16/07/2026
የሀራ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት በሐሙስ ገበያ ላይ የተቀናጀ የቁጥጥር ስራ እየሰራ ነው፤
ሀራ፣ ሐምሌ ፣9፣ 2018 ዓ.ም – የሀራ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት በከተማዋ ትልቁ የገበያ ማዕከል በሆነው “ሐሙስ ገበያ” ላይ የተቀናጀ የቁጥጥርና የክትትል ስራ እያከናወነ ነው።
ጽ/ቤቱ የሸማቹን ማህበረሰብ ጤንነት ከመጠበቅ ባሻገር፣ ህጋዊ የንግድ ስርዓትን ለማስፈን ባደረገው በዚህ የአሰሳ ስራ በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጿል። በቁጥጥር ስራው ወቅት የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈባቸውና ለጤና ጎጂ የሆኑ ምርቶች ለገበያ እንዳይቀርቡ ጥብቅ ክትትል የተደረገ ሲሆን፣ የህግ ጥሰት ፈጽመው የተገኙ ምርቶች ከገበያው እንዲወገዱ ተደርጓል።
በተጨማሪም፣ የንግድ ፈቃድ ሳይኖራቸው የንግድ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበሩ አካላት ከገበያው እንዲወገዱ በማድረግ፣ የዘርፉን ህጋዊነት የማስከበር ስራ ተሰርቷል። ይህ እርምጃ ህጋዊ ግዴታቸውን እየተወጡ የሚሰሩ ነጋዴዎችን ተወዳዳሪነት የሚያረጋግጥና የሸማቾችን መብት የሚያስጠብቅ መሆኑን የጽ/ቤቱ ኃላፊ ያሲን ሙሐመድ ገልፀዋል።
በአሁኑ ወቅት በተከናወነው የቁጥጥር ስራ አማካኝነት በገበያው ላይ የተሻለ የምርት አቅርቦት መፈጠሩና የንግድ እንቅስቃሴውም በህጋዊ ማዕቀፍ ውስጥ እየተመራ መሆኑን የጽ/ቤቱ ባለሙያዎች ገልጸዋል።
ጽ/ቤቱ በቀጣይም የህገ-ወጥ ንግድ እንቅስቃሴዎችን ለመከላከልና የገበያ ስርዓቱን ለማዘመን የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል። ሸማቾችም በገበያ ወቅት የገዙትን ምርት የጥራት ምልክትና የአገልግሎት ጊዜ መፈተሽ እንደሚገባቸው ጽ/ቤቱ መልእክቱን አስተላልፏል።
ሀራ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት