02/04/2026
የግል እና የመንግስት ተቋማት ሰልጣኞች እና አሰልጣኞች በሀገራዊ ምርጫ መሳተፍ አለበቸው:- ወ/ሮ ኢማን መሐመድ
----------------------------------------------------
የሀ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኤጀንሲ በክልሉ የሚገኙ የግል እና የመንግስት ተቋማት ተጠሪዎች ጋር ውይይት አካሄደ።
በውይይቱ ላይ የተገኙት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ኢማን መሐመድ ምርጫው እንዲሳከ የግል እና የመንግስት ተቋማት ሰልጣኞች እና አሰልጣኞች በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ መሳተፍ አለበቸው ሲሉ ገልፀዋል።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አክለውም ሁሉም ሰልጣኞች ተገቢውን ኦሬንቴሽን በመውሰድ ምርጫ ካርድ በመውሰድ ድምፃቸውን መስጠት እንደሚገበ አሳውቋል።
በዕለቱ ውይይት ላይ የተገኙት አቶ አፈንዲ ሰለሞን በግል ተቋማት የሚገኙ ሰልጣኞች በርካታ በመሆነቸው ሁሉም ሰልጣኞች በሚኖሩበት አከባቢያቸው የምርጫ ካርድ በመውሰድ እንዲሳተፉ አሳስቧል።
በመድረኩ የተገኙት የግል እና የመንግስት ተቋማት ዲን እና ተጠሪዎች ለሰልጣኞች እና ለአሰልጣኞች ተገቢውን ኦሬንቴሽን በመስጠት በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ እንዲሳተፉ ለማድረግ እንደሚሰሩ ገልፀዋል።
በመጨረሻም ለተነሱት ጥያቄዎች እና አስተያየቶች የኤጀንሲው ዳይሬክተር መልስ በመስጠት የዕለቱ ስብሰባ ተጠናቀቀ።
በውይይቱ ላይ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ኢማን መሀመድ፣ አቶ አፈንዲ ሰለሞን፣ የኤጀንሲው ተወካዮች እንዲሁም የግል እና የመንግስት ዲኖች ተገኝቷል።
መጋቢት 23/2018 አመት
ሐረር
ፌስቡክ:-https://www.facebook.com/harar.tvet?mibextid=ZbWKwL
ቴሌግረም:- https://t.me/H_Tvetagency