Hadiya Zone Education Sector

Hadiya Zone Education Sector የሀዲያ ዞን ትምህርት መምሪያ የሚገኘው በማዕከላዊ ኢቲዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ ውስጥ ሲሆን በትምህርት ሚንስቴር ስር ሆኖ ከተዋቀረበት ጊዜ ጀምሮ ዓላማውን አንግቦ ኢየሰራ ይገኛል፡፡

29/06/2026

የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ነገ ሰኔ 23 ይጀምራል።

(ሰኔ 22/ 2018 ዓ.ም )የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ በ607 የፈተና ማዕከላት በስድስት ዙር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

ለፈተናው በድምሩ 563,501 ተፈታኞች የተመዘገቡ ሲሆን፣ 306,456 የተፈጥሮ ሳይንስ እና 257,045 የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ናቸው።

አገልግሎቱ ለፈተናው የሚያስፈልጉ ሁሉንም ዝግጅቶች ማጠናቀቁንና የፈተና አስፈጻሚዎችን ወደ ፈተና ማዕከላት ማሰማራቱን ገልጿል።

ተፈታኞች ወደ ፈተና ማዕከላት ሲቀርቡ የመፈተኛ መግቢያ ካርዳቸውን (Admission Card)፣ የተማሪ ወይም ህጋዊ መታወቂያ፣ በፈተና አስተዳደሩ የተፈቀደ እስክሪብቶ እና ባዶ ወረቀት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

ሞባይል ስልክ፣ ስማርት ሰዓት፣ ብሉቱዝ፣ ጆሮ ማዳመጫ፣ ፍላሽ ዲስክ፣ ሜሞሪ ካርድ፣ የግል ላፕቶፕ ወይም ታብሌት እና ሌሎች ያልተፈቀዱ መሳሪያዎችን ይዞ ወደ ፈተና ክፍል መግባት አይፈቀድም።

ፈተናው በበይነ መረብ በ6 ዙር የሚሰጥ ሲሆን፣ በወረቀት የሚፈተኑ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከሐምሌ 1 እስከ 3፣ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ደግሞ ከሐምሌ 6 እስከ 8 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚፈተኑ ተገልጿል።

የትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም ተፈታኞች መልካም እድል እየተመኘ፣ ፈተናውን በመረጋጋት፣ በሥነ ምግባር እና በራስ መተማመን እንዲወስዱ ጥሪ አቅርቧል።

06/06/2026
የሀዲያ ዞን ት/መምሪያ ሀላፊና ሰራተኞች በግቤ ወረዳ ሲደማ ት/ቤት ተገኝተዋል::21/8/2018 የዞኑ ግብረሀይሉ በዕለቱ በዚህ በሲደማ በመገኘት በአከባቢው መህበረሰብ ተሳትፎ የተሰራውን የት...
29/05/2026

የሀዲያ ዞን ት/መምሪያ ሀላፊና ሰራተኞች በግቤ ወረዳ ሲደማ ት/ቤት ተገኝተዋል::
21/8/2018 የዞኑ ግብረሀይሉ በዕለቱ በዚህ በሲደማ በመገኘት በአከባቢው መህበረሰብ ተሳትፎ የተሰራውን የት/ቤት ግንባታ ጎብኝተዋል::
በዚሁ በጉብኝት ወቅት የተኙት የዞኑ ት/መምሪያ ሀላፊ አቶ ዴታሞ ጡምደዶ ከሰራተኞቻቸው ጋር በመሆን የት/ቤቱን ነባርዊ ሁኔታ ይህ አድስ ህንፃ ከመጀመሩ በፊት ምን እንደምመስልና እንዴት እንደነበረ ተዘዋውሮ አይቶዋል::
የአከባቢውንም ሕብረተሰብ ሥራ እያሉ ለማበረታታት በመምሪያው ስም የ100,000 ብር ድጋፍ አሻም በማለት አበርክቶዋል::

25/05/2026

የምስራች ለተማሪዎች በሙሉ! 📢
የ2018 ዓ.ም የክልላዊ ሞዴል ፈተና በኦንላይን (Online) ተለቋል!
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ትምህርት ቢሮ የዘንድሮውን የክልላዊ ሞዴል ፈተና በዌብሳይት ዝግጁ ስላደረገላችሁ፣ ለዋናው ፈተና የሚረዳችሁን ቅድመ-ዝግጅት እና ልምምድ እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
📱 እንዴት መፈተን ይቻላል?
መጀመሪያ ወደዚህ ድረ-ገጽ ይግቡ 👉 lms.cereb.edu.et
የተጠቃሚ ስም (Username)፦ የአድሚሽን ቁጥራችሁን (Admission Number) ያስገቡ።
የይለፍ ቃል (Password)፦ 123456 በመጠቀም ይግቡ።
💡 ማሳሰቢያ፦ ይህ ፈተና ለዋናው ፈተና ራሳችሁን በሚገባ እንድታዘጋጁ የሚረዳ ስለሆነ ሳይዘገዩ አሁኑኑ ልምምድ ይጀምሩ!
መልካም ዕድልና ስኬት! የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ትምህርት ቢሮ ICT ዳይሬክቶሬት

31/03/2026
22/02/2026
20/02/2026
በኢንሼቲቭ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸሀውን የሀዲያ ዞን ትምህርት መምሪያ ገለጸ፡፡ሰሞኑን የውይይትና የንቅናቄ በሁሉም መዋቅሮች አዘጋጅቶ ስራውን ስሰረ የቆየው መምረው በ2018 ት/...
20/02/2026

በኢንሼቲቭ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸሀውን የሀዲያ ዞን ትምህርት መምሪያ ገለጸ፡፡

ሰሞኑን የውይይትና የንቅናቄ በሁሉም መዋቅሮች አዘጋጅቶ ስራውን ስሰረ የቆየው መምረው በ2018 ት/ት ዘመን በንቅናቄና እንሼቲቭ የሚሰሩ ስራዎችን ገምግመዋል፡፡ ከዞኑም ወደ እያንዳንዱ ወረዳና ከተማ አስተዳደር የሄዱ ደጋፊዎች በአብዛኛው በገመገሙባቸው መድረኮች አመርቂ ዉቴት መመዝገባቸውን ወደ ዞን ሪፖርት አድረጎዋሉ፡፡

Address

Hossana
Hossana
0024

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hadiya Zone Education Sector posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share