Harari Urban Development and Construction Bureau

Harari Urban Development and Construction Bureau ይህ ገጽ የሐረሪ ከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽን ቢሮ ፌስ ቡክ ?

የ መ/ቤቱ ተግባርና ስልጣን
• ያመለካከት ለውጥ በማምጣት የለውጥሰራዊት በመገንባትና የአገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል የዘርፉን ተልኮ ያሳካል፤
• የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋሞች ልማት እንዲስፋፋ ያደርጋል፤
• የጥቃቅንና አነስተኛኢንተርፕራይዞች ልትበዘርፉ ስትራቴጂ መሰረት ይመራል እንቅስቃሴዎችን ያስተባብራል በተገቢዉ ሁኔታ መተግበሩን ያረጋገረጣል
•ስለመሬት ልማትና አስተደደር በዘር ስትራቴጂ መሰረት ይመራል እንቅስቃሴዎችን ያሥተባብራል በተገቢዉ ሁኔታ መከበሩን ያረጋግጣል፡፡
•ግልጽና ፍታዊ የመሬት አስተዳደር በክልሉ እነዲከበር ያደርጋል፤
• የከተማውን መሬትና መሬት ነክ ንብረት አስተዳደር መረጃ ያጠናቅራል፤ ያደራጃል፤ያሰራ

ጫል፤
• በአገሪቱ የህንጻ አዋጅ መሰረት የህንጻ ፍቃድ ይሰጣል፤ ቁጥጥር ያደርጋል፤
• የመሬት ልማት ፖሊሲዎች እንዲሁም የግንባታ ህጎች ኮዶች በክልሉ መከበሩን ያረጋግጣል፤
• በሊዝ መነሻ ዋጋ በየጊዜዉ ተጠንቶ ተግባራዊ መሆኑን ይከታተላል ያረጋግጣል፤
•የከተማ ፕላን ፖሊሲዎችና ማፈፀሚያ ሰነዶች ደንብ፤ መመሪያ ወዘተ ያዘጋጃል ፤
• የከተማዉን ፕላን መሰረታዊ ፕላንና የአከባቢ ልማት ፕላን ያዘጋጃል አተገባበራቸዉን ይከታተላል ፤
• ለከተማዉ ፕላን ዝግጅት የሚረዱ ጥናቶች ያካሂዳል ፕላኑን ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ ዝርዝር ጥናቶች አንዲዘጋጁ ያደርጋል ከሚመለከታቸዉ የፌዴራል መንግስት አካላት ጋር በፕላን ዝግጅት ረገድ አስፈላጊዉን ትብብር ያደርጋል አፈጻጸማቸዉን ይከታተላል ፤
• በክልሉ የከተማ መሬት አስተዳደር ስርዐት ከኪራይ ሰብሳቢነት በጸዳ መንገድ ለላቀ ልማታዊ ስራ እንዲዉል ያደርጋል፤
•ማንኛዉም በክልል የሚካሄድ የከተማ ፕላን እና የከተማ ቦታ ደረጃ መስፈርትና ደረጃ ይዘጋጃል አተገባበራቸዉን ይቆጣጠራል ድጋፍ ያደርጋል ፤
• በክልሉ የሚካሄደዉን የቤቶች ልማት ይከታተላ የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል ይቆጣጠራል የከተማ ነዋሪ ህዝብ ከአቅሙ ጋር የተመጣጠነ የመኖሮያ ቤት የሚሰራበት ስልት ይቀይሳል ተግባዊነቱን ይከታተላል፡፡
• በክልሉ መንግስት በጀት የሚሰሩ የመንግስት የኮንስትራክሽን ስራ ዉሎች ህግ በሚያዘዉ መሰረት እንዲዘጋጅ ያርጋል እንዲሻሻሉና እንዲጠገኑ ድጋፍ ያደርጋል
• በክልሉ መንግስት በጀት የሚሰራ የኮንስትራክሽን ስራ በተደረገ ዉል መሰረት የጥራት ደረጃዉን ጊዜና የዋጋ ገደቦች ተጠብቀዉ መስራቱን የሚያስችል የቁጥጥር ስርዐት እንዲኖር ያደርጋል በበላይነት ይቆጣጠራል
• በክልሉ ዉስጥ ለሚንቀሳቀሱ ስራ ተቋራጭና ለኮንስትራክሽን አማካሪዎች ፍቃድ ይሰጣል አቅማቸዉ እንዲጎለብት እገዛ ያደርጋል ይቆጣጠራል

•የከተማ ልማት ስራ ከስራ ፈጠራና ከድህነት ቅነሳ ጋር የተቀናጀ እንዲሆን ያግዛል አፈፃፀሙን ይከታተላል
•በክልሉ የሚቋቋሙትን የኮንስትራክሽን ሞያ ማህበራት ይመዘግባል የሃገሪቱን የንግድና ኢንደስተሪ ልማት ፖሊሲ መሰረት በማድረግ የክልሉ ንግድና ኢንደስትሪ እንዲስፋፋ ያበረታታል የቴክኒክ ምክሮችና የሌሎች አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶች ይሰጣል
• በክልሉ ንግድና ኢንደስተሪ ስራ ለሚሰሩ ለሀገር ዉስጥ ባለሀብቶች ፍቃድ ይሰጣል ይመዘግባል ይቆጣጠራል እንዲሁም ተገቢዉን የአገልግሎት ገቢ በአግባቡ ገቢ መሆኑን ያረጋግጣል
•የክልሉ ንግድና ኢነንደስትሪ እንቅስቃሴ በሃገሪቱ ፖሊሲና ህግ መሰረት መካሄዱን ይቆጣጠራል እንዲሁም ህጋዊ ያልሆኑ የማምረት አገልግሎት መስጠትና የንግድ ልዉዉጥ ስራ እንዳይካድ ያደርጋል
•በክልሉ መሰረታዊ የንግድ ኢንደስተሪ ዕቃዎች አገልግሎቶች ስርጭት አግባብነት ባለዉ አካል የተወሰነዉ የዋጋ ተመንና የጥራት ደረጃ መከበሩን ይቆጣጠራል
•ተገቢ ያልሆነ የንግድ አሰራርን ለመከላከል የሚያሥችል የተᎂላ ስርዐት ይዘረጋል የንግድና ኢነደስተርሪ ህጎች መከበራቸዉን ያረጋግጣል አፈፃፀማቸዉን ይከታተላል በህጉ መሰረት ለሸማቾች ጥበቓ ያደርጋል
•አግባብ ባላቸዉ ህጎች መሰረት የንግድምዝገባና ፍቃድ አገልግሎት ይሰጣል ይቆጣጠራል ይሰርዛል
•ኢንቨስትመንትን በተመለከተ አግባብ ባለዉ ህግ የተደነገገዉ እንደተጠበቀዉ ሆኖ የክልሉን ኢነቨስትመንት ጉዳዮች ይመራል እንቅስቃሴዎችን ያስተባብራል ያበረታታል ያስፋፋል
•በኢንቨስትመንት ፖሊሲና ህግ መሰረት ሊጠኑና በስራ ላይ ሊዉሉ የሚገባቸዉን የኢንዱስትሪ ፕሮጀክት ሃሳቦች በስራ ላይ እንዲዉሉ ሁኔታችን ያመቻቻል
•በክልሉ ዉስጥ የማዕድን ና ኢነርጂ ልማት እንዲስፋፋ ያበረታታል •
•የማዕድን ና ኢነርጂ ሃብትን የሚያመለክቱ ጥናቶች ያካሂዳል ወይም እንዲጠና ያደርጋል መረጃዎችን ያሰባስባል ያደራጃል
•ስለ ማዕድን ጥበቃና አጠቃቀም የወጡ ህጎች ደንቦችና መመሪያዎች በክሉ ዉስጥ መከበራቸዉን ያረጋግጣል
•በክልሉ የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦትን ማዳረስ የሚያስችል ጥናቶችን ያካሂዳል ባህላዊ ማገዶ ቆጣቢ የሃይል አቅርቦት በስራ ላይ እንዲዉል ያመቻቻል
•ባህላዊ የማዕድን ስራዎችን ያበረታታል በመስኩ የስራ ፍቃድ ይሰጣል ገቢ ይሠበስባል በአግባቡ መያዙን ያረጋግጣል
•ከተማ የልማት ምዕከል እንዲሆን የተቀናጀ ድጋፍ ይሰጣል፤ ያስተባብራል
•የከተማ ልማት ከገጠሩ ልማት ጋር በተቀናጀ መንገድ የሚከናወንበት ሁኔታ በሚመለከት ጥናት ያደርጋል ፤ተግባራዊ እንዲሆን ያግዛል አፈፃፀሙን ይከታተላል፡፡

04/06/2026
04/06/2026
02/06/2026
02/06/2026
02/06/2026

ከሀረሪ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ

የሀረሪ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከ7ኛው ክልላዊና ሀገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ መግለጫ ሰጥቷል።

ምክር ቤቱ በመግለጫውም በ7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫው ሂደት ወቅት የታዩ አዎንታዊ ጅምሮችን ይበልጥ በማጠናከር የምርጫውን ሰላማዊነት፣ ዲሞክራሲያዊነት፣ ነፃና በሕዝብ ዘንድ ታማኒነቱን ማጠናከር ይገባል ብሏል።

የጋራ ምክር ቤቱ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የሕዝቡን ውሳኔ እና ድምፅ እንዲያከብሩ፣ ደጋፊዎቻቸውን ወደ ሰላም፣ መከባብር እና ሕጋዊ አሠራር እንዲመሩ እና ማንኛውንም ልዩነት በውይይት እና በሕግ ማዕቀፍ እንዲፈቱ ጥሪውን አቅርቧል።

የምርጫው ውጤት በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሕግ መሠረት ተረጋግጦ እስከሚገለፅ ድረስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትዕግሥትና በኃላፊነት ስሜት እንዲቀሳቀሱ ጠይቋል።

ከምርጫ በኋላም በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የምክክር እና የመግባባት ባህል እንዲጠናከር ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብርና በጋራ እንደሚሰራ ነው ያስታወቀው።

ማንኛውም ቅሬታ በሕጋዊ መንገድ ብቻ መፍታት እና በሰላምና በብሔራዊ ጥቅቅም ጉዳይ ትብብርን መሠረት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ተመላክቷል።

የፖለቲካ ልዩነቶችን በውይይት እና በዴሞክራሲያዊ ሂደት የመፍታት ባሕላችንን ማጠናከር እና የትብብር እና የፉክክር ሚዛንን በማስጠበቅ የመደብለ ፓርቲ የዲሞክራሲ ባሕልን ማጠናከር ወሳኝ መሆኑን የጋራ ምክር ቤቱ በሰጠው መግለጫ ገልጿል።

02/06/2026

ኢትዮጵያውያን በሰላማዊ መንገድ መርጠዋል፤ ኢትዮጵያ አሸንፋለች- የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ኢትዮጵያውያን በ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ መንገድ በመምረጥ ኢትዮጵያን አሸናፊ አድርገዋል ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

ጠቅላላ ምርጫው በሰላማዊ ሁኔታ በስኬት መጠናቀቁንም አመልክቷል።

አገልግሎቱ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ ኢትዮጵያውያን መርጠዋል፤ ኢትዮጵያ አሸንፋለች! ሲል ገልጿል።

አገልግሎቱ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመላከተው፣ ኢትዮጵያ ከዜጎቿ የፈለገችውን ሁሉ በፈለገችው ጊዜና ሁኔታ የምታገኝ ሀገር መሆኗንና ለሀገራቸው የተጠየቁትን ሁሉ ለመስጠት ወደኋላ የማይሉ ዜጎች ስላሏት በእጅጉ እንደምትኮራ ገልጿል።

ከዓድዋ እስከ ሕዳሴ ግድብ፣ ከወገን ለወገን መረዳዳት እስከ አረንጓዴ ዐሻራ የዜጎቿን ተሳትፎ ጠይቃ ከመሻቷ በላይ እንደተሳካላትና ዛሬም የተደገመው ይኸው እንደሆነ አብራርቷል።

ኢትዮጵያ ዴሞክራሲን ለማንበር፣ በግልጽና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መንግሥትን ለመምረጥ እንዲሁም ሕገ-መንግሥታዊነትን ፅኑ መሠረት ለማስያዝ እንደምትሻ የጠቀሰው መግለጫው፤ ለዚህ ደግሞ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ እንደ ትልቅ አጋጣሚ መጠቀም ማስፈለጉን አስታውቋል።

ለዚህ አገራዊ ጥሪ በምላሹ ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለመራጭነት ተመዝግበው ቀኑን ሲጠባበቁ መቆየታቸውንና የእናት ሀገር ጥሪን በመቀበልም በነቂስ ወጥተው ሲመርጡ መዋላቸውን አገልግሎቱ ገልጿል።

መራጮች ሌሊቱንም ጭምር አጋምሰው ድምፅ የሰጡ ሲሆን፣ ይህም በኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክ ዜጎች ለረዥም ሰዓታት ተሰልፈው ድምፅ የሰጡበት ልዩ ምርጫ ያደርገዋል ብሏል።

ምርጫው እንዳይካሄድ ባዳ እና ባንዳ ተቀናጅተው ያልቆፈሩት ጉድጓድና ያልደረደሩት እንቅፋት እንዳልነበረ የጠቀሰው መግለጫው፤ ነገር ግን ኢትዮጵያ ለጠራችው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የማይቻል ነገር ባለመኖሩ ሂደቱ በስኬት መጠናቀቁንና ኢትዮጵያውያን በሰላማዊ መንገድ መርጠው ኢትዮጵያ ማሸነፏን አረጋግጧል።

የኢትዮጵያን የዴሞክራሲያዊ ምርጫ ጥሪ ተቀብሎ ከንጋት እስከ ምሽት በመምረጥ ምላሽ ለሰጠው ሕዝብ፣ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱ እንዲጸና እና ዜጎች በሰላም እንዲመርጡ ምቹ ዓውድ ለፈጠሩ የፀጥታ አካላት፣ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ በየደቂቃው ሲያደርሱ ለነበሩ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት እንዲሁም የምርጫውን ሂደት ለመሩ፣ ላስተባበሩ እና ለታዘቡ ሁሉ ኢትዮጵያ የላቀ ምስጋና ታቀርባለች ሲል አገልግሎቱ አስታውቋል።

Address

Located Inside Ethiopia
Harar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Harari Urban Development and Construction Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Harari Urban Development and Construction Bureau:

Share