Harari Region Prosperity Party - ብልፅግና

Harari Region Prosperity Party - ብልፅግና Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Harari Region Prosperity Party - ብልፅግና, Political organisation, Bote Street, Harar.

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና ዋና ፅ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ አደም ፋራህ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምክክር መድረክ (Inter-Continental Dialogue ...
06/09/2026

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና ዋና ፅ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ አደም ፋራህ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምክክር መድረክ (Inter-Continental Dialogue among Political Parties - ICDPP) ላይ ለመሳተፍ ሴኡል፣ ደቡብ ኮሪያ ገብተዋል።

ከሴፕቴምበር 6 እስከ 9 ቀን 2026 ዓ.ም በሚካሄደው በዚህ ከፍተኛ አለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ከአፍሪካ፣ ኤሽያ፣ አውሮፓ፣ ላቲን አሜሪካ እና ሰሜን አሜሪካ የተወጣጡ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በአሁን ወቅት የተሳታፊዎች እንኳን በደህና መጣችሁ መርሃ ግብር እየተደረገ ይገኛል።

ጉባኤው በዓለም አቀፍ ደረጃ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የጋራ ግንዛቤ እና ትብብር ማጠናከርን ዋና አላማው አድርጎ የተነሳ ሲሆን በቀጣይ ቀናት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።

06/09/2026

በሀረሪ ክልል የተገነባውና በ8 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ዘመናዊ የሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ በተፋጠነ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌቱ ነገዎ

ጳጉሜን 1 - የእመርታ ቀን፡ ጳጉሜን 1 "የእመርታ ቀን" ሲከበር፣ ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ያሳካቻቸውን ዘርፈ ብዙ የስኬት ጉዞዎችና ለሁለንተናዊ ብልጽግና መሰረት የሆኑ ታላላቅ ምዕ...
06/09/2026

ጳጉሜን 1 - የእመርታ ቀን፡

ጳጉሜን 1 "የእመርታ ቀን" ሲከበር፣ ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ያሳካቻቸውን ዘርፈ ብዙ የስኬት ጉዞዎችና ለሁለንተናዊ ብልጽግና መሰረት የሆኑ ታላላቅ ምዕራፎችን በማሰብ ነው። በብልጽግና ፓርቲ የሚመራዉ የመደመር መንግሥት ተስፋን ወደ ተግባር፣ ህልምን ወደ እውነታ በመቀየር በተለያዩ የልማት መስኮች የያዘዉን የዕድገት መስመር በግልጽ ያሳየበት ወቅት ላይ እንገኛለን። በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በዲፕሎማሲዉ መስክ የተመዘገቡ እምርታዊ ስኬቶች ኢትዮጵያን ወደሚገባት የብልጽግና ከፍታ የሚያሻግሩ መሰረቶች ናቸዉ፡፡

በግብርና እና በምግብ ሉዓላዊነት የተመዘገበዉ እመርታ ትልቅ አብነት ነዉ፡፡ በበጋ መስኖ የተሸፈነው መሬት ከ400 ሺህ ሄክታር ወደ 3 ሚሊዮን ሄክታር በማደጉ ከ100 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ተሰብስቧል። ኢትዮጵያ የበጋ መስኖ በመጠቀም በስንዴ ምርት ላይ ያካሄደችዉ አብዮት ከስንዴ አስመጪነት ወደ አምራችነትና ላኪነት አሸጋግረዋታል፡፡ በዚህ ዘርፍ የተመዘገበዉ እመርታ ሀገራችን የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋጥ የምታደርገዉ ጥረት ተጨባጭ ዉጤት ማምጣቱ የማይቀር መሆኑን የሚያስረግጥ ሀቅ ነዉ፡፡

መላዉን ኢትዮጵያዉያንን በአንድነት በማነሳሳት ለአንድ ታሪካዊ አላማ በህብረት ቆመዉ ዘመን ተሻጋሪ ታሪክ እንዲጽፉ ምክንያት ሆኗል የአረንጓዴ አሻራ፡፡ እኛ ስንደመር የማናሳካዉ ድል አለመኖሩን የተከልናቸዉ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞች ይመሰክራሉ፡፡ በአንድነት የተከልናቸዉ ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞች የአየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም፣ የአፈር ለምነትን የመጠበቅና የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ አህጉራዊ አርአያነት ያለው ስራ ማከናወናችንን ይመሰክራሉ፡፡

በመላዉ ኢትዮጵያውያን የተቀናጀ ህብረት እና የኢኮኖሚ ነፃነት ምልክት የሆነው የህዳሴው ግድብ ተጠናቅቆ የኤሌክትሪክ ሓይል ማምረት መጀመሩ፤ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች እየተካሄደ ያለዉ የኮሪደር ልማት የከተሞችን ውበት፣ የትራፊክ ፍሰት እና የዜጎችን የመኖሪያ ምቾት ወደ አዲስ ደረጃ ማሸጋገሩና የቱሪዝም ዘርፉን ለማነቃቃት በገበታ ለሀገር፣ በገበታ ለትዉልድና በገበታ ለሸገር የተሰሩ የልማት ስራዎች ያስመዘገቡት እመርታ በተምሳሌትነት ከሚጠቀሱ አበይት ስኬቶች መካል ናቸዉ፡፡

ባለፉት የለዉጥ አመታት በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የሀገር ውስጥ አምራች ኢንዱስትሪዎችን በማጠናከርና ለወጣቶች የቴክኖሎጂና አዲስ የስራ እድሎችን በመፍጠር ረገድ ተጨባጭ ውጤት ተመዝግቧል።

ጳጉሜን 1 የእመርታ ቀን፣ ያለፉትን ስኬቶች ከማሰብ በላይ ወደፊት ለሚጠብቁን ታላላቅ ሀገራዊ ግቦች አዲስ የቁርጠኝነትና የጋራ ጥረት መንፈስ የምናድስበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው።

በሐረሪ ክልል በ2018 በሁሉም ዘርፎች የተመዘገቡ ስኬቶች ዘላቂ ሰላምን በመገንባታችን የተገኙ ናቸው" — አቶ ጌቱ ወዬሳ በሐረሪ ክልል በ2018 የበጀት ዓመት በጤና፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ...
05/09/2026

በሐረሪ ክልል በ2018 በሁሉም ዘርፎች የተመዘገቡ ስኬቶች ዘላቂ ሰላምን በመገንባታችን የተገኙ ናቸው" — አቶ ጌቱ ወዬሳ

በሐረሪ ክልል በ2018 የበጀት ዓመት በጤና፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ዘርፎች የተመዘገቡ አበራታች ስኬቶች በክልሉ የተረጋገጠው ዘላቂና አንፃራዊ ሰላም ውጤቶች መሆናቸውን የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ገለጹ።

አቶ ጌቱ ወዬሳ በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት፤ በበጀት ዓመቱ በጤናው ዘርፍ በርካታ የጤና ተቋማት ተገንብተው ወደ ሥራ ከመግባታቸው ባሻገር፤ ተጨማሪ አዳዲስ ግንባታዎችና የማስፋፊያ ሥራዎች ተከናውነው ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነዋል።

አቶ ጌቱ አያይዘውም ክልሉ ከ40 በላይ ብሔረሰቦች በሰላምና በፍቅር አብረው የሚኖሩበት ልዩ የኅብረብሔራዊነትና የመቻቻል ተምሳሌት መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህ አብሮነትና በገጠርና ከተማ ነዋሪዎች መካከል ያለው ጠንካራ ትስስር ለክልሉ ሰላም መረጋገጥ ትልቁን ድርሻ ማበርከቱን ተናግረዋል።

"ሕዝባችን ከማንኛውም በላይ ሰላምን የሚወድ ነው" ያሉት አቶ ጌቱ፤ በክልሉ የተገኘው ሰላም ዜጎች በ24 ሰዓት ሙሉ በነፃነትና በሰላም ወጥተው እንዲሠሩ ዕድል በመፍጠሩ ለምርጫው ሂደት፣ ለከተማና ገጠር ልማት እንዲሁም ለኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች መሳካት መሠረት መሆኑን አብራርተዋል።

ለዚህ አስተማማኝ ሰላም መረጋገጥ የሕዝቡ ንቁ ተሳትፎ እንዳለ ሆኖ የክልሉ ፖሊስና ሚሊሻ፣ የፌደራል ፖሊስ እንዲሁም የምሥራቅ ዕዝ የሀገር መከላከያ ሠራዊት በቅንጅት የሠሩት ሥራ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ገልጸዋል።

በተጨማሪም ከአጎራባች የኦሮሚያ ክልል የምሥራቅ ሐረርጌ ዞንና ማያ ሲቲ አመራሮችና ሕዝብ ጋር እንደ አንድ ቤተሰብ በመሆን በልማትና በሰላም ላይ በጋራ መሠራቱ ለውጤቱ መገኘት አወንታዊ ሚና መጫወቱን ጠቁመዋል።

በመጨረሻም በ2018 የበጀት ዓመት የሐረሪ ክልል ሕዝብ በሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን መድረኮች ላይ ተወካዮቹን በመላክና ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የተጣለበትን ታሪካዊ ኃላፊነት በብቃት መወጣቱን የጠቀሱት አቶ ጌቱ ወዬሳ፤ የተገኙ ስኬቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ ሌብነት በቃኝ ብሏል፤ ሌቦችን ከዉስጣችሁ አጥሩ ብሏል፤ ሌብነት የተንሰራፋበት ብልጽግና የመጨረሻ ዉጤት አያመጣም ብሏል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር)
05/09/2026

የኢትዮጵያ ህዝብ ሌብነት በቃኝ ብሏል፤
ሌቦችን ከዉስጣችሁ አጥሩ ብሏል፤
ሌብነት የተንሰራፋበት ብልጽግና የመጨረሻ ዉጤት አያመጣም ብሏል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር)

04/09/2026

ጳጉሜ ቀናት የወንድማማችነታችን፣ አገራዊ አንድነታችንን የወደፊት ተስፋችንን የምናረጋግጥበት በመሆኑ በልዩ ልዩ ተግባራት በደመቀ ሁኔታ ይከበራል: -

አቶ ጌቱ ወዬሳ
የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ

በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት  አብሮነትና መደጋገፍ እሴት በመጎልበት  የዜጎችን ህይወት በላቀ ደረጃ እየተቀየረ ይገኛል :- አቶ ጌቱ ዋዬሳበሀረሪ ክልል በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት  አ...
04/09/2026

በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት አብሮነትና መደጋገፍ እሴት በመጎልበት የዜጎችን ህይወት በላቀ ደረጃ እየተቀየረ ይገኛል :- አቶ ጌቱ ዋዬሳ

በሀረሪ ክልል በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት አብሮነትና መደጋገፍ እሴት በመጎልበት የዜጎችን ህይወት በላቀ ደረጃ እየቀየረ ይገኛል ሲሉ የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አቶ ጌቱ ዋዬሳ ገለፁ።

በሀረሪ ከልል በክረምት በጎ ፍቃድ እየተከናወኑ በሚገኙ ተግባራት ሳምታዊ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ተካሄደ።

በዚህ ወቅትም በብልፅግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ እንደገለፁት በክልሉ በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት አብሮነትና መደጋገፍ እሴት በመጎልበት የዜጎችን ህይወት በላቀ ደረጃ እየቀየረ ይገኛል ።

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተደመረ አቅም ዜጎችን በማገዝና ሃብትን አቀናጅቶ በመምራት ረገድ የላቀ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል።

በተለይም በክረምቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በርካታ አቅመ ደካሞችንና አረጋዊያንን ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ ስራዎች እውን ማድረግ መቻሉን አንስተዋል።

በዘንድሮ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያጎለብቱ ተግባራት በተጠናከረ መልኩ እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል።

በመርሃግብሩም በ14 መስኮች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በዚህም በአሁኑ ወቅት የአረጋውያንና አቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤት እድሳትና መልሶ ግንባታ፣ የአካባቢ ንጽህና ጥበቃ፣ ችግኝ ተከላ፣ ደም ልገሳ፣ የማጠናከሪያ ትምህርት የመስጠትና ሌሎች ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል

ከዚህ በተጨማሪም ማዕድ ማጋራት፣ አዳዲስና ነባር የመማሪያ ክፍል ግንባታ እና እድሳት ፣ የትምህርት ቤቶች የተማሪ ወንበሮች ጥገና፣ ጽዳትና ውበት ስራዎችን ጨምሮ የማጣቃሻ መጽሀፍት የማሰባሰብ ስራ በበጎ ፍቃድ አገልግሎቱ የትኩረት የተሰጣቸው ጉዳዮች መሆናቸውን ገልጸዋል።

የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ መደጋገፍ፣ የመተጋገዝና አብሮነትን ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን ጠቁመው የዜጎችን እውቀት፣ ገንዘብ፣ ጉልበት እና ሌሎች ምቹ ሁኔታዎችን በሚገባ መጠቀምና ከድህነት መላቀቅ እንደሚያስፈልግ ነው የጠቆሙት።

ይህ የመተጋገዝና የአብሮነት ባህል ድህነትን ለማሸነፍ ትልቅ አቅም የሚፈጥር በመሆኑ፣ አመራሩ የታቀዱትን ግቦች ወደ ሙሉ ተግባር ለመቀየር በቁርጠኝነት መስራት እንዳለበት አቶ ጌቱ አሳስበዋል።

​ከክረምቱ የበጎ ፈቃድ ስራዎች ጎን ለጎን የጳጉሜን ቀናት አከባበር ዝግጅት ተገምግሟል።

ጳጉሜን የወደፊት ተስፋችንን፣ ወንድማማችነታችንን፣ አገራዊ አንድነታችንን እና የሰራናቸውን አዎንታዊ ተግባራት የምናስብበት ልዩ ድልድይ በመሆኗ፤ ቀናቱ እንደየፅንሰ ሀሳባቸው (የመደመር፣ የሪፎርም፣ የሉአላዊነት፣ የጽናትና የዕድገት ቀናት ተደርገው) በደመቀ ሁኔታ እንዲከበሩ ዝግጅት ተደርጓል።

ህብረተሰቡ በነቂስ በመውጣት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን፣ አብሮነትንና የበጎ ፈቃድ ባህልን በሚያጎለብቱ ተግባራት ላይ ንቁ ተሳትፎ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

04/09/2026

"ኢትዮጵያን ወደሚመጥናት የታላላቅ ዓለም ሥልጣኔዎች ጎራ ለማሰለፍ የሚያስችለን የ25 ዓመት ዐቢይ (Grand) ስትራቴጂ!"

​ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመር መንግሥት ኢትዮጵያን ወደ ታላቅ የሥልጣኔ ማዕከልነት ለማሸጋገር ስላዘጋጀው የ25 ዓመት ዐቢይ (Grand) ስትራቴጂ ምን ብለዉ ነበር?

03/09/2026

ታዝማ ውስጥ ደዌ ና የቀዶ ህክምና ልዩ ማእከል በሐረሪ ክልል በነፃ የልብ ህክምና አገልግሎት እየሰጡ ነው

ታዝማ ውስጥ ደዌ ና የቀዶ ህክምና ልዩ ማእከል የተወጣጡ ከፍተኛ የህክምና ስፔሻሊስቶች በሐረሪ ክልል በአቅም ማነስ ምክንያት የልብ ህክምና ማግኘት ላልቻሉ ወገኖች ነፃ የሕክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

ይህ የህክምና ስፔሻሊስት ቡድን በክልሉ ባደረገው የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁና ልዩ ክትትል የሚያስፈልጋቸውን የልብ ህመሞች የመለየት፣ የምክርና የቀዶ ህክምና አገልግሎቶችን በነፃ በማቅረብ ላይ እንደሆነ ተገልጿል።

የልኡካን ቡድኑ አባላት እንደገለጹት፤ የእንቅስቃሴው ዋና ዓላማ በኢኮኖሚ ምክንያት የህክምና አገልግሎቱን ማግኘት ያልቻሉ ህሙማንን መደገፍና በክልሉ ያለውን የልብ ህክምና ተዳራሽነት ማሳደግ ነው።

የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎችና የሕሙማን ቤተሰቦች በበኩላቸው የተደረገላቸው ድጋፍ በህይወታቸው ላይ ትልቅ ተስፋ የፈጠረና የገንዘብ እጥረት ደቅኖባቸው የነበረውን ስጋት ያቀለለ መሆኑን ገልጸው ለቡድኑ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የስፔሻሊስቶች ቡድኑ በሐረሪ ክልል የሚያደርገውን ይህንኑ የበጎ አድራጎት የህክምና አገልግሎት በተቀናጀ መልኩ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል።

Address

Bote Street
Harar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Harari Region Prosperity Party - ብልፅግና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share