Awi InspectionandEthics commission

Awi InspectionandEthics commission Awi InspectionandEthics commission

02/05/2026

የሳቃችን ምንጭ ኮሜዲያን ፍልፍሉ ከሆስፒታል ቤቱ ገብቷል ኢትዮጵያን ሁላችሁም በእየምነታችሁ ፈጣሪ ጨርሶ ይማርህ በሉት

01/05/2026
01/05/2026
01/05/2026

የያዘው የተረዘዘው የሚያምርለትወጣትና ብልህ መሪ!!!!

01/05/2026

ኢትዮጵያ በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የጀመረችው ጉዞ ወደ አዲስ ምዕራፍ ተሸጋግሯል

በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች ወደሀገር ውስጥ እየገቡ ነው።

በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የተጀመረው የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ኢነርጂ አብዮት ወደ ግዙፍ ማሽነሪዎች ተሸጋግሯል። የነገዋን ኢትዮጵያ በፅኑ መሠረት ላይ ለመገንባት፣ ሀገራችን በከባድ ማሽነሪዎችና በኢንዱስትሪ መሣሪያዎች ዘርፍም ጭምር ወደ "አረንጓዴ ኢነርጂ" ሙሉ በሙሉ ለመግባት ቆርጣ ተነስታለች!

በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ብልህ መሪነት፣ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን በዝምታ የምትመለከት ሳይሆን በተግባር የምትመክት ሀገር መሆኗን ለዓለም እያሳየች ነው። አዲሱ የፖሊሲ አቅጣጫችን በተፈጥሮ ጋዝ የሚሠሩ የኤሌክትሪክ ከባድ ተሽከርካሪዎችንና የኢንዱስትሪ ማሽነሪዎችን ወደ ሥራ በማስገባት ላይ ያተኩራል።እነሆ በኤሌክትሪክ ብቻ ሳይሆን በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች ወደሀገር ውስጥ እየገቡ ነው።





01/05/2026

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ጦርነቱ በተኩስ አቁም ስምምነት ከመቆሙ በፊት የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር በቴሌቪዥን በተላለፈ የካቢኔ ስብሰባ ላይ በኢራን ላይ ስላገኙት ወታደራዊ ስኬት ከፎከሩ ማግስት፣ ኢራን በሳዑዲ አረቢያ በሚገኝ የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ ባደረሰችው የሚሳኤል እና ድሮን ጥቃት 700 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ የራዳር አውሮፕላን አውድማለች።

በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የስትራቴጂክ እና ዓለም አቀፍ ጥናቶች ማዕከል ባወጣው አዲስ መረጃ መሰረት፣ አሜሪካ በጦርነቱ ከ2.3 ቢሊዮን እስከ 2.8 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ወታደራዊ መሳሪያዎቿን አጥታለች። አልጀዚራ ይዞት የወጣው ይህ ዘገባ፣ ፌብሩዋሪ 28 ከተጀመረው ጦርነት ወዲህ የወጣ የመጀመሪያው ዝርዝር የኪሳራ ጥናት ነው።

በማዕከሉ ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ማርክ ካንሲያን እንደገለጹት፣ ይህ የኪሳራ ግምት በጦር ሰፈሮች እና በልዩ የባህር ኃይል ሀብቶች ላይ የደረሰውን ጉዳት አያካትትም። አሜሪካ የሳተላይት ምስሎች ለህዝብ እንዳይደርሱ ብታግድም፣ ማዕከሉ በኢራን የሳተላይት ምስሎች ተጠቅሞ ጉዳቱን ሊገመግም ችሏል።

ዋና ዋና ኪሳራዎቹ ምን ይመስላሉ?

በማርች ወር መጀመሪያ ላይ በኩዌት፣ አሜሪካ በራሷ ጦር (friendly fire) በፈጸመችው ስህተት ሶስት F-15 የጦር አውሮፕላኖች ተመትተው ወድቀዋል።

በማርች 1 ደግሞ፣ ከ485 ሚሊዮን እስከ 970 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ እና ሚሳኤሎችን ለማምከን የሚያገለግል የ THAAD ሚሳኤል መከላከያ ራዳር ወድሟል።

በማርች 27 በሳዑዲ አረቢያው የልዑል ሱልጣን አየር ሀይል ሰፈር ላይ በተሰነዘረ ጥቃት፣ 700 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣውና በአየር ላይ የዕዝ ማዕከል በመሆን የሚያገለግለው E-3 AWACS/E7 የራዳር አውሮፕላን ወድሟል።

የዶሃ ኢንስቲትዩት የጸጥታ እና ወታደራዊ ጥናቶች ፕሮፌሰር የሆኑት ኦማር አሹር፣ የትራምፕ አስተዳደር በመጪው ህዳር ወር በሚካሄደው ምርጫ የፖለቲካ ዋጋ ላለመክፈል ሲል ጉዳቱን በግልፅ እያሳወቀ እንዳልሆነ ተናግረዋል። አሜሪካ በቬትናም እና አፍጋኒስታን እንዳደረገችው ሁሉ አሁንም ጊዜያዊ ወታደራዊ ድሎችን ብታገኝም፣ ስትራቴጂካዊ ኪሳራ ሊገጥማት እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። ፕሮፌሰሩ አክለውም፣ በአሁኑ ወቅት በቀጠናው ያለው የአሜሪካ ጦር ቁጥር በ2003 ኢራቅን ለመውረር ከተጠቀመችው ጦር ከአስር እጅ አንዱን እንኳን እንደማይሞላ አብራርተዋል።

በጦርነቱ መጀመሪያ ኢራን የሆርሙዝ ባህረ-ሰላጤን መዝጋቷ ለአሜሪካ የባህር ኃይል ያልተጠበቀ ፈተና ሆኖበታል። ምንም እንኳን ኤፕሪል 13 ላይ አሜሪካ የራሷን የባህር ላይ እገዳ በኢራን ወደቦች ላይ ብትጥልም፣ ካንሲያን እንዳሉት ሁኔታው አሜሪካን ያልተዘጋጀች አድርጎ አሳይቷታል።

ፕሮፌሰር አሹር እንዳብራሩት በአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት የኢራን መደበኛ ወታደራዊ አቅም በእጅጉ ቢዳከምም፣ የሀገሪቱ የባህር ኃይል እና የሚሳኤል አቅም ግን ሙሉ በሙሉ አልተደመሰሰም። አሁንም ቢሆን መደበኛ ባልሆነ የባህር ኃይል ውጊያ የማድረግ አቅማቸውን ይዘው እንደሚገኙ ተንታኙ ገልጸዋል።

30/04/2026
30/04/2026

"ኋላ ቀርነትን በስራ እንቀይራለን!"-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

30/04/2026

Address

Injibara

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Awi InspectionandEthics commission posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share