Hadiya Zone Lemo Woreda Government Communication Affairs

Hadiya Zone Lemo Woreda Government Communication Affairs Central Ethiopia Regional Government Hadiya Zone Lemo Woreda Government Communication Affairs office Hossana ,Ethiopia

07/08/2026
በሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራ በተጠናከረ ሁኔታ መቀጠሉ ተገለፀ ። ‎ሆሣዕና፣ሐምሌ 30/2018(ሌሞ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን)በሌሞ ወረዳ ድግባ ቀበሌ የ2018 ...
06/08/2026

በሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራ በተጠናከረ ሁኔታ መቀጠሉ ተገለፀ ።

‎ሆሣዕና፣ሐምሌ 30/2018(ሌሞ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን)

በሌሞ ወረዳ ድግባ ቀበሌ የ2018 ዓ.ም ክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት"በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል የአቅመ ደካሞች አዲስና ነባር ቤት ግንባታ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ።

የክረምት ወራት ወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎች በወረዳው በሁሉም ቀበሌያት በመንግስት፣ በበጎ አድራጊ ግለሰቦችና የእምነት ተቋማት እየተከናወነ መሆኑ ተገልጿል።

በሌሞ ወረዳ ድግባ ቀበሌ በሰባተኛ ቀን አክባሪ
አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን ወጣቶች ለሁለት አቅመ ደካማ ቤተሰቦች ሁለት ቤት እየተገነባ መሆኑን የወረዳው አስተባባሪ ኮሚቴ ምልከታ አድርጓል ።

‎በምልከታው የሌሞ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ደምሴ እንደገለጹት በወረዳው በሁሉም ቀበሌያት ለአቅመ ደካማና አረጋውያን አዲስ ቤት የመገንባትና የማደስ ሂደት ተጠናክሮ በመከናወን ላይ መሆኑን በመግለጽ በችግር ውስጥ ያሉ ወገኖችን መርዳት ከፈጣሪ ዘንድም ትልቅ ዋጋ ያለው በመሆኑ ይህንን በጎ ሥራ ከመንግስት ጎን በመሆን ለሚያከናውኑ ግለሰቦችና የሀይማኖት ተቋማት በወረዳው ስም ለሚያደርጉት ድጋፍ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ዘጋቢ:-ዕፁብ አዳነ

በራስ አቅም ከተረጂነት ለመላቀቅ እየተሰራ ያለው የመኸር የስንዴ ልማት ስራ የምግብ ሉዓላዊነትን እንደሚያረጋግጥ የሌሞ ወረዳ አስተዳደር ገለጹ። ሆሣዕና፣ሐምሌ 30/2018(ሌሞ ወረዳ ኮሚዩኒኬ...
06/08/2026

በራስ አቅም ከተረጂነት ለመላቀቅ እየተሰራ ያለው የመኸር የስንዴ ልማት ስራ የምግብ ሉዓላዊነትን እንደሚያረጋግጥ የሌሞ ወረዳ አስተዳደር ገለጹ።

ሆሣዕና፣ሐምሌ 30/2018(ሌሞ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን)

‎በሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ ድግባ ቀበሌ “ከተረጂነት ወደ ምርታማነት፤ ለተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነት” በሚል ሀሳብ የታረሱ መሬቶችን በህዝብ ንቅናቄ በስንዴ ዘር የመሸፈን ስራ ተከናውኗል።

በቦታው የተገኙት የሌሞ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ደምሴ እንደገለጹት በወረዳው ያለውን ፀጋ በመጠቀም ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር፣ ዜጎችን ከተረጂነት አስተሳሰብ ለማላቀቅና በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትና እንዲረጋገጥ ለማስቻል በራስ አቅም ለማምረት በተዘጋጁ ማሳዎችን በሰብል የመሸፈን ተግባር መከናወኑን ገልጸው የወረዳውን ምርትና ምርታማነት በማሳደግ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋዎች የተጎዱ ወገኖችን ለመደገፍ የሚሰራ ተግባር እንደሆነም ተናግረዋል ።

የሌሞ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰልፋሞ ወ/ዮሐንስ በበኩላቸው ፕሮግራሙ አርሶ አደሮች ኑሯቸውን እንዲያሻሽሉና ከራሳቸው አልፈው በሀገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት ላይ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ያግዛል ብለው በወረዳው በራስ አቅም ለድንገተኛ አደጋ እና ለሰብአዊ ድጋፍ ምላሽ ለመስጠት በሁሉም መስክ የሚሰሩ ስራዎች አበረታች መሆኑን በመግለጽ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር እና ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን በሚሰራው ስራ አንዱ የሆነው 2018/19 የመኸር እርሻ እንደ ወረዳ 4 ሄክታር ማሳ ለማልማት ከታቀደው በዛሬው እለት ሁለት ሄክታር መሬት በስንዴ ዘር መሸፈን መቻሉንና በተጠናከረ መልኩ ማስቀጠል እንደሚገባም አንስተዋል።

የሌሞ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊና የወረዳው መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አዳነ ከበደ እንደተናገሩት ይህ ተረጂነትን ዜሮ የማድረግ ሀገራዊ የፓርቲ የልማት ኢኒሼቲቮች አንድ አካል የሆነው ተግባር ከድህነት ለመላቀቅ የሚደረገውን ጥረት ከግብ ለማድረስ ተግባሩን በወረዳው በሁሉም አካባቢዎች በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በሌሞ ወረዳ ድግባ ቀበሌ በመኸር ስንዴ ልማት በዘር የመሸፈን ንቅናቄው ላይ የሌሞ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ደምሴ፣የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዳነ ከበደ እንዲሁም ሌሎች የወረዳው አመራሮችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

ዘጋቢ:-ዕፁብ አዳነ

በሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በሊሳና ሴና ቀበሌ በፎቶ
03/08/2026

በሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በሊሳና ሴና ቀበሌ በፎቶ

በሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ተካሄደ። ሆሣዕና፣ሐምሌ 27/2018(ሌሞ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን) በሌሞ ወረዳ...
03/08/2026

በሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ተካሄደ።

ሆሣዕና፣ሐምሌ 27/2018(ሌሞ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን)

በሌሞ ወረዳ በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን የመትከል መርሃ-ግብር የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ደምሴና የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ኃላፊና የወረዳው መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አዳነ ከበደ በተገኙበት በታች አምብቾ ቀበሌ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በከፍተኛ የህብረተሰብ ተሳትፎ ተከላው ተካሂዷል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የሌሞ ወረዳ ዋና አሰተዳዳሪ አቶ ታደለ ደምሴ በአንድ ጀምበር 800 ሚሊየን የሚተከል የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ብዝኃ ህይወትን ከመጥፋት የመታደግ፣ በአየር መዛባት ምክንያት የሚከሰት ድርቅን የመከላከል እና የተፈጥሮ ሚዛንን የመጠበቅ ሚናው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

ለአካባቢያችን ችግኝ ማለት ዘርፈ ብዙ ትርጉም አለው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ዛሬ የምንተክለው ችግኝ የነገ ጥላ፣ የንጹህ አየር፣ የውሃ ጥበቃ፣ የአረንጓዴ ከባቢ እና የተሻለ ሕይወት መሠረት ስለሆነ ችግኞቹ እስኪጸድቁ ድረስ የውሃ አማራጮችን በመጠቀም ማጠጣት እንዲሁም የጥበቃ ስራዎች በልዩ ትኩረት መከናወን እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

የሌሞ ወረዳ ደንና አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበራ አሸንቾ በበኩላቸው የመሬት መራቆትን ለመጠበቅ፣ አካባቢውን ውብና ማራኪ ለማድረግ በአንድ ጀምበር የተጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብርን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸው የተተከሉት ችግኞች እስከሚጸድቁ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ልዩ ትኩረት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

የሌሞ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰልፋሞ ዮሐንስ በአንድ ጀንበር “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል በወረዳው በአንድ ጀምበር በወረዳው በ33ቱም ቀበሌያት ችግኞች መተከላቸውን ገልጸዋል።

በመርሃ-ግብሩ የወረዳው ስራ አስፈጻሚ አካላት፣የወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ሌሞ አካባቢ ፕሮግራም ሠራተኞች፣የታች አምብቾ ቀበሌ ማህበረሰብን ጨምሮ ህጻናት፣ ሴቶች እና ወጣቶች ተሳትፈዋል።

ዘጋቢ:-ዕፁብ አዳነ

በሌሞ ወረዳ የአንድ ጀምበር 800 ሚሊየን ችግኝ ተከላ በፎቶ
03/08/2026

በሌሞ ወረዳ የአንድ ጀምበር 800 ሚሊየን ችግኝ ተከላ በፎቶ

በሀድያ ዞን ሌሞ ወረዳ በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን የተከላ መርሃ-ግብር እየተካሄደ ነው። ሆሣዕና፣ሐምሌ 27/2018(ሌሞ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን) በሌሞ ወረዳ በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን የመ...
03/08/2026

በሀድያ ዞን ሌሞ ወረዳ በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን የተከላ መርሃ-ግብር እየተካሄደ ነው።

ሆሣዕና፣ሐምሌ 27/2018(ሌሞ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን)

በሌሞ ወረዳ በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን የመትከል መርሃ-ግብር የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ደምሴና የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ኃላፊና የወረዳው መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አዳነ ከበደ በተገኙበት በታች አምብቾ ቀበሌ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ተከላው እየተካሄደ ነው።

የቀበሌው ነዋሪዎችም የነገን ተስፋ በመትከል ለሚቀጥለው ትውልድ ጠቃሚ ሀብት ለማስቀመጥ ችግኞችን በመትከላቸው ደስተኘ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በዚህ የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሃ -ግብር የምግብ ዋስትናን የሚያግዙ ችግኞችን ጨምሮ የተለያዩ ዝርያ ያላቸው ችግኞች እየተተከሉ ይገኛሉ።

ዘጋቢ:-ዕፁብ አዳነ

አንድ ቀን ብቻ ቀረው!የ2018 የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር - የችግኝ ተከላ መርሃግብር #ተስፋንእንትከል  #አረንጓዴዐሻር
02/08/2026

አንድ ቀን ብቻ ቀረው!

የ2018 የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር - የችግኝ ተከላ መርሃግብር
#ተስፋንእንትከል #አረንጓዴዐሻር

በአረንጓዴ አሻራችን 800 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀምበር ልንተክል 1 ቀን ብቻ ቀረንበጋራ ተስፋን እንትከል
02/08/2026

በአረንጓዴ አሻራችን 800 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀምበር ልንተክል 1 ቀን ብቻ ቀረን

በጋራ ተስፋን እንትከል

Address

Hossana

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hadiya Zone Lemo Woreda Government Communication Affairs posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share