Jiga town prosperity party youth league

Jiga town prosperity party youth league Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Jiga town prosperity party youth league, Political organisation, Jiga.

"ውጫዊ የወረራ ስጋትን እና  ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምን እናረጋግጣለን" በሚል መሪ ቃል  በምዕራብ ጎጃም ዞን በጅጋ ከተማ አስተዳደር ከነጋዴው ማህበረሰብ ጋር ውይ...
24/08/2026

"ውጫዊ የወረራ ስጋትን እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምን እናረጋግጣለን" በሚል መሪ ቃል በምዕራብ ጎጃም ዞን በጅጋ ከተማ አስተዳደር ከነጋዴው ማህበረሰብ ጋር ውይይት ተካሄደ። ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ነጋዴ የበኩሉን አስተዋፅኦ ሊወጣ እንደሚገባ ከመድረኩ ተሳታፊዎች ተገልጿል።

"ውጫዊ የወረራ ስጋትን እና  ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምን እናረጋግጣለን" በሚል መሪ ቃል በምዕራብ ጎጃም ዞን በጅጋ ከተማ አስተዳደር  ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከሀይ...
21/08/2026

"ውጫዊ የወረራ ስጋትን እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምን እናረጋግጣለን" በሚል መሪ ቃል በምዕራብ ጎጃም ዞን በጅጋ ከተማ አስተዳደር ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከሀይማኖት አባቶች ጋር ውይይት ተካሄደ። ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ሊወጡ እንደሚገባ ከመድረኩ ተሳታፊዎች ተገልጿል።

"ውጫዊ የወረራ ስጋትን እና  ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምን እናረጋግጣለን" በሚል መሪ ቃል በምዕራብ ጎጃም ዞን በጅጋ ከተማ አስተዳደር  ከመንግስት ሰራተኛ አባላት ጋ...
20/08/2026

"ውጫዊ የወረራ ስጋትን እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምን እናረጋግጣለን" በሚል መሪ ቃል በምዕራብ ጎጃም ዞን በጅጋ ከተማ አስተዳደር ከመንግስት ሰራተኛ አባላት ጋር ውይይት ተካሄደ። ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የመንግስት ሰራተኛው በተመደበበት የስራ ዘርፍ በአገልጋይነት መንፈስ በመስራት የበኩሉን አስተዋፅኦ ሊወጣ እንደሚገባ ከመድረኩ ተሳታፈ ተገልጿል።

የተማሪ ወላጆች ልጆቻቸውን በወቅቱ ሊያስመዘግቡ እንደሚገባ ጥሪ ቀረበ።በምዕራብ ጎጃም ዞን በጅጋ ከተማ አስተዳዱር የትምህርት ቤት አመራሮችና መምህራን ለ2019 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተ...
19/08/2026

የተማሪ ወላጆች ልጆቻቸውን በወቅቱ ሊያስመዘግቡ እንደሚገባ ጥሪ ቀረበ።

በምዕራብ ጎጃም ዞን በጅጋ ከተማ አስተዳዱር የትምህርት ቤት አመራሮችና መምህራን ለ2019 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደት የተሳካ እንዲሆን አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ስራ እየተከናወነ ነው።

በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ትምህርት ቤቶችን የማጽዳት ፣የውስጥ ቁሳቁሰችን የመጠገንና የተጓደሉትን በማሟላት ተማሪ የመመዝገብ ስራ እየተከናወነ ይገኛል።

ወላጆች ልጆቻቸውን በወቅቱ በማስመዝገብ አስፈላጊውን የትምህርት ቁሳቁስ በማሟላት ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።በዚህም በጅጋ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትሞህርት ቤቶች የተማሪ ምዝገባ በንቅናቄ ተጀምሯል።

የተማሪ ወላጆች ልጆቻቸውን በወቅቱ ሊያስመዘግቡ እንደሚገባ ጥሪ ቀርቧል።

ዓለም አቀፍ የወጣቶች ተከበረ!!!በምዕራብ ጎጃም ዞን በጅጋ ከተማ አስተዳደር  ሴቶችና ወጣቶች ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ከባህልና ስፖርት ጽ/ቤት በጋራ የተዘጋጀው አለማቀፍ የወጣቶች ቀን "ብዝ...
13/08/2026

ዓለም አቀፍ የወጣቶች ተከበረ!!!
በምዕራብ ጎጃም ዞን በጅጋ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ወጣቶች ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ከባህልና ስፖርት ጽ/ቤት በጋራ የተዘጋጀው አለማቀፍ የወጣቶች ቀን "ብዝሀ የወጣቶች እውቀት ለጋራ ትልም" በሚል መሪ ቃል በአለም ለ26ኛ በኢትዮጵያ ለ23ኛ ጊዜ ከከተማ አስተዳደሩ ወጣቶች ጋር ተከብሯል። በፕሮግራሙ የተገኙ ወጣቶች የአካባቢ የጽዳት ስራ ያከናወኑ ሲሆን ለዝግጅቱ መሳካት የባህልና ስፓርት ጽ/ቤት እና የሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ሰራተኞች ተሳትፈዋል።
*Jiga town prosperity Party*

"በጎነት ለአብሮነትና ለኢትዮጵያ ከፍታ"በምዕራብ ጎጃም ዞን በጅጋ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት አስተባባሪነት "በጎነት ለአብሮነትና ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ...
09/08/2026

"በጎነት ለአብሮነትና ለኢትዮጵያ ከፍታ"
በምዕራብ ጎጃም ዞን በጅጋ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት አስተባባሪነት "በጎነት ለአብሮነትና ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል ለአቅመ ደካሞችና ለድሀ ድሀ የማህበረሰብ ክፍሎች "የማዕድ ማጋራት" ፕሮግራም አካሄደ።ከማዕድ ማጋራት ፕሮግራሙ በተጨማሪ የንጽህና መጠበቂያ የሚሆኑ ኦሞ የልብስና የገላ ሳሙና ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።
በፕሮግራሙ የሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ሰራተኞች፣የቀበሌና የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

"የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሸማግሌዎች እውነት ላይ በመቆም ለከተማዋ ዘላቂ ሰላምና ልማት ልትሰሩ ይገባል"አቶ አባይ አለሙየምዕራብ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊየምዕራብ...
06/08/2026

"የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሸማግሌዎች እውነት ላይ በመቆም ለከተማዋ ዘላቂ ሰላምና ልማት ልትሰሩ ይገባል"

አቶ አባይ አለሙ
የምዕራብ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ

የምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ከጅጋ ከተማ የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሸማግሌዎች ጋር በወቅታዊ ሰላምና ልማት ላይ ውይይት መድረክ አካሂደዋል።

በመድረኩ የተገኙት የምዕራብ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አባይ አለሙ ባለፉት ሦስት ዓመት ያህል የቆየው ግጭት የጅጋ ከተማና አካባቢው ሰባዊ፣ ቁሳዊና ማህበራዊ ምስቅልቅሎች የደረሱት ግጭቱን የሚያወግዝ የሀገር ሸማግሌና የሀይማኖት አባት መኖር ባለመቻሉ ነው ብለዋል።

ጽንፈኛው ቡድን አማራን ነጻ አወጣለሁ የሚል ግን በተግባሩ አማራን የሚገድል፤ በኢኮኖሚ የሚያጎሳቁል፤ የሚዘርፍ አለፍ ሲልም ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ተቀናጅቶ አማራን በተራዘመ ግጭትና ጦርነት እንዲቆይ እየሰራ ያለ የጥፋት ሀይል መሆኑን አስገንዝበዋል።

የጅጋ ከተማ የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሸማግሌዎች ለእውነት በመቆም ለከተማዋ ዘላቂ ሰላምና ልማት ልትሰሩ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።

የሀገር ሸማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ወደ ጫካ የወጡ ሰዎችን መክራችሁ መልሱ የመንግስት የሰላም በር ሁሌም ክፍት ነው ሲሉ አሳስበዋል።

ብልጽግና ፓርቲ ከተመሠረተ በኋላም የጅጋና አካባቢው የልማት ተጠቃሚ እየሆነ ነው ብለዋል።

በከተማዋ ጤና ጣቢያና በየደረጃው የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለዜጎች ማህበራዊ ብልጽግና መረጋገጥ ጎልተው ውጤት ያመጡት በብልጽግና ፓርቲ ዘመን መሆኑንም አቶ አባይ አንስተዋል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከተማ አስተዳደሩ በፀጥታ ችግር ላይ ሆኖም ያከናወናቸው የልማት ስራዎች አበረታች መሆኑንም ተናግረዋል።

የምዕራብ ጎጃም ጎጃም ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አጉማሴ አንተነህ እንዳሉት ከተማ የሚለማው ህብረተሰቡ በሚያደርገው የጉልበትና የገንዘብ ተሳትፎ ልክ በመሆኑ ነዋሪዎች ለከተማው እድገት ከአስተዳደሩ ጎን በመሰለፍ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሸማግሌዎቾ ሰላምና ልማት እንዲረጋገጥ ስለ ሰላም አብዝተው በመምከር በባለቤትነት መስራት ይገባል ብለዋል።

ሰላም እንዲመጣ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር ተቀራርቦ በመስራት የተጓደሉ ልማቶች ደረጃ በደረጃ ምላሽ እንዲያገኙ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ነው ያሉት አቶ አጉማሴ።

የጅጋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ምስጋናው ድንቁ ጅጋ ላይ ሰላም ለማምጣት የሀገር ሸማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች የድርሻችሁን ለመወጣት ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ተቀራርባችሁ መስራት ይገባል ብለዋል።

ከተማ አስተዳደሩ በብዙ ፈተና ውስጥ ሆኖም አበረታች የልማት ስራዎች እያከናወነ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

"ታሪክ የሚሰራ ትዉልድ አካል ነን"ወጣት ተስፋሁን ተሰማየአማራ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ  ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ
03/08/2026

"ታሪክ የሚሰራ ትዉልድ አካል ነን"

ወጣት ተስፋሁን ተሰማ
የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ

"ተስፋን እንትከል  የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራ"በምዕራብ ጎጃም ዞን በጅጋ ከተማ አስተዳደር "ተስፋን እንትከል"በሚል መሪ ቃል የአንድ ጀምበር የአርንጓዴ አሻራ የችግኞች ተከላ በወጣቶች ...
03/08/2026

"ተስፋን እንትከል የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራ"
በምዕራብ ጎጃም ዞን በጅጋ ከተማ አስተዳደር "ተስፋን እንትከል"በሚል መሪ ቃል የአንድ ጀምበር የአርንጓዴ አሻራ የችግኞች ተከላ በወጣቶች እና በቀበሌ አመራሮች እየተካሄደ ይገኛል።

"ተስፋን እንትከል የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራ"በምዕራብ ጎጃም ዞን በጅጋ ከተማ አስተዳደር "ተስፋን እንትከል"በሚል መሪ ቃል የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ ፕሮግራም እየተካሄደ ይገኛል። ...
03/08/2026

"ተስፋን እንትከል የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራ"
በምዕራብ ጎጃም ዞን በጅጋ ከተማ አስተዳደር "ተስፋን እንትከል"በሚል መሪ ቃል የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ ፕሮግራም እየተካሄደ ይገኛል።
በችግኝ ተከላ ፕሮግራሙ የቀበሌና የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፤ የመከላከያና የጥምር ጦር አመራሮች እንዲሁም በጎ ፈቀደኛ ወጣቶችና የከተማ ነዋሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

Address

Jiga

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Jiga town prosperity party youth league posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share