Kewot Wereda Government Communication affairs office

  • Home
  • Kewot Wereda Government Communication affairs office

Kewot Wereda Government Communication affairs office የቀወት ወረዳ በአማራ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳደር የሚገኝ ወረዳ ነው።

የቀወት ወረዳ በአማራ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳድር ትገኛለች፡፡ወረዳዋን በሰሜን ኤፍራታና ግድም፣በደቡብ ጣርማ በር ፣በምእራብ ጣርማበርና መንዝ ማማ ወረዳዎች እንዲሁም በምስራቅ የአፋር ክልል ያዋስኗታል፡፡ የወረዳ ዋና ከተማ ሸዋሮቢት ስትሆን ከአዲስ አባባ 225 ኪ.ሜ ፣ከደብርብርሃን /ዞን ከተማ/ 95 ኪ.ሜ፣ከባህር ዳር /ክልል ከተማ/ በአዲስ አበባ በኩል 785 ከ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡የሸዋረሮቢት

ሰላምንና ልማትን የሚያጠናክር ውይይት ተካሄደየለን፡ ሃምሌ 29/2018 ዓ.ም (ቀ/ወ/መ/ኮ) በዛሬው ዕለት የቀወት ወረዳ አስተዳደር ከየለን ቀበሌ ነዋሪዎች ጋር ሰላምና ልማትን ሊያመጡና ሊያ...
05/08/2026

ሰላምንና ልማትን የሚያጠናክር ውይይት ተካሄደ

የለን፡ ሃምሌ 29/2018 ዓ.ም (ቀ/ወ/መ/ኮ) በዛሬው ዕለት የቀወት ወረዳ አስተዳደር ከየለን ቀበሌ ነዋሪዎች ጋር ሰላምና ልማትን ሊያመጡና ሊያፋጥኑ በሚችሉ አንኳር ጉዳዮች ላይ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በመሆን የህዝብ ውይይት ማካሄዱን አስታውቋል።

05/08/2026
"ዞናችን ለዋና ከተማው ባለው ቅርበት፣ በተፈጥሮ እና በታሪክ ሀብቱ የተነሳ ለትልቅ ኢንቨስትመንትና ልማት ምቹ አካባቢ ነው"!!... አቶ ኤልያስ አበበ  የሰሜን ሸዋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽሕ...
04/08/2026

"ዞናችን ለዋና ከተማው ባለው ቅርበት፣ በተፈጥሮ እና በታሪክ ሀብቱ የተነሳ ለትልቅ ኢንቨስትመንትና ልማት ምቹ አካባቢ ነው"!!... አቶ ኤልያስ አበበ የሰሜን ሸዋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ

ሸዋሮቢት፦ሐምሌ 28 ቀን 2018 (ቀ/ወ/መ/ኮ) ኃላፊው ይህን ያሉት የአረንጓዴ አሻራ፣ የቤት ግንባታና የትምህርት ድጋፍን ያቀፈ የበጎ ፈቃድ መርሐ-ግብር በአንጎለላና ጠራ ወረዳ ኮቱ ከተማ በተካሄደ በዛሬው ዕለት ነው።

የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኤልያስ አበበ እንዳስታወቁት፣ ሰሜን ሸዋ ለዋና ከተማው ባለው ቅርበት፣ በተፈጥሮ እና በታሪክ ሀብቱ የተነሳ ለትልቅ ኢንቨስትመንትና ልማት ምቹ አካባቢ ነው ብለዋል።

በዚህ ሂደት የወፎ ዋሻ ፓርክ ወደ ብሔራዊ ፓርክነት የማሳደግ ፕሮጀክት በቅንጅት እየተፈጸመ ሲሆን፣ ከነባሩ የለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ በተጨማሪ በቅርቡ ሶስት አዳዲስ ፋብሪካዎች ግንባታ እንደሚጀምርም ተገልጿል።

"የሕዝባችን እውነተኛ ፍላጎት ሰላምና ልማት ነው ያሉት አቶ ኤልያስ አስተማማኝ ሰላምን እየገነባን ከፌደራል ተቋማት ጋር ያለንን ትብብር ወደ ተጨባጭ የሕዝብ ጥቅም እንቀይራለን።" ሲሉ ተናግረዋል።

ሰላም፣ ትብብር እና ልማት ተጣምረው ሰሜን ሸዋን ወደ አዲስ የእድገት ምእራፍ እየመሩት ነው ሲሉ አንስተዋል።

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላን፣ ለአቅመ ደካማ ቤተሰቦች የመኖሪያ ቤት ግንባታን፣ ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ እና የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳትፎ አድርጓል።

በመርሐ-ግብሩ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃን ከማኅበራዊ ልማት ጋር በማስተሳሰር ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ የተቋሙ ቁርጠኝነት መሆኑን ገልጸዋል።

የአረንጓዴ አሻራ እንቅስቃሴ የአካባቢ ጥበቃን ሲያጠናክር፣ የቤት ግንባታና የትምህርት ድጋፉ ደግሞ የማኅበረሰብ ኑሮን ለማሻሻል የሚያግዝ መሆኑን አስታውቀዋል።

አረንጓዴ አሻራ ከማኅበራዊ ኃላፊነት ጋር በማጣመር ተፈጥሮን የሚጠብቅ፣ ማኅበረሰብን የሚያጠናክር እና ዘላቂ ልማትን የሚያፋጥን የትብብር አቅጣጫ መሆኑን ባለሥልጣኑ ተገልጸዋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን ሴቶች ሕጻናትና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ የሮምነሽ ጋሻውጠና በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ9 መቶ 80 ሺህ በላይ የኅብረተሰብ ክፍል በማሳተፍ ከ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጭ ለማዳን እየተሠራ ነው ብለዋል።

በኮቱ ከተማ ከ4 ሚሊዮን በላይ በሆነ የገንዘብ ወጭ የተገነባ ቤት ለአረጋዊያንና ተጋላጭ የኅብረተሰብ ቁልፍ የፍራሽ ማስረከብ ሥነ- ሥርዓት ተካሒዷል ብለዋል።

ኃላፊዋ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ባለሥልጣን ከ4 መቶ 50 ሺህ ብር በላይ ወጭ የተደረገበት የ1 ዓመት የትምህርት ቁሳቁስ ለ3 መቶ ተማሪዎች ድጋፍ ማድረጉን ገልጸው በቀጣይም ከ20 ሚሊዮን በላይ በጀት በመመደብ ደረጃውን የጠበቀ የአረጋውያን ቤት ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ መቀመጡን ተናግረዋል።

የዞናችን ማኅበረሰብ በዚህ ክረምት በ17 ዋና ዋና ዘርፎች በምናደርገው የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የአረጋዊያንና የሕጻናትን ተጠቃሚነት እናረጋግጥ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በመርሐ-ግብሩ ላይ የሰሜን ሸዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ተክለየስ በለጠ ፣ የሰሜን ሸዋ ዞን ፖለቲካ ዘርፍ እና አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊዎች አቶ ዓይነኩሉ አበበ እና ወይዘሮ ሰዓዳ ኢብራሂም ፣ የዞኑ የየመምሪያ ኃላፊዎች ፣ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ባለሥልጣን የማኔጅመንት አባላትና ሠራተኞች ፣ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደረሰ ደመመን ጨምሮ ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
መረጃው;ሰሜን ሸዋ ኮሙኒኬሽን

04/08/2026
በክረምት በጎፈቃድ ንቅናቄ የደም ልገሳ መርሀ ግብር ተካሄደሸዋሮቢት ፡ ሀምሌ27/2018 (ቀ/ወ/መ/ኮ) በቀወት ወረዳ ጤና ፅ/ቤት እና በወረዳው ሴቶች ህፃናት ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤ...
03/08/2026

በክረምት በጎፈቃድ ንቅናቄ የደም ልገሳ መርሀ ግብር ተካሄደ

ሸዋሮቢት ፡ ሀምሌ27/2018 (ቀ/ወ/መ/ኮ) በቀወት ወረዳ ጤና ፅ/ቤት እና በወረዳው ሴቶች ህፃናት ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት አስተባባሪነት የደም ልገሳ መርኃ ግብር ተካሂዷል ።

ከክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎች መካከል አንዱ የሆነው የደምልገሳ መርሀግብር "ደሜን ለወገኔ " በሚል መሪ ቃል የመጀመሪያ ዙር በዛሬው እለት የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን ያሳተፈ ንቅናቄ ተካሂዷል ።

Address


251

Telephone

+251336640635

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kewot Wereda Government Communication affairs office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Kewot Wereda Government Communication affairs office:

Shortcuts

  • Want your organization to be the top-listed Government Service?

Share