29/06/2020
መረጃውን ከዳሰነች ወረዳው የመንግስት ኮሙዮኒኬሽ ጉዳዮች ጽ/ቤት ለሚዲያችን የላኩት መልእክት ፡፡
============================
መነሻውን ሻሸመኔ አድርጎ ወደ ጎረቤት ሀገር ኬንያ ሊሻገር ሲል የነበረ 10 ኩንታል ካናቢስ የተሰኘው አደንዛዥ ዕፅ በዳሰነች ወረዳ በሎኮሮ ንዑስ ፖሊስ ጣቢያ በቀን 14/10/2012 ዓ.ም በፀጥታ መዋቅሩ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ ኦሞራቴ ሰኔ 15 ቀን 2012 ዓ.ም ኮድ AA 93661 በሆነ አይሱዚ መኪና ሲንቀሳቀስ የነበረው 10 ኩንታል ካናቢስ የተሰኘው አደንዛዥ ዕፅ በቁጥጥር ስር መዋሉን የገለፁት የዳሰነች ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ ረ/ኢ/ር ጴጥሮስ የቶክ ሲሆኑ መነሻውን ሻሸመኔ በማድረግ የተለያዩ የሀገሪቱን ክፍሎች አቋርጦ መዳረሻውን ኬንያ ለማድረግ በመንቀሳቀስ ላይ ባለበት ወቅት በሎኮሮ ንዑስ ፖሊስ ጣቢያ በፀጥታ መዋቅሩ ፍተሻ 10 ኩንታል ዕፅ በቁጥጥር ስር መዋሉን የተገለፀ ሲሆን
ተሸከርካሪውና አሽከርካሪውን ጨምሮ በጉዳዩ የተጠረጠሩ 3/ሶስት/ ተጠርጣሪዎች በህግ በቁጥጥር ስር ውለው የምርመራ ስራ መጀመሩ ተግልጻል፡፡ የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤቱ አዛዥ ረ/ኢ/ር ጴጥሮስ የቶክ እንደገለፁቱ በንዑስ ፖሊስ ጣቢያ ለነበሩ ለፀጥታ መዋቅሩ እጅ መንሻ 28,000.000/ሃያ ስምንት ሺህ/ ብር የቀረበ ቢሆንም የፀጥታ ሀይሉ በህዝብና መንግስት የተጣለበትን ሀገርን የመጠበቅ ቃል ኪዳንን በማክበር ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስራ ማዋል በመቻላቸው በወረዳው ህዝብና መንግስት ስም ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ፖሊስ በህዝብና መንግስት የተሰጠውን የሀገር ሰላምንና ደህንነት የማስጠበቅ ተግባሩን ከዚህ በበለጠ እንዲያጠናክር ጥሪ ያስተላለፉ ሲሆን ህዝቡ ከፀጥታ መዋቅሩ ጎን በመሆን ሀገርንና ህዝብን ሊጎዱ የሚችሉ ማንኛንም ዓይነት እንቅስቃሴዎችን በሚመለከት ወቅት በአከባቢው ለሚገኝ የፀጥታ መዋቅር ጥቆማ በመስጠት ከፀጥታ መዋቅሩ ጎን እንዲሆኑ ጥሪ ቀርባል፡፡