ የ250 ተመካካሪዎች የስልታዊ ቡድን ውይይት ጀምሯል።

የ250ዎቹ ስብስብ እነዚህን አጀንዳዎች በአንክሮ ያደምጣል፣ በስልታዊ እይታ ይመዝናል፣ በመጨረሻም የጋራ መግባቢያና መመሪያ እንዲሆኑ ተወያይቶ ያጸድቃቸዋል።

የ250ዎቹ ስልታዊ የቡድን ውይይት የተለያዩ እይታዎችን በሃሳብ ሚዛን ላይ አስቀምጦ፣ የጋራ መጻኢ ዕድልን በሰከነ መንፈስ ለመቅረጽ የሚደረግ ታላቅ የዲሞክራሲ ልምምድ ነው።

የዚህ ሀገራዊ ምክክር ዋናውና ትልቁ ጥንካሬ በሃሳብ ልውውጥና በጋራ ግንዛቤ ላይ ብቻ መመስረቱ ነው።

ሁሉም ነገር በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረግ መደማመጥ ላይ ብቻ የተንተራሰ መሆኑ የኮሚሽኑን ገለልተኝነትና የሂደቱን ታማኝነት ያሳያል።

አሁን እየተካሄደ ያለው የስልታዊ ቡድን ውይይት እንደተጠናቀቀ ምክክሩ በቀጣዩ ሳምንት 500 ተመካካሪዎችን ወደሚያሳትፈው ሰፊና ቀጣይ የምክክር ምዕራፍ ይሸጋገራል።

ይህም የኢትዮጵያ ህዝቦች በጋራ ጉዳዮቻቸው ላይ ለመወሰን እያደረጉት ያለው ጉዞ ተስፋ ሰጪ መሆኑን ያሳያል።

በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እየተከተለው ያለው ሳይንሳዊና ደረጃ በደረጃ የማሳደግ ስነ ዘዴ ሀገሪቱ ለዘመናት የተሸከመቻቸውን ውስብስብ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ትልቅ መሰረት እየጣለ ይገኛል።

ችግሮችን በውይይት በጠረጴዛ ዙሪያ መፍታት ኢትዮጵያ ወደ አዲስና አስተማማኝ የጋራ ተስፋ ምዕራፍ እየተሻገረች መሆኑን የሚያበስር ታሪካዊ ስኬት ነው።

በሶስና አለማየሁ

26/07/2026

"የመደመር መንግስት አሁን ባለው ስኬት መርካት የለብንም የበለጠ ለማግኘት መትጋት አለብን ብሎ ያምናል"

ጠቅላይ ሚኒስተር
ዐብይ አህመድ (ዶ/ር)

የእኖር ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ፌስቡክ ገጽ
https://www.facebook.com/share/18tfxPk7XC/

"ኢትዮጵያ እያማረባት ነው! በማንኛውም መመዘኛ እየወደቀ ካለ ሀገር ይልቅ እያደገ ካለ ሀገር ጋር መጓዝ ይመረጣል።"  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
06/07/2026

"ኢትዮጵያ እያማረባት ነው! በማንኛውም መመዘኛ እየወደቀ ካለ ሀገር ይልቅ እያደገ ካለ ሀገር ጋር መጓዝ ይመረጣል።" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Address

Wolkite

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Posetivity is prefer To all things. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Posetivity is prefer To all things.:

Shortcuts

Share