Social Affairs

Social Affairs you can know about country's politics, social, ways of life, currently condition and learn about to know English,

 ፦ ኢራን ‘የመፈራረስ አደጋ ላይ’ እንደሆነች በቅርቡ ‘አሳውቃናለች”- ትራምፕ“ኢራን ‘የመፈራረስ አደጋ ላይ’ እንደሆነች በቅርቡ አሳውቃናለች ስሉ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ገለ...
28/04/2026

፦ ኢራን ‘የመፈራረስ አደጋ ላይ’ እንደሆነች በቅርቡ ‘አሳውቃናለች”- ትራምፕ

“ኢራን ‘የመፈራረስ አደጋ ላይ’ እንደሆነች በቅርቡ አሳውቃናለች ስሉ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ገለጹ።

ትራምፕ አክለዉም የአመራር ሁኔታቸውን ለመፍታት በሚሞክሩበት በዚህ ወቅት ‘የሆርሙዝ ስትሬትን (Hormuz Strait)’ በተቻለ ፍጥነት ‘እንድንከፍትላቸው’ ይፈልጋሉ” ስሉ ገልጸዋል።

 ፡ የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን የቀረበላቸዉን የሰላም የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ አደረጉ!የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን የቀረበላቸዉን የሰላም የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ ...
28/04/2026

፡ የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን የቀረበላቸዉን የሰላም የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ አደረጉ!

የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን የቀረበላቸዉን የሰላም የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ ማድረጋቸውን ተከትሎ ተስፋ ተጥሎበት የነበረውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ጥያቄ ምልክት ውስጥ ከቶታል።

የኢራን የውሳኔ ሃሳብ በደረጃ የተከፋፈለ የድርድር ሂደት ያካተተ ሲሆን፤ ሂደቱም በተኩስ አቁም ስምምነት ተጀምሮ፣ በመቀጠል የባህር ላይ ትራንስፖርት ገደቦችን በማንሳት እና በመጨረሻም የኒውክሌር ጉዳዮችን ለመወያየት ያለመ ነበር።

ይሁን እንጂ ዋሽንግተን የኒውክሌር ድርድሩ በቅድሚያ እንዲከናወን ጽኑ አቋም መያዟ፣ በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለውን ልዩነት አቀራርቦ የነበረውን ተስፋ አጨልሞታል።

ይህ የዲፕሎማሲ መቋረጥ የተከሰተው፣ የዓለም አቀፍ የነዳጅ አቅርቦት መስተጓጎል በከፍተኛ ሁኔታ እየተባባሰ በመጣበት እና ይህም በዓለም ኢኮኖሚ ላይ የዋጋ ግሽበትንና አለመረጋጋትን እየፈጠረ ባለበት ወቅት ነው።

በተለይም በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ (Strait of Hormuz) በኩል የሚደረገው የመርከቦች እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ ተገድቧል። ቀደም ሲል በቀን በአማካይ ከ120 በላይ መርከቦች ይተላለፉበት የነበረው መስመር፣ በአሁኑ ወቅት ወደ ነጠላ አሃዝ ዝቅ ማለቱ ተመልክቷል።

 : በሩሲያ ቁጥጥር ስር በሚገኘው የክራይሚያ ግዛት፣ የሩሲያ ኢስካንደር (Iskander) ኦፕሬሽናል-ታክቲካል ሚሳኤል ሲስተሞች የሚገኙበት የጦር ሰፈር በሌሊት በተሰነዘረ የዩክሬን የድሮን ጥ...
28/04/2026

: በሩሲያ ቁጥጥር ስር በሚገኘው የክራይሚያ ግዛት፣ የሩሲያ ኢስካንደር (Iskander) ኦፕሬሽናል-ታክቲካል ሚሳኤል ሲስተሞች የሚገኙበት የጦር ሰፈር በሌሊት በተሰነዘረ የዩክሬን የድሮን ጥቃት መመታቱ ተዘገበ።

 : ሂዝቦላህ በደቡብ ሊባኖስ የሚገኙ የ‘እስራኤል’ ወታደራዊ አባላትን እና ቁሳቁሶችን ኢላማ ማድጉን ገለጸ!ሂዝቦላህ የባህር ላይ እና የድንበር ዘለል ጥቃቶቹን በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ያስታ...
28/04/2026

: ሂዝቦላህ በደቡብ ሊባኖስ የሚገኙ የ‘እስራኤል’ ወታደራዊ አባላትን እና ቁሳቁሶችን ኢላማ ማድጉን ገለጸ!

ሂዝቦላህ የባህር ላይ እና የድንበር ዘለል ጥቃቶቹን በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ያስታወቀ ሲሆን፣ ለዚህም በርካታ የ‘እስራኤል’ ኢላማዎችን ለመምታት አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ (one-way) አጥቂ ድሮኖችን ተጠቅሟል።

ቡድኑ ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ ቢንት ጅቤል በተባለችው የድንበር ከተማ ውስጥ የመኖሪያ ቤቶችን በማፍረስ ላይ የነበረች የ‘እስራኤል’ ወታደራዊ ቡልዶዘር በአጥፍቶ ጠፊ ድሮን በተሳካ ሁኔታ ተመትታለች።

በተመሳሳይ ጊዜ፣ በአል-ቃንታራ ከተማ አደባባይ ተሰብስበው በነበሩ የ‘እስራኤል’ ወታደሮች ላይ ሌላ የድሮን ጥቃት የተፈጸመ ሲሆን፣ ቡድኑ በወታደሮቹ ላይ “ትክክለኛ ድብደባ” ማረፉን ገልጿል።”

 : ባንግላዴሽ የመጀመሪያውን የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በመክፈት ወደ አዲሱ የኢነርጂ ዘመን ተሸጋገረች!ባንግላዴሽ በሩሲያው የመንግሥት የኒውክሌር ኃይል ኮርፖሬሽን (ሮሳቶም) የተገነባው...
28/04/2026

: ባንግላዴሽ የመጀመሪያውን የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በመክፈት ወደ አዲሱ የኢነርጂ ዘመን ተሸጋገረች!

ባንግላዴሽ በሩሲያው የመንግሥት የኒውክሌር ኃይል ኮርፖሬሽን (ሮሳቶም) የተገነባውን የመጀመሪያውን የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በይፋ ሥራ በማስጀመር፣ የኒውክሌር ኃይል አምራች አገራት ተርታ ተቀላቅላለች።

የዚህ ግዙፍ የኃይል ማመንጫ ተቋም ግንባታ መጠናቀቅ ባንግላዴሽ ለመጀመሪያ ጊዜ የኤሌክትሪክ ፍላጎቷን ከኒውክሌር ኃይል ለማሟላት ለምታደርገው ጥረት ትልቅ ታሪካዊ ምዕራፍ መሆኑ ተገልጿል።

ይህ ፕሮጀክት ከሩሲያ ጋር በጋራ የተገነባ ሲሆን፤ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን እያደገ የመጣ የኢነርጂ እና የመሠረተ ልማት ትብብር ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።

የአገሪቱ ባለሥልጣናት እንደገለጹት፤ የዚህ ስትራቴጂካዊ ፕሮጀክት ዋና ዓላማ፦

የአገሪቱን የኤሌክትሪክ ማመንጨት አቅም በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ፤

የረጅም ጊዜ የኢነርጂ ዋስትናን ለማረጋገጥ፤ እና

የኢኮኖሚ ዕድገቱን የሚመጥን አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት ለመፍጠር ነው።

 ፦ ሩሲያ ማዕቀቦችን በመጣስ በምዕራባውያን ቴክኖሎጂ የተሰራ አዲስ ሚሳኤል መጠቀሟን ዩክሬን አጋለጠች!የዩክሬን ወታደራዊ መረጃ ምንጮች S-71K ስለተሰኘው አዲሱ የሩሲያ የክሩዝ ሚሳኤል ዝር...
28/04/2026

፦ ሩሲያ ማዕቀቦችን በመጣስ በምዕራባውያን ቴክኖሎጂ የተሰራ አዲስ ሚሳኤል መጠቀሟን ዩክሬን አጋለጠች!

የዩክሬን ወታደራዊ መረጃ ምንጮች S-71K ስለተሰኘው አዲሱ የሩሲያ የክሩዝ ሚሳኤል ዝርዝር መረጃዎችን ይፋ አድርገዋል። እንደ መረጃው ከሆነ ሩሲያ ከፍተኛ ማዕቀቦች ቢጣሉባትም ሚሳኤሉን ለመስራት የውጭ አገራት የኤሌክትሮኒክስ መለዋወጫዎችን በስፋት ተጠቅማለች።

ከተደመሰሱ ሚሳኤሎች ፍርስራሽ ላይ በተደረገ ምርመራ፤ ከአሜሪካ፣ ቻይና፣ ጃፓን፣ ጀርመን፣ ስዊዘርላንድ፣ ታይዋን እና አየርላንድ የተገኙ ክፍሎች ተገኝተዋል።

ይህ ግኝት ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ውጤቶች የሆኑ ቺፖች እና የመምሪያ (guidance) ሥርዓቶች አሁንም ድረስ ወደ ሩሲያ የጦር መሣሪያ ማምረቻዎች እየገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ ሲሆን፣ ይህም በዓለም አቀፍ የወጪ ንግድ ቁጥጥር ላይ ያሉ ክፍተቶችን አሳሳቢነት አመልክቷል።

የS-71K ሚሳኤል ቁልፍ መረጃዎች፦
ተሸካሚ፦ ከSu-57 ተዋጊ ጄቶች ላይ የሚተኮስ።

የመምታት ርቀት፦ እስከ 300 ኪሎ ሜትር የሚደርስ።

ልዩ ባህሪ፦ በሚሳኤል እና በድሮን መካከል ያለ ድብልቅ (hybrid) ንድፍ ያለው።

ቴክኖሎጂ፦ በራስ-ሰር ኢላማን የመለየት እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የታገዘ የጥቃት ሥርዓት ያለው።

በተጨማሪም ሩሲያ ይህንን ሥርዓት ከ S-70 Okhotnik የረቀቀ ድሮን (stealth drone) ጋር ልታቀናጅ እንደምትችል ምልክቶች አሉ። ይህም ወደፊት የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ለመለየት እና ለመከላከል አስቸጋሪ ያደርጋቸዋል።

ይህ አዲስ ክስተት የማዕቀብ አፈጻጸም ላይ ያለውን ፈተና ከማሳየቱም በላይ በጦር ሜዳው ላይ የታየ ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ሽግግር ተደርጎ ተወስዷል።

 : ሩሲያ ዘመናዊ ድሮኖችን ለኢራን ልታቀርብ እንደሆነ የአውሮፓ ደህንነት ተቋማት ማስጠንቀቂያ ሰጡ!በርካታ ከፍተኛ የአውሮፓ ባለስልጣናት እንደገለጹት፤ ሩሲያ ከዩናይትድ ስቴትስ እና ከእስራኤ...
28/04/2026

: ሩሲያ ዘመናዊ ድሮኖችን ለኢራን ልታቀርብ እንደሆነ የአውሮፓ ደህንነት ተቋማት ማስጠንቀቂያ ሰጡ!

በርካታ ከፍተኛ የአውሮፓ ባለስልጣናት እንደገለጹት፤ ሩሲያ ከዩናይትድ ስቴትስ እና ከእስራኤል ጋር ለገባችበት ግጭት ይረዷታል የተባሉ የላቁ ሰው አልባ የጦር አውሮፕላኖችን (ድሮኖችን) ለኢራን ለማስተላለፍ ዝግጅት እያደረገች ነው።

ሩሲያ እስካሁን ድረስ የተባለውን የድሮን ዝውውር በይፋ ያላረጋገጠች ሲሆን፣ የመንግሥት ባለስልጣናትም የቀረበውን ክስ ውድቅ አድርገዋል።"

ኢትዮጵያ  ከሚቀጥለው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ጀምሮ ከራሷ ምድር የተገኘን ድፍድፍ ነዳጅ በራሷ ምድር ማጣራት ትጀምራለች።የኢነርጂ ነገር ስናነሳ በተለይ ደግሞ የነዳጅና ነዳጅ ነክ ጉዳይ "መ...
28/04/2026

ኢትዮጵያ ከሚቀጥለው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ጀምሮ ከራሷ ምድር የተገኘን ድፍድፍ ነዳጅ በራሷ ምድር ማጣራት ትጀምራለች።

የኢነርጂ ነገር ስናነሳ በተለይ ደግሞ የነዳጅና ነዳጅ ነክ ጉዳይ "መሀሉ አይነገርም" እየተባለ የሚሰራ ስራ ነው።

ከላይ የነዳጅና ነዳጅ ነክ ጉዳይ "መሀሉ አይነገርም" እየተባለ የሚሰራ ስራ ነው እንዳልኳችሁ በኢትዮጵያ የነዳጅ ማውጣት ስራ ረጂም ጊዜ የፈጀበት አንዱ ምክንያት ስራ በራሱ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅ የደህንነት ስራ በመሆነ ነው::

አሁን ላይ በኢትዮጵያ በዓመት ተጣርቶ ለተለያዩ አገልግሎቶች ልውል የሚችል 24 ሚልየን በርሜል #ድፍድፍ ነዳጅ ዝግጁ ሆኗል:: በዓመት ይሄን 24 ሚልየን #በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ እያጣራ ወደ ተለያዩ የነዳጅ ምርቶች የሚቀይር የድፍድፍ ነዳጅ

ማጣሪያ ፋብሪካ ግብንባታ በኢትዮጵያ ለመጀመር የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ የተደረሰ ስሆን ፋብሪካው በሚቀጥለው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ግባታው ተጠናቆ ሪቫን ስቆረጥ ከኢትዮጵያ ምድር የተገኘ የድፍድፍ ነዳጅ ማጣራት ስራ በይፋ በኢትዮጵያ ምድር ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል።

North Korea opens museum commemorating troops killed fighting for Russia,  ፦ Al Jazeera
27/04/2026

North Korea opens museum commemorating troops killed fighting for Russia,

፦ Al Jazeera

ቻይና በጠቅላላ የምርምር እና ልማት (R&D) ወጪ አሜሪካን በይፋ በመብለጥ ለቴክኖሎጂ እድገት 1.03 ትሪሊዮን ዶላር ገደማ ኢንቨስት አድርጋለች።ቻይና ከመቅደሟ በፊት አሜሪካ ለአሥርተ ዓመታ...
27/04/2026

ቻይና በጠቅላላ የምርምር እና ልማት (R&D) ወጪ አሜሪካን በይፋ በመብለጥ ለቴክኖሎጂ እድገት 1.03 ትሪሊዮን ዶላር ገደማ ኢንቨስት አድርጋለች።

ቻይና ከመቅደሟ በፊት አሜሪካ ለአሥርተ ዓመታት በዓለም አቀፍ የምርምር እና ልማት ወጪ ቀዳሚ ነበረች።

ምንጭ፦ OECD (የኢኮኖሚ ትብብር እና ልማት ድርጅት)"

ቻይና ወደ ምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ቀጥተኛ የባሕር ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ጀመረች።ቻይና ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን የንግድ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር ታሪክ ተሻጋሪ የተባለ የባሕር...
27/04/2026

ቻይና ወደ ምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ቀጥተኛ የባሕር ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ጀመረች።

ቻይና ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን የንግድ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር ታሪክ ተሻጋሪ የተባለ የባሕር ትራንስፖርት መስመር በይፋ መጀመሯን አስታውቃለች።

በምስራቅ ቻይና ሻንዶንግ ግዛት የሚገኘው የቺንግዳኦ ወደብ ትላንት እሁድ ወደ ምዕራብ አፍሪካ የሚያቀና አዲስ የኮንቴይነር ማጓጓዣ መስመር የጀመረ ሲሆን፤ አገልግሎቱም 13 መርከቦችን በማሰማራት በየሳምንቱ በቋሚ መርሃ-ግብር የሚከናወን ይሆናል።

ይህ አዲስ ቀጥተኛ የባሕር ትራንስፖርት አገልግሎት በአካባቢው ያለውን የሎጂስቲክስ ቅልጥፍና በእጅጉ ያሳድጋል ተብሎ ይጠበቃል።

በተለይም በቲያንጂን ወደብ በኩል ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚደረገውን የ50 ቀናት ጉዞ ወደ 40 ቀናት ዝቅ በማድረግ የ10 ቀናት የጊዜ ቅናሽ ያስገኘ ሲሆን፤ ይህም የትራንስፖርት ጊዜንና ወጪን በመቀነስ የሁለትዮሽ የንግድ ልውውጡን ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግራል።

ቺንግዳኦ ወደብ በአሁኑ ወቅት ወደ አፍሪካ የሚጓዙ 11 የኮንቴይነር መስመሮችን በማንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ትላንትም የመኪና መለዋወጫዎችን፣ ጎማዎችን እና የፀሐይ ብርሃን ኃይል ሰሌዳዎችን የጫነች መርከብ ወደ ጋና እና ናይጄሪያ ቁልፍ ወደቦች አሰማርቷል።

ቻይና አዳዲስ የማጓጓዣ መስመሮችን የጀመረችው ለ53 የአፍሪካ ሀገራት ከግንቦት 1 ቀን ጀምሮ 100 በመቶ ከቀረጥ ነፃ የንግድ ዕድል ለመስጠት መወሰኗን ተከትሎ መሆኑ ልዩ ትርጉም ይሰጠዋል።

ግሎባል ታይምስ እንደዘገበው እነዚህ መስመሮች የቻይና የቴክኖሎጂ ውጤቶች ወደ አፍሪካ በዝቅተኛ ወጪ እንዲደርሱ የሚያደርጉ ብቻ ሳይሆን፣ የአፍሪካ የግብርና እና የማዕድን ውጤቶች ወደ ቻይና ገበያ በፍጥነት እንዲገቡ በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታሉ።

በተመሳሳይ የያንታይ ወደብ ወደ አልጄሪያ እና ናሚቢያ አዳዲስ መስመሮችን በመክፈት የጭነት መጠኑ ለመጀመሪያ ጊዜ የ2 ሚሊዮን ቶን ወሰንን ማለፉ ተመልክቷል።

በሄዋን ጌታቸው

/Ethiopian Broadcasting Corporation

የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞስኮ ገቡ፦የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ በፓኪስታን እና በኦማን የነበራቸውን ጉብኝት አጠናቀው ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሩሲያ መግባታቸው ተዘገበ።በቴህ...
27/04/2026

የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞስኮ ገቡ፦የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ በፓኪስታን እና በኦማን የነበራቸውን ጉብኝት አጠናቀው ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሩሲያ መግባታቸው ተዘገበ።

በቴህራን እና በዋሽንግተን መካከል ያለው ቀጥተኛ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ተቋርጦ ባለበት በዚህ ወቅት፥ኢራን በፓኪስታን በኩል ለዩናይትድ ስቴትስ የጽሁፍ መልእክት ማስተላለፏ ተመልክቷል። በመልእክቱም የኒውክሌር መርሃ-ግብርን እና የሆርሙዝ ስትሬት የጸጥታ ሁኔታን በተመለከተ የኢራን "ቀይ መስመሮች" ተብራርተዋል።

የዲፕሎማሲ ምንጮች እንደገለጹት፣ የተላኩት መልእክቶች ከመደበኛ ድርድር ጋር ግንኙነት የሌላቸው በመሆኑ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የፖለቲካ አለመግባባት አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን ያመላክታል።

አባስ አራግቺ በሞስኮ ቆይታቸው ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተገናኝተው ቀጠናዊ የተኩስ አቁም ሂደቶችን እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጉዞ፣ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት በከረረበት በዚህ ወቅት ኢራን በጓሮ በር ዲፕሎማሲ (backchannel diplomacy) አማካኝነት ያላትን አቋም ለማሳወቅ እየጣረች መሆኑን የሚያሳይ ነው ተብሏል።

Address

Hossana, Hadiya
Hossana

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Social Affairs posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share