Central Ethiopia Region - Prosperity Party - ብልፅግና

Central Ethiopia Region - Prosperity Party - ብልፅግና This is the official Central ER Prosperity Party page where you can get all the latest info.
(12)

Detail contact information
phone number :+251939060376
E-mail:[email protected]

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀላባ ዞን ሴቶች ክንፍ በጠምባሮ ልዩ ወረዳ ወሰን ተሻጋሪ የበጎ አድራጎት ድጋፍ አደረጉሆሳዕና ነሀሴ 27/2018 ዓ.ም"በጎነት ለእህትማማችነትና ለሴቶች ተሳትፎና...
02/09/2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀላባ ዞን ሴቶች ክንፍ በጠምባሮ ልዩ ወረዳ ወሰን ተሻጋሪ የበጎ አድራጎት ድጋፍ አደረጉ

ሆሳዕና ነሀሴ 27/2018 ዓ.ም

"በጎነት ለእህትማማችነትና ለሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት!" በሚል መሪ ሀሳብ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀላባ ዞን የሴቶች ክንፍ ልዑካን ቡድን በጠምባሮ ልዩ ወረዳ በመገኘት እህትማማችነትና ወንድማማችነት የሚያጠናክር ወሰን ተሻጋሪ የበጎ አድራጎት ድጋፍ አበርክተዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ኃላፊ ወ/ሮ ኤልሳቤት ሽመልስ በስነ-ስርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልእክት እንደገለጹት፤ የሴቶች ክንፍ አባላት በክልሉ በሚካሄዱ መደበኛና ወቅታዊ የንቅናቄ አጀንዳዎች ላይ ግንባር ቀደም በመሆን የመሪነት ሚናቸውን ሲወጡ ቆይተዋል፤ አሁንም አጠናክረው ቀጥለዋል።

ኃላፊዋ አክለውም በክረምት ወራት በየደረጃው የሚገኙ የሴቶች ክንፍ አመራሮችና አባላት ባደረጉት የተቀናጀ እንቅስቃሴ በርካታ አርአያነት ያላቸው ተግባራት መከናወናቸውን ጠቅሰዋል።

ወ/ሮ ኤልሳቤት እንደገለጹት በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ በክልሉ በተለዩ 14 የንቅናቄ አጀንዳዎች ላይ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ዘርፈ-ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

የበጎ አድራጎት ስራው በዋናነት በመንግስትና በህብረተሰቡ ብቻ ሊሸፈኑ የማይችሉ፣ የኢኮኖሚ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙና በእድሜ የገፉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ፍላጎት ለማሟላት ያለመ መሆኑንም አስረድተዋል።

የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አዳነ ወጫቶ ከቅርብ ጊዜ ወድህ የተጀመረው በጎ ፍቃድ አገልግሎት የብልጽግና ፓርቲ አንዱ ዓለማ ነው ያሉ ስሆን የአቅም ውስንነት ያለባቸው ሰዎችም በዚህ በጎ ተግባር ተደራሽ እየተደረጉና መጠለያ እያገኙ መሆኑን ጠቁመዋል።

አቶ አደነ ወጫቶም የሀላባ ዞን ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፍቃደኞችን ስለተግባራቸውም አመስግነዋል።

የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ሀላፍ አቶ ፈይሳ ሙንድን የበጎ አድራጎት ስራው ከቁሳቁስ ድጋፍ በላይ በዞኖች እና በወረዳዎች መካከል ያለውን እህትማማችነት፣ አብሮነትና ወንድማማችነት የሚያጠናክር መሆኑን ገልጸዋል።

አክለውም «በጎነት የቋንቋና የወሰን ገደብ የለውም። "ሴትናት በራሱ ደግናት" ማለት ነዉ ያሉት አቶ ፈይሳ የሴቶችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥና አቅመ ደካሞችን መደገፍ የሁልጊዜም ትኩረታችን ነው» ብለዋል።

መርሃ-ግብሩ በክልሉ ባሉ ሁሉም መዋቅሮች እየተከናወነ የሚገኝ ስሆን ተግባሩ የሰብዓዊነት ግዴታም ጭምር መሆኑ ነው በሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ የሴቶች ክንፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሀሊማ ወርቁ ተናግረዋል።

የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጎዴቦ ጆርጋ እንደ ሀገር አቀፍ የተጀመረው የበጎ ፍቃድ አገልግሎት አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ ያለ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ጎዴቦ ተግባሩን የማስቀጠል ኃላፊነት የሁሉም ግለሰብ ኃላፊነትና አደራ ጭምር በመሆኑ ልዩ ትኩረት በየደረጃው ልደረግ ይገባል ብለዋል።

የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ የሴቶች ክንፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ብርቅነሽ መንደሮ በበኩላቸው በሴቶች የሚጀመር በጎ ተግባር ሁል ጊዜ ቀጣይነት ያለውና ከቅንነት የሚመነጭ ፍጹም ተግባር ነው ያሉ ስሆን ተግባሩ በእኛ ሴቶች የሚገታ ሳይሆን ሁሉም ግለሰብ ጋ መዳረስ አለበትም ብለዋል።

አክለውም እኛ ሴቶች የበጎነት ተምሣሌቶች የሰላም ባለቤቶች መሆናችንን ጭምር ይህ መርሃግብር በግልጽ የሚናገር ነው በማለት አገልግሎቱ ዛሬ ብቻ ሚፈጻም ሳይሆን የዘወትር ተግባር ነው ብለዋል።

በተመሳሳይ ማህበራዊ ኃላፊነትን በመወጣት ለአቅመ ደካማ ወገኖች የሚደረገውን ድጋፍ ለማጠናከር በተከናወነ የበጎ አድራጎት ተግባር፤ ለአንድ ለአቅመ ደካማ ቤተሰብ የአዲሱ መኖሪያ ቤት ግንባታን ለመጀመር የሚያስችሉ መሠረታዊ ቁሳቁሶች ድጋፍ የተደረጉ ሲሆን፣ ድጋፉ የቤተሰቡን የኑሮ ጫና በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገልጿል።

ለተጨማሪ መረጃ፦
በቴሌግራም፦ https://t.me/CentralERProsperity

በፌስቡክ፦https://www.facebook.com/CentralEthiopiaRegionprosperitypartyBranchoffice

በቲክቶክ፦tiktok.com/

ቲውተር፦ https://x.com/central94872?t=PyH4QvYNmJyPb4xLPJhGzQ&s=08

ዩቲዩበ=https://youtu.be/31PATodXf20?si=I5ZKltV2OayDr2Ca

ዌብሳይት https://www.cerprosperity.org.et/

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች ወሰን ተሻጋሪ የክረምት  የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ልኡካን ቡድን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ያከናወነው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በምስል
02/09/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች ወሰን ተሻጋሪ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ልኡካን ቡድን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ያከናወነው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በምስል

የኢትዮጵያ ማንሰራራት!የዘንድሮው የጳጉሜን ወር "የኢትዮጵያ ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል በልዩ ልዩ መርሃ-ግብሮች ይከበራል።ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ዘርፈ-ብዙ ድሎችን እያስመዘገበች፣...
02/09/2026

የኢትዮጵያ ማንሰራራት!

የዘንድሮው የጳጉሜን ወር "የኢትዮጵያ ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል በልዩ ልዩ መርሃ-ግብሮች ይከበራል።

ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ዘርፈ-ብዙ ድሎችን እያስመዘገበች፣ ውስብስብ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ፈተናዎችን በፅናትና በፈጠራ በመሻገር፣ በአሁን ወቅት በማንሠራራት ምዕራፍ ላይ ትገኛለች።

የጳጉሜን ወር በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ዘይቤ ውስጥ ወደ አዲሱ ዓመት መሸጋገሪያ ድልድይ በመሆን የተገኙ ወረቶች የሚደመሩበት እንዲሁም ለቀጣዩ ዓመት የከፍታ ጉዞ አዲስ ተስፋ የሚሰነቅበት ልዩ ሀገራዊ መለያችን ነው።

የዘንድሮው የጳጉሜን ቀናት አከባበር የነበሩ ጥንካሬዎችን የሚያስቀጥል፣ የታዩ ክፍተቶችን የሚያርም፣ አዳዲስ የፈጠራ ስልቶችን ታሳቢ ያደረገ፣ የቴክኖሎጂ አቅሞችን በሚገባ የሚጠቀም፣ የተመዘገቡ ትላልቅ ስኬቶችን የሚያስታውስ፣ አዳዲስ ብስራቶችን የሚያበስር በመሆሃ በሳቢ ኹነቶችና የንቅናቄ መንገዶች የሚመራ ይሆናል።

የ 2018 ዓ.ም የጳጉሜን ቀናት አከባበር ከቀደሙት ዓመታት በተለየ መልኩ በብሥራት፣ በተስፋ እና በሁለንተናዊ የብልጽግና ራዕይ ላይ ያተኮረ እንደሚሆንም የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ በሰጠዉ መግለጫ አመላክቷል።

የ 2018 ዓ.ም የጳጉሜን ቀናት፤ ጳጉሜን 1 (የእመርታ ቀን)፣ ጳጉሜን 2 (የማንሰራራት ቀን)፣ ጳጉሜን 3 (የጽናት ቀን)፣ ጳጉሜን 4 (የኅብር ቀን) እንዲሁም ጳጉሜን 5 (የነገ ቀን) በሚሉ መርሃ-ግብሮች በድምቀት የሚከበሩ ይሆናል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች ወሰን ተሻጋሪ የክረምት  የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ልኡካን ቡድን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የልማት ፕሮጀክቶችን ተመለከቱ ወጣቶቹ በክልሉ በነበራቸው ቆይታ ግንባ...
02/09/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች ወሰን ተሻጋሪ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ልኡካን ቡድን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የልማት ፕሮጀክቶችን ተመለከቱ

ወጣቶቹ በክልሉ በነበራቸው ቆይታ ግንባታቸው በስድስት ወራት ብቻ የተጠናቀቁ የልማት ፕሮጀክቶችን ተመልክተዋል።

የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት፣የመሰብሰቢያ አዳራሽ እና ቤተ መንግስት ወጣቶቹ ከተመለከቷቸው የልማት ፕሮጀክቶች ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች ወሰን ተሻጋሪ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ልኡካን ቡድን በክልሉ ልዩ ልዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እያከናወነ ይገኛል።

02/09/2026
የሰዎች እርስ በርስ የመረዳዳት ባህል  ዘመናትን የተሻገረ ነው :-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) (ሆሳዕና፣ነሐሴ 27/2018)ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)ለደቡብ ኢት...
02/09/2026

የሰዎች እርስ በርስ የመረዳዳት ባህል ዘመናትን የተሻገረ ነው :-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

(ሆሳዕና፣ነሐሴ 27/2018)ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች ወሰን ተሻጋሪ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ልኡካን ቡድን በጽ/ቤታቸው አቀባበል አደረጉ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የረጅም ዘመናት ታሪክ አለው ብለዋል።

የሰዎች እርስ በርስ የመረዳዳት ሂደት ዘመናትን የተሻገረ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በተለይ በአድዋ ታሪክ ወጣቶች እና ሴቶች ከፍተኛ ድርሻ እንደነበራቸው ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውሰዋል።

ሴቶች ቀለብ ማዘጋጀት ወጣቶች ደግሞ በአርበኝነት ሀገርን የማዳን ትግል ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ እንደነበራቸው ርዕሰ መስተዳድሩ በአብነት ጠቅሰዋል።

ወጣቶች ሚዛናዊ አስተሳሰብ እንዲሰርጽ በማድረግ በሀገር እድገት ላይ የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባም አመላክተዋል።

ወጣቶች በቴክኖሎጂው ዘርፍ የሚኖራቸውን ተወዳዳሪነት በማላቅ ኢኮኖሚያዊ አቅማቸውን ሊያሳድጉ እንደሚገባም ጠቅሰዋል።

ወጣቶች ለህዝቦች አንድነት እና ትስስር በጋራ መስራት እንዳለባቸው የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህም ኢትዮጵያ የጀመረችውን ጉዞ ማጠናከር ይጠበቃል ሲሉም አብራርተዋል።

ክልሉ በአጭር ጊዜ ተመስርቶ ወደ ስራ ከገባ ወዲህ በርካታ አብነታዊ ስራዎችን ተግባራዊ ማድረጉን ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።

በክልሉ የልማት ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ በመገንባት ስራ ማስጀመር መቻሉን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።

የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት፣የመሰብሰቢያ አዳራሽ እና ቤተ መንግስት በስድስት ወራት ማጠናቀቅ ተችሏል ብለዋል።

በክልሉ በሁሉም ዘርፍ የህዝብ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት እያደገ ስለመምጣቱም ርዕሰ መስተዳድሩ በአብነት ጠቅሰዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ሌሊሾ በበኩላቸው "በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ በሚል መሪ ሀሳብ "እየተካሄ ያለው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በህዝቦች መካከል ጠንካራ አንድነት እና ትስስር ይፈጥራል ብለዋል።

የዘንድሮውን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ልዩ የሚያደርገው ኢትዮጵያ በልማት፣በሰላም በዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ በላቀ ከፍታ ለመሻገር በምታደርገው ማዕቀፍ ውስጥ በሆነችበት ጊዜ መሆኑን አቶ ጌታቸው ጠቁመዋል።

በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ ወጣቶችን በማቀናጀት አካባቢን ከመቀየር ባሻገር የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እና ወዳጅነትን እንደሚያጠናክር ኃላፊው አስታውቀዋል።

በአለም አቀፍ ደረጃ ወጣቶች ድንበር ተሻግረው እንዲሰሩ ማድረግ በመቻሉ የወጣቶችን አቅም ከማሳደጉም ባሻገር አህጉራዊ አንድነትና ትስስር እንዲኖር ያደርጋል ብለዋል።

ወጣቶች ከተለያዩ የአለም አቀፍ ክፍሎች ተንቀሳቅሰው በማህበረሰብ ልማት በአካባቢ ጥበቃ እና በትምህርት ዘርፍ አገልግሎት እየሰጡ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወጣቶች ጉዳይ እና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ኮሚሽነር ማርቆስ ማቲዎስ እንደገለጹት በክልሉ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ምስጋና አቅርበዋል ።

የክልሉ መንግስት ወደ ቀድሞ ቤታችን ሲልከን በደም የተጋመደ አንድነታችንን ይበልጥ እንድናጠናክር ነው ብለዋል።

ከወንድሞቻችን ጋር በደም ልገሳ፣ማዕድ ማጋራት ችግኝ ተከላ እና በሌሎችም የበጎ ፈቃድ ስራዎች ላይ ተሳትፎ እንደሚያደርጉም ኮሚሽነሩ አብራርተዋል።

ወጣቶቻችንን ሀብት ከማዳን ባለፈ ለወገኖቻችን በነጻ የምንሰጠው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አብሮነትን በማጠናከር ረገድ የጎላ አበርክቶ አለው ብለዋል።

የክልሉ ወጣቶች ክንፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወጣት አብዱ ድንቁ እንደገለጸው በክልሉ ያለውን እምቅ የመልማት አቅም በማጠናከር በሁሉም ዘርፍ የላቀ ውጤት ተመዝግቧል ብሏል።

በክልሉ ለተመዘገበው የላቀ ውጤት የአመራር ቁርጠኝነት እና የስራ ባህል ለውጥ መሆኑን ወጣት አብዱ አስረድቷል።

የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የብልፅግና ፓርቲን የለውጥ ሥራ አደነቀ።በብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ የውጭ ግንኙነት ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ነብዩ ስሑል የተመራ...
01/09/2026

የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የብልፅግና ፓርቲን የለውጥ ሥራ አደነቀ።

በብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ የውጭ ግንኙነት ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ነብዩ ስሑል የተመራ የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ልዑክ በቻይና ጉብኝት እያደረገ ይገኛል።

ልዑኩ በቤጂንግ ከቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የአፍሪካ ጉዳዮች ኮሚቴ ጋር የፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነትን በተመለከተ ውይይት አካሂዷል።

በውይይቱ ላይ አቶ ነብዩ ስሑል፣ ብልፅግና ፓርቲ የሚመራበት የመደመር እሳቤና የፓርቲው ፕሮግራሞች በኢትዮጵያ ለሚታዩት ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ለውጦች ዋነኛ መሠረት መሆናቸውን ገልጸዋል።

የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ፖሊሲው ውጤታማነት፣ የከተማና የገጠር ልማትን በተቀናጀ መልኩ ማከናወን፣ ሕዝብን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎች እና የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ የፓርቲውን የእሳቤ ጥራትና የማስፈጸም አቅም የሚያሳዩ ዋነኛ ተግባራት መሆናቸውንም አቶ ነብዩ ጠቁመዋል።

የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ከሀገር ውስጥ የልማት ሥራ ባሻገር፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ አቅም እያጠናከረ ያለ ተግባር መሆኑንም ገልጸዋል።

በፖለቲካው መስክ እየተመዘገቡ ያሉ አበረታች ለውጦችን በመጥቀስ፣ ኢትዮጵያ በ2026 የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤን በአዲስ አበባ ለማስተናገድ መመረጧንና ለጉባኤው ዝግጅት እያደረገች መሆኗን አስረድተዋል።

በሌላ በኩል፣ ልዑኩን የተቀበሉት የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል ወ/ሮ ሪኦ ዩሃ ብልፅግና ፓርቲ “ጠንካራ ፓርቲ ለጠንካራ መንግሥት፤ ጠንካራ መንግሥት ለጠንካራ ሀገር” በሚል እሳቤ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እያስመዘገበ ያለውን ለውጥ ፓርቲያቸውና መንግሥታቸው በከፍተኛ አድናቆት እንደሚከታተሉ ገልጸዋል።

ወ/ሮ ሪኦ ዩሃ አክለውም፣ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲና ብልፅግና ፓርቲ በፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነት የሚያደርጉትን ትብብር እና የጋራ ጥቅሞችን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ቅንጅት በቀጣይ ለማጠናከር ፓርቲያቸው ጠንካራ አቋም እንዳለው አረጋግጠዋል።

የብልፅግና ፓርቲ ልዑክ በቤጂንግ በነበረው የመጀመሪያ ቀን ውሎ፣ ከሁለትዮሽ ውይይቱ በተጨማሪ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲን ታሪክ፣ ልምድ፣ ድሎችና ተግዳሮቶች የሚያሳየውን የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ሙዚየም ጎብኝቷል።

ጉብኝቱ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ካለፈው ታሪኩ በመማር የአሁኑን ስኬቶች እንዴት እያጠናከረ እንደሚገኝና የወደፊት ራዕዩን ለማሳካት እያከናወነ የሚገኘውን እንቅስቃሴዎች ለመመልከት ጠቃሚ የመማማሪያ ልምድ ሆኗል።

በቀጣዮቹ ቀናት የሁለቱ ፓርቲዎች አመራሮች የጋራ ልምድ የሚጋሩበትና እርስ በእርስ የሚማማሩበት መርሃ ግብር ይከናወናል።

የጉራጌ ዞን የሴቶች ክንፍ በሀላባ ዞን ወሰን ተሻጋሪ የበጎ አድራጎት ድጋፍ አደረጉሆሳዕና ነሀሴ 26/2018 ዓ.ምበማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ ዞን የሴቶች ክንፍ ልዑካን ቡድን በሀላባ ...
01/09/2026

የጉራጌ ዞን የሴቶች ክንፍ በሀላባ ዞን ወሰን ተሻጋሪ የበጎ አድራጎት ድጋፍ አደረጉ

ሆሳዕና ነሀሴ 26/2018 ዓ.ም

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ ዞን የሴቶች ክንፍ ልዑካን ቡድን በሀላባ ዞን ሀላባ ቁሊቶ ከተማ በመገኘት ህዝባዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነትን የሚያጠናክር ወሰን ተሻጋሪ የበጎ አድራጎት ድጋፍ አበርክተዋል።

የዚሁ የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴ አካል የሆነው ለአረጋውያን የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፤ በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ሜጦማ ቀበሌ በመገኘት ለአንዲት አቅመ-ደካማ እናት የሚሆን የቤት ግንባታ አስጀምረዋል።

የልዑካን ቡድኑ ለቤት ግንባታው የሚሆኑ ቆርቆሮዎችና ሚስማሮችን ጨምሮ ለቤት ውስጥ አገልግሎት የሚውሉ ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን አበርክተዋል።

ይህ አርአያነት ያለው ተግባር የብልጽግና ፓርቲን ህዝባዊነት፣ አብሮነትና ማህበራዊ እሴቶች በተግባር ያሳየ ሲሆን፤ በዞኖች መካከል ያለውን አብሮነት፣ ወንድማማችነትና እህትማማችነትን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር መሆኑ ተገልጿል።

ለተጨማሪ መረጃ፦
በቴሌግራም፦ https://t.me/CentralERProsperity

በፌስቡክ፦https://www.facebook.com/CentralEthiopiaRegionprosperitypartyBranchoffice

በቲክቶክ፦tiktok.com/

ቲውተር፦ https://x.com/central94872?t=PyH4QvYNmJyPb4xLPJhGzQ&s=08

ዩቲዩበ=https://youtu.be/31PATodXf20?si=I5ZKltV2OayDr2Ca

ዌብሳይት https://www.cerprosperity.org.et/

 ! በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ ቀቤና ልዩ ወረዳ በፈቃዶ፣ ሩሙጋ እና ፈረጀቴ ቀበሌዎች እየለማ የሚገኘው የበቆሎ ክላስተር ማሳ የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተከናወኑ ካሉ ሥራዎች መካከ...
01/09/2026

!

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ ቀቤና ልዩ ወረዳ በፈቃዶ፣ ሩሙጋ እና ፈረጀቴ ቀበሌዎች እየለማ የሚገኘው የበቆሎ ክላስተር ማሳ የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተከናወኑ ካሉ ሥራዎች መካከል አንዱ ነው።

የበቆሎ ክላስተር ልማቱ የአርሶ አደሩን ምርታማነት በማሳደግ፣ የምግብ ዋስትናን በማጠናከርና ከተረጂነት ወደ ራስን በመቻል እና ወደ ምርታማነት የሚደረገውን ሽግግር ለማረጋገጥ የሚያግዝ የልማት ሥራ ነው።

"የአማራ ክልል ፈተና የማይበግረው እና ጽናት ያለው መሪ እየፈጠረ ነው" በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኀላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል...
01/09/2026

"የአማራ ክልል ፈተና የማይበግረው እና ጽናት ያለው መሪ እየፈጠረ ነው"

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኀላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ የአማራ ክልል ከፍተኛ እና መካከለኛ መሪዎች የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲ እና የመንግሥት ሥራዎች አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት የዕቅድ ትውውቅ መድረክ ላይ ካስተላለፉት መልዕክት የተወሰደ

Address

HOSSANA
Hossana

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Central Ethiopia Region - Prosperity Party - ብልፅግና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Central Ethiopia Region - Prosperity Party - ብልፅግና:

Shortcuts

Share