26/08/2026
የዕቅድ ግብ ስምምነት ፊርማ ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ!
ነሐሴ 20/2018 ዓ.ም ሆሳዕና
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ዘርፎችና ተጠሪ ተቋማት ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከክልሉ ሚሊሻ ጽ/ቤት እና ከክልሉ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ጋር የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የግብ ስምምነት ፊርማ ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ፣ ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች በተገኙበት ከቢሮዉ ተጠሪ ተቋማት ጋር በ2019 በጀት ዓመት ታቅደው በሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ላይ የግብ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ተጠሪ ተቋማት በበኩላቸዉ የዕቅድ ግብ ስምምነት ሰነዱ ሲፈርሙ ባስተላለፉት መልእክት በሁሉም ተቋማት መካከል የሚደረገውን የትብብር ሥራዎች ለማጠናከር፣ የዕቅድ አፈጻጸምን በውጤታማነት ለመከታተል እና የተቋማቱን የጋራ ግቦች ለማሳካት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገለፀዋል።
የፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ከሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ እና ከአራት የዘርፍ አመራሮችና ከሶስቱም ተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች ጋር የተከናወነ ሲሆን፣ በቀጣይ በጀት ዓመት የሚተገበሩ ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ላይም ውይይት ተደርጓል።