Tehuledere Woreda Gov. Communication/ተሁለደሬ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን

  • Home
  • Ethiopia
  • Haik
  • Tehuledere Woreda Gov. Communication/ተሁለደሬ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን

Tehuledere Woreda Gov. Communication/ተሁለደሬ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን በአለም ዙርያ የተከናወኑና የሚከናወኑ ሁነቶችን የምናስተላ?

01/09/2026
01/09/2026

በጠላቶች ትብብር የማይገታው የኢትዮጵያ ጽናት

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በታሪኳ በርካታ የውስጥና የውጭ ፈተናዎችን፣ የታሪካዊ ጠላቶቿን ጥምረትና የተደራጁ ሴራዎችን በጽናት በማሸነፍ ነጻነቷን አስከብራ የኖረች ሀገር ናት።

ትናንት አባቶቻችን በዓድዋ ድል የተባበረውን የቅኝ ግዛት ኃይል በጽናትና በአንድነት እንዳሸነፉት ሁሉ፣ ዛሬም እኛ የዚህ ትውልድ ልጆች ያንን ድል በዘመናዊ መልክ እየደገምነው እንገኛለን።

በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች ሀገሪቱ የኢኮኖሚ፣ የዲፕሎማሲና የደኅንነት ጫናዎች ሲያርፉባትም፣ የሕዝቡ የጋራ ማንነትና አገራዊ ፍቅር ፈተናዎቹን ወደ ዕድል የመቀየር አቅም ሆኖ አገልግሏል።

ለዚህም ማሳያ ከሆነው ሁነት ውስጥ በውስጥ ጉዳያችን ጣልቃ ለመግባትና ሉዓላዊነታችንን ለመገዳደር የተነሱ ኃይሎችን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብና በዓለም ዙሪያ የሚገኘው ዳያስፖራ ማህበረሰብ በአንድ ድምፅ “ኖሞር” (No More) በማለት የውጭ ሴራዎችን አክሽፏል፤ የኢትዮጵያ ጽናት ጊዜያዊ ሳይሆን ጥንታዊና መዋቅራዊ መሠረት ያለው መሆኑንም አሳይቷል።

በቅርብ ጊዜያት የኢትዮጵያ ጽናት በከፍተኛ ዓለም አቀፋዊ፣ ቀጣናዊና የውስጥ ፈተናዎች ውስጥ ያለፈበትና ጥንካሬዋ የተመሰከረበት ወቅት ነው። የውጭ ታሪካዊ ጠላቶችና የጥቅም ተጻራሪዎች የሀገሪቱን ጉዞ ለማደናቀፍ በተቀናጀና በተባበረ መልኩ የሰነዘሯቸው ተጽዕኖዎች በሕዝቡና በመንግሥት ጽናት መክነዋል።

እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያሉ ፕሮጀክቶች፣ የተለያዩ የውጭ ተፅዕኖዎችና የጠላቶች ዲፕሎማሲያዊ ትብብር ቢኖርባቸውም፣ በሕዝቡ ጽናትና የገንዘብ ድጋፍ እውን መሆን ችለዋል። የ”አጎዋ”(AGOA) ዕድልን በመሰረዝና በመጫን ሀገራዊ ውሳኔዎችን ለመጠምዘዝ ቢሞከርም፣ ኢትዮጵያ እነዚህን ጫናዎች ተቋቁማ በራሷ አቅም መደበኛ ሥራዎቿንና ግዙፍ የኮሪደር ልማቶቿን ሳታቋርጥ አስቀጥላለች።

ኢትዮጵያ የምትገኝበት ቀጣና ለዓለም አቀፍ ንግድና ደኅንነት ወሳኝ በመሆኑ፣ የተለያዩ ጥቅምና ፍላጎት ያላቸው ኃይሎች በጋራም ሆነ በተናጠል ተፅዕኖ ለማሳደር ይሞክራሉ።

ነገር ግን የኢትዮጵያ የመንግሥት መዋቅር፣ ጠንካራ ማኅበራዊ እሴቶች እና ለነፃነት የሚሰጠው የላቀ ክብር ሀገሪቱ በማንኛውም ዓይነት የጠላቶች ትብብር እንዳትገታ ያደረጓት ዋና ምስሶዎች ናቸው።

ይህ የኢትዮጵያ የአይበገሬነት ታሪክ ለወደፊት ትውልድም ትልቅ ትምህርትና የጥንካሬ ምንጭ ሆኖ የሚቀጥል ነው።

ኢትዮጵያ ለቀጠናው ሰላም ያላትን ቁርጠኝነት ሳታጥፍ፣ የሕዝቦቿን የህልውና ጥያቄ ለመመለስ የምታደርገውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት በጽናትና በማይናወጥ አቋም እየገፋችበት ትገኛለች።

የቅርብ ጊዜ ታሪካችን የሚያሳየው የኢትዮጵያ ጠላቶች ስልታቸውን ቀይረው በዲጂታል ሚዲያ፣ በዲፕሎማሲና በኢኮኖሚ ማዕቀብ ተባብረው ቢመጡም፤ የሀገሪቱ የቆየ የመንግሥትነት መዋቅርና የሕዝቡ የነፃነት አርበኝነት ጽናት ዛሬም የማይበገር ጋሻ ሆኖ መቀጠሉን ነው።

በትዕግስት ግዛቸው

"የሕዝብን መብት እና ጥቅም ማስከበር የጋራ ግባችን መኾን አለበት" ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደየአማራ ክልል ከፍተኛ እና መከካለኛ መሪዎች የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲ እና የመንግሥት ሥራ...
31/08/2026

"የሕዝብን መብት እና ጥቅም ማስከበር የጋራ ግባችን መኾን አለበት" ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

የአማራ ክልል ከፍተኛ እና መከካለኛ መሪዎች የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲ እና የመንግሥት ሥራዎች አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት የዕቅድ ትውውቅ መድረክ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ክልሉ በፈተና ውስጥም ኾኖ ውጤታማ የፓርቲ እና የመንግሥት ሥራዎችን ማከናወኑ ተመላክቷል። የክልሉ ፈተና የኾነውን ጽንፈኝነትን በመታገል እና የክልሉን ሰላም ለማረጋገጥ በርካታ ሥራ ተሠርቷል። አሁንም የክልሉን የጸጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት በአንድነት መሥራት እንደሚገባ ተነስቷል።
ብልሹ አሠራርን እና ሌብነትን መታገል እንደሚገባም ተገልጿል።

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ መሪዎች በሁሉም ሥራዎች ላይ የጋራ መዳረሻ ርዕይ ይዘው እየሠሩ ነው ብለዋል። የጋራ መዳረሻ ርዕይ ብቻ ሳይኾን የጋራ መግባባት እና ዕውቀት የያዙ ናቸው ነው ያሉት።

ችግሮችን እየተጋፈጡ ውጤት የሚያመጡ መሪዎች መፈጠራቸውን ገልጸዋል። አብዛኛዎቹ መሪዎች መስዋዕትነት እየከፈሉ ለሕዝብ እየሠሩ መኾናቸውንም አንስተዋል። በችግር የማይረበሽ እና ችግሩን የሚጋፈጥ መሪ ተፈጥሯል ነው ያሉት።

በበጀት ዓመቱ ወገንን ያኮራ፤ ጽንፈኛውን ደግሞ ያሳፈረ ስኬታማ ምርጫ በክልሉ መካሄዱን ገልጸዋል። የክልሉ ሕዝብ ለሀገራዊ ምክክር አጀንዳዎችን እንዲያሠባሥብ እና በጉባኤ ላይ ውጤታማ አስተዋጽኦ እንዲያደርግ የተደረገበት ዓመት እንደነበርም ተናግረዋል።

የልማት ሥራዎችን በውጤታማነት ለመፈጸም በርካታ ሥራዎች መፈጸማቸውንም አንስተዋል። በርካታ የታጠቁ ጽንፈኞችን ወደሰላም የመመለስ ሥራ ተሠርቷልም ነው ያሉት።

ጽንፈኛው ቡድን ከሕዝብ መነጠሉንም ገልጸዋል። ሕዝብ የጽንፈኛውን ሀሳብ እና ድርጊት አምርሮ መጥላቱንም አንስተዋል። በርካታ ቁጥር ያላቸው ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለው መግባታቸውን ገልጸዋል። የጽንፈኛው መሪዎች የነበሩ የሰላም አማራጭን እየተቀበሉ መኾናቸውን ተናግረዋል።

አሁንም ጽንፈኝነትን የመታገል ሥራችን ይቀጥላል ብለዋል። ብሔርን፣ ሃይማኖትን፣ አካባቢን እና ሌሎችን መነሻ ያደረገን ጽንፈኝነት መታገል እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የክልሉን አንድነት ለመሸርሸር የሚሠሩ ኀይሎች እንዳሉ ያነሱት ርእሰ መሥተዳድሩ ይሄን አካሄድ አምርሮ መታገል እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የክልሉን ሕዝብ መብት እና ጥቅም ማስከበር ዋናው ዓላማችን እና ግባችን ነው ብለዋል። የክልሉን አንድነት ማጠናከር፣ በኢኮኖሚም ጠንካራ ማድረግ የሁላችንም ግብ መኾን አለበት ነው ያሉት። የትኛውም አይነት የፖለቲካ አካሄድ ልዩነት ይኑር በሕዝብ መብት እና ተጠቃሚነት ግን በጋራ መቆም አለብን ብለዋል።

መሪዎች ሙስና እና ብልሹ አሠራርን መታገል እንደሚገባቸውም አሳስበዋል። በታጠቁ ጽንፈኞች ላይ አሁንም ሕግ የማስከበር ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ነው ያሉት። ኀይልን ማሠባሠብ፣ ማጠናከር እና ሰላምን ማረጋገጥ ያስፈልጋልም ብለዋል። ከሕዝብ ሰላም ማስከበር ሥራዎች ባለፈ ሰላማዊ አማራጮች እና ውይይቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አንስተዋል።

ሕገ ወጥ ንግድን፣ እገታን፣ ሕገ ወጥ የመሳሪያ ዝውውርን እና ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን መታገል እንደሚገባም ተናግረዋል።

በሁሉም ዘርፍ ምርታመነትን ማሳደግ እና የአገልግሎት ቅልጥፍናን ማሻሻል እንደሚገባም ገልጸዋል። ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን ማሳደግ ያስፈልጋል ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ የክልሉን የማምረት አቅም በማሳደግ እንደ ሀገር የሚኖረውን አስተዋጽኦ ማሳደግ እንደሚገባም ተናግረዋል። ዘመናዊ ግብርናን ማሳደግ፣ በአትክልት እና ፍራፍሬ ያለውን አቅም አሟጦ መጠቀም እንደሚገባም ገልጸዋል።

በእንስሳት ሃብት ያለውን እምቅ አቅም መጠቀም እንደሚጠበቅም አንስተዋል። የኢንዱስትሪ ልማትን እና ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚገባም ገልጸዋል።

የኮንስትራክሽን ዘርፉን ማሳደግ ግድ እንደሚልም አንስተዋል። በክልሉ የተጀመሩ የልማት ፕሮጄክቶችን በወቅቱ ማጠናቀቅ ይገባልም ብለዋል።

በጸጥታ ችግር አካባቢያቸውን የለቀቁ ባለሀብቶችን መመለስ እንደሚገባም አስገንዝበዋል። የቱሪዝም መዳረሻ ልማትን ማስፋት እና ያለውን አቅም መጠቀም ይገባልም ነው ያሉት።

ትምህርት ላይ በትኩረት መሥራት አለብን ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ የተማረ ዜጋ ተወዳዳሪ ሀገር ይገነባል፤ ባለፉት ዓመታት የተጎዳውን የትምህርት ዘርፍ ማሻሻል እና ውጤታማ ማድረግ አለብን ነው ያሉት። በ2019 የትምህርት ዘመን የታቀደው ሁሉ እንዲሳካ ሁሉም በትኩረት እንዲሠራም አስገንዝበዋል።

የገቢ አሠባሠብ አቅምን ማሳደግ ይገባል፤ ገቢውን ያላሳደገ ክልል ራሱን አይችልም ነው ያሉት። በቅንጅት እና በቁርጠኝነት መሥራት ከቻልን ክልሉን በሁሉም ዘርፍ ማሳደግ እንችላለን፤ የክልሉን ሕዝብ ተጠቀሚነትም እናረጋግጣለን ብለዋል። መሪዎች በቁርጠኝነት እና በቅንጅት እንዲሠሩም አሳስበዋል።

አሚኮ

31/08/2026

እራስን የመቻል እና ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ እቃዎችን በተተኪ ምርት መቀየር የመቻል ሀገራዊ ኅልማችን የሚሳካው ቀጣይነት ባለው ፈጠራ እና ጠንክሮ በመስራት ብቻ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

30/08/2026
30/08/2026
በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ ከሀገር ውጭ እና በሀገር ውስጥ የሚኖሩ ባለ ሃብቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባር ላይ የላቀ አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ መሆናቸው ተገለፀ።ተሁለደሬ ፦ ነሃሴ...
28/08/2026

በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ ከሀገር ውጭ እና በሀገር ውስጥ የሚኖሩ ባለ ሃብቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባር ላይ የላቀ አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ መሆናቸው ተገለፀ።

ተሁለደሬ ፦ ነሃሴ 22/2018 (የተሁለደሬ ኮሙዩኒኬሽን)

በወረዳው የ02 ቆርኬ ቀበሌ ተወላጅ በውጭ ሀገር የሚኖሩት ወ/ሮ ሳራ እሸቱ የዘንድሮውን ጨምሮ በቀበሌው በተለያዩ ጊዜያት በዘርፉ ብዙ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ ተሳትፎ እያደረጉ መሆናቸውን የቀበሌው አሰተዳደር አስታወቀ።

ወ/ሮ ሳራ እሸቱ የቆርኬ የመጀመሪያ ጀረጃ ት/ቤት ለማሻሻል የመማሪያ ክፍሎች ፣ደረጃውን የጠበቀ መፀዳጃ ቤት በመገንባት እና የንፁህ መጠጥ ዉሃ አቅርቦት የሚሆን የውሃ መስመር በመዘርጋት የት/ቤቱን ማህበረሰብ ተጠቃሚ አድርገዋል።

በተጨማሪም በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ወላጆቻቸው ላጡ እና የኢኮኖሚ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው 34 ተማሪዎች ለ3 ተከታታይ ዓመታት 1ሚሊዮን ሰማኒያ ስምንት ሽ ብር ድጋፍ እያደረጉ ከመሆናቸውም በላይ በ2019 ዓ.ም የት/ዘመን 50 ደርዘን ደብተር 150 ባኮ እስክርቢቶ ገዝተው በመደገፍ ለወገናቸው ያላቸውን አለኝታነት በተግባር አረጋግጠዋል።

ሌላኛዋ በጎ አድራጊ ወ/ሮ ሉባባ ሰይድ ሲሆኑ 90 የተመሪዎች መቀመጫ ወንበሮች ፣250 ደርዘን ደብተር ፣550 እስክርቢቶ 536 እርሳስና የቤተ ሙከራ ቁሳቁስች ፣1ደስክ ቶፕ ከነ-ፕሪንተሩ 95 የማሪያ መፅሀፍትን ጨምሮ የማጠናከሪያ ትምህርት ለሚያስተምሩ መምህራን ክፍያ በመፈፀም የበጎ አድራጎት ተግባር አርዓያ መሆን ችለዋል።

አቶ አፈወርቅ አስፋው የአካባቢ ተወላጅ እና በጎ አድራጊ ሲሆኑ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት 400 የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ፣ሳኒታይዘርና ፈሳሽ ሳሚና ፣ በ2019 ዓ.ም የት/ርት ዘመን ደግም 50 ደርዘን ደብተር ለተማሪዎች ድጋፍ በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን በመወጣት ላይ መሆናቸውን የአከባቢው ማህበረሰብ ምስክርነቱን ሰጥቷል።

በድጋፍ መርሃግብር ላይ የተገኙት የተሁለደሬ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት ኃለፊ እና የአስተዳደር ም/ቤት ተወካይ አቶ አያሌው አደም እንደገለፁት የተደረገው ድጋፍ የትሞህርት ጥራትን ለማምጣት የሚኖረው አስተዎጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

የተሁለደሬ ወረዳ ብልጽግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ደመቁ አበበ የተደረገው ድጋፍ በራሳችን አቅም ተደጋግፈን የሚያጋጥሙንን ችግሮች ማለፍ እንደምንችል ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ መሆኑን ያየንበት አርአያነት ያለው ተግባር ነው ብለዋል።

በመጨረሻም ለበጎ አድራጊዎቹ የእውቅና እና ምስጋና የምስክር ወረቀት በተወካዮቻቸው በኩል ተበርክቶላቸዋል።

*******************************************
ተጨማሪ መረጃዎችን ከተሁለደሬ ኮሙኒኬሽን ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጫኑ።
Facebook: https://www.facebook.com/tehulederecomunication
Telegram ፡https://t.me/+ehhHs-eR9n44OTA0
Twitter: https://x.com/Tehulederejxak
You Tube: https://youtube.com/?si=QQOZ7nnuOGI2jPBd
Tiktok: http://tiktok.com/
Instagram: https://www.instagram.com/tehuleder?igsh=bDdnNTN6NTlrcGFr

28/08/2026

ኢትዮጵያ እንደ ሕዳሴ ግድብ ሁሉ የባሕር በር ጥያቄዋንም ማሳካት የምትችል ታላቅ ሀገር ናት - ኡስታዝ ጀማል በሽር

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 22/2018 (ኢዜአ) ፦ ኢትዮጵያ እንደ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ሁሉ የባሕር በር ጥያቄዋን ማሳካት የምትችል ታላቅ ሀገር መሆኗን የዓባይ ንጉሶች ሚዲያ ባለቤት ኡስታዝ ጀማል በሽር ተናገሩ።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ የውሃ ሀብቶቿን በራሷ አቅም አልምታ መጠቀም እንደምትችል ያሳየ መሆኑንም ገልጸዋል።

ኡስታዝ ጀማል በሽር፤ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ቀጣናውን በኤሌክትሪክ ኃይል በማስተሳሰር ትብብርን ከማጠናከር አኳያ ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ለኢዜአ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ከተፋሰሱ ሀገራት ጋር ያላት ትብብር በጋራ ተጠቃሚነትና ልማት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ታላቁ የህዳሴ ግድብ በተግባር ማሳየቱንም ነው የጠቆሙት።

ኢትዮጵያ የውሃ ሀብቷን እንዳትጠቀም የሚከለክላት ማንም አካል እንደሌለ ጠቅሰው የሀገሪቷ የመልማት መብት ዓለም አቀፍ ህጎችና መርሆዎችን ያከበረ እንደሆነም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የውሃ ሀብቷን ተጠቅማ በቀጣይ ለማከናወን ያሰበቻቸው ስራዎች ሀገሪቷን ወደ ተሻለ ምዕራፍ የሚያሸጋግሩ ናቸው ሲሉም ተናግረዋል።

እየተጠናቀቁ ያሉ የመስኖ ግድቦች፣ አብዛኛው ስራ የተጠናቀቀው የኮይሻ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ፕሮጀክትና ሌሎች ስራዎች የኢትዮጵያን የልማት ውጥን እውን የሚያደርጉ ናቸው ብለዋል።

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ በሁሉም መስኮች ያሰበችውን እያሳካች መሆኑን ጠቅሰው፤ በከተማ ልማት፤ ቱሪዝም እንዲሁም በምክክር የመግባባት ዴሞክራሲን በመገንባት ረገድ ውጤታማ ስራ እያከናወነች ስለመሆኑ አብራርተዋል።

አሁን ደግሞ የኢትዮጵያ የብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ የሆነውን የባሕር በር ጥያቄ በይፋ አንስታለች ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ የህልውና ጉዳይ እና በፍትሃዊነት የመልማት ጥያቄ መሆኑን በማንሳት፤ ይህንን ማሳካት ደግሞ የትውልዱ የማይቀር እውነት ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ የባህር በር ማግኘቷ አይቀሬ መሆኑን ጠላት ሳይቀር እየመሰከረው ያለው ሃቅ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ እንደ ሕዳሴ ግድብ እና ሌሎች ታላላቅ ፕሮጀክቶች ሁሉ የባሕር በር ጥያቄዋንም ማሳካት የምትችል ታላቅ ሀገር ስለመሆኗም ኡስታዝ ጀማል ተናግረዋል።

Ethiopian News Agency #ኢዜአ #ህዳሴ

የተሁለደሬ ወረዳ ጤና ጥበቃ እና መንገድ ጽ/ቤቶች በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ያሰባሰቧቸውን የትምህርት ቁሳቁሶች እና ዱቄት ለወረዳው ሃብት አሰባሳቢ ኮሚቴ ማስረከባቸውን አስታወቁ።ተሁለደ...
28/08/2026

የተሁለደሬ ወረዳ ጤና ጥበቃ እና መንገድ ጽ/ቤቶች በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ያሰባሰቧቸውን የትምህርት ቁሳቁሶች እና ዱቄት ለወረዳው ሃብት አሰባሳቢ ኮሚቴ ማስረከባቸውን አስታወቁ።

ተሁለደሬ፣ነሃሴ 22/2018 ዓ.ም (የተሁለደሬ ኮሙዩኒኬሽን)

በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የኢኮኖሚ እጥረት ላለባቸው ተማሪዎችን ለመደገፍ በወረዳው ካሉ የግል ጤና ድርጅቶች ያሰባሰባውን መቶ ደርዘን ደብተር ለወረዳው የበጎ ፈቃድ ሃብት አሰባሳቢ ኮሚቴዎች ማስረከቡንና ቁሳቁሶቹም ለተማሪዎቹ መሰራጨታቸውን የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ መልሳቸው አለበል የገለፁ ሲሆን በጎ ያደረጉ ድርጅቶችን አመስግነዋል።

በሌላ በኩል የተሁለደሬ ወረዳ መንገድ ትራንስፖርት ጽ/ቤት ከጽ/ቤቱ ሰራተኞች፣ ከባጃጅ ማህበራት ፣አሽከርካሪዎችና ባለ ንብረቶች እንድሁም ከመንገድ ተቋራጮች ያሰባሰበውን 64 ደርዘን ደብተር፣3 በኮ እስክርቢቶ እና ባለ 10 ኪሎ ግራም 20 ከረጢት ዱቄት ለወረዳ ሃብት አሰባሳቢ ኮሚቴ ያስረከ ሲሆን ድጋፉም ለችግር ተጋለጭ ለሆኑ ተማሪዎች የተበረከተ ሲሆን የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ያሲን በጎ አድራጊዎችን አመስግነዋል።

**********************************
ተጨማሪ መረጃዎችን ከተሁለደሬ ኮሙኒኬሽን ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጫኑ።
Facebook: https://www.facebook.com/tehulederecomunication
Telegram ፡https://t.me/+ehhHs-eR9n44OTA0
Twitter: https://x.com/Tehulederejxak
You Tube: https://youtube.com/?si=QQOZ7nnuOGI2jPBd
Tiktok: http://tiktok.com/
Instagram: https://www.instagram.com/tehuleder?igsh=bDdnNTN6NTlrcGFr

28/08/2026

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ኢትዮጵያ ያካሄደችው የኢኮኖሚ ሪፎርም እንደ ሀገር ጸንታ እንድትቀጥል አስችሏል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

Address

Haik

Telephone

+251332220491

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tehuledere Woreda Gov. Communication/ተሁለደሬ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share