06/08/2026
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ የሥራ ዘመን 12ኛ መደበኛ ጉባኤውን ነገ ሀምሌ 23 እንደሚጀምር ተገለጸ።
የአማራ ክልልምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋዬ 6ኛ ዙር 5ኛ የሥራ ዘመን 12ኛ መደበኛ ጉባዔን አሰመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል ።
አፈጉባዔዋ በመግለጫቸው የ2018 በጀት ዓመት የአስፈፃሚ አካላት እቅድ ክንውን፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የዋና ኦዲተር የእቅድ አፈፃፀሞች ቀርበው በውይይት እንደሚጸድቁ ተናግረዋል ።
በተጨማሪም በባለፈው ዓመት ጥቅም ላይ የዋለው ተጨማሪ በጀት ቀርቦ እንደሚጸድቅ በመግለጫው አንስተዋል ።
በጉባዔው የ2019 በጀት ዓመት ረቂቅ የበጀት እቅድ ቀርቦ በውይይት እንደሚጸድቅም ጠቁመዋል ።
ጉባዔው የመጨረሻ ጉባዔ በመሆኑ የ6ኛው ዙር የሥራ ዘመን ምክር ቤቱ በአምስት ዓመታት ያከናወናቸውን ጥቅል ተግባራት ሪፖርት ቀርቦ የሚገመገምበት መሆኑን አንስተዋል ።
የክልሉ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎችን በተመለከተም ውይይት ይደረጋል ብለዋል ።
ምክር ቤቱ ባለፉት 5 ዓመታት ሕግ የማውጣት፣ የክትትልና ቁጥጥር እንዲሁም የሕዝብ ውክልና ኃላፊነቱን ሲወጣ
መቆየቱን አንስተዋል ።
የሕዝቡን የመልማት፣ የፍትሕና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ የሚያስችሉ 32 አዋጆች፣ ሁለት ደንቦች እና ሁለት ሞሽኖች ጸድቀው ሥራ ላይ መዋላቸውንም ገልፀዋል ።