17/08/2026
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የክረምት ወራት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ኮማንድ ፖስት የ6ኛ ሳምንት የዕቅድ ክንውን ሪፖርት ገምግሟል።
በግምገማው ወቅት ጠንካራ ውጤቶችን፣ ክፍተቶችንና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በግልጽ አስቀምጧል።
በ6ኛው ሳምንት የክልሉ አጠቃላይ አፈጻጸም ሲታይ፣ የተሳታፊዎች አፈጻጸም 70.93%፣ የተጠቃሚዎች 86.49% እና የዳነ ገንዘብ 45.28% ደርሷል።
ይህ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ለህብረተሰቡ ዘረፈ ብዙ ጠቀሜታ እየሰጠ መሆኑን የሚያመላክት ቢሆንም፣ የተሳትፎንና የሥራ ውጤትን በተገቢው የገንዘብ ዋጋ መመዝገብ አሁንም ትኩረት እንደሚሻ ያመላክታል።
በእስካሁኑ ሂደት በአረንጓዴ አሻራ ፣በጤና፣በስነ-ልቦና ድጋፍና ምክር፣ በተዋልዶ ጤና፣ የድልድይና የፍሳሽ መውረጃ ሥራዎች፣ የመንገድ ደህንነት፣ የአየር ንብረት ግንዛቤ፣ የሕይወት ክህሎትና የሙያ በጎ ፈቃድ ዘርፎች ጠንካራ አፈጻጸም አሳይተዋል።
ከ84 የውጤት አመላካቾች ውስጥ 13 ከፍተኛ፣ 42 መካከለኛ እና 29 የሚሆኑት ደግሞ ዝቅተኛ አፈጻጸም ውስጥ የሚገኙ መሆኑ በግምገማው ወቅት ተነስተዋል።
በተለይ ከ50% በታች የሆኑ የውጤት አመላካቾች የተለየ ድጋፍና ክትትል የሚፈልጉ መሆናቸው በግምገማ ወቅት ተለይቷል።
በዋናነት የምግብና አልባሳት ድጋፍ ፣ማዕድ ማጋራት ፣የአደባባይና መናፈሻ ማስዋብ፣የጽዳት አገልግሎት ፣የወጣት ማዕከላት እድሳት እና የሰዎች ዝውውር መከላከያ አደረጃጀት ቀጣይ ትኩረት የሚፈልጉ የውጤት አመልካቾች ናቸው።
በተጨማሪም የተገነቡና የታደሱ ቤቶች የXY ኮርዲኔት መረጃ አለመሟላት፣አንዳንድ መዋቅሮች ሪፖርታቸውን በአብይና ቴክኒክ ኮሚቴ ሳይገመግሙ መላካቸው እና የፌዴራል ደረጃ የቤት ግንባታ መረጃ ለክልሉ በበቂ ሁኔታ አለመድረሱ ክፍተቶች ሆነው በግምገማው ወቅት ተነስተዋል።
ቀጣዩ የአፈጻጸም ወቅት ዝቅተኛ ውጤት ያላቸውን መስኮች በተለየ ክትትል ማሻሻል፣ መካከለኛ ውጤቶችን ወደ ከፍተኛ ማሻገር እና ከፍተኛ ውጤቶችን ማስቀጠል ላይ ትኩረት እንደሚደረግም ተብራርተዋል።
በተለይ ምግብና አልባሳት ድጋፍ፣ ማዕድ ማጋራት፣ አደባባይና መናፈሻ ማስዋብ፣ ጽዳት፣ የሰዎች ዝውውር መከላከያ ስራ፣ የትራፊክ ምልክት/ዜብራ፣ የወጣት ማዕከል እድሳትና ግብዓት እና የመማሪያ ግብአቶች ድጋፍ በቀጣይ ልዩ ድጋፍና ክትትል የሚፈልጉ ዋና የትኩረት መስኮች ናቸው።
እንዲሁም በወጣቶች የቴክኖሎጂና ክህሎት ልማት ላይ ትኩረት መጨመር፣ የኢትዮ-ኮደርስና የሙያ አገልግሎቶችን ማጠናከር እና ለወጣቶች የሥራ አቅም ግንባታ ልዩ በጀትና ክትትል ማድረግ እንደሚገባ ተገልፆል።