Argoba Special worda educational office /አርጎባ ልዩ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Harbu
  • Argoba Special worda educational office /አርጎባ ልዩ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት

Argoba Special worda educational office /አርጎባ ልዩ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት የትምህርት ጥራትን ማስጠበቅ ትዉልድን ወደ ተሻለ ቦታ በማሻገር ተወዳዳሪ እና ብቁ ዜጋ መፍጠር ነዉ አላማችን !!!

ማስታወቂያ ለፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ተቀብሎ ለማስተማር  የምዝገባ ማስታወቂያ ማውጣታችን ይታወሳል። ሆኖም አንዳንድ ክልሎች ዘግይተው የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ...
21/08/2026

ማስታወቂያ
ለፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ተቀብሎ ለማስተማር የምዝገባ ማስታወቂያ ማውጣታችን ይታወሳል። ሆኖም አንዳንድ ክልሎች ዘግይተው የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት በመልቀቃቸውና በኢንተርኔት ምክንያት ያልተመዘገቡ ተማሪዎች በመኖራቸው ምዝገባው እስከ ነሃሴ 20/2018 ደረስ የተራዘመ መሆኑን እንገልጻለን።
የመመዝገቢያ መስፈርቶች
✍️ ለ9ኛ ክፍል ተመዝጋቢዎች
👉 የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና 80 በመቶ እና በላይ አማካኝ ውጤት ያለው/ያላት እንዲሁም በእንግሊዝኛና በሂሳብ ትምህርቶች 80 እና በላይ ያመጣ/ያመጣች ።
👉 ጥሩ ስነ -ምግባር ያለው/ያላት
✍️ ለ10ኛ ክፍል ተመዝጋቢዎች
👉 በ2017 የትምህርት ዘመን በ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና 70 እና በላይ አማካኝ ውጤት ያመጣ/ያመጣች
👉 በ9ኛ ክፍል ትራንስክሪብት 85 በመቶና በላይ አማካኝ ውጤት ያመጣ/ያመጣች እንዲሁም በእንግሊዝኛ እና ሂሳብ ትምህርት ዓይነቶች 80 በመቶና በላይ ያመጣ/ያመጣች፤

መሆኑን በድጋሚ እያስታወስን በዚህ ሊንክ https://sbs.moe.gov.et/apply በመግባት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
MOE

በአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ በሎኮ ትምህርት ቤት የ2019 የተማሪዎች የፓይለት ምዝገባ ተጀመረመዲና - ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም (አርጎባ ኮሙኒኬሽን)በአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ የ2019 ...
20/08/2026

በአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ በሎኮ ትምህርት ቤት የ2019 የተማሪዎች የፓይለት ምዝገባ ተጀመረ

መዲና - ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም (አርጎባ ኮሙኒኬሽን)

በአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ሙከራ ምዝገባ በሎኮ ትምህርት ቤት ተጀምሯል።

በምዝገባው መርሃ ግብር የአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊዎች በቦታው ተገኝተው የተማሪዎችን የፓይለት ምዝገባ አስጀምረዋል።

የፓይለት ምዝገባው የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ሂደትን በተግባር ለመፈተሽና ለማስተካከል ያለመ ሲሆን፣ በቀጣይም በወረዳው በሚገኙ ሌሎች ትምህርት ቤቶች እንደሚቀጥል ተገልጿል ።

በወረዳው በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በርካታ ተማሪዎች ይመዘገባሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ የምዝገባ ሂደቱ በተቀመጠው ዕቅድ መሠረት እንዲከናወን ትኩረት ተሰጥቷል።

20/08/2026
የአርጎባ ብሄረሰብ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ዕቅድ ትውውቅና የተማሪዎች ምዝገባ የንቅናቄ መድረክ እያካሄደ ይገኛል ።መዲና- ነሃሴ 13/2018 ዓ.ም(አርጎባ ኮ...
19/08/2026

የአርጎባ ብሄረሰብ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ዕቅድ ትውውቅና የተማሪዎች ምዝገባ የንቅናቄ መድረክ እያካሄደ ይገኛል ።

መዲና- ነሃሴ 13/2018 ዓ.ም(አርጎባ ኮሙኒኬሽን)

የአርጎባ ብሄረሰብ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ዕቅድን ለማስተዋወቅና የተማሪዎችን ምዝገባ ለማሳለጥ ያለመ የንቅናቄ መድረክ እያካሄደ ይገኛል ።

መድረኩ የትምህርት ቤት አመራሮች፣ የትምህርት ጽ/ቤት ባለሙያዎችና የቀበሌ አስተዳዳሪዎች በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን፣ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ዕቅድ ዋና አቅጣጫዎችን በማስተዋወቅና ተግባራዊ አፈጻጸሙን ለማጠናከር ትኩረት ተሰጥቷል።

በመድረኩ በተለይም የተማሪዎችን ምዝገባ በወቅቱ ማከናወን፣ ከትምህርት ውጭ የሆኑ ህፃናትን በመለየት ወደ ትምህርት ገበታ ማምጣትና የተማሪዎችን የትምህርት ተሳትፎ ማሳደግ በዋና አጀንዳነት ተነስቷል።

በተጨማሪም የትምህርት ጥራትን ለማሻሻልና የትምህርት ዘመኑን በተሻለ ውጤት ለማስፈጸም የትምህርት ቤት አመራሮች፣ የጽ/ቤቱ ባለሙያዎችና የቀበሌ አስተዳዳሪዎች የጋራ ሚና እንዳላቸው ተገልጿል።

መድረኩ በቀጣይም በዕቅዱ ላይ በመወያየት፣ በተማሪዎች ምዝገባና በትምህርት ተሳትፎ ዙሪያ የሚገኙ ተግዳሮቶችን በመለየት የመፍትሔ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ እንደሚቀጥል ታውቋል።

13/08/2026
13/08/2026
13/08/2026
11/08/2026

ማስታወቂያ

የ ኢፌዴሪ የትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት በሚሰጥባቸው የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የ9ኛና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል። በመሆኑም በልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶቹ ተመዝግባችሁ ለመማር ፍላጎቱ ያላችሁና መስፈርቱን የምታሟሉ ተማሪዎች በዚህ ሊንክ https://sbs.moe.gov.et/apply መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

✍️ ነጻ የትምህርት እድሉ የሚሰጣቸው ጥቅሞች
👉 ሙሉ የትምህርት ክፍያ ሽፋን
👉 የመኝታና የምግብ አገልግሎት
👉 የተሟላ እና ልዩ ሥርዓተ ትምህርት የሚከተል ጥራት ያለው ትምህርት
👉 ምቹ የመማሪያ አካባቢ
✍️ትምህርት የሚሰጥባቸው ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች
✍️ 9ኛ እና 10ኛ ክፍል
👉 ቡኢ ልዩ አዳሪ
👉 ጅግጅጋ ልዩ አዳሪ
👉 ጋምቤላ ልዩ አዳሪ
👉 ወሊሶ ልዩ አዳሪ
👉 ቦንጋ ልዩ አዳሪ
✍️ 9ኛ ክፍል ብቻ
👉 አርባ ምንጭ ልዩ አዳሪ
👉 ድሬዳዋ ልዩ አዳሪ
👉 አሶሳ ልዩ አዳሪ
👉 ባህር ዳር ልዩ አዳሪ
የመመዝገቢያ መስፈርቶች
✍️ ለ9ኛ ክፍል ተመዝጋቢዎች
👉 የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና አማካይ ውጤት 85 በመቶ እና በላይ አማካኝ ውጤት ያለው/ያላት እንዲሁም በእንግሊዝኛና በሂሳብ ትምህርቶች 80 እና በላይ ያመጣ/ያመጣች ።
👉 ጥሩ ስነ -ምግባር ያለው/ያላት

✍️ ለ10ኛ ክፍል ተመዝጋቢዎች
👉በ2017 የትምህርት ዘመን በ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና 70 እና በላይ አማካኝ ውጤት ያመጣ/ያመጣች
👉በ9ኛ ክፍል ትራንስክሪብት 85 በመቶና በላይ አማካኝ ውጤት ያመጣ/ያመጣች እንዲሁም በእንግሊዝኛ እና ሂሳብ ትምህርት ዓይነት 80 በመቶና በላይ ያመጣ/ያመጣች።
✍️ የምዝገባ ሁኔታ
👉 ባሉበት በበየነ መረብ ( Online) ይመዝገቡ፡_ https://sbs.moe.gov.et/apply
✍️ መስፈርቱን የምታሟሉ ተማሪዎች ምዝገባችሁን ባላችሁበት ቦታ ሆናችሁ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የመመዝገቢያ ፖርታል በኦንላይን መመዝገብ እና አስፈላጊ የተባሉ መረጃዎችን ማያያዝ ይጠበቅባችኋል
✍️ ምዝገባው እስከ ነሃሴ 15/2018 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል።
✍️ ለፈተና የሚቀርቡ ተማሪዎች ዝርዝር እና የፈተና ጊዜ ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል
✍️ የመመልመያ መስፈርቱን አሟልተው ፈተናውን የሚያልፉ ተማሪዎች ባሉን ክፍት ቦታዎች በሚመደቡበት ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ለመማር ፈቃደኛ የሆኑ መሆን አለባቸው።

Address

South Wollo Harbu City
Harbu

Telephone

+251913832392

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Argoba Special worda educational office /አርጎባ ልዩ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Argoba Special worda educational office /አርጎባ ልዩ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት:

Shortcuts

Share