Jinka city administration Communication office page .

Jinka city administration Communication office page . About organizations

ዛሬ በቀን 01/10/2015 ዓም በጂንካ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መዋቅር በሚታዩ ጉድለቶችና በቀጣይ ትኩረት በሚሹ እንደዚሁም ትኩረት ልሰጥ በሚያስፈልጋቸው አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ከፖሊስ አመ...
08/06/2023

ዛሬ በቀን 01/10/2015 ዓም በጂንካ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መዋቅር በሚታዩ ጉድለቶችና በቀጣይ ትኩረት በሚሹ እንደዚሁም ትኩረት ልሰጥ በሚያስፈልጋቸው አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ከፖሊስ አመራሩ አካላት እና ከአባላቱ ጋር የግምገማ ነክ የውይይት መድረክ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ዋና አዛዥ በተገኙበት የከተማው ፖሊስ ጽ/ቤት ከከተማው አሰተዳደር የሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን ማካሄድ ጀመሩ የገምገማውንም መድረክ የከተማው አስተዳደር ምክቲል ከንቲባና የጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይሄነው ተስፋዬ የመክፈቻ ንግግር በማድረግ በይፋ አስጀምረውታል የመድረኩን አጠቃላይ ሂደት ይዘን የምንመለስ ይሆናል ።
ሰኔ 01/10/2015 ዓም ።
------------------------------

ለመረጃው የጂንካ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

03/06/2023

ወደ መደበኛ ፖሊስና ወደ ማረሚያ ፖሊስ የሚቀላቀሉ የቀድሞ የልዩ ሀይል አባላትን የተሀድሶ ስልጠና ሰጥቶ ማስመረቁን የደቡብ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀስልጠናውን የወሰዱ የፖሊስ አባላትም...

03/06/2023
""የበጎነት አሻራ ለትውልድ"" በሚል መሪ ቃል በጂንካ አንደኛ ደረጃ በቄራ ትምህርት ቤት በበጎ አድራጊ በሆኑት በዶ/ር ደረጀ ለገሰ የገንዘብ ድጋፍና በወጣት ተንሳይ ኃይሉ እንደዚሁም በር/መ...
03/06/2023

""የበጎነት አሻራ ለትውልድ"" በሚል መሪ ቃል በጂንካ አንደኛ ደረጃ በቄራ ትምህርት ቤት በበጎ አድራጊ በሆኑት በዶ/ር ደረጀ ለገሰ የገንዘብ ድጋፍና በወጣት ተንሳይ ኃይሉ እንደዚሁም በር/መ በወ/ሮ ሽቱ ሻሆ አስተባባሪነት ለአካል ጉዳተኞች የተገነባ መማሪያ ክፍል ዛሬ በቀን 25/09/2015 ዓም በከተማው ክቡር ከንቲባ በአቶ ጉራልቅ ይጅማልቅ እና በከተማው የም/ር ቤት ዋና አፌ-ጉባኤ በሆነችው በክብርት ወ/ሮ ዘይነባ ሀሰን በተጨማሪም ሌሎች የከተማው አመራር እና የዞን አመራር አካላቶች እንዲሁም ሌሎች መምህራናትና ታዳሚዎች በተገኙበት በይፋ የምርቃ ስነስርዓት ተካሄደ ። በተጨማሪም የምረቃውን ሰነ-ስርዓት ምክንያት በማድረግ ለአካል ጉዳተኞች የተለያዩ የመማሪያ ቁሳቁሶችን ለመግዛት እንዲያመች የገቢ ማሰባሰቢያ የባዛር ዝግጅት የተዘጋጀ ስሆን በዝግጅቱም የከተማው ነዋሪ የሆናችሁ በሙሉ በመገኘት እንዲትታደሙም ጭምር መልእክት ተላልፏል ።

ግንቦት 25/09/2015 ዓም
# # # # # # # # # # # # # #
ለመረጃው የጂንካ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

"ጂንካችንን በጋራ እናልማ ውበቷን እንጠብቅ " "የከተማ ልማት ላይ አንደራደርም ""የከተማችን ጉዳይ የሁላችንም ነው !!             👉  ከህዝብ መድረክ በኋላ የከተማ ውበትና ጽዳት ...
02/06/2023

"ጂንካችንን በጋራ እናልማ ውበቷን እንጠብቅ "
"የከተማ ልማት ላይ አንደራደርም "
"የከተማችን ጉዳይ የሁላችንም ነው !!

👉 ከህዝብ መድረክ በኋላ የከተማ ውበትና ጽዳት ኮሚቴ ከአስፋልት ዳር ላይ ሸራና ቆርቆሮ የሰሩ ግለሠቦች ላይ እንዳነሱ ተወሰነ።

ለማንሳት ከመወሰናችን በፊት በግለሰቦች ቤት ለቤት በመዞር ግንዛቤ መፈጠሩን ገልፀው

ግለሰቦችም በሻይ ቡና እና ጫማ በመጥረግ ለሚተዳደሩ ግለሰቦች ስለሆኑ ለሻይ ቡናና ጫማ በመጥረግ ለሚተዳደሩ ቦታ ለመስጠት በመስማማት እንደፈረሰ የኮሚቴው አባል አቶ ገዛኽኝ ገቶ ገልፀዋል ።

በሱቅ ፍት የተሰሩ ቆርቆሮዎች ያለ አንዳች አስገዳጅ ሁኔታ እያነሱ ላሉ ግለሰቦች ምስጋና ይገባቸዋል ስሉ ማህበረሰቡን አመስግነዋል ።

16/03/2023

አጠር ያለ በከተማ አስተዳደሩ ት/ት ጽ/ቤት ላይ ያተኮረና አሁን ላይ የተማሪዎች የንባብ ክሂሎታቸው ምን ደረጃ ላይ ይገኛል በሚል በከተማው አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት አማካይነት የተዘጋጀ የዶከመንተሪ ፍልም ያዳምጡት ።

የጂ/ከ/አስ/ር የተፋሰስ ልማት ማህበር ከ ከአሰ/የግ/ጽ/ቤት ጋር ተቀናጅቶ እንደሚሠራ ተገለጸ።።።።።።።።።።።።።።።። የጂከ/ከ/አስ/ር ከንቲባ አቶ ጉራልቅ ይዥማልቅ ፣የዞኑ የተፋሰስ ልማት...
16/03/2023

የጂ/ከ/አስ/ር የተፋሰስ ልማት ማህበር ከ ከአሰ/የግ/ጽ/ቤት ጋር ተቀናጅቶ እንደሚሠራ ተገለጸ።
።።።።።።።።።።።።።።።
የጂከ/ከ/አስ/ር ከንቲባ አቶ ጉራልቅ ይዥማልቅ ፣የዞኑ የተፋሰስ ልማት ማህበር ዋና ሰብሳቢ አቶ መንግስቱ አስፋዉ ፣ የከ/አስ/የግ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተክለ በላይ፣ እንድሁም የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ፦የተፋሰስ ልማት ያለበትን ደረጃና ከዚህ በኋላ መሆን ያለበት አቅጣጫ ላይ በሰፊዉ መወያዬታቸዉን የጂንካ ከተማ መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ተከታትሎታል።
በዉይይቱም ፦የማህበሩ ዋና ሰብሳቢዉ ፦አጠቃላይ በከተማ አስተዳደሩ ሥር በተፋሰስ ለማልማት ከተመረጡ ሁለት ክላስተሮች ማለትም የባዘትና አልጋ ፕሮጀክት መካከል ነባሩ የባዘት የተፋሰስ ልማት ጥሩ ደረጃ ላይ እንደደረሰና አሁን የተመረጠዉ የአልጋ ፕሮጀክት ከአጀማመሩ ጀምሮ የለበትን ሁኔታ በዝርዝር አቅሪበዋል ።
ባለፉት የተፋሰስ ልማት ሥራ ላይ ያጋጠሙ ችግሮችች 👉የበጀት ዉስንነት፣የአባላቱ የፍላጎት ዉስብስብነት፣በGPs የሰለጠነ የባለሙያ እጥረት እንዳለ ሆኖም ተግባሩ ሳይቋረጥ ባለው ተጣጥሞ እንደተሰራም ገልጸዋል ።
መጋቢት 7/2015
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
//የጂ/ከ/አስ/ር/መ/ጉ/ጽ/ቤት//
# # # # # # # # # # # # # # # # # #

16/03/2023

በፔጃችን ያሎትንና የምሰማዎትን አስተያዬት ይስጡ !!!

ዛሬ በቀን 2/06/2015 ዓ,ም የጂንካ ከተማ አስተዳደር አጠቃላይ የሴክተር መስሪያቤቶችን የ2015 ዓ,ም የ6ት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም በከተማው አስተዳደር ሚኒ  አዳራሽ ከንቲባውን ጨምሮ ...
09/02/2023

ዛሬ በቀን 2/06/2015 ዓ,ም የጂንካ ከተማ አስተዳደር አጠቃላይ የሴክተር መስሪያቤቶችን የ2015 ዓ,ም የ6ት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም በከተማው አስተዳደር ሚኒ አዳራሽ ከንቲባውን ጨምሮ የሴክተር መስሪያ ቤት ኃላፊዎች በተገኙበት እየገመገሙ መሆናቸዉን የጂንካ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት አሳወቀ ። የአፈጻጸም ግምገማውን ሙሉ መረጃ ይዘን በመመለስ የምናደርስ ይሆናል ።

የካቲት 2/06/2015 ዓ,ም
--------------------
ለመረጃው የጂንካ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

በነገው ዕለት ጥር 29/05/2015 ዓ,ም የሚካሄደውን አድሱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምስረታ የህዝበ ውሳኔ ድምጽን በሚመለከት ክቡር ከንቲባ አቶ ጉራልቅ ይጅማልቅ መግለጫ አስተላልፈዋል ።፤...
05/02/2023

በነገው ዕለት ጥር 29/05/2015 ዓ,ም የሚካሄደውን አድሱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምስረታ የህዝበ ውሳኔ ድምጽን በሚመለከት ክቡር ከንቲባ አቶ ጉራልቅ ይጅማልቅ መግለጫ አስተላልፈዋል ።
፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤

በቅድሚያ ለአድሱ ክልል ምስረታ የህዝበ ውሳኔ ድምጽ አጣጣል ቀን መላው የከተማችንና የአከባቢዋ ነዋሪዎች በሙሉ ክቡር ከንቲባው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸውን በማስተላለፍ በጉግት ስጠበቅ የነበረውንና የህዝቡን የክልል እንሁን ጥያቄ መንግስት የመልካም አስተዳደር መልስ ለመመለስ በማሰብ በየደረጃው ጥናቶችን በማከናወን ከጥናቱ በኋላ ህጉን ተከትሎ የመጣ የምርጫ ማስፈጸም ስራ ስለሆነ እሄን ምርጫ ለማስፈፀም ከሌሎች የምርጫ ማስፈፀም በተለዬ መልኩ የሚታይ ነው ። ይህን ምርጫ ለማስፈፀም ምንም አይነት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ ባይኖርም ሁሉም ኢትዮጵያዊያን አንድ ሆኖ በጋራ ሁሉም የሚወሱኑበት ምርጫ ስለሆነ የምርጫውን ሂደት ለማስፈፀም በ24ቱም የምርጫ ጣቢያዎች በሙሉ ዝግጅት እንደ ከተማ አስተዳደርም ሆኔ እንደ መንግስት የሚያስፈልጉትን በሙሉ በሟሟላት ለድምጽ አሰጣጡ ሂደት ምቹ ሁኔታዎችን የማመቻቸት ስራ በበቂ ሁኔታ የተዘጋጀ መሆኑንና ዘጎች ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው
እንዲመርጡ አከባቢውንና አጠቃላይ ዝግጅቱን ከማመቻቸት አኳያ ዝግጁ ማድረጋቸውን ክቡር ከንቲባና የኮማንድ ፖስት ዋና ሰብሳቢ የሆኑት ክቡር ከንቲባ አቶ ጉራልቅ ይጅማልቅ አሳውቀዋል ። ሌላው ከሰላምና ፀጥታ አኳያ ከፀጥታው ኮማንድ ፖስት አባላት አማካይነት በከተማው በሚገኙ በ24ቱም የምርጫ ጣቢያዎች ፀጥታ ኃይሉን የመመደብና የመሰማራት ስራ እንደተሰራና በየምርጫ ጣቢያው ተዟዙረው ዝግጅቱን በሚመለከት መመልከታቸውንም ክቡር ከንቲባው አብራርተዋል ። በመጨረሻም የድምጽ አሰጣጡ ሂደት ሰላማዊ ሆኖ መጠናቀቅ እንዲችል የከተማው ነዋሪ ማህብረሰብ ከፀጥታው አካላት ጎን በመሆን የራሳቸውን አስተዋጽኦ በማበርከትና የምርጫውን ካርድ የወሰዱት በሙሉ የነጌዋን ቀን በመቻል ከሚሄድበት በመቆጠብ የራሱን የአሻራ ድምጽ በመስጠት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጡም ክቡር ከንቲባ አቶ ጉራልቅ ይጅማልቅ በማሳሰብ መልካም የድምጽ አሰጣጥ ቀን እንዲሆን ደግመው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል ።

ጥር 29/05/2015 ዓ,ም
-------------------
ለመረጃው የጂንካ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ።
፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤

Address

South Omo Zone
Jinka
YFSR1234Y

Telephone

+251967911730

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Jinka city administration Communication office page . posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Jinka city administration Communication office page .:

Shortcuts

Share