Awi Zone Road Department

Awi  Zone Road Department Constructing road play a key role for the developments of once country

24/03/2026
09/01/2026
የአዊ ብሔ/ አስ /መንገድ መምሪያ ኅላፊ አቶ ጥላሁን ሽቴ የጌታችን የመድሐኒታችን  የእየሱስ ክርስቶስን ልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ መልእክት አስተላልፈዋል ።******በመልክታቸውም ለመ...
06/01/2026

የአዊ ብሔ/ አስ /መንገድ መምሪያ ኅላፊ አቶ ጥላሁን ሽቴ የጌታችን የመድሐኒታችን የእየሱስ ክርስቶስን ልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ መልእክት አስተላልፈዋል ።
******
በመልክታቸውም ለመላው ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድሐኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን እያሉ
የአዊ ብሔ /አስ/ መንገድ መምሪያ የመንገድና ድልድይ ግንባታ ስራዎችን በውጤታማነት ከመፈፀም እና ከማስተዳደር ባሻገር በዞን ደረጃ ፕሮጀክቶችን በጥራት በማቀድና በውጤታማነት መምራት የሚያስችል አቅም የፈጠረ መሆኑን በመግለፅ የተፈጠረውን አቅም የበለጠ በማጠናከር ፕሮጀክቶችን በጊዜና በጥራት መፈፀም አለብን የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ለዚህ ደግሞ ብሔረሰብ አስተዳደሩ የመንግስትን ፤የህዝብንና የልማት ድርጅቶን አቅም አሟጦ በመጠቀም የዞኑን ሁለተናዊ ብልፅግና የሚያረጋግጡ የልማት ሥራዎችን በስፋት እና በጥራት እየተሰራ ይገኛል።
ስለሆነም በተያዘው በጀት ዓመት ከ 160 ሚሊዮን ብር በላይ ከወረዳ ም/ቤት ፤ ከተለያዩ ረጅ ድርጅቶችና ማህበረሰብ በማሰባሰብ 42 ኪ.ሜ የአዲስ መንገድ ግንባታ፣ የ180ኪ.ሜ መንገድ በማሽን ጥገና ፣ 240ኪሜ በሰው ሀይል ጥገና ፣ በአዲስ የአንድ ከፍተኛ ድልድይ ግንባታ እና የሁለት ነባር ከፍተኛ ድልድዬችን ግንባታ ማጠናቀቅ እንዲቻል በእቅድ ተይዞ ወደ ስራ የተገባ ከመሆኑ በተጨማሪ የአንድ ከፍተኛ የኮንክሪት ድልድይ ግንባታ በክልል ካፒታል በጀት ፣ሁለት የእግረኛ ተንጠልጣይ ድልድይ ግንባታ በመቀናጆ በጀት ፤ በገጠር ትስስር ኘሮግራም በተመረጡ ሁለት ወረዳዎች በነባር 7 ኘሮጀክት በአዲስ ለ 10 ኘሮጀክቶች በድምሩ 17 የተለያዬ ኘሮጀክቶች ተከታትሎ ማጠናቀቅ ፤ በክልል መደበኛ መንገድ ለ407 ኪ.ሜ መንገድ ጥገና እና ለ 20 ኪ.ሜ የአዲስ መንገድ ግንባታ ስራ በመደገፍና በማስተባበር በህዝባችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ እድገት ዘላቂነትን ለማረጋገጥ በብሔረሰብ አስተዳደራችን ከ330 ኪ.ሜ የሚሸፍን የአስፓልት ኘሮጀክቶችን ጨምሮ በርካታ የመንገድና የድልድይ ግንባታዎችና ጥገናዎች በሁሉም አካባቢ በስፋትና በጥራት እየተሰሩ እና ከፊሎቹ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ።
ለዚህ ደግሞ ፕሮጀክቶችን በዉጤታማነት በመምራትና በማስፈጸም አቅማችንን በማሳደግ የመንገድ መሰረተ ልማት ተደራሽነትን እናረጋግጣለን፡፡
መንገድ ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ብልፅግና መሠረት ነው። በመሆኑም በገጠርም ሆነ በከተማ በዘርፉ የህዝባችንን የበርካታ ዓመታት ጥያቄዎች የሚመልስ የመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታ ፕሮጀክቶችን በማቀድ እና ወደ ተግባር በመግባት የህዝብ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ስራ በመስራት ላይ እንገኛለን።
የልደት በዓል የአለም ቤዛ የሆነው ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጅ መተላለፍ ከልጅ ልጅህ ተወልጀ አድንሀለሁ ብሎ ለአዳም በገባው ቃል ኪዳን መሰረት በቅዱስ ገብርኤል ብስራት በእናታችን በቅድስት ድንግል ማሪያም ማህፀን ተወስኖ በከብቶች ግርግም የተወለደበት ትልቅ የብስራት ቀን ነው።
የመንገድ መሰረተ ልማት ደግሞ ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ፓለቲካዊ ዋና ቁልፍ በመሆኑ በዘርፉ ለምንሰራቸው ተግባራት መነሳሳትና ቁጭት የምንፈጥርበትና የህዝባችንን ጥያቄዎች የመንመልስበት ቁልፍ ተግባር በመሆኑ ለዚህ ውጤት ሁሉም ዜጋ አስፈላጊውን ድጋፍ እና ትብብር እንዲያደርግ እያሳሰብን
በድጋሚ እንኳን ለጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን !!
መልካም የልደት በዓል !!!
ጥላሁን ሽቴ

መንግስት በመደበኛው መርሃግብር   መንገድ  ለመገንባት አስቸጋሪ የሆኑ ቦታዎችን የእግረኛ ተንጠልጣይ ድልድይ በመገንባት  ህብረተሰቡን   ከእንግልትና ከውሀ መበላት መታደግ ተችሏል።ለዚህ  መ...
15/07/2025

መንግስት በመደበኛው መርሃግብር መንገድ ለመገንባት አስቸጋሪ የሆኑ ቦታዎችን የእግረኛ ተንጠልጣይ ድልድይ በመገንባት ህብረተሰቡን ከእንግልትና ከውሀ መበላት መታደግ ተችሏል።
ለዚህ መማሳያ እነሆ በበጀት ዓመቱ ተገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት የሆነው የባሪ ወንዝ ተንጠልጣይ ድልድይ ይሄው ማሳያ ነው።

የአዊ ብሔ/ አስ/መንገድ መምሪያ    ኘሮጀክት ጀምሮ በመጨረስ እና የህዝብን የመልካም አስተዳደር  ችግር ከመፍታት በዘለለ የተሰጠውን ራዕይና ተልዕኮ በሚገባ  በመወጣት  ላይ ይገኛል።ለዚሁም...
14/07/2025

የአዊ ብሔ/ አስ/መንገድ መምሪያ ኘሮጀክት ጀምሮ በመጨረስ እና የህዝብን የመልካም አስተዳደር ችግር ከመፍታት በዘለለ የተሰጠውን ራዕይና ተልዕኮ በሚገባ በመወጣት ላይ ይገኛል።
ለዚሁም ማሳያ ይሆን ዘንድ እነሆ በበጀት ዓመቱ በዳንግላ ወረዳ ከጊሳ ከተማ 2.5ኪ.ሜ ወጣ ብሎ ተገንብቶ የተጠናቀቀው የአውሲ ከፍተኛ ድልድይ ይሂያው ማሳያ ነው።
ይህ ድልድይ ገንብቶ ለማጠናቀቅ ድጋፍና ክትትል ላደረጉ ተቋማትና ማህበረሰብ መምሪያው ከልብ እያመሰገነ ለወደፊት ይህንን መሰል ተግባር በሌሎች ተደራሽ ባልሆኑ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።
እናመሠግናለን ።።።።

የአዊ ብሔ/ አስ  መንገድ መምሪያ የመንገድ ተደራሽነትን  እና የድልድይ  ሽፍንን በማሳካት የህዝብን የመልካም አስተዳደር  ጥያቄዎችን በመመለስ ላይ ይገኛል።በተለያዩ ኘሮግራም እና የበጀት ም...
13/07/2025

የአዊ ብሔ/ አስ መንገድ መምሪያ የመንገድ ተደራሽነትን እና የድልድይ ሽፍንን በማሳካት የህዝብን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በመመለስ ላይ ይገኛል።
በተለያዩ ኘሮግራም እና የበጀት ምንጭ በብሔ/ አስተዳደሩ ውስጥ የሚገነቡ ድልድዮች እና መንገዶችን አፈፃፀማቸውን እና በጥራት መገንባታቸውን የመከታተል ሀላፊነት መንገድ መምሪያ ተሰጥቶታል ።
ይህነንም ተግባር እውን ለማድረግ ዛሬ በአንከሻ ወረዳ በወረዳ በግብረና ፅ/ ቤት ባለቤትነት በFSRP ኘሮራም እና በማህበረሰብ ተሳትፎ የበጀት ምንጭ የተገነባውን የዳንዲኒ ከፍተኛ ድልድይ ግንባታ አፈፃፀም እና የጥራት ደረጃ መከታተል ዋናው ተግባሩ ነበር።
በዚህም ጥረት በበጀት ዓመቱ በጥራት ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ መምሪያችን ከፍተኛ ድጋፍና ክትትል አድርጓል።
ስለሆነም ለዚህ ድልድይ በጥራት መገንባት እና በበጀት ዓመቱ እንዲጠናቀቅ የወረዳው አስ ም/ ቤት እና መን/ትራ/ ፅ/ቤት ከፍተኛ አስተዋፅእ ያላቸው በመሆኑ መንገድ መምሪያ ከልብ እያመሰገነ ሌሎች ወረዳዎችም ለዚህ መሰል ተግባር ተጠናክረን በመስራት የዞናችንን የድልድይና የመንገድ ተደራሽነት አጠናክረን እንቀጥል ሲል
መንገድ መምሪያ ያሳስባል።።።።

በብሔ/ አስ/ዞን   ባሉ መምሪያዎች  መንገድ መምሪያ በብልፅግና ቤተሰብ እቅድ አፈፃፀም  1 ኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቋል።
12/07/2025

በብሔ/ አስ/ዞን ባሉ መምሪያዎች መንገድ መምሪያ በብልፅግና ቤተሰብ እቅድ አፈፃፀም 1 ኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቋል።

Address

Injibara

Telephone

+251582271013

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Awi Zone Road Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share