Injibara General Hospital

Injibara General Hospital Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Injibara General Hospital, Amhara Region, Awi Zone, Injibara Town, Injibara.

01/08/2023

መልዕክት

አምስቱ ቁልፍ የኮሌራ በሽታ መከላከያ መንገዶች

01/08/2023
25/07/2023
25/07/2023
መልዕክት የኮሌራ በሽታ!!!የኮሌራ በሽታ መተላለፊያ መንገዶች፣ የሚያሳያቸዉ ምልክቶች እና የበሽታው መከላከያ መንገዶችኮሌራ ከሰዉነት ዉስጥ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችንና ፈሳሽን በብዛት እና በአጣዳ...
25/07/2023

መልዕክት

የኮሌራ በሽታ!!!
የኮሌራ በሽታ መተላለፊያ መንገዶች፣ የሚያሳያቸዉ ምልክቶች እና የበሽታው መከላከያ መንገዶች
ኮሌራ ከሰዉነት ዉስጥ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችንና ፈሳሽን በብዛት እና በአጣዳፊ ሁኔታ በተደጋጋሚ ተቅማጥና ትውከት በማስከተል ሰዉነትን አድርቆ የሚገል በሽታ ነዉ፡፡
በሽታዉ የሚያሳያቸዉ ምልክቶች፡-
የሰውነት ድርቀት፣
የአፍ መድረቅ፣
የአይን መሰርጎድ፣
የእንባ መድረቅ፣
የሽንት መቀነስ፣
የቆዳ መሸብሸብና አጠቃላይ የሆነ የድካም ስሜት ያስከትላል፡፡
መተላለፊያ መንገዶች:- በአካባቢና የግል ንጽህና መጓደል አማካኝነት ነው። ማለትም:-
• በሽታው በተበከለ ምግብና ውሃ አማካኝነት ከሰው ወደ ሰው በከፍተኛ ፍጥነት ይተላለፋል፡፡
• ንጹህ ባልሆኑ እጆች ምግብን በማዘጋጀት፣ በማቅረብና በመመገብ፣
• በበሽታ አምጪ ተህዋስያን የተበከለ የምንጭ፣ የጉድጓድ፣ የወንዝ፣ የዝናብ፣ የቧንቧና ወዘተ ውሃን መጠቀም፣
• በበሽታ አምጪ ተህዋስያን የተበከለ የውሃ ማጠራቀሚያና መገልገያ እቃዎችን በመጠቀም፣
• ክዳን የሌላቸውና ለዝንቦች የተጋለጡ የምግብ ማስቀመጫና መመገቢያ እቃዎችን በመጠቀም፣
• በበሽታ አምጪ ተህዋስያን የተበከሉ ምግቦችን፣ አትክልቶችንና ፍራፍሬዎችን በመመገብ፤ወዘተ ይተላለፋል፡

የኮሌራ በሽታ መከላከያ መንገዶች:-
• ሁልጊዜ ውሃን አፍልቶ እና አቀዝቅዞ መጠጣት ወይም በውሃ ማከሚያ ኬሚካል የታከመ ውሃ መጠቀም፤
• ምግብን በሚገባ አብስሎ በትኩስነቱ መመገብ፤
• የምግብ እቃዎችን በንጹህ ወይም በኬሚካል በታከመ ውሃ ማጠብ እና መጠቀም፣
• መጸዳጃ ቤትን አዘጋጅቶ በአግባቡ መጠቀም፤
• እጅን በሚከተሉት ወሳኝ ጊዜያት በንጹህ ውሃና በሳሙና ሳሙና ከሌለ በአመድ በሚገባ መታጠብ፣
• ከመጸዳጃ ቤት መልስ፣
• ምግብ ከማዘጋጀት በፊት
• ምግብ ከማቅረብ በፊት፣
• ምግብ ከመመገብ በፊት፣
• ሕጻናትን ካጸዳዱ በኃላ፣
• ሕጻናትን ጡት ከማጥባት በፊት ፣
• በበሽታው ለተያዙ ሰዎች እንክብካቤ ካደረጉ በኃላ፣
• በበሽታው የሞቱ ሰዎችን አስክሬን በድንገት ከነኩ፣
• ማንኛውንም ከቤት የሚወጣ ደረቅ ወይም ፈሳሽ ቆሻሻን ውሃንና አካባቢን እንዳይበክል በአግባቡ በተመደበለት ስፍራ ማስወገድ፣
• በኮሌራ በሽታ የታመመን ሰው ልብስ በፈላ ውሃ መቀቀል ወይም በበረኪናና በልብስ ማጽጃ ሳሙና ዘፍዝፎ ማጠብ፣
• በበሽታው የተያዘን ሰው በፍጥነት ወደ ሕክምና ተቋም በመዉሰ የህክምና እርዳታ እንዲያገኝ ማድረግ ናቸው።
• የግልና የአካባቢን ንጽህና በመጠበቅ ዝንቦች እንዳይራቡ ያድርጉ፣
• ፈሳሽና ደረቅ ቆሻሻን በአግባቡ በተመደበለት ስፍራ ያስወግዱ
• ሽንት ቤት በመገንባት በአግባቡ ይጠቀሙ እንዲሁም በንጽህና ይያዙ፣
• በተቅማጥና ተውከት የተነካካ እቃን፣ ወለልና መሬትን ከማጽዳትዎ በፊት በረኪና በማፍሰስ ብክለትን ይከላከሉ።
የበሽታ ምልክት ሲታይ መከናወን ያለባቸው ተግባራት:-
- በሽታው የሰውነትን ፈሣሽና ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን በብዛት ከሰውነት የሚያስወጣ ስለሆነ የሚከተሉትን እርምጃዎች በፍጥነት በመውሰድ እንዲተኩ ያድርጉ።
-በመጀመሪያ ቤት ውስጥ የሚገኘውን ማንኛውም ንጽህናው የተጠበቀ ፈሣሽ የሚችሉትን ያህል ይጠጡ።
-ህይወት አድን ንጥረ ነገር ወይም ኦ.አር.ኤስ በቤት ውስጥ ካለ አንድ ፓኬት ተፈልቶ በቀዘቀዘ አንድ ሊትር ውሃ በመበጥበጥ ይጠጡ፤ የተበጠበጠ ኦ.አር.ኤስን መጠቀም የሚቻለው በተበጠበጠ በ24 ሰዓት ውስጥ ነው።
- ኦ.አር.ኤስ በቤት ውስጥ ከሌለ 8 የሻይ ማንኪያ ስኳር እና ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጨው በአንድ ሊትር ንጹህ ውሃ በመበጥበጥ ባስቀመጥዎ ቁጥር ይጠጡ።

የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል ዛሬ በ9/11/2015 ዓ.ም የነርስ ሚድዋይፈሪ የ2015 በጀት አመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ እያካሄደ ይገኛል።በዚህ ግምገማ በአመቱ የተሻለ አፈፃፀም ያሳዩ የስራ...
16/07/2023

የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል ዛሬ በ9/11/2015 ዓ.ም የነርስ ሚድዋይፈሪ የ2015 በጀት አመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ እያካሄደ ይገኛል።
በዚህ ግምገማ በአመቱ የተሻለ አፈፃፀም ያሳዩ የስራ ክፍሎችና ባለሙያዎች/ሰራተኞች የእውቅና ሰርቲፊኬትና የማበረታቻ ሽልማት ይበረከትላቸዋል። ለዚህም ይረዳ ዘንድ ስታንዳርድ መመዘኛ ቸክሊስት በማዘጋጀትና የተሻለ ልምድ የት/ት ዝግጅትና ክህሎት ያላቸውን ባለሙያዎች በመምረጥ ሁሉም የስራ ክፍሎች የተመዘኑ ሲሆን የዛሬው ግምገማ ደግሞ ያን የሚያጠናክር ወይም ሊቀይር የሚችል በመሆኑ ውድድሩን አጓጊ አድርጎታል።
መልካም እድል!!

15/07/2023
15/07/2023

መልዕክት
የኩላሊት ካንሰር

የኩላሊት ካንሰር በአዋቂዎች እንዲሁም በህፃናት ላይ ሊከሰት የሚችል የካንሰር አይነት ነው።

ትንባሆ ማጨስ እና አንድ አንድ የሕመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን ያለ አግባብ መጠቀም ለዚህ ካንሰር እንደሚያጋልጡ የታወቁ ናቸው።

የኩላሊት ካንሠር ወደ መጨረሻ ደረጃ እስኪደርስ ድረስ ምንም አይነት የሕመም ምልክት ላያሳይ ይችላል።
በዚህም ምክንያት አብዛኛው ታካሚ የህመሙ ደረጃ ከገፋ በኋላ ነው ወደ ህክምና ተቋም የሚመጡት፤ ነገር ግን አልፎ አልፎ ደም የቀላቀለ ሺንት መሺናት ፣ የጎን ህመም ወይም እብጠት ፣ ያልተፈለገ የሰውነት መቀነስ ወይም የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ትኩሳት የመሳሰሉት ምልክቶች ሊኖር ይችላል።

15/07/2023

Address

Amhara Region, Awi Zone, Injibara Town
Injibara

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Injibara General Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share