የባካ ዳውላ ኣሪ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

  • Home
  • Ethiopia
  • Jinka
  • የባካ ዳውላ ኣሪ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

የባካ ዳውላ ኣሪ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የባካ ዳውላ ኣሪ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት, Government Organization, በኣሪ ዞን የባካ ዳዉላ ኣሪ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት, In Aari Zone Baka Dawula Aari Woreda Government Communication Affairs, Jinka.

የኣሪ ዞን ፖሊስ መምሪያ የተጠናቀቀዉን በጀት አመት  የሥራ ዕቅድ አፈጻጸም በመገምገም በ2019 በጀት ዓመት የውጤት ተኮር ስራ ዕቅድ ላይ የዉይይት መድረክ አካሄዴ።  ነሐሴ14/ ቀን 2018...
20/08/2026

የኣሪ ዞን ፖሊስ መምሪያ የተጠናቀቀዉን በጀት አመት የሥራ ዕቅድ አፈጻጸም በመገምገም በ2019 በጀት ዓመት የውጤት ተኮር ስራ ዕቅድ ላይ የዉይይት መድረክ አካሄዴ።

ነሐሴ14/ ቀን 2018 ዓ/ም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የኣሪ ዞን ፖሊስ መምሪያ የ2018 ዓ.ም የሥራ ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና በ2019 በጀት ዓመት የውጤት ተኮር ስራ ዕቅድ ላይ ተወያይቷል።

በዉይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ አብራሃም አታ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ላይባለፈዉ በጀት አመት የዞኑ ፖሊስ የዜጎችን ሠላምና ደህንነት አስተማማኝ በማድረግ ህብረተሰቡ ከወንጀል ስጋት ተላቆ በነፃነት ተንቀሳቅሶ መስራት እንዲችል ምቹ ሁነታ በመፍጠር መላዉ ህዝባችን የልማት ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ፖሊስ የተጣለበትን ኃላፊነት ተወጥታል ብለዋል ።

የህግ የበላይነት ሰፍኖ የህዝብ ሠላምና ደህንነት የተረጋገጠበትን ከወንጀል ነጻ የሆነ ህብረተሰብ ለመፍጠር እና ወንጀልን አስቀድመው ለመከላከል ህብረተሰቡን በማስተባበር በቅንጂት በመስራት ፣አጋዥ ኃሎችን በማጠናከር ፣ የማህበረሰብ አቀፍ የወንጀል መከላከል ፖሊስ ተቋማትን ማስፋፋት በተጠናከረ መልኩ በቀጣይ በጀት አመት መሰራት እንዳለበት ገልጸዋል።

በመቀጠልም የ2018 ዓ.ም ዕቅድ ክንውን ሪፖርት እና የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት መነሻ ዕቅድ የኣሪ ዞን ፖሊስ መምሪያ ልማት ዕቅድ ዲቪዥን ኃላፊ ኮማንደር ጥላሁን ተስፋዬ አቅርበዋል።

መድረኩን የመሩት የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኮማንደር መሰለ ገብሬ እንደገለጹት ፖሊስ ባለፈዉ በጀት አመት ዉስጥ ጠንካራ አፈፃፀም ያስመዘገበበት ብሆንም በቀጣይ በጀት አመት ዉስጥ ጉድለቶችን በመለየት የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገብ ያስፈልጋል ብለዋል።

አክለዉም ፖሊስ ከማህበረሰቡ ጋር በጋራ በመሥራት ወንጀልን አስቀድሞ ለመከላከል፣ የሰላምና ጸጥታ ደህንነትን አስተማማኝ ለማድረግ እንዲሁም የሕብረተሰቡን ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላትና የአጋዥ ኃይሎችን በማደራጀት የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ትምህሪቶችን በማጠናከር እንደምሰራ ጠቁመዋል።

በመጨረሻም በ2018 በጀት ዓመት የተስተዋሉ ጉድለቶችንና ስኬቶችን በመለየት በቀጣይ የ2019ዓ/ም ዕቅድ ላይ የትኩረት አካል በማድረግ መስራት እንደሚገባም የዉይይቱ ተሳታፊዎች አስገንዝበዋል።

በመድረኩም የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የ2019 ዓ.ም መነሻ ዕቅድ ላይ በመወያየት ቀጣይ የመፍትሔ አቅጣጫ በዞኑ ዋና አስተዳደር፣በዞኑ ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፍና በዞኑ ፖሊስ አዛዥ ተቀምጦ ዉይይቱ ተጠናቋል።

የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ አብራሃም አታ ፣የኣሪ ዞን ምክር ቤት ህግና ፍትህ መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሊደት መኮንን ፣የኣሪ ዞን ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ማታዶ በርብ ፣የዞን ፖሊስ መምሪያ ማናጅመንት አባላት ፣የከተማና የወረዳ ፖሊስ አዛዦችና ማናጅመንት አካላት በመድረኩ ተሳትፈዋል ሲል የኣሪ ዞን ፖሊስ መምሪያ በገፁ ዘግቧል።

በባካ ዳዉላ ኣሪ ወረዳ ለህብረተሰቡ የንቃተ ህግ ግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በሁሉም ቀበሌያት በተጠናከረ መልኩ እየቀጠለ እንደሚገኝ ተገለፀ።   ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም         (አርክሻ...
20/08/2026

በባካ ዳዉላ ኣሪ ወረዳ ለህብረተሰቡ የንቃተ ህግ ግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በሁሉም ቀበሌያት በተጠናከረ መልኩ እየቀጠለ እንደሚገኝ ተገለፀ።

ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም
(አርክሻ -ካይሳ)

በኣሪ ዞን በባካ ዳዉላ ኣሪ ወረዳ የንቃተ ህግ ግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በዛሬዉ ዕለትም ከ6 ቀበሌያት የተወጣጡ ወደ ሃያ ሺህ ለምጠጉ የህብረተሰብ ክፍሎች ግንዛቤ መፈጠር መቻሉን የወረዳዉ ፍትሕ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሸብር ልሳኑ ገልፁዋል።

ይህ የንቃተ ህግ ንቅናቄ በክልል ደረጃ የተቀመጠውን አቅጣጫ ተከትሎ እየተከናወነ ያለ ሰፊ ስራ በመሆኑ ዛሬም በወረዳችን በሴኔጋል፣በአሊ፣በባኮ፣በሰንማመር እና በአሽቲ ቀበሌያት የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቱን፤

በትምህርቱ ወቅት በማህበረሰቡ ሰላምና ደህንነት ላይ ስጋት በሆኑ ዋና ዋና የወንጀል አይነቶች ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን በተለይም በግድያ ወንጀል፣ በጋብቻ ላይ ጋብቻ መፈጸም፣ በአስገድዶ መድፈር፣ በመሬት ወረራ፣ በሙስና ወንጀሎች፣ የጥላቻ ንግግር ‎፣በደንና በአካባቢ ጥበቃ፣፣ያለእድሜ ጋብቻ እና በሰው አካል ላይ ጉዳት በማድረስ ጉዳዮች ዙሪያ በሴኔጋል ክላስተር ግንዛቤ ለመፍጠር ተችሏል።

ኃላፊዉ ባስተላለፉት መልእክትም ፤ ወንጀልን አስቀድሞ ለመከላከል የማህበረሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም ወጣቱ ክፍልና የሃይማኖት ተቋማት ወንጀልን በመጸየፍና በማስተማር ረገድ የበኩላቸውን ሃላፊነት እንዲወጡም ጥሪ ‎አቅርበዋል።

ሰዎች ከአልባሌ ከህገ ወጥ ተግባር በመቆጠብ ራሳቸዉን ከወንጀል በመከላከል አካባቢውን ቀበሌውን ከወንጀል የጸዳ በልማትና በመልካም ስነ ምግባር የምትታወቅ ሞደል ቀበሌ መፍጠር ያስፈልጋል ስሉም የጽህፈት ቤት ገልጸዋል።

የሴቶችን መብት ባለመጠበቅና ባለማክበር የመጀመሪያን ሚስት መብት በመጣስ በንብረቷ ላይ ሁለተኛ ሚስት በህገ ወጥ መንገድ በማግባት ንብረቷን ባልተገባ መንድ እንድባክንና ከቤት ንብረቷ አፈናቅሎ ልጆቿ የመንገድ ተዳዳሪ እንድሆኑ የተደረገበት ዘመን ማብቃት አለበት ስሉ በማሳሰብ፥

ሙሉ በሙሉ አርሶ አደሩ ፊቱን ወደ ልማት በማዞር የህግ የበላይነትን በማክበር ከቤተሰቡ ጋር ሰብሰብ ብሎ ከመጀመሪያ ሚስቱ ጋር በመተባበር ድህነት ላይ አብዮት በማወጅ የተሻለ ኢኮኖሚ ለመፍጠር መትጋት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ያለዕድሜ ጋብቻ በተለይ ከአስራ ስምንት ዓመት በታች ከአስራ ሦስት ዓመት በላይ የሆኑትን ሕጻናት ልጆች ጋር የሚደረግ ማንኛውም ያለዕድሜ ጋብቻ ከህግ አንጻር ተቀባይነት እንደሌለ በመገንዘብ ሰው ሁሉ ከዝህ ድርጊት እንድታቀብ በማሳሰብ ዕድሜ ያልደረሳትን የዳረም ሆነ ያገባ ጭምር በህግ እንደሚጠየቅ በጥብቅ በማስገንዘብ የዕለቱን መድረክ አጠናቀዋል።።

20/08/2026
በኣሪ ዞን የባካ ዳዉላ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት የ2019 የትምህርት ዘመን የተማሪ ምዝገባ እና ከ5 ዓመት በላይ የተማሪዎች ብሔራዊ ፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ጀመረ።    ነሐሴ14 /2018 ዓ....
20/08/2026

በኣሪ ዞን የባካ ዳዉላ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት የ2019 የትምህርት ዘመን የተማሪ ምዝገባ እና ከ5 ዓመት በላይ የተማሪዎች ብሔራዊ ፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ጀመረ።

ነሐሴ14 /2018 ዓ.ም
አርክሻ -ካይሳ

የባካ ዳዉላ ኣሪ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በመሃል አርክሻ መጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የ2019 ትምህርት ዘመን የተማሪ ምዝገባ እና ከ5 ዓመት በላይ የተማሪዎች የብሔራዊ ፋይዳ መታወቂያ (National Id🪪) ምዝገባ በይፋ ጀምሯል።

ትምህርት የአንድ ሀገር እድገት መነሻ በመሆኑ ማንኛውም ለትምህርት የደረሰ ህፃን ወደ ትምህርት ቤት መግባት አለበትና ተማሪዎች ከምዝግባ ጀምሮ ውጤት እስከሚያስመዘግቡ ድረስ የወላጆች እና የመምህራን ሚና ከፍተኛ ስለሆነ አጠናክረው መቀጠል አለባቸዉ።

በዚህም የምዝገባ ህደት ክልሉም ሆነ ዞኑ ያስቀመጠው ጊዜ ሰሌዳ በጣም ውስን ከመሆኑ አንፃር ሁሉም ወላጅ ልጆችን በተቀመጠው ጊዜ በማስመዝገብ የድርሻውን እንድወጣ ጥሪ እናቀርባለን።

በተጨማሪም ለመጪው የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የተጀመረ በመሆኑም ወላጆች ከ 5 አመት በላይ የሆኑ ህጻናት ተማሪዎችን ከወዲሁ እንድታስመዘግቡ እናሳስባለን፡፡

በምዝገባ ቦታዉም የባካ ዳዉላ ኣሪ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ ጽ ቤት ወጣቶች ክንፍ ኃላፊና የቀበሌዉ ደጋፊ አመራር አቶ ነብዩ ኃይሌ፣የወረዳዉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከተማ ሽፈራዉ፣የት/ቤቱ ርዕሰ መምህርን ጨምሮ የአርክሻ ቀበሌ አስተዳደርና ሥራአስኪያጅ እና ሌሎች ተገኝተዋል።

ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም ሁሉም!!

የኣሪ ዞን ትምህርት መምሪያ የ2019 ዓ/ም የተማሪ ምዝገባ እስከ ነሐሴ 30/2019 ድረስ ልጠናቀቅ እንደሚገባ አቅጣጫ መቀመጡን አስታወቀ ።ነሐሴ 13/2018ዓ.ም  አርክሻ -ካይሳ የኣሪ ዞ...
20/08/2026

የኣሪ ዞን ትምህርት መምሪያ የ2019 ዓ/ም የተማሪ ምዝገባ እስከ ነሐሴ 30/2019 ድረስ ልጠናቀቅ እንደሚገባ አቅጣጫ መቀመጡን አስታወቀ ።

ነሐሴ 13/2018ዓ.ም
አርክሻ -ካይሳ

የኣሪ ዞን ትምህርት መምሪያ ዋና ኃላፊ የሆኑት የተከበሩ አቶ እልፊዮስ ባድሜ እንደተናገሩት የ2019 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ የሚጀምረዉ መስከረም 5/2019 ዓ/ም እንደሆኔና አጠቃላይ የምዝገባና የተማሪ ቅበላ የሚጠናቀቀው ከነሐሴ 13/2018 ጀምሮ ባሉት 17 ቀናት ዉስጥ ብቻ መሆኑንም ገልፀዋል ።

አክለዉም በዘንድሮዉ የተማሪ ምዝገባ የፋይዳ መታወቂያ መኖር አስፈላጊ እንደ ሆነም ጠቁመዉ ለስኬታማነቱም ወላጆችና የልጆች አሳዳጊዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ኃላፊነታቸዉን እንድወጡም በማለት ጥሪ አስተላልፈዋል ።

በተጨማሪ ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ ዕድሜያቸዉ ለትምህርት የደረሱ ህፃናትን ጨምሮ ነባርና አዳዲስ ተማሪዎችን ወቅቱን ጠብቀዉ እንድያስመዘግቡ አሳስበዉ ትምህርት ቤቶችም ከተጠቀሰዉ የምዝገባ ቀን አንስቶ መደበኛ የመንግስት የሥራ ሰዓትን በመጠበቅ ምዝገባ እንድያካህዱና አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድያደርጉም የጥንቃቄ መልዕክትም አስተላልፈዋል።

በስተመጨረሻም እንደ ኣሪ ዞን በዚህ ዓመት ከ120 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ለመቀበል መታቀዱንና የምዝገባው ሥርዓት በስኬት እንድጠናቀቅ የትምህርት ባለድርሻ አካላት አሳታፊ የሆነ ቅንጂታዊ አሠራርን በመዘርጋት የሐይማኖት ተቋማትን ጭምር በማሳታፍ በምዝገባ ወቅት ልፈጠሩ የሚችሉ ያልተገባ የክፍል እርከን ዝዉዉር እና ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ መበራከትም እንዳይስተዋል በጥብቅ ዲሲፕሊን እየተመራ በየትምህርት ቤቶችም የተግባሩን ተፈፃሚነትና ፍጥነት እንድሁም ጥራት የሚፈትሹ ግብረሃይል በማቋቋም ወደ ትግበራ እንደሚገባም አበክረዉ ተናግረዋል ።

"ጥራት ያለዉ ትምህርት ለሁሉም !!"

በባካ ዳዉላ ኣሪ ወረዳ በካይሣ ቀበሌ በአሸዋ አምራችነት የተደራጁ ማህበራት አቅማቸዉን ከፍ በማድረግ ወደ ፍየል ማሞከት ሥራ እንደተሸጋገሩ ተገለፀ       ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም      ...
19/08/2026

በባካ ዳዉላ ኣሪ ወረዳ በካይሣ ቀበሌ በአሸዋ አምራችነት የተደራጁ ማህበራት አቅማቸዉን ከፍ በማድረግ ወደ ፍየል ማሞከት ሥራ እንደተሸጋገሩ ተገለፀ

ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም
(አርክሻ -ካይሳ)

በኣሪ ዞን በባካ ዳዉላ ኣሪ ወረዳ ሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ወጣቶች ከዚህ ቀደም በአሸዋ አምራችነት በማህበር በመደራጀት እድገት በህብረት በሚል ስያሜ አሸዋ ስያመርቱ ቆይተዉ አቅማቸውን ከፍ በማድረግ ወደ ፍየል ማሞከት ሥራ መሸጋገራቸዉን የወረዳዉ ሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ባማይ ካሣ ገልፀዋል።

ጽ/ቤቱ ከሱስ ነፃ የሆነ ወጣት በመገንባት ነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለማፍራት በየቀበሌው ወጣቶች ተደራጅተው እንዲሰሩ እድል እያመቻቸ እንደምገኝም ጠቅሰዋል።

እነዚህ ማህበራት ጠንክረው ከሰሩ ከራሳቸው አልፈው ድጋፍ የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተቋማትንና የወረዳውን መንግስት በልማት በመደገፍ የሚበረታታ ተግባር እንደ ምፈፅሙ ምንም ጥርጥር የለውም እና ሳይታክቱ በርትተዉ ከፊታቸዉ የምገጥሙ ማንኛዉንም ተግዳሮት ተቋቁመዉ ተስፋ ባለመቁረጥ በፅናት ከሰሩ ለሌሎች ማህበራት ዓረአያ ይሆናሉ ብለዋል።

በስተመጨረሻም ኃላፊዉ በወረዳው የሚገኙ ሁሉም ወጣቶች ወደ አልተፈለገ እና አልባሌ ቦታ ውድ ጊዜአቸውን ከማዋል በመጠበቅ በማህበር በመደራጀት ጠንክረው በመስራት እራሳቸውን ቤተሰባቸውን እና ሀገራቸውን እንዲጠቅሙ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በኣሪ ዞን በባካ ዳዉላ ኣሪ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የወባ በሽታ ወረርሽኝ መከላከያ የቤት ለቤት ርጭት መርሃ ግብር በካይሣና አርክሻ ቀበሌ በይፋ ተጀመረ።    ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም       ...
19/08/2026

በኣሪ ዞን በባካ ዳዉላ ኣሪ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የወባ በሽታ ወረርሽኝ መከላከያ የቤት ለቤት ርጭት መርሃ ግብር በካይሣና አርክሻ ቀበሌ በይፋ ተጀመረ።

ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም
አርክሻ-ካይሣ

በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የወረዳዉ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አባተ ባማይ በንግግራቸዉም የወረዳችን ማህበረሰብ ከሰኔ ወር 2018 ዓ/ም ጀምሮ በወባ በሽታ ወረርሽኝ እየተፈታነነ መቆየቱን አንሰተው፤እንደ ጤና ጽ/ቤት ከተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት ጋር በመሆን የወባን ወረርሽኝ ለመከላከል ከግንዛቤ ስራዎች ጀምሮ የአከባቢ ቁጥጥር ስራዎችና የብዙሃን የህክምና ስራዎች በስፋት እየተሰራ ነው።

ቢሆንም ግን የወባ በሽታ ጫና ከህብረተሰቡ እየቀነሰ አለመሆኑን ተከትሎ ከዞንና ከክልል የዘርፉ ባለሙያዎች ጋር በቅርበት በመናበብ እንደ ወረዳ ከ6000 በላይ አባወራዎችንና ከ43000 በላይ የወረዳውን ህዝብ ከወባ በሽታ ወረርሽኝ ለመጠበቅ ታቅዶ በዛሬው እለት በካይሣና አርክሻ ቀበሌ የቤት ለቤት ኬሚካል ርጭት በሰለጠኑ የርጭት ባለሞያዎች እንደተጀመረ ገልፀዋል፤

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የባካ ዳዉላ ኣሪ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ መሠረት ቦጋለ በበኩላቸዉ የወባ በሽታ ወረርሸኝን ለመቀነስ የጽዳትና የአከባቢ ቁጥጥር ስራዎችን አመራሩ ስምርት ወስዶ ከጤና ባለሞያዎች ጋር በቅንጅት እየሰራ መቆየቱን አንስተው፤

አሁንም የበሽታውን ጫና ከህብረተሰቡ ለመቀነስ የቤት ለቤት ኬሚካል ርጭት መደረጉ ለህብረተሰቡ እፎይታን የምሰጥ እና አላስፈላጊ የህክምና ወጪን የምቀንስ በአስፈላጊ ሰዓት ላይ የተወሰነ ውሳነ በመሆኑ ለርጭት የተሰማሩ የርጭት ባለሞያዎች በኩል የህብረተሰቡን ችግር እንደ ራስ ችግር በማየት የተሰጠቸውን የህዝብ አደራ በጥንቃቄ እንድወጡ በማሳሰብ፤

የርጭቱን ተግባር ለምመሩና ለምያስተባበሩ አካላት ከጅማረ እስከ ፍጻሜ ድረስ እንድታዘዙና አንድም ኬሚካል ከታለመለት ዓላማ ውጪ ጥቅም ላይ መዋል እንደለለበት በጥብቅ በማሳሰብ የወባ በሽታ መከላከያ የቤት ለቤት ኬሚካል ርጭቱን በይፋ አስጀምረዋል።

!!

የባካ ዳዉላ ኣሪ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት

የባካ ዳዉላ ኣሪ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የወባ በሽታ ወረርሽኝ መከላከያ የቤት ለቤት ርጭት ለማካሄድ ከየቀበሌያት ለተወጣጡ የርጭት ባለሞያዎች ስልጠና መስጠቱን ገለፀ።ነሐሴ 12/2018 ዓ.ም   ...
18/08/2026

የባካ ዳዉላ ኣሪ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የወባ በሽታ ወረርሽኝ መከላከያ የቤት ለቤት ርጭት ለማካሄድ ከየቀበሌያት ለተወጣጡ የርጭት ባለሞያዎች ስልጠና መስጠቱን ገለፀ።

ነሐሴ 12/2018 ዓ.ም
አርክሻ-ካይሣ

በኣሪ ዞን በባካ ዳዉላ ኣሪ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት በወረዳው ስር በምገኙ በ12ቱ ቀበሌያት ላይ የወባ በሽታ በወረርሽኝ መልክ በመከሰቱ ምክንያት ዘርፈ ብዙ ችግሮችን እያስከተለ እንዳለ እዉን ነዉ።

ይህንን ተከትሎ የወረዳ ጤና ጽ/ቤት ወረርሽኙን ለመከላከል ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ የቆየ ብሆንም በምፈለገው ልክ የበሽታው ጫና ከህብረተሰቡ እየቀነሰ አለመሆኑን በመገንዘብ የቤት ለቤት ርጭት ለማካሄድ የወረዳ ጤ/ጽ/ቤት ዝግጅት ስያደርግ እንደቆየ የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አባተ ባማይ ገልፀዋል፤

ጽ/ቤቱ ከዚህ በፊት በግስቴና ባያሞር ቀበለያት የቤት ለቤት ርጭት ማድረጉን በመጠቆም ከነሐሴ 13/2018 ዓ/ም ጀምሮ በቀሪዎቹ 10 ቀበሌያት ላይ ከፍተኛ የወባ በሽታ ጫና ወዳለባቸው የርጭት ፕሮግራሙን ቅድሚያ ሰጥቶ እንደምጀምርም ተናግረዋል።

በዚሁ መሠረት የርጭት ፕሮግራሙ በምካሄድበት ጊዜ ማህበረሰቡ ለርጭት አስፈላጊ የምሆኑ ቅድሜ ጥንቃቄዎችን በማሟላት አስፈላጊውን ትብብር ለርጭት ባለሞያዎች እንድያደርጉ ኃላፊዉ ጥሪያቸዉን አስተላልፈዋል።

"የባ/ዳ/አ/ወ/ጤ/ጽ/ቤት"

የባካ ዳዉላ ኣሪ ወረዳ የደን ግብረ-ሃይል በተለያዩ አጀንዳዎች ዙሪያ በጋራ ተወያዩ ።      ነሐሴ 12/2018 ዓ.ም          (አርክሻ -ካይሳ)በኣሪ ዞን የባካ ዳዉላ ኣሪ ወረዳ የደ...
18/08/2026

የባካ ዳዉላ ኣሪ ወረዳ የደን ግብረ-ሃይል በተለያዩ አጀንዳዎች ዙሪያ በጋራ ተወያዩ ።

ነሐሴ 12/2018 ዓ.ም
(አርክሻ -ካይሳ)

በኣሪ ዞን የባካ ዳዉላ ኣሪ ወረዳ የደን ግብረ ኃይል በህገ ወጥ መንገድ ደን የሚወሩ አካላትን ለይቶ በህግ እንዲጠየቁ የማድረግ ስራዎች ፣ከደን ውድመት ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ ወንጀሎችን ቀድሞ ለመከላከል የተጠናከረ ክትትል እና የተጀመሩ እርምጃ የመዉሰድ ስራዎች እና ሌሎች አጀንዳዎች ዙሪያ የጋራ ውይይት አድርገዋል።

የዉይይት መድረኩ የባካ ዳዉላ ኣሪ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ መሠረት ቦጋለን ጨምሮ ሌሎች የግብረ ኃይሉ አባላት በተገኙበት ተካሂዷል።

18/08/2026

Address

በኣሪ ዞን የባካ ዳዉላ ኣሪ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት, In Aari Zone Baka Dawula Aari Woreda Government Communication Affairs
Jinka

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የባካ ዳውላ ኣሪ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share