21/08/2026
የ2019 ዓ.ም የዕቅድ ትውውቅ እና የጋራ መግባቢያ ስምምነት ፊርማ ተካሄደ!
********************
የሐረሪ ክልል የወጣቶች ስብዕና ልማት ማዕከል በ2019 የስራ ዘመን እቅድ አፈጻጸም ዙሪያ ከማኔጅመንት አባላት እና አጠቃላይ ሰራተኞች ጋር ሲያካሂድ የቆየውን የሁለት ቀናት ውይይት በስኬት አጠናቋል። የመድረኩ ዋነኛ አላማ "የአንድ እቅድ አንድ ሪፖርት" አሰራርን በተቋሙ ውስጥ ስር በማስረፅ፣ ለወጣቶች ቀልጣፋና ጊዜውን ያዋጀ አገልግሎት መስጠት ነው።
ባለፉት ሁለት ቀናት የ2018 የስራ አፈጻጸም ክፍተቶቻችንን በዝርዝር በመገምገም፣ በቀጣይ የተሻለ የስብዕና ግንባታ ስራዎችን ለመስራት የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ተለይተዋል። ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ ሁሉም የማዕከላችን ሰራተኞች የ2019ን "ዓመታዊ ዕቅድ አፈፃፀም እና የጋራ ስምምነት ቅጽ" ተረክበው በመፈራረም በይፋ ወደ ስራ ገብተዋል።
#የ2019እቅድ