Awi Communication

Awi Communication Official

21/06/2026
የአጣዬ ከተማ የኮሪደር ስራ የእግረኛ መንገድ የቴራዞ ማንጠፍ ተጀመረ፤በአጣዬ ከተማ አስተዳደር እየተከናወነ ባለው የመጀመሪያ ዙር የኮሪደር ልማት ግንባታ ፕሮጀክት የእግረኛ መንገድ የቴራዞን ...
21/06/2026

የአጣዬ ከተማ የኮሪደር ስራ የእግረኛ መንገድ የቴራዞ ማንጠፍ ተጀመረ፤

በአጣዬ ከተማ አስተዳደር እየተከናወነ ባለው የመጀመሪያ ዙር የኮሪደር ልማት ግንባታ ፕሮጀክት የእግረኛ መንገድ የቴራዞን ማንጠፍ ስራ በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል።

በቴራዞ ማንጠፍ ስራው ማስጀመሪያ ሥነ-ስርዓት ላይ የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ተመስገን ተስፋ፣ የሰንበቴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኑረዲን አህመድ፣ የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከድር እንድሪስ እንዲሁም ሌሎች የከተማው አመራሮች ተገኝተዋል።

በዚሁ ወቅት የአጣዬ ከተማ መሰረተ ልማት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኢንጅነር አበቡ ማሞ እንደገለፁት፦ የከተማው ኮሪደር ልማት ግንባታ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እየተከናወነ ሲሆን እና የቴራዞን ማንጠፍ ስራ መጀመሩ የፕሮጀክቱ አንዱ ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል የአጣዬ ከተማ ኮንስትራክሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኢንጅነር እንድሪስ የሱፍ እንደተናገሩት፣ በመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት ግንባታ አብዛኛው ስራ ተጠናቆ በአሁኑ ወቅት የቴራዞ ማንጠፍ ስራ መጀመሩ የፕሮጀክቱን እድገት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።

ኃላፊው አክለውም በቀጣይ የአረንጓዴ ቦታዎች ልማትና የፖል መብራት ተከላ ስራዎች እንደሚከናወኑ ገልጸው፣ ቀሪ ስራዎችም በቅርቡ ተጠናቀው ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ወደ አገልግሎት እንደሚገባ አስታውቀዋል።

በመጨረሻም የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቱ የከተማውን ውበት፣ የእግረኞች ምቹነት እና የትራፊክ ደህንነት በማሻሻል ለነዋሪዎች እና ለእንግዶች የተሻለ የከተማ አካባቢ ለመፍጠር እንደሚያግዝ ተገልጿል።

21/06/2026
በደጀን ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት በጠደን ቀበሌ  የምረጫ ምዕልክት፣የምረጫ ማንፌስቶና የዕጩ ትውውቅ   መድረክ ተካሄደ ።‎ #​ምልክታችን _የስንዴ ነዶ ነው!  ሃገር! !
11/05/2026

በደጀን ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት በጠደን ቀበሌ የምረጫ ምዕልክት፣የምረጫ ማንፌስቶና የዕጩ ትውውቅ መድረክ ተካሄደ ።

#​ምልክታችን _የስንዴ ነዶ ነው!
ሃገር!
!

08/05/2026
ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር! የባህርዳር ከተማ አስተዳደር በአሽከርካሪዎች በታጀበ  ትርኢት የብልጽግና ፓርቲ የጎዳና ላይ የምረጡኝ ቅስቀሳ በድምቀት አካሂዷል።  #​ምልክታችን _የስንዴ ነዶ...
08/05/2026

ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር!

የባህርዳር ከተማ አስተዳደር በአሽከርካሪዎች በታጀበ ትርኢት የብልጽግና ፓርቲ የጎዳና ላይ የምረጡኝ ቅስቀሳ በድምቀት አካሂዷል።

#​ምልክታችን _የስንዴ ነዶ ነው!
ሃገር!
!

16/03/2026

Address

Spantov

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Awi Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Awi Communication:

Shortcuts

Share