Konta zone communication

Konta zone communication በዞኑ ልማት፣ሰላም ፣መልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲ ማስፈን ነው!

 #ሶፊያበኮንታ ብሔር ሴቶች በቡድን ሆነው በባህላዊ አልባሳት እና ጌጣጌጦች ደምቀው አደባባይ ወጥተው የሚታዩበት ኹነት
30/08/2026

#ሶፊያ
በኮንታ ብሔር ሴቶች በቡድን ሆነው በባህላዊ አልባሳት እና ጌጣጌጦች ደምቀው አደባባይ ወጥተው የሚታዩበት ኹነት

የ"ህንግጫ" በዓል ዋዜማን አስመልክቶ የጎዳና ላይ ሩጫ በአመያ ከተማ አስተዳደር ተካሄደ‎በየዓመቱ የሚከበረውን የኮንታ ብሔር ዘመን መለወጫ "ህንግጫ" በዓልን ምክንያት በማድረግ የጎዳና ላይ ...
30/08/2026

የ"ህንግጫ" በዓል ዋዜማን አስመልክቶ የጎዳና ላይ ሩጫ በአመያ ከተማ አስተዳደር ተካሄደ

በየዓመቱ የሚከበረውን የኮንታ ብሔር ዘመን መለወጫ "ህንግጫ" በዓልን ምክንያት በማድረግ የጎዳና ላይ ሩጫ በአመያ ከተማ አስተዳደር በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል።

በመርሃ-ግብሩ የተገኙት የአመያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ተመስገን ደጀኔ እንኳን ለ2019 ዓ.ም የኮንታ ብሄር ዘመን መለወጫ "ህንግጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ይህ ስፖርታዊ ውድድር ባህላችንን ከማስተዋወቅ ባሻገር ማህበረሰብ ውስጥ ፍቅር የሚሰበክበትና አንድነት የሚጠናከርበት ውድድር መሆኑን ገልጸዋል።

"ህንግጫ" በዓልን ለማስተዋወቅ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ገለጸው በመዋቅር ደረጃ ነሐሴ 25/2018 ዓ.ም ላይ የሚከበረውን የህንግጫ በዓል ሁሉም የከተማችን ህብረተሰብ በፍቅር፤ በአንድነትና በአብሮነት እንዲያከብር ጥሪ አቅርበዋል።

የኮንታ ዞን በርካታ ቅርሶች ያሉበት መሆኑን ጠቁመው "ህንግጫ የኮንታ ህዝብ መገለጫ በመሆኑ ሁሉም በባለቤትነት ባህሉን የማስቀጠል ኃላፊነት መውሰድ እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።
ዘገባው፦ የአመያ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

በኮንታ ዞን የ2018 የአመራር ግምገማና ምዘና መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።በኮንታ ዞን የብልፅግና ፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት የአፈጻጸም ማጠቃለያ የአመራር ግምገማና ምዘና መድረክ እየተካሄደ...
29/08/2026

በኮንታ ዞን የ2018 የአመራር ግምገማና ምዘና መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

በኮንታ ዞን የብልፅግና ፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት የአፈጻጸም ማጠቃለያ የአመራር ግምገማና ምዘና መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ መክፈቻ ላይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ብላቴ እንደገለፁት ምዘናው በ2018 በጀት ዓመት የተከናወኑ ተግባራትን አጠቃላይ አፈጻጸም መነሻ በማድረግ የመንግሥትና የፓርቲ የልማት ሥራዎች በሕዝብ ውግንና የተመሩበትን አግባብ ለመፈተሽ ዓላማ ያነገበ መሆኑን ተናግረዋል።

የምዘና መድረኩ የበጀት ዓመቱን አፈጻጸም በመፈተሽ ጥንካሬዎችን ለማጠናከር፣ ድክመቶችን ለማረም እና አመራሩን ለቀጣይ ተልዕኮዎች በብቃት ዝግጁ እንዲሆን ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን አመላክተዋል ።

​በመድረኩ የክልሉ ባ/ቱ/ስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ብላቴ፣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ህግና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች አማካሪ አቶ ዳግም ዳንኤል፣ የክልሉ ቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ም/ል ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ ኮጃአብን ጨምሮ የዞን አጠቃላይ አመራርና የወረዳ/ከተማ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

ይህ የግምገማና ምዘና መድረክ ለተከታታይ ሦስት ቀናት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተመላክቷል።

ዘገባው የኮንታ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።
‎ወቅታዊ፣ሀገራዊና ዞናዊ የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ
‎📌ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/profile.php?id=100069156401354
‎📌ቴሌግራም:- https://t.me/kontazone
‎📌tiktok:-tiktok.com/
‎📌Whatsapp:-https://whatsapp.com/channel/0029Vb5TJ8fHwXbGsJPZj00C
‎📌 instagram:- https://www.instagram.com/?igsh=MTByaHJyZjEwbG90dw==
‎📌 YouTube:- https://www.youtube.com/KontaZoneCommunication
‎📌Twitter :- https://x.com/KontaZone?t=7e24P4Vs1VJi4_2-EGaC2w&s=09
‎ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

29/08/2026
ህዩዋ ...ባላ ህዩዋየ"ህንግጫ" እሴቶቻችን ለመጪው ትዉልድ ግንባታ" በሚል መሪ ቃል በኤላ ሀንቻኖ ወረዳ ባህል፣ ቱርዝምና ስፖርት ጽ/ ቤት አዘጋጅነት የሩጫ መርሃ ግብር በደማቅ ሁኔታ ተካሂ...
29/08/2026

ህዩዋ ...ባላ ህዩዋ

የ"ህንግጫ" እሴቶቻችን ለመጪው ትዉልድ ግንባታ" በሚል መሪ ቃል በኤላ ሀንቻኖ ወረዳ ባህል፣ ቱርዝምና ስፖርት ጽ/ ቤት አዘጋጅነት የሩጫ መርሃ ግብር በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል ።

በመርሃ-ግብሩ የተገኙት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማላ ማዴሶ የኮንታ ብሔር ዘመን መለወጫ ለሆነው ህንግጫ በዓል ዋዜማ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈው ስፖርት ለአንድነት፣ ለጤንነት እንዲሁም ለማህበራዊ መስተጋብር ከማጎልበት ረገድ ሚናው የጎላ እንደሆነ ተናግረዋል።

አክለውም "ህንግጫ" የኮንታ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል እንደሆነ አንስተው በውስጡ ከያዛቸው ብዙ ባህል መዳረሻዎች አንዱ ስፖርት እንደሆነ ተናግረዋል።

የወረዳው ብ/ፓ/ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አጥናፉ ሰሎሞን በበኩላቸው በወረዳ ደረጃ ነሐሴ 25/2018 ዓ.ም የብሔሩን ዘመን መለወጫ በዓል የሆነውን "ህንግጫ" በደመቀ ሁነታ እንደሚከበር አስታውሰው ሁሉም ባለድርሻ አካል ሚናቸውን እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የወረዳው ባ/ቱ/ስ/ጽ ቤት ኃላፊ አቶ መኮንን ትግሮ ህንግጫ በዓል የኮንታ ብሔር ማንነት መገለጫ መሆኑን ገልጸው ዋዜማው በወረዳችን በተለያዩ ባህላዊ ኩነቶች እየተከበረ እንደሚገኝ አንስተዋል።

አያይዘውም የስፖርት ዘርፍን በማጠናከር ፣ የኮንታ ብሔረሰብ" ህንግጫ" በዓል ውስጥ እንደ ባህል መዳረሻ ሆኖ እንድታይ ብሔረሰቡ ትኩረት ሰጥቶ እንድሰራ ባለድርሻ አካላት ሚናቸው የጎላ እንደሆነ አስረድተዋል።

🌻🌻 ህዮዋ.... ህዮዋ ...ባላ ህዮዋ🌻🌻
ዘገባው የኤላ ሀንቻኖ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

"‎ሶፊያ" ‎በኮንታ ብሔር ዘንድ ከጥንት ጀምሮ ከሚከበሩ ባህል፣ ወግና ትውፊት መካከል አንዱ ሶፊያ ነው።‎‎ሶፊያ ከብሔሩ ውብ ባህልና እሴቶች መካከል አንዱ ሲሆን አንዲት ያገባች ሙሽሪት የሙ...
28/08/2026

"‎ሶፊያ"
‎በኮንታ ብሔር ዘንድ ከጥንት ጀምሮ ከሚከበሩ ባህል፣ ወግና ትውፊት መካከል አንዱ ሶፊያ ነው።

‎ሶፊያ ከብሔሩ ውብ ባህልና እሴቶች መካከል አንዱ ሲሆን አንዲት ያገባች ሙሽሪት የሙሽራነት ጊዜዋን አብቅታ ወደ ገበያ ለመውጣትና በሌሎች ማህበራዊ ህይወት ለመቀላቀል ስትል ካገባች ጊዜ ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ከእኩዮቿ እና ከአጃቢዎች ጋር ሆና ተመሳሳይ ለብሳ ወደ ገበያ የምትወጣበት ስርዓትና ባህል ነው።

‎ከሙሽሪት ውጭ የወለደች እናትም የአራስነት ጊዜዋን ስታበቃ አራስ ቤት እያለች ቤተሰቦቿ ተንከባከቧት እንዳማረባት ገበያው እንዲመሰክር ሶፊያ ትወጣላች፤ እንዲሁም አዲስ ልብስ የገዛች ሴትም ከጓደኞቿና ከእኩዮቿ ጋር ሆና ሶፊያ የምትወጣ ሲሆን በዕለቱ ሴቶች አምረውና ተውበው ለብሰው አግጠው ተኳኩለው ይወጣሉ፥

‎ይህ የሶፊያ ስርዓት ለቀጣይ ትውልድ እንዲተላለፍ ያሁኑ ትውልድ በጥንቃቄ መያዝና ባህሉንና አከባበር ስርዓቱን ለመጪው ትውልድ በአግባቡ ማስተላለፍ ይኖርበታል።
‎ የጪዳ ከተማ አስ/ር ኮሙኒኬሽን


በዞኑ የወጣቶችና የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት በማረጋገጥና የሚስተዋሉ ጉድለቶችን በመቅረፍ ሁሉ አቀፍ ብልፅግና ለማስመዝገብ ይሰራል፤ አቶ ገዛኸኝ ገዝሙበኮንታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ...
28/08/2026

በዞኑ የወጣቶችና የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት በማረጋገጥና የሚስተዋሉ ጉድለቶችን በመቅረፍ ሁሉ አቀፍ ብልፅግና ለማስመዝገብ ይሰራል፤ አቶ ገዛኸኝ ገዝሙ

በኮንታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

በዞኑ በፓርቲ መሪነት ባለፉት ጊዜያት በተሰሩ ስራዎች አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸው ተገልጿል።

መድረኩን የመሩት የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አቶ ገዛኸኝ ገዝሙ ብልፅግና ፓርቲ ሀገሪቷን ተረክቦ ተጨባጭ ለውጦችን ለማምጣት ሰፊ ስትራቴጂዎችን ነድፎ ወደ ተግባር በመግባት የህብረተሰቡን ህይወት በዘላቂነት ልለውጡ የሚችሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት መከናወናቸውን አንስተዋል።

በሂደቱም ከውስጥና ከውጭ ብዙ ፈተናዎች ቢያጋጥሙም ለፈተናዎች ሳይበገር በመስራቱ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ዘርፈ ብዙ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ውጤቶች ተመዝግበዋል ብለዋል።

በተለይም የኮርደር ልማት፣ የሞዴል መንደር፣ የሌማት ትሩፋትና ሌሎች ኢንሼቲቮችን ጨምሮ ሌሎች ሰፊ መደበኛ ተግባራት በትኩረት መከናወናቸውን የገለፁት አቶ ገዛኸኝ በቀጣይም የተቋማት ግንባታና ውስጠ ፓርቲ አደረጃጀት በማጠናከር ለበለጠ ውጤት እንደሚሰራ አመላክተዋል።

በዞኑ የወጣቶችና የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት በማረጋገጥና የሚስተዋሉ ጉድለቶችን በመቅረፍ ሁሉ አቀፍ ብልፅግና ለማስመዝገብ ይሰራል ያሉት ኃላፊው ሁሉም በየደረጃው መትጋት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የዞኑ ብልፅግና ፓ/ቅ/ጽ/ቤት ፖለቲካና ህዝብ ግኑኝነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ባሻ በላቸው ያለፈው በጀት ዓመት በሀገሪቱ ብሎም በዞኑ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በድል የተጠናቀቀበትና ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን እየተካሄደ የሚገኝበት መሆኑን በማንሳት ከዚህ ስራ ጎን ለጎን የተለያዩ ኢንሼቲቮችና መደበኛ ተግባራት በተሳካ ሁኔታ የተከናወኑበት እንደሆነ ገልፀዋል።

የዞኑን የፖለቲካ አዝማሚያ ትንተና በማድረግ አስፈላጊ እሪምጃዎች እየተወሰዱ ውጤቶች መመዝገባቸውንም አክለዋል።

የዞኑ ብልፅግና ፓ/ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ እንግዳወርቅ ዶኖቾ በበኩላቸው በዞኑ በ279 ህብረቶች የተደራጁ 43,481 በላይ አባላት መኖራቸውን በመግለፅ ይህንን በማጠናከር ላይ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ሊመሩ እንደሚገባ አስረድተዋል።

በፓርቲ አሰራር በመመራት የጠባቂነት፣ የመረጃ አደረጃጀትና መሠል ችግሮችን በመቅረፍ የትኩረት አቅጣጫዎች በመከተል የህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የበለጠ መስራት ይገባናል ብለዋል።

በዞኑ በ2018 በጀት ዓመት ተቋማዊ ጥንካሬና ቅቡልነት ማሳደግ፣ ህብረ ብሄራዊ አንድነትና ሰላም ማጠናከር፣ የ2018 ሀገራዊ ምርጫ ስኬት ለቀጣይ የብልጽግና ጉዞ እድል ብቻም ሳይሆን ከፍተኛ አደራና ኃላፊነት የተሰጠበት በመሆኑ የመራጩንና መላውን ህብረተሰብ እኩል ለማገልገል ከምንም ጊዜ በላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባና ሌሎች ተቋማዊ አሰራሮችን ማጠናከር ላይ የትኩረት አቅጣጫዎች ተቀምጠው ወደ ተግባር መገባቱ በመድረኩ በቀረበው ሪፖርት ላይ የተገለፀ ሲሆን በዚህም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ዘርፈ ብዙ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተግባራት መከናወናቸው ተገልጿል።

በዞኑ በፖለቲከና ህዝብ ግኑኝነት፣ በአደረጃጀት፣ በሴቶችና ወጣቶች ክንፎች፣ በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታና ሌሎች ዘርፎች አበረታች ስራዎች መሰራታቸው የቀረበ ሲሆን በ2019 በጀት ዓመትም የታየውን የማስፈፀም አቅም የበለጠ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተመላክቷል።

የመድረኩ ተሳታፊ አመራር አካላት ያለፈው ዓመት ከመቼውም ጊዜ በላይ ስኬት የተመዘገበበት ዓመት ስለመሆኑ ተናግረው የፓርቲ አደረጃጀቶችን የበለጠ ማጠናከር፣ የአቅም ግንባታ፣ ክትትልና ድጋፍ ስራዎችን ማሻሻልና የተጀመረውን ስራ ማጠናከር ይገባል ብለዋል።

በህዝብ ስነሱ በነበሩ ቀሪ ጉዳዮች ላይ በማተኮር መስራት ይገባል ያሉት ተሳታፊ አመራር አካላት በተለይም የአገ/ሎት አሰጣጥ ማሻሻል፣ የኑሮ ውድነትን ማርገብ፣ እንዲሁም በቀሪ የመሠረተ ልማትና የወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባቸው ጠቁመዋል።

በመድረኩ የዞኑ ብልፅግና ፓ/ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገዛኸኝ ገዝሙን ጨምሮ ሌሎች የዞን፣ የወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች የፓርቲ ስራ ኃላፊዎች እና የመንግስት ሰራተኛ የህብረት አመራሮች የተገኙ ሲሆን በቀጣይ በትኩረት በሚሰሩ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል።

መድረኩ በ2018 በጀት ዓመት የላቄ ውጤት ላስመዘገቡ መዋቅሮችና ህብረቶች ማበረቻ ሽልማት በመስጠትና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ግብ ስምምነት በመፈራረም እንዲሁም ባለ 8 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።

ዘገባው:-የኮንታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ቤት የህዝብ ግኑኝነት ነዉ።

‎እየተካሄደ ባለው የወረዳ ሽግግር ምክር ቤት 1ኛ ዙር 4ኛ አመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤ የአስፈፃሚ መስሪያ ቤቶች አፈፃፀም የወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ማርቆስ ወንድሙ ለምክ...
27/08/2026

‎እየተካሄደ ባለው የወረዳ ሽግግር ምክር ቤት 1ኛ ዙር 4ኛ አመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤ የአስፈፃሚ መስሪያ ቤቶች አፈፃፀም የወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ማርቆስ ወንድሙ ለምክር ቤቱ እያቀረቡ ይገኛል።

የኮንታ ዞን የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ኦሬንቴሽን መድረክ መካሄድ ላይ ይገኛል።በበጀት ዓመቱ በፓር...
27/08/2026

የኮንታ ዞን የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ኦሬንቴሽን መድረክ መካሄድ ላይ ይገኛል።

በበጀት ዓመቱ በፓርቲው መሪነት የተከናወኑ የተለያዩ ሀገራዊ ኢኒሼቲቮች፣ መደበኛ የፓርቲ ተግባራት በጥንካሬና በድክመት ቀረበው የሚገመገም ይሆናል።

በተጠናቀቀው ዓመት የተገኙ ስኬቶችን በማስቀጠልና የታዩ ክፍተቶችን በማረም፣ የዞኑን ሕዝብ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የትኩረት አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

​መድረክ ላይ የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገዛኸኝ ገዝሙ ጨምሮ የወረዳና ከተማ የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች የዞኑ የብልጽግና ህብረት አመራሮች እንዲሁም የወረዳ እና የከተማ አስተዳደር የፓርቲ አመራሮች ተገኝተዋል።

ዘገባው የኮንታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የህዝብ ግኑኝነት ነዉ።

የፕሮጀክቱ አጠቃላይ አፈጻጸም ከ77 በመቶ በላይ ደርሷል…….///……...የኮይሻ የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ አጠቃላይ አፈጻጸም ከ77 በመቶ በላይ መድረሱን የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ...
26/08/2026

የፕሮጀክቱ አጠቃላይ አፈጻጸም ከ77 በመቶ በላይ ደርሷል
…….///……...
የኮይሻ የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ አጠቃላይ አፈጻጸም ከ77 በመቶ በላይ መድረሱን የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር መብራቱ ተሾመ ገለጹ።

201 ሜትር ርዝመት ያለው የግድብ ግንባታው 6 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የአፈር ቁፋሮ በማካሄድ አጠቃላይ ግድቡ ከሚፈልገው 7 ነጥብ 72 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ የኮንክሪት ሙሊት ውስጥ 81 ነጥብ 2 በመቶው ማለትም 6 ነጥብ 27 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የኮንክሪት ሙሊት (RCC) ሥራ መከናወኑን ተናግረዋል።

የኃይል ማመንጫ ቤቱ የቁፋሮ ሥራ እንዲሁም የሲቪል ሥራው የመጀመሪያ ደረጃ የኮንክሪት ሙሌት ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁንም ተናግረዋል።
EEPethiopia

Address

Konta
Harerge
KONTA

Telephone

+251903725854

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Konta zone communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share