Gazer Primary Hospital

  • Home
  • Gazer Primary Hospital

Gazer Primary Hospital Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gazer Primary Hospital, .

GPH is found in South Ethiopia Region Ari zone Gazer town administration , Started at Nov 10/2010 EC a 17km from Jinka town.The Gazer hospital is found 1568 meter above sea level and located at latitude of 5.89˚N and longitude of 36.58˚

‎ ‎📌 ወርልድ ቪዥን በአሪ ዞን ከ2.6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የህክምና ግብዓቶችን አበረከተ!‎‎     ሐምሌ 2/2018_ጋዘር‎‎የህዝባችንን ጤና ለመጠበቅና ጥራት ያለው የህክምና አገ...
09/07/2026

‎ ‎📌 ወርልድ ቪዥን በአሪ ዞን ከ2.6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የህክምና ግብዓቶችን አበረከተ!

‎ ሐምሌ 2/2018_ጋዘር

‎የህዝባችንን ጤና ለመጠበቅና ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት የሚደግፍ አበረታች ዜና ከአሪ ዞን ተሰምቷል።

‎የረጅም ጊዜ አጋር የሆነው ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞን ለሚገኙ ሁለት መዋቅሮች—ለደቡብ አሪ ወረዳ እና ለጋዘር ከተማ አስተዳደር—ከ2.6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎችን፣ መድኃኒቶችንና ፍራሾችን በይፋ አስረክቧል።

‎በርክክቡ ላይ የሁለቱ ወረዳዎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የጤና ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች እና የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ በተገኙበት፣ የድርጅቱ አስተባባሪ አቶ አለማየሁ ፍቅሩ ቁሶቹን በሰነድ አስረክበዋል። ከእነዚህ ድጋፎች መካከል ለጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ብቻ የተደረገው ድጋፍ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሲሆን፣ በተለይም እጅግ ወሳኝ የሆነ የላብራቶሪ "Chemistry Machine" (የባዮኬሚስትሪ መመርመሪያ ማሽን) ይገኝበታል።
‎🩺 ይህ ድጋፍ ለህብረተሰቡ ያለው ፋይዳ ምንድነው?

‎ይህ የወርልድ ቪዥን ድጋፍ ተራ ቁሳቁስ ማበርከት ሳይሆን፣ በአካባቢው ያለውን የህክምና ጥራት አንድ ደረጃ ከፍ የሚያደርግ ትልቅ የጤና አምድ ነው። ፋይዳውን በሶስት ዋና ዋና ነጥቦች ማየት ይቻላል፡

‎1.የባዮኬሚስትሪ ማሽን (Chemistry Machine) አስፈላጊነት፦
‎ይህ ማሽን ለአንድ ሆስፒታል የጀርባ አጥንት ነው። የታካሚዎችን የኩላሊት ስራ (Kidney Function)፣ የጉበት ጤና (Liver Function)፣ የስኳር መጠን፣ የኮሌስትሮል እና የተለያዩ የሰውነት ፈሳሾችን በትክክል ለመመርመር ያገለግላል። ማሽኑ መኖሩ ከዚህ ቀደም ታካሚዎች ለከፍተኛ ወጪ ተዳርገው ወደ ሩቅ ቦታዎች ሄደው የሚታዩትን እንግልት ያስቀራል፤ ሐኪሞችም በሽታን ፈጥነው እንዲያውቁና ትክክለኛ ህክምና እንዲሰጡ (Accurate Diagnosis) ይረዳል።
‎2. የመድኃኒቶችና ፍራሾች አቅርቦት፦
‎ወቅቱን የጠበቀ የመድኃኒት አቅርቦት ህይወትን ይታደጋል። እንዲሁም የፍራሾች መሟላት በሆስፒታል ተኝተው የሚታከሙ ህሙማንን ምቾት ከመጠበቁ ባሻገር፣ ረጅም ጊዜ በመተኛት የሚመጡ የቆዳ መቁሰል (Bedsores) ችግሮችንና በሆስፒታል ውስጥ የሚመጡ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው።
‎3. የመከላከልና የሪፈራል ስርዓትን ማጠናከር፦
‎የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎችና የወረዳ ጤና ተቋማት ሲጠናከሩ፣ ህብረተሰቡ በአቅራቢያው ጥራት ያለው ህክምና ያገኛል። ይህ ደግሞ ወደ ከፍተኛ ሆስፒታሎች የሚሄደውን የታካሚ ፍሰትና ጫና ይቀንሳል።

‎🙏 ምስጋና እና አደራ

‎ወርልድ ቪዥን አካባቢውንና ሆስፒታሉን በመደገፍ የዘለቀውን የረጅም ዓመታት አጋርነት ዛሬም በተግባር አሳይቷል። አሁን የሚጠበቀው ትልቁ ስራ፣ እነዚህ ውድ የህክምና ግብዓቶች ሳይበላሹ፣ ሳይባክኑና በአግባቡ ተጠብቀው ለታለመላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ቀጣይነት ባለው መልኩ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ነው።ለተደረገው ድጋፍ ለወርልድ ቪዥን እና ለአስተባባሪው አቶ አለማየሁ ፍቅሩ ታላቅ ምስጋና እያቀረብን፣ የጤና ተቋማቱ አመራሮችም የቁሳቁሶቹን ደህንነትና አገልግሎት በጥብቅ እንዲከታተሉ አደራ እንላለን!

‎ #ጤና #ወርልድቪዥን #አሪዞን #ደቡብኢትዮጵያ #የህክምናአገልግሎት #ጋዘርሆስፒታል

‎‎🏥 የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ2018 ዓ.ም የ4ኛ ሩብ ዓመት የሥራ አመራር ቦርድ ስብሰባና የፕሮጀክቶች ምረቃ በስኬት ተካሄደ!‎ ‎   ሃምሌ 1/2018_ጋዘር‎‎በደቡብ ኢትዮጵያ ...
08/07/2026


‎🏥 የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ2018 ዓ.ም የ4ኛ ሩብ ዓመት የሥራ አመራር ቦርድ ስብሰባና የፕሮጀክቶች ምረቃ በስኬት ተካሄደ!

‎ ሃምሌ 1/2018_ጋዘር

‎በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞን በጋዘር ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል፤ የ2018 በጀት ዓመት የ4ኛ ሩብ ዓመት (የ12 ወራት) የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እና የቦርድ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት አካሂዷል።

‎በስብሰባው ላይ የቦርዱ ዋና ሰብሳቢና የዞኑ አስተዳደር ተወካይ አቶ ታፈሴ ተስፋዬን ጨምሮ ሁሉም የቦርድ አባላት በሙሉነት ተገኝተዋል።

‎ 📈 ዋና ዋና የ12 ወራት የሥራ አፈጻጸም ስኬቶች፦
‎የእናቶች ጤና ጥበቃ፦ባለፉት 12 ወራት 1,996 እናቶች በሆስፒታሉ በሰላም የተገላገሉ ሲሆን፣ 248 እናቶች ደግሞ በቀዶ ጥገና (ኦፕራሲዮን) የህክምና አገልግሎት አግኝተዋል።በተጨማሪም የእርግዝና ክትትል፣ የላብራቶሪ፣ የፋርማሲ እና ሌሎች የህክምና አገልግሎቶች ዙሪያ ሰፊ ግምገማና ውይይት ተደርጎባቸዋል።

‎🛠️ የተቋሙ የልማትና የመሠረተ ልማት እንቅስቃሴዎች፦

‎የቦርድ አባላቱ የተቋሙን የመድኃኒት አቅርቦት ሁኔታ የገመገሙ ሲሆን፣ የሆስፒታሉን ግቢ ሙሉ በሙሉ በመዘዋወር በቅርቡ በተቋሙ ራስን በራስ የማገዝ (የውስጥ) አቅም የተገነቡትን፦

‎* የነርሶች ጣቢያ (Nurse Station)
‎* የልብስ ማጠቢያ ክፍል (Laundry Room)
‎* የህክምና ቆሻሻ ማቃጠያ (Incinerator)
‎* የኤክስሬይ ማሽን (X-ray machine) መገኛ ክፍል እና
‎* የተሻሻለ የፋርማሲ አገልግሎት ሥርዓትን (APTS) በመመልከት ተቋሙ በራሱ ጥረት ላከናወናቸው ተግባራት ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።

‎🎖️ አመርቂ ውጤት ያስመዘገቡ የጥራት ማሻሻያ ፕሮጀክቶች ምረቃ፦

‎1. የእናቶች ቅድመ ወሊድ ክትትል ፕሮጀክት፦ ከሁለት ወራት በፊት እናቶች ከ12 ሳምንታት በፊት ቀድመው የእርግዝና ክትትል እንዲጀምሩ የማድረግ ምጣኔን ከ17% ወደ 90% በማሳደግ የመጀመሪያው ፕሮጀክት መመረቁ ይታወሳል።
‎2. የማኅፀን በር ጫፍ ካንሰር ቅድመ ምርመራ (CA) ፕሮጀክት፦ ዛሬ ደግሞ በቦርዱ ፊት እጅግ አስደሳች የሆነው ሁለተኛው ፕሮጀክት ተመርቋል። ይህም የማኅፀን በር ጫፍ ካንሰር ቅድመ ምርመራ ተደራሽነትን ከነበረበት 33% ወደ 87% ማሳደግ የተቻለበት ደማቅ ስኬት ነው። በሆስፒታሉ ጥራት ማሻሻያ ክፍል አስተባባሪ በአቶ ተፈራ አዳሙ ቀርቧል

‎ 🤝 ማኅበራዊ ኃላፊነት (Social Service) እና የወደፊት አቅጣጫ፦

‎የሆስፒታሉ የህክምና ባለሙያዎች እና የማኔጅመንት አባላት የራሳቸውን ደሞዝ በመቁረጥ ለአቅመ ደካሞች ነፃ የህክምና አገልግሎት (Social Service) እየሰጡ ይገኛሉ። ይህንን የተከበረና የተቀደሰ ተግባር የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ወንድሙ ገዛኽኝ በሰነድ አስደግፈው ለቦርዱ ያቀረቡ ሲሆን፣ ቦርዱም አነሳሽነቱን በከፍተኛ አድናቆት በመቀበል ከተቋሙ ጎን ለመቆምና ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብቷል።

‎የቀጣይ ትኩረት፦
‎የተቋሙ ሥራ አስኪያጅና የቦርዱ ፀሐፊ እንዳመለከቱት፤ በቀጣይ ሆስፒታሉን ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል አሠራር (Digitized) ለመቀየር እና ግብዓቶችን ለማሟላት ቦርዱ በልዩ ትኩረት ለመሥራት መፍትሔዎችን አስቀምጧል።

‎የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለኅብረተሰቡ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የሚሰጠውን አገልግሎት አጠናክሮ ይቀጥላል!

ለክቡራን የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የቦርድ አባላትበአክብሮት ባሉበት፤ጉዳዩ፡- የቦርድ ስብሰባ ጥሪን ይመለከታልሆስፒታላችን ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ልዩ ልዩ የጤና አገልግሎቶችን...
05/07/2026

ለክቡራን የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የቦርድ አባላት
በአክብሮት ባሉበት፤
ጉዳዩ፡- የቦርድ ስብሰባ ጥሪን ይመለከታል
ሆስፒታላችን ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ልዩ ልዩ የጤና አገልግሎቶችን፣ የቴክኖሎጂ ዘመናዊነትን፣ የሰው
ሃይል አቅም ግንባታንና የመሰረተ-ልማት ማስፋፊያዎችን በአግባቡ በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል። በእነዚህ
የሆስፒታሉ ስትራቴጂካዊ የልማት ጉዞዎች፣ በተመዘገቡ ዋና ዋና ስኬቶች፣ ወቅታዊ ፈተናዎችና መስተካከል
በሚገባቸው አንኳር የሥራ ሂደቶች ላይ በሰፊው ለመወያየትና ውሳኔዎችን ለማሳለፍ የቦርድ ስብሰባ መጥራት
አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።
በመሆኑም የፊታችን ረቡዕ (ሃምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም / July 8, 2026) ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ
በሆስፒታሉ ሚኒ አዳራሽ በሚደረገው የቦርድ ውይይት ላይ እንድትገኙ በአክብሮት እያሳሰብኩ፣ በዕለቱ የሚነሱ ዋና
ዋና የውይይት አጀንዳዎች የሚከተሉት መሆናቸውን እገልጻለሁ፡-
1. የሆስፒታሉን አሰራር ወደ ዘመናዊና ወረቀት አልባ (Digital Health Information System) ለመቀየር
እየተደረገ ስላለው ዝግጅትና የሂደት ሪፖርት ግምገማ፤
2. የሆስፒታሉን የሕክምና አገልግሎት ጥራት ይበልጥ ለማሳደግና ተደራሽ ለማድረግ የሚያስፈልገውን የሰው
ሃይል (Staffing) ማሟላትና ስምሪትን በተመለከተ፤
3. አዲስ የተገነባውን የማህበረሰብ ፋርማሲ (Community Pharmacy) ቀጣይ የአገልግሎት አሰጣጥ፣
አቅርቦትና ዝግጁነት መገምገም፤
4. የሆስፒታሉን የስራ እንቅስቃሴና አገልግሎት ለማስቀጠል የቀረበውን የባጀት ማጽደቂያ (Budget
Approval) ሀሳብ መመርመርና ማጽደቅ፤
5. የቦርድ አባላት ጠቅላላ አስተያየት፣ ውሳኔዎችና የቀጣይ አቅጣጫዎች ማጠቃለያ።
የተከበራችሁ የቦርድ አባላት ለሆስፒታላችን ዕድገትና ለጤናው ዘርፍ መሻሻል የምታደርጉትን ያልተቆጠበ ድጋፍና
ሙያዊ አስተዋጽዖ እያመሰገንኩ፣ በእነዚህ ወሳኝ የሆስፒታሉ አጀንዳዎች ላይ ተወያይተን የጋራ አቅጣጫ እንድንቀይስ
በዕለቱ በሰዓቱ እንድትገኙ በአክብሮት እጠይቃለሁ።

‎ በጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የተመዘገበ ድንቅ የህክምና ስኬት! ‎‎   ሰኔ 27/2018_ጋዘር‎‎በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞን የሚገኘው የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የህክምና...
04/07/2026

‎ በጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የተመዘገበ ድንቅ የህክምና ስኬት!

‎ ሰኔ 27/2018_ጋዘር

‎በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞን የሚገኘው የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች ዛሬ በፅናትና በጥበብ የተሞላ ድንቅ ነፍስ አድን ስራ አከናውነዋል።

‎በምስሉ እንደሚታዩት በአንዲት ታካሚ ማህፀን/እንቁላል ማምረቻ አካባቢ ተፈጥሮ የነበረን፣ ከ4 ኪሎ ግራም በላይ የሚመዝን እና ከ14-15 ሳንቲ ሜትር ስፋት ያለውን እጅግ ግዙፍ እጢ በቀዶ ጥገና በስኬት ማውጣት ተችሏል።

‎እንዲህ ያሉ ግዙፍ የእንቁላል ከረጢት እጢዎች (Giant Ovarian Tumors) በሴቶች የሆድ ዕቃ ውስጥ በፈሳሽ ወይም በጠንካራ ሥጋ (solid mass) መልክ የሚፈጠሩ የጤና እክሎች ናቸው። እጢው እያደገ ሲሄድ በሆድ ዕቃ ውስጥ ባሉ እንደ ፊኛ፣ አንጀትና ዋና ዋና የደም ስሮች ላይ ከባድ ጫና (compression effect) በመፍጠር ለከፍተኛ ህመም፣ ለሆድ መነፋትና ለሜታቦሊዝም መዛባት ይዳርጋል። በተለይ መጠኑ ከ4 ኪሎ በላይ የደረሰን እጢ ያለምንም የአካል ክፍሎች መጎዳትና ያለ ደም መፍሰስ በቀዶ ጥገና ለይቶ ማውጣት ከፍተኛ የክህሎትና የጥንቃቄ ደረጃን ይጠይቃል።

‎ይህን ውስብስብና ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሻውን ቀዶ ጥገና በበላይነትና በስኬት ለመሩት፦
‎👨‍⚕️ ለማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስቱ ዶክተር ወንድሜነህ ካሳሁን እና 🏥 አጠቃላይ በኦፕሬሽን ክፍሉ ውስጥ በቁርጠኝነት ለደከሙት የህክምና ቡድን አባላት በሙሉ ላቅ ያለ ምስጋናና አክብሮት ይድረሳቸው!

‎ይህ ስኬት የሆስፒታላችንን የቀዶ ጥገና አገልግሎት አቅም ከማሳየቱም በላይ፣ ማህበረሰባችን በአቅራቢያው ጥራት ያለውና የላቀ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኝ እየተደረገ ላለው ጥረት ትልቅ ማሳያ ነው።

‎ለታካሚዋ ፈጣን ማገገምን እየተመኘን፣ ሌሊት ከቀን ለህዝብ ጤና ለምትተጉ የጤና ባለሙያዎቻችን በሙሉ ክብርና ምስጋና ይሁን!

‎ 🇪🇹

‎ከልብ የሆነ በጎነት—የተስፋ ብርሃን ለወገኖቻችን! ‎‎በሆስፒታላችን የሚገኘው የወንጌል አማኞች ህብረት በተግባር የተገለጠ፣ እጅግ የሚያስመሰግንና ልብ የሚነካ ታላቅ በጎ ሥራ ሰርተዋል።‎‎ህ...
03/07/2026

‎ከልብ የሆነ በጎነት—የተስፋ ብርሃን ለወገኖቻችን!

‎በሆስፒታላችን የሚገኘው የወንጌል አማኞች ህብረት በተግባር የተገለጠ፣ እጅግ የሚያስመሰግንና ልብ የሚነካ ታላቅ በጎ ሥራ ሰርተዋል።

‎ህብረቱ ቲሸርቶችን በማሳተምና ልዩ ልዩ ስጦታዎችን በማሰባሰብ፣ በሆስፒታሉ ውስጥ ታክመው መክፈል ለማይችሉ አቅመ-ደካማ ወገኖቻችን መታደጊያ የሚሆን 31,355 (ሰላሳ አንድ ሺህ ሶስት መቶ ሃምሳ አምስት) ብር አሰባስበዋል። ይህ የተሰበሰበው ገንዘብ በቀጥታ በሆስፒታሉ ውስጥ ለዚሁ ተብሎ በተከፈተው የሶሻል ሰርቪስ (Social Service) የባንክ አካውንት ውስጥ ገቢ ተደርጓል።

‎ይህንን ታላቅ የበጎ አድራጎት ስራ በግንባር ቀደምትነት ያስተባበሩት ዶክተር ሳሙኤል ዳዊት ከህብረቱ መሪዎች ጋር በመሆን ዛሬ በሆስፒታሉ ተገኝተው ለሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ የገንዘብ ርክክብ አድርገዋል።

‎የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅም ለዚህ አይነቱ ክቡር እና የሰውን ህይወት ለመታደግ ለሚደረግ ድንቅ ተነሳሽነት፣ በሆስፒታሉ ማህበረሰብ እና በታካሚዎች ስም ለህብረቱ አመራሮችና አባላት በሙሉ የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

‎📌 መልዕክታችን፡
‎"የሰው ልጅ ለሰው ልጅ መድኃኒቱ ነው!" እንዲሉ፣ በችግር ላይ ላሉ ወገኖቻችን ደራሽ መሆን ከምንም በላይ ትልቅ የህሊና እርካታ ነው። ይህ መልካም ተግባር ለሁላችንም አርአያ የሚሆን ነው።

ለዚህ አገልግሎት ልባችሁ የፈቀደውን ከ10ብር ጀምራችሁ በዚህ አካውንት ገቢ በማድረግ በገንዘብ እጥረት መታከም የማይችሉትን ወጌኖቻችንን እናግዝ👉1000451135353

‎ፈጣሪ በጎነታችሁን ይክፈል! አብሮነታችሁ አይለየን። 🙏❤

‎ #በጎነት #ማህበራዊአገልግሎት #ምስጋና #አብሮነት

‎📢 መልካም ዜና ከጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል!‎‎     ሰኔ 25/2018_ጋዘር‎‎በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞን በጋዘር ከተማ አስተዳደር ሥር የሚገኘው የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒ...
02/07/2026

‎📢 መልካም ዜና ከጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል!

‎ ሰኔ 25/2018_ጋዘር

‎በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞን በጋዘር ከተማ አስተዳደር ሥር የሚገኘው የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል፤ ለማህበረሰቡ ጥራት ያለው የሕክምና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችለውን ታላቅ የምሥራች ይዞ ቀርቧል!

‎🏥 ሆስፒታላችን የማህበረሰቡን የመድኃኒት ፍላጎት ለማሟላት የ2018 በጀት ዓመት የ4ኛውን ሩብ ዓመት የመድኃኒት ግዥ ከ40 ምንጭ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት አገልግሎት (EPSA) በመግዛት ሙሉ በሙሉ ወደ ተቋሙ አስገብቷል።ከ60 በላይ Oxygen Cylinder ተሞልቶ መጥቷል።

‎💰 ለዚህ ግዥ ከ2.2 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገ ሲሆን፣ ይህም ለሆስፒታሉ በቂና አስተማማኝ የመድኃኒት አቅርቦት እንዲኖር ያደርጋል።

‎🗣️ የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ያዕቆብ ጥላሁን እንደገለጹት፤ ከEPSA ጋር በተገባው ውል መሠረት በ2018 በጀት ዓመት ያለምንም ማቋረጥ አገልግሎት የተሰጠ ሲሆን፣ ለቀጣዩ ለ2019 በጀት ዓመታም አዲስ ውል ተገብቶ ዝግጅቱ ተጠናቋል።

‎🔬 የሥራ አስኪያጁ ልዩ መልዕክት፦
‎የመድኃኒት ግዥው በዋናነት ማህበረሰባችንን ከእንግልትና ካልተገባ ተጨማሪ ወጪ ለመታደግ የተደረገ ነው።
‎1️⃣ ወገኖቻችን መድኃኒት ፍለጋ ወደ ውጭ ፋርማሲዎች በመሄድ አላስፈላጊ ለሆነ ከፍተኛ ወጪ እንዳይዳረጉ፤
‎2️⃣ በአሁኑ ወቅት በአካባቢያችን የወባ ወረርሽኝ ስጋት ስላለ፣ "ሆስፒታል ውስጥ መድኃኒት አይኖርም" በሚል የተሳሳተ ግምት ከጤና ተቋም ቀርተው ለከፋ አደጋ እንዳይጋለጡ አሳስበዋል።

‎ሆስፒታላችን ለማንኛውም የጤና እክል በቂ መድኃኒትና ዝግጅት አድርጎ እየጠበቃችሁ ስለሆነ፣ ሕክምና የሚያስፈልጋችሁ ወገኖቻችን በሙሉ ሳይዘገዩ ወደ ሆስፒታላችን በመምጣት አገልግሎቱን እንድታገኙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

‎"የማህበረሰባችን ጤና የሥራችን ስኬት መለኪያ ነው!"

‎📍 ጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

‎ 🚨 የወባ ወረርሽኝን በጋራ እንመክት! 🚨‎‎ ሰኔ 25/2018 ዓ.ም _ጋዘር‎‎በአሪ ዞን በደቡብ አሪ ወረዳ እና በጋዘር ከተማ አስተዳደር በጋራ ያስተባበሩት ታላቅ የወባ በሽታ መከላከል እ...
02/07/2026

‎ 🚨 የወባ ወረርሽኝን በጋራ እንመክት! 🚨

‎ ሰኔ 25/2018 ዓ.ም _ጋዘር

‎በአሪ ዞን በደቡብ አሪ ወረዳ እና በጋዘር ከተማ አስተዳደር በጋራ ያስተባበሩት ታላቅ የወባ በሽታ መከላከል እና ቁጥጥር ንቅናቄ መድረክ በስኬት ተካሂዷል።

‎በመድረኩ ላይ ከክልል የመጡ ደጋፊ ባለሙያዎች አቶ ታምራት አሰፋ እና አቶ አብርሃም ሞጋ ጨምሮ የሁለቱ ወረዳዎች አስተባባሪዎች፣ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች፣ የጤና ጣቢያ ኃላፊዎች፣ የሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ እንዲሁም የቀበሌ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት በሙሉ በንቃት ተሳትፈዋል።

‎ 📌 ከመድረኩ የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች፦

‎ 🤝 የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት፦ በደቡብ አሪ ወረዳ ጤና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በአቶ ሳሙኤል ደይስ የቀረበ ሲሆን፣ የወባን ጫና ለመቀነስ የጋራ ርብርብ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
‎ 🎬 ይፋዊ የመድረክ መክፈቻ፦ የጋዘር ከተማ አስተዳደር ዋና ከንቲባ አቶ በለጤ ማጎ እና የደቡብ አሪ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ኃላፊና የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ትንሹ ተክሌ መድረኩን በጋራ በመክፈት፣ አመራሩ በቀጣይ የወባ በሽታን ለመቆጣጠር በትኩረትና በቁርጠኝነት መሥራት እንዳለበት አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
‎ 📊 የሁኔታው ግምገማ፦የሁለቱ ወረዳዎች የወባ ወረርሽኝ ያለበት ወቅታዊ ደረጃ በሰነድ ቀርቦ ጥልቅ ግምገማ ተካሂዶበታል።
‎🙏 ምስጋና ለረድኤት ድርጅቱ፦ ይህንን ወሳኝ የንቅናቄ መድረክ በበጀት በመደገፍ ትልቅ አስተዋጽኦ ላበረከተው ዎርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ (World Vision Ethiopia) በደቡብ አሪና በጋዘር ከተማ ፕሮጀክቱን እያስተባበሩ ለሚገኙት ለአቶ አለማየሁ ፍቅሩ የላቀ ምስጋና ቀርቧል።

‎ 📉 ወቅታዊው የወባ ጫና እና ሊደረግ የሚገባው ጥንቃቄ!
‎ በአሁኑ ወቅት የወባ በሽታ ስርጭትና ጫና በተለይም በዚህ በሰኔ ወር ላይ ከ 58% በላይ የደረሰ በመሆኑ ጉዳዩ አሳሳቢና እጅግ ከፍተኛ ጥንቃቄን የሚሻ ነው።

‎ወባን መከላከል የሚቻለው በጤና ተቋማት ጥረት ብቻ ሳይሆን እያንዳንዳችን በየቤታችንና በየአካባቢያችን የምንወስደው እርምጃ ሲታከልበት ነው። ስለዚህ፦

‎1. 🦟 አልጋ አጎበርን በአግባቡ መጠቀም፦ ማታ ማታ ሁልጊዜ በአልጋ አጎበር ውስጥ መተኛትን ልማድ እናድርግ።
‎2. 💧 የወባ ትንኝ መራቢያዎችን ማጥፋት፦ በቤታችን ዙሪያ የሚገኙ የቆሙ ውኃዎችን ማፍሰስ፣ ሣርና ቁጥቋጦዎችን መመንጠር እንዲሁም ጉድጓዶችን መድፈን።
‎3. 🩺 ፈጣን ሕክምና፦ ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት፣ ራስ ምታትና ተመሳሳይ የሕመም ስሜቶች ሲታዩ በአቅራቢያችን ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ በአስቸኳይ መታየትና ሕክምና መጀመር።

‎"ጤናችን በእጃችን ነው! አካባቢያችንን በማጽዳትና አጎበርን በአግባቡ በመጠቀም ራሳችንንና ቤተሰባችንን ከወባ በሽታ እንጠብቅ!"

‎ #የወባመከላከል #የአሪዞን #ጋዘርከተማ #ደቡብአሪ #ጤና #ዎርልድቪዥን

‎ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞን በጋዘር ከተማ አስተዳደር የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የተሻለና ግልጽነት ያለው የፋርማሲ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ ነው!‎‎   ሰኔ 19/2018_...
26/06/2026

‎ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞን በጋዘር ከተማ አስተዳደር የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የተሻለና ግልጽነት ያለው የፋርማሲ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ ነው!

‎ ሰኔ 19/2018_ጋዘር

‎ዛሬ ጠዋት በሆስፒታሉ ግልጽነትና ተጠያቂነትን ያሰፈነውን የ APTS (Auditable Pharmaceutical Transactions and Services) አሰራር በይፋ ለማስጀመር የሚያስችል ወሳኝ ስልጠና በክልሉ እና ሌሎች ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን መስጠት ጀምረናል።
‎ የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አመራሮች እንደተናገሩት ይህ አገልግሎት ከዛሬ 2 እና 3 ዓመት በፊት ክፍት እንድሆን ጥረት ተደርጎ ሳይሳካ አሁን መጀመሩ ለተቋማችን ጥራት ወሳኝ ምና እንዳለው እና የመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለትን ለማዘመን፣ የፋይናንስ ግልጽነትን ለማረጋገጥ እና ለታካሚዎቻችን ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት በፍትሃዊነት ለማቅረብ የAPTS አሰራር ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋሉ።
‎በዚህ ስልጠና ላይ የፋርማሲ ባለሙያዎች፣ የዕለት ገቢ ሰራተኞች፣ የኦዲትና የግዥ ባለሙያዎች፣ የጥራት ማሻሻያ አስተባባሪ እንዲሁም የሰው ሀብት ልማት የስራ ክፍሎች በጋራ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ ያዕቆብ ጥላሁን እንደተናገሩት ‎ይህ አዲስ አሰራር በሆስፒታላችን ያለውን የመድኃኒት አቅርቦትና የፋይናንስ ፍሰት ዘመናዊ፣ ኦዲት የሚደረግና ከብክነት የጸዳ በማድረግ ለተገልጋዮቻችን የምንሰጠውን አገልግሎት ጥራት በእጅጉ ያሻሽላል ብለዋሉ።

‎ በተግባር የተደገፈ ግልጽነትና ጥራትን ለማምጣት የምናደርገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል!!




‎  ! ‎‎      ሰኔ 17/2018_ጋዘር‎‎በሆስፒታላችን ለረጅም ጊዜያት አብረውን በመሆን፣ በተለይም በሥርዓተ-ምግብ ሕክምና (Nutrition) ክፍል ላይ በዋጋ የማይተመን ትልቅ አሻራ ጥ...
24/06/2026

‎ !

‎ ሰኔ 17/2018_ጋዘር

‎በሆስፒታላችን ለረጅም ጊዜያት አብረውን በመሆን፣ በተለይም በሥርዓተ-ምግብ ሕክምና (Nutrition) ክፍል ላይ በዋጋ የማይተመን ትልቅ አሻራ ጥለው ያለፉትን Doctors with Africa (CUAMM) የተባለውን ታላቅ ድርጅት በዛሬው ዕለት በደማቅ ሁኔታ ሸኝተናል።

‎CUAMM በተለይ እጅግ አሳሳቢ በሆኑ የሥርዓተ-ምግብ ሕክምና ዘርፎች ላይ፦
‎✍️የሕክምና ግብዓቶችን (Medical Supplies) በማቅረብ፣
‎✍️ዘመናዊ የሕክምና መሣሪያዎችን (Medical Equipment) በማሟላት፣
‎✍️ እንዲሁም በሌሎች ዘርፈ-ብዙ የጤና ድጋፍና የአቅም ግንባታ ሥራዎች ላይ ሌሊት ከቀን በመሥራት የበርካታ ወገኖቻችንን ሕይወት ለመታደግ ትልቅ አስተዋጽዖ አድርገዋል።

‎በሆስፒታላችን የነበራቸውን የአገልግሎት ጊዜ አጠናቀው በሚወጡበት በዚህ ወቅት፣ የሆስፒታላችን ማናጅመንት እና መላው የሕክምና ባለሙያ የተሰማቸውን ጥልቅ ምስጋና ለመግለጽ ደማቅ የሽኝት ፕሮግራም አዘጋጅቷል።

‎ የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ያዕቆብ ጥላሁን ድርጅቱን ባደረጋችሁት ሁለንተናዊ ድጋፍና ለህዝባችን ባሳያችሁት ቅንነት መላው የሆስፒታላችን ማኅበረሰብ እና የአካባቢው ነዋሪ ሁሌም ሲያስታውሳችሁ ይኖራል በማለት አመስግኗል።

‎Doctors with Africa (CUAMM) ለፈጸማችሁት ድንቅ የበጎ አድራጎት እና የሕክምና አገልግሎት በሆስፒታላችን እና በሕዝባችን ስም ከልብ እናመሰግናለን! በቀጣይ የሥራ ዘመናችሁ ሁሉ መልካም ዕድልና ስኬትን እንመኛለን! 🕊️💙

‎ Program

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gazer Primary Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Want your organization to be the top-listed Government Service?

Share