የኣሪ ዞን ገቢዎች መምሪያ/ Aari Zone Revenue Department

  • Home
  • Ethiopia
  • Jinka
  • የኣሪ ዞን ገቢዎች መምሪያ/ Aari Zone Revenue Department

የኣሪ ዞን ገቢዎች መምሪያ/ Aari Zone Revenue Department ይህ ፔጅ የኣሪ ዞን ገቢዎች መምሪያ ሲሆን ፔጁ የተከፈተበት ምክንያት ከግብር ጋር ተያይዞ ወቅታዊ እና እዉነተኛ መረጃዎችን በተቀላጠፈ መንገድ ለማስተላለፍ ነው

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉውድ የቢሯችን አመራሮች፣ መላው የገቢዎች ባለሙያዎች እና የክልላችን ግብር ከፋዮች! ...
07/09/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ውድ የቢሯችን አመራሮች፣ መላው የገቢዎች ባለሙያዎች እና የክልላችን ግብር ከፋዮች!

በመጀመሪያ በ2018 በጀት ዓመት በተለያዩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ኢኒሼቲቮች በተደረገው ከፍተኛ እንቅስቃሴና በተመዘገበው የላቀ የሥራ አፈጻጸም፣ ተቋማችን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ የክልሉ ከፍተኛ የእውቅና ሽልማትና የመኪና ተሸላሚ በመሆኑ የተሰማኝን ወሰን የሌለው ደስታና ኩራት ለመግለጽ እወዳለሁ።

ይህ ድል በአጋጣሚ የተገኘ ሳይሆን፣ የመላው የተቋማችን ሰራተኞች እና አመራሮች የቀን ከሌሊት የጽናት፣ የትጋትና የተቀናጀ ሥራ ግልጽ ጥረት ውጤት ነው። በየደረጃው የሚገኙ የመዋቅራችን አባላት ያለመታከት ያሳያችሁት የባለቤትነት ስሜት፣ ከፍተኛ የሙያ ሥነ-ምግባር እና ለአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ያደረጋችሁት ያልተቆጠበ ጥረት ለዚህ ታላቅ ስኬት አብቅቶናል።

በተጨማሪም የዚህ ታላቅ ስኬት ባለቤቶች የሆናችሁ፦

👉 ታማኝ ግብር ከፋዮቻችን የክልላችንን ልማትና እድገት በመደገፍ ግብራችሁን በወቅቱና በትክክል በመክፈል የዜግነት ግዴታችሁን ስለተወጣችሁ ፤

👉 ባለድርሻ አካላትና የክልሉ ስለተወጣች ለተቋማችን ስኬት አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ስላደረጋችሁልን፤

ላቀረባችሁልን ድጋፍና ላሳያችሁት አጋርነት በቢሮዬ እና በራሴ ስም የላቀ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

ውድ የሥራ ባልደረቦቼ!

ይህ የተሰጠንም ከፍተኛ እውቅና እና የሽልማት ተሽከርካሪ ያለፉ ስኬቶቻችን ማክበሪያ ብቻ ሳይሆን፣ ለቀጣዩ የ2019 በጀት ዓመት የበለጠ እንድንሰራ፣ የተቀመጡ የገቢ እቅዶችን አበልጽገን እንድናሳካ እና ዘመናዊና ፍትሃዊ የገቢ አሰባሰብ ስርዓትን አጠናክረን እንድንቀጥል የተጣለብን ትልቅ ኃላፊነትና የቤት ሥራ ነው።

በቀጣይም ይህንን የተከበሬ የላቀ አፈጻጸም ባህል አድርገን በመቀጠል፣ ለክልላችን ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ለህዝባችን ተጠቃሚነት በጋራና በጠንካራ መንፈስ እንደምንሰራ ሙሉ እምነት አለኝ።

በድጋሚ እንኳን ደስ አለን!

ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ

07/09/2026
የክልሉ መንግስት በ 2018 የበጀት ዓመት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ሴክተር ቢሮዎች እዉቅና ሰጥቷልጳጉሜን 02/2018 ዓ.ምየደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በ 2018 የበጀት ዓመት የላቀ ...
07/09/2026

የክልሉ መንግስት በ 2018 የበጀት ዓመት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ሴክተር ቢሮዎች እዉቅና ሰጥቷል

ጳጉሜን 02/2018 ዓ.ም

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በ 2018 የበጀት ዓመት የላቀ ዉጤት ላስመዘገቡ ሴክተር ቢሮዎች እዉቅና ሰጥቷል።

በዚህም መሠረት፦

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ፣ ፋይናንስ ቢሮ፣ ፕላን ቢሮ፣ ገቢዎች ቢሮ፣ የመስኖና ቆላማ አከባቢዎች ልማት ቢሮ፣ ጤና ቢሮ እና ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮዎች ተሸላሚ ሆነዋል።

የክልሉ ገቢዎች ቢሮ በበጀት ዓመቱ ባስመዘገበው የላቀ አፈፃፀም ልዩ ተሸላሚ በመሆን መኪና ተሸልሟል።

የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገብረመስቀል ጫላ ሽልማቱን ለተሸላሚ ሴክተር ቢሮዎች ሰጥተዋል።

ደረሰኝ አለመሰጠት (ወይም አለመቀበል) በሀገር ኢኮኖሚ፣ በሸማቹ እና በነጋዴው ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል። 1. በሀገር እና በሕዝብ ላይ የሚደርስ ጉዳት👉የታክስ ገቢ ማጣት፦ መንግሥት ለሕዝ...
07/09/2026

ደረሰኝ አለመሰጠት (ወይም አለመቀበል) በሀገር ኢኮኖሚ፣ በሸማቹ እና በነጋዴው ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል።

1. በሀገር እና በሕዝብ ላይ የሚደርስ ጉዳት

👉የታክስ ገቢ ማጣት፦ መንግሥት ለሕዝብ አገልግሎት (ለምሳሌ ለትምህርት ቤት፣ ለጤና፣ ለሕክምና እና ለሕዝብ መሠረተ ልማት) የሚጠቀምበትን የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እና ሌሎች ቀረጥ ማሰባሰብ እንዳይችል ያደርጋል።
👉የሕገ-ወጥ ንግድ መስፋፋት፦ ደረሰኝ የማይሰጡ ነጋዴዎች ገቢያቸውን ስለሚደብቁ ኮንትሮባንድ እና ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር እንዲስፋፋ በር ይከፍታል።

2. በሸማቹ (በገዢው) ላይ የሚደርስ ጉዳት

👉የዋስትና መብት ማጣት፦ የተገዛው ዕቃ ቢበላሽ ወይም ጉድለት ቢገኝበት፣ ደረሰኝ ከሌለ ዕቃውን ለመቀየር ወይም ገንዘብ ለማስመለስ ሕጋዊ ማስረጃ አይኖርም።
👉ለማጭበርበር መጋለጥ፦ ነጋዴው የተጋነነ ዋጋ ቢጠይቅ ወይም ጥራት የሌለው ዕቃ ቢሸጥ፣ ሸማቹ መብቱን ለማስከበር እና አቤቱታ ለማቅረብ ይቸገራል።

3. በነጋዴው ላይ የሚደርስ ጉዳት

👉የሕግ ተጠያቂነት እና ከባድ ቅጣት፦ ደረሰኝ አለመስጠት በኢትዮጵያ የታክስ ሕግ መሠረት የወንጀል ድርጊት ነው። ደረሰኝ ሳይሰጡ መገኘት እስከ ከባድ የገንዘብ መቀጮ እና የእስራት ቅጣት ሊያደርስ ይችላል።
👉ፍትሐዊ ያልሆነ ውድድር፦ ሕጋዊ ነጋዴዎች ታክስ ከፍለው ሲሸጡ፣ ደረሰኝ የማይሰጡት ግን ታክስ ስለማይከፍሉ ገበያውን ያዛባሉ። ይህ ደግሞ በታማኝ ነጋዴዎች ላይ ጉዳት ያደርሳል

07/09/2026
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእመርታ ቀን መልዕክት *******ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጳጉሜን 1 ቀን የእመርታ ቀንን በማስመልከት ባስተላለፉት መልዕክት አባቶ...
07/09/2026

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእመርታ ቀን መልዕክት
*******

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጳጉሜን 1 ቀን የእመርታ ቀንን በማስመልከት ባስተላለፉት መልዕክት አባቶቻችን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በደምና በአጥንታቸው አስከብረው ታላቅ ሀገር አውርሰውናል ብለዋል።

ዛሬ ደግሞ እውነተኛ ሉዓላዊነትን እያረጋገጥን ያለነው ከልመናና ከጥገኝነት በተላቀቀው አዲሱና ታሪካዊው መንገዳችን ነው ሲሉ ገልጸዋል።

በሚሊዮን በሚቆጠር ዶላር ስንዴ ከማስገባት ተነስተን ዛሬ የአፍሪካ ቀዳሚ ስንዴ አምራች በመሆን የሚሊዮን ዶላሮችን ወጪ ማስቀረት ችለናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ«ሌማት ትሩፋት» የምግብ ዋስትናን በተግባር እያረጋገጥን፣ በ«ኢትዮጵያ ታምርት» ንቅናቄም አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋትና የሥራ ዕድል በመፍጠር ሉዓላዊነታችንን እያረጋገጥን እንደምንገኝ አስታውሰዋል።

ከዚህ ቀደም የማይደፈሩና አይነኬ ይባልላቸው የነበሩ ከባድ የማክሮ-ኢኮኖሚ ሪፎርም ውሳኔዎችን በቁርጠኝነት በመተግበር፤ የሀገራችንን ኢኮኖሚ በፅኑ መሠረት ላይ እየገነባን እንገኛለን።

እነዚህ ሁሉ ታላላቅ ድሎች ኢትዮጵያ በሚያጋጥሟት ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች ሸብረክ ሳትል በፅናት መጓዝ መቻሏን የሚያረጋግጡ ህያው ምስክሮች ናቸው፤ ይህ የእመርታ ጉዟችን ለመጪው ዓመት የሰነቀው ተስፋ እጅግ ግዙፍ ነው ብለዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ከቢሊዮን ወደ ትሪሊዮን የኢትዮጵያ የገቢ አሰባሰብ ታሪካዊ እመርታ በጳጉሜን 1 የእመርታ ቀን ሲቃኝጷግሜን 1/2018 ዓ.ምሀገራችን ኢትዮጵያ የ13ኛዋ ወር ጳጉሜን የመጀመሪያ ቀን በሆነው የእ...
06/09/2026

ከቢሊዮን ወደ ትሪሊዮን የኢትዮጵያ የገቢ አሰባሰብ ታሪካዊ እመርታ በጳጉሜን 1 የእመርታ ቀን ሲቃኝ

ጷግሜን 1/2018 ዓ.ም

ሀገራችን ኢትዮጵያ የ13ኛዋ ወር ጳጉሜን የመጀመሪያ ቀን በሆነው የእመርታ ቀን የሁለንተናዊ እድገቷን ፍሬዎች እና የተመዘገቡ ታሪካዊ ስኬቶችን በጋራ ታከብራለች።

ከእነዚህም የልማት እና የብልጽግና ስኬቶች መካከል በለውጥ ዓመታት የታየው የግብር አሰባሰብ ሥርዓት ከቢሊዮን ወደ ትሪሊዮን ብር ማደግ የሀገራችንን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትና የፋይናንስ ነፃነት ማረጋገጫ ታላቅ እመርታ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ2018 በጀት ዓመት ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ ባለፉት 27 ዓመታት በአጠቃላይ የሰበሰበችው ገቢ 1 ትሪሊዮን ብር እንኳን የማይሞላ የነበረ ቢሆንም፣ በ2018 በጀት ዓመት ብቻ ግን 1.5 ትሪሊዮን ብር ገቢ በመሰብሰብ ከ150% በላይ ታሪካዊ ብልጫ ያለው እመርታ ማስመዝገብ ተችሏል።

ይህ በምርት ቀን የምናከብረው ታሪካዊ ሽግግር የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማስፋፋት፣ የግብር ህጎችን በማሻሻል እና የታክስ መሠረቱን በማስፋት የተገኘ ታላቅ ውጤት ነው።

ግብር ከፋዮች በአካል ሳይገኙ በይነመረብን በመጠቀም ግብራቸውን የሚያስታውቁበትና የሚከፍሉበት የዲጂታል ታክስ ሥርዓት በመዘርጋቱ የታክስ ስወራን እና የቢሮክራሲ እንግልትን በእጅጉ መቀነስ ተችሏል።

በተጨማሪም አዳዲስ የንግድ ዘርፎችን ወደ ግብር ሥርዓቱ በማስገባትና ግብር መክፈል የሀገር ፍቅር መገለጫ ነው የሚል ባህል እንዲዳብር በማድረግ ሰፊ የገቢ መሠረት ተጥሏል።

የግብር ገቢ ከቢሊዮን ወደ ትሪሊዮን ማደጉ እንደ የኮሪደር ልማት፣ የትምህርትና ጤና መሰረተ ልማቶች እንዲሁም የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን የመሳሰሉ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን በራስ አቅም ለመሸፈን የሚያስችል አቅም በመፍጠሩ የጳጉሜን 1 የእመርታ ቀን አዲሱን የኢትዮጵያ የብልጽግና ምዕራፍ በግልጽ ያበስራል።

ምንጭ:- ኢቢሲ

«ሲሸጡ ደረሰኝ ይስጡ፣ ሲገዙ ደረሰኝ ይቀበሉ!» የሚለው መልዕክት የወቅታዊ ግብይት መመርያ ብቻ ሳይሆን ህጋዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ያለው አሰራር ነው።ለገዢው:- የገዙት እቃ ህጋዊ ባለቤት መሆ...
05/09/2026

«ሲሸጡ ደረሰኝ ይስጡ፣ ሲገዙ ደረሰኝ ይቀበሉ!» የሚለው መልዕክት የወቅታዊ ግብይት መመርያ ብቻ ሳይሆን ህጋዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ያለው አሰራር ነው።

ለገዢው:- የገዙት እቃ ህጋዊ ባለቤት መሆንዎን ያረጋግጣል፤ እቃው ቢበላሽ ወይም ጉድለት ቢኖረው ለመቀየርና ዋስትና ለመጠየቅ ማስረጃ ይሆናል።

ለሻጩ:- ትክክለኛና ህጋዊ ነጋዴ መሆንዎን ያሳያል፤ በሂሳብ አያያዝ ወቅት ከታክስ አካላት ጋር የሚኖርን ግንኙነት ጤናማ ያደርጋል።

ለሀገር:- ተገቢው ግብር ለሀገር ገቢ እንዲሆን በማድረግ የልማት ስራዎችን ያፋጥናል።

ህጋዊ አሰራርን በመከተል ደረሰኝ በመስጠትና በመቀበል ራሳችንንም ሆነ ሀገራችንን እንጠብቅ!

በበጀት ዓመቱ ከግማሽ ቢልዮን  ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዷል።✅✅ ነሐሴ ፦ 29/2018ዓ.ም (ጂንካ)➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖የጁንካ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት "የ2018 ዕቅድ አፈፃ...
04/09/2026

በበጀት ዓመቱ ከግማሽ ቢልዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዷል።

✅✅ ነሐሴ ፦ 29/2018ዓ.ም (ጂንካ)
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
የጁንካ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት "የ2018 ዕቅድ አፈፃፀም እና 2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የግምገማ መድረክ አካሄዷል ።

የዕለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት የጂንካ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ አቶ ደግፌ ጌታቻው "የከተማው ገቢ የመሰብሰብ አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱ እንደ በጎ ጎን በመጥቀስ በ2018 በጀት ዓመት ለዘመናት የህዝባችን ጥያቄ የነበረዉ የማብራት መሰረተ ልማት በውስጥ ገቢ ሰብስበን መክፈላችን ፤ አዲስ የትምህርት ቤት ግንባታ በባይጽማል ቀበሌ መጀመራችን ለህዝባችን ጭላንጭል ልማቶችን ማበርከታችን አይነተኛ ማሳያ ቢሆንም የልማት ጥያቄዎች በርካታ መሆናቸው ህግን በተከተለ መንገድ ገቢን መሰብሰብ የህዝባችንን የልማት ጥያቄዎች በዘላቂነት ለመመለስ ይረዳናል ብለዋል።

በ2018 በጀት ዓመት ዝቅተኛ አፈፃፀም ያስመዘገብንባቸዉ ተግባሮችን በመለየት ስንጥቆችን በአፋጣኝ በመደፈን ለውጥ ማምጣት ይጠበቅብናል ሲሉም አክለዋል።

የገጠር መሬት ገቢ አሰባሰብ፤ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ክፍያዎች፤ እንዲሁም ሌሎች የመደበኛ ስራዎችን በትጋት በመፈፀም መስራት እንደሚገባ ክብሩ ከንቲባው አሳስበዋል።

የጂንካ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ ቤት ሀላፊ አቶ ማንጎ ከበደ በ2018 በጥንካሬ የተለዮ ጉዳዮችን በማስቀጠል ጉድለቶችን በማረም በ2019 የተጣለውን ዕቅድ ለማሳካት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አመላክተዋል።

እንደ ኃላፊው ገለፃ የበጀት ዓመቱን ገቢ ለመሰብሰብ ከተጨማሪ ዕሴት ታክስ ፣ ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች ፣ ቀጥታ ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች ፣ ከገጠር መሬት መጠቀሚያ ኪራይ ግብር እና ከ እርሻ ስራ ገቢ ግብር ፣ ከጤና ፣ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች የሰራተኛ ስራ ገቢ፣ ከግል ተቋማቶችና እንድሁም ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ክፍያዎች ፤ ከመሬት እና ከመሬት ነክ ገቢዎች ከመሳሰሉት የገቢ ርዕሶች ለመሰብሰብ መታቀዱን ኃላፊው ገልጸዋል ።

መንግስት ህብረተሰቡንና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ በሚያከናውነው የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ውስጥ ከግብር/ታክስ የሚሰበሰበው ገቢ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለውም አቶ ማንጎ ተናግረዋል።

ለውይይት መነሻ የሚሆን ሰነድ ያቀረቡት የታክስ ኦፕሬሽን ዳይሬክቶረት አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ ደልቦሌ ያቀረቡ ሲሆን
የ2019 በጀት ዓመት የመደበኛ ገቢ ዕቅድ 5 መቶ 91 ሚሊየን 817 ሺህ 380 ገቢ ለመሰብሰብ የታቀደ ሲሆን የማዘጋጃ ገቢ ዕቅድ 87 ሚሊየን 136 ሺህ 820 ገቢ ይሰበሰባል ተብሎ ታቅዷል።

በአጠቃላይ 6 መቶ 85 ሚሊየን 553 ሺህ 303 ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን ከተሰነደዉ ሰነድ ለመረዳት ተችሏል።

በ2018 የተሻለ የፈፀሙ የቀበሌ ስራ አስኪያጆች ፤ ባለድርሻ ተቋማት፤ እንድሁም ባለሙያዎች የማበረታቻ እና የዕዉቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ።

ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም፣ ጂንካበኣሪ ዞን የጂንካ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ የንቅናቄ መድረክ የከተማዉ ከንቲባ ...
04/09/2026

ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም፣ ጂንካ

በኣሪ ዞን የጂንካ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ የንቅናቄ መድረክ የከተማዉ ከንቲባ በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የከተማዉ ዋና አፌ ጉባኤን ጨምሮ አስተባባሪ ኮሚቴዎች፣
አጠቃላይ አመራሮች፣ የገቢ ባለድርሻ አካላት እና የቀበሌ ሊቀ-መናብርት እንዲሁም የከተማዉ ገቢ ጽ/ቤት ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

"የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ" ሰነድ በከተማዉ ገቢዎች ጽ/ቤት የታክስ ኦፕሬሽን ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ ደልቦሌ እየቀረበ ይገኛል።
ሰነዶቹን መሰረት አድርጎ ጥልቅ ዉይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

Address

Mehal Arada
Jinka

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የኣሪ ዞን ገቢዎች መምሪያ/ Aari Zone Revenue Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share