21/08/2026
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ከክልሉ ንግድ ዘርፍና ማህበራት ምክር ቤት ጋር በመተባበር በሀዋሳ ከተማ ለሁለተኛ ጊዜ “የኢትዮጵያን ይግዙ” በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ የንግድ ሣምንት ባዛርና ኤግዚቢሽን ነሐሴ 18 ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 5/2018 ዓ.ም ድረስ ለ15 ቀናት የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ በይፋ ይጀመራል፡፡
በባዛሩና ኤግዚቢሽኑ ላይ በክልሉ የተመረቱ የተለያዩ ለሀገር ውስጥና ለወጪ ገበያ የሚቀርቡ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች በተለይም ክልሉን በዓለም አደባባይ እያስተዋወቀ ያለው የባለ ልዩ ጣዕም ቡና እና አቡካቶ ዘይት ጨምሮ ለዕይታ ይቀርባል፡፡
ለ5 ተከታታይ ቀናት በሚቆየው ባዛርና ኤግዚቢሽን ላይ የክልሉና ከክልሉ ውጭ ያሉ አምራች ኢንዱስትሪዎች፣ ላኪዎች፣ ጅምላ አከፋፋዮች፤ዩኔኖች፤ሸማቾች ሕብረት ሥራ ማህበራት፤ሱፐር-ማርከቶች፤የሰንበት ገበያ ምርት አቅራቢዎች ተሳታፊ ሲሆኑ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች፣ የእንስሳት ተዋጽኦ፣በሀገር ውስጥ የተመረቱ የቆዳና ቆዳ ውጤቶች እንዲሁም የተለያዩ የፍጆታ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቹ ይቀርባሉ፣ ዘላቂ የገበያ ትስስር ይፈጠራል፡፡
በመሆኑም በተጠቀሰው ቀን መላው የክልሉ እንዲሁም አጎራባች አከባቢዎች ያላችሁ ማህበረሰብ በሙሉ በኩነቱ ላይ በመገኘት የሀገርዎን ምርት ይግዙ፣ ይጎብኙ እንላለን!!