South Ethiopia Regional State Health Bureau

South Ethiopia Regional State Health Bureau ይህ የደቡብ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ትክክለኛው የፌስቡክ ገጽ ነው!
(1)

04/09/2026
04/09/2026
04/09/2026
የምግብና የጤና ግብዓት ቁጥጥር የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃጸም ግምገማ መድረክ ተሳታፊዎች በአርባ ምንጭ ከተማ የእግር ጉዞ አካሄዱ። ነሐሴ 28/2018 ጤና ቢሮ ኮሚኒኬሽን| ጂንካ___...
04/09/2026

የምግብና የጤና ግብዓት ቁጥጥር የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃጸም ግምገማ መድረክ ተሳታፊዎች በአርባ ምንጭ ከተማ የእግር ጉዞ አካሄዱ።

ነሐሴ 28/2018 ጤና ቢሮ ኮሚኒኬሽን| ጂንካ
____________

የጉባኤው ተሳታፊዎች ከአርባ ምንጭ ከተማ ባህል ማዕከል እስከ ሲቻ አደባባይ የእግር ጉዞ ያደረጉ ሲሆን፥ በዚሁ ወቅት በከተማው አስተዳደር የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን መመልከት ችለዋል፡፡

ከዓመታት በፊት በዚሁ ከተማ ተመሳሳይ የምግብና የጤና ግብዓት ቁጥጥር እቅድ አፈፃጸም ግምገማ መድረክ መካሄዱን ያስታወሱት ተሳታፊዎቹ፥ የዘንድሮውን ልዩ የሚያደርገው ከተማዋን ለነዋሪዎቿና ለጎብኚዎች ይበልጥ ምቹ የሚያደርጉ የመሰረተ-ልማት ዝርጋታዎች በጥራትና በስፋት የተከናወኑበት በመሆኑ የተለየ ስሜት እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል፡፡(EFDA)

ገዳይ የሆነ የወባ በሽታን ለመከላከል የህብረተሰቡ ድርሻ የጎላ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮና ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት አስታወቀ፡፡ድጋፍና ክትትልን አጠናክሮ ባለማቋረጥ በመስራት ድንገተኛ ክስ...
04/09/2026

ገዳይ የሆነ የወባ በሽታን ለመከላከል የህብረተሰቡ ድርሻ የጎላ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮና ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት አስታወቀ፡፡

ድጋፍና ክትትልን አጠናክሮ ባለማቋረጥ በመስራት ድንገተኛ ክስተትና ጤና ተግባራትን ማሻሻል ተችሏል፡፡

በሣምንት 5ኛ ቀን የድንገተኛ አደጋዎች ቁጥጥር ማዕከል በIMS ወረዳዎች የወባ በሽታ ወረርሽኝ እና የተወሳሰበ ሥርዓተ ምግብ በሽታ ተግባር አፈፃፀም ገምግመዋል፡፡

ነሐሴ 29/2018 ጤና ኮሚኒኬሽን ዳሬክቶሬት | ጂንካ
———————

የIMS ወረዳዎች የወባ ወረርሽኝ እና የተወሳሰበ ሥርዓተ ምግብ በሽታ ተግባር አፈፃፀም ሪፖርት በአቶ ይታገሱ በላይ ቀርቧል፡፡

ድንገተኛ ክስተት አስተዳደር ሥርዓቱን በማጠናከር በየመዋቅሩ የተከሰቱ የወባ እና ሥርዓተ ምግብ ችግርን ለማስቀረት በተደረገው ርብርብ የተገኘውን ውጤት ማስቀጠል እንደሚገባ ምክትል ጤና ቢሮ ኃላፊው አስታወቁ፡፡

ምክትል ጤና ቢሮ ኃላፊና ጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ መና መኩሪያ እንዳስታወቁት የተወሳሰበ ህፃናት ሥርዓተ ምግብ አለመመጣጠን ችግሩ በበዓላት ወቅት መዘናጋቶች እንዳይኖር ከወዲሁ ጤና መዋቅሮች ትኩረት እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

በክልል የተለዩ እና የተወሳሰበ ሥርዓተ ምግብ አለመመጣጠን በሽታ ያለባቸው ወረዳዎች ከፍተኛ መሻሻሎችን ያስመዘገቡ ሲሆን፤ ተጨማሪ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ወረዳዎችን በመለየት ለውጤት መስራት እንደሚገባ አቶ መና አስታውቀዋል፡፡

በማዕከሉ የዘርፉ ባለሙያዎች አስተያየት የሰጡ ሲሆን መሻሻሎች ያለባቸውን እና ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው መዋቅሮችን ለይተው አስታውቀዋል።

መሻሻሎች የታየባቸው መዋቅሮች በማጠናከር የቁጥጥር ተግባራትን በማስቀጠል ለማህበረሰቡ ጤና የበለጠ መስራት እንደሚገባ የክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ምክትል ዳይሬክተር አቶ አሳምነው አይዛ አስታውቀዋል፡፡

ከአከባቢ ቁጥጥር አንፃር በሁሉም አከባቢዎች በጥንካሬ የተሰሩ ሥራዎች ቢኖርም፤ ተግባሩን ያልጨረሱ መዋቅሮች እንዲጨርሱ አቶ አሳምነው አሳስበዋል፡፡

የሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ምንተስኖት መልካ በበኩላቸው ዞኖች የIMS ወረዳዎች ላይ ቁጥጥሩን ከዚህ በበለጠ ማጠናከር ይገባል ብለዋል፡፡

ዶ/ር ምንተስኖት ጨምረው የህፃናትን ሞት ለማስቀረትና ጤናቸውን ለማስጠበቅ ህብረተሰቡ ኃላፊነቱን በመወጣት ወረዳዎች እና ዞን ጤና መዋቅሩ ቅንጅቱን እንዲያጠናክርና፤ ከክልል የወረደው የክትትል ቡድን ጋር በመተባበር የጤና አገልግሎት ስርዓቱን ማጠናከር ይገባል ብለዋል፡፡

ምክትል ጤና ቢሮ ኃላፊና ጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ መና መኩሪያ፤ ተለይተው በጤና አመራሮች የሚደገፉና ዝቅተኛ አፈፃፀም ያስመዘገቡ መዋቅሮች በህፃናት ጤና ላይ ትኩረት በማድረግ የተወሳሰበ ሥርዓተ ምግብ በሽታን መቆጣጠር እንዲቻል አሳስበዋል፡፡

በክልሉ የተሸለ የጤና ሥርዓት እንዲገነባ በማድረግ ዞን ጤና መዋቅሮች ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ አቶ መና መክረው፤ በበዓላት ወቅት ባለመዘናጋት ለህፃናት ጤና እና ወባ ቁጥጥር ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ላቦራቶሪ አዲስ የምርመራ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።የክልሉ ጤና ቢሮና ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት አገልግሎቱ በቅርበት ለህብረተሰቡ መስጠት...
03/09/2026

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ላቦራቶሪ አዲስ የምርመራ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

የክልሉ ጤና ቢሮና ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት አገልግሎቱ በቅርበት ለህብረተሰቡ መስጠት በመጀመሩ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

ነሐሴ 28/2018 ጤና ቢሮ ኮሚኒኬሽን | ጂንካ
________

የአርባ ምንጭ የህብረተሰብ ጤና ላቦራቶሪ የሄፓታይተስ ቢ (HBV) እና ሄፓታይተስ ሲ (HCV) Viral Load ምርመራ በዘመናዊ ማሽኖች አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

ሄፓታይተስ ቢ (HBV) እና ሄፓታይተስ ሲ (HCV) ቫይረስ የጉበት በሽታ አምጪ ቫይረሶች ሲሆኑ፤ ሥር የሰደደ የጉበት በሽታ፣ የጉበት ጠባሳ (cirrhosis) እና የጉበት ካንሰር ሊያስከትሉ የምችሉ ተዋሲያን መመርመር የሚያስችል አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የአርባ ምንጭ የህብረተሰብ ጤና ላቦራቶሪ አስተባባሪ አቶ ከበደ ሙሊሳ አስታውቋል።

ዜጎች ለጤና መጠበቅ በወቅቱ መመርመርና የሕክምና ክትትል ማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለዉ በመሆኑና፤ ምርመራ አገልግሎት በአርባምንጭ መጀመሩን አቶ ከበደ አስታውቀዋል።

በክልሉ የቫይራል ሄፓታይተስ ምርመራና የታካሚዎች የሕክምና ክትትል አቅምን ለማጠናከር ወሳኝ ስኬት መሆኑንም አስተባባሪው አስታውቀዋል።

የHBV እና HCV Viral Load ምርመራ በመጀመሩ ሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች ናሙና ተሰብስቦ በተገቢው ሁኔታ ወደ ማዕከሉ በማድረስ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲትሆኑም የአርባ ምንጭ የህብረተሰብ ጤና ላቦራቶሪ ጥሪ ያቀርባል።

የህብረተሰቡን ጤና በተሻለ ሁኔታ ለመጠበቅ የቁጥጥር ሥርዓቱን አጠናክረው እየሰሩ መሆናቸውን የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ። በ250 የመድሃኒት አከፋፋይ ድርጅቶች ...
03/09/2026

የህብረተሰቡን ጤና በተሻለ ሁኔታ ለመጠበቅ የቁጥጥር ሥርዓቱን አጠናክረው እየሰሩ መሆናቸውን የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።

በ250 የመድሃኒት አከፋፋይ ድርጅቶች ላይ የእርምት እርምጃ መወሰዱ ተገልጿል።

ባለስልጣኑ በ2018 የበጀት ዓመት በተከናወነው ተግባራትና በቀጣይ የበጀት ዓመት ትኩረት በሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

ነሐሴ 28/2018 ጤና ቢሮ ኮሚኒኬሽን | ጂንካ
___________

ጋዜጣዊ መግለጫውን የሰጡት የኢትዮጵያ ምግብ መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ሄራን ገርባ የዜጎችን ጤና በተሻለ መልኩ ለመጠበቅ እንዲቻል የተለያዩ ስርዓቶች ተዘርግተው እየተተገበሩ ነው ብለዋል።

የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ ጥራታቸውና ደህንነታቸው የተጠበቁ መድሃኒቶችን ለዜጎች ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባም ዋና ዳይሬክተሯ በመግለጫቸው ጠቁመዋል።

በምግብና መድሃኒት ዘርፍ የቅድመና ድህረ ገበያ ቁጥጥር በማጠናከር ከ233 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ጊዜያቸው ያለፈባቸውን መድሃኒቶች ማስወገዳቸውን ጠቁመዋል ።

የጤና ልማት ዕቅዱን ለማሳካት የጤና ቁጥጥር ዘርፍ የህግ፣ዲጂታል ስርዓት፣መሰረተ ልማትና አደረጃጀት ማሻሻያ እንዲሁም በመግቢያና መውጫ ኬላዎች ቁጥጥር ማጠናራቸዉንም አስረድተዋል ።

አሰራሮች እንዲዘምኑ ዘርፈ ብዙ የጥራትና የቁጥጥር መሰረተ ልማቶች ተዘርግተው እየተተገበሩ እንደሆነም ዋና ዳይሬክተሯ አሳዉቀዋል።

በ2018 በጀት ዓመት ለ1939 መድኃኒት ቤቶች የንግድ ፈቃድ ስለ መሰጠቱ ጠቁመው፣ከእነዚህ ውስጥ 818 አዲስ የገበያ ንግድ ፈቃድ አግኝተዋል ብለዋል።

የትምባሆ ማጨስ በተከለከለባቸው 107 ሺህ 240 ተቋማት ላይ የቁጥጥር ሥራ መከናወኑን ገልፀው፣ የጤና ማስጠንቀቂያ መኖሩ በተመለከተ የቁጥጥር ስራ ተሰርቷል፡፡

በተጨማሪም በ554 አምራቾች እና በ1509 አስመጪና አከፋፋይ ተቋማት ላይ ስጋት ተኮር ድህረ-ፈቃድ ኢንስፔክሽን የማድረግ ስራ ስለ መሰራቱ አብራርተዋል ።

ወደ አገር ውስጥ የገቡ ምግቦች አስፈላጊው የጥራትና ደህንነት ቁጥጥር ተደርጎላቸው የመልቀቂያ ፈቃድ ከተሰጣቸው መካከል ከ2ሚሊዮን 827 ቶን በላይ የምግብ ምርቶች እንደሚገኙ ጠቁመዋል ።

በሀገር ውስጥ የሚያመረቱ የምግብ ነክ ምርቶች ምርታቸውን በየትኛውም ገበያ እንዲያቀርቡ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሯ በመግለጫቸው ገልጸዋል ።

የምግብና የጤና ግብዓት የቁጥጥር ስራዎች መጠናከራቸዉ የማህበረሰቡን ጤና የተሻለ እንዲሆን ማስቻሉን የኢትዮጵያ ምግብ መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።ነሐሴ 28/2018 ጤና ቢሮ ኮሚኒኬ...
03/09/2026

የምግብና የጤና ግብዓት የቁጥጥር ስራዎች መጠናከራቸዉ የማህበረሰቡን ጤና የተሻለ እንዲሆን ማስቻሉን የኢትዮጵያ ምግብ መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።

ነሐሴ 28/2018 ጤና ቢሮ ኮሚኒኬሽን| ጂንካ
———————

ባለስልጣኑ የምግብና የጤና ግብዓት ቁጥጥር የ2018 የበጀት አመት ዕቅድ አፈፃፀምና የ2019 ዕቅድ ላይ ያተኮረ ጉባኤ በአርባምንጭ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

በወቅቱ መልዕክት ያስተላለፉት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና ማህበራዊ ልማትና የባህልና ስፖርት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወርቀሰሙ ማሞ የባለስልጣኑ ዋነኛ ተልዕኮ የህብረተሰቡን ጤና መጠበቅ መሆኑን ገልጸዋል ።

ይህንኑ ውጤታማ ለማድረግ በባለስልጣኑ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን አድንቀዋል።

ጥራታቸውና ደህንነታቸው የተጠበቁ መድሃኒቶች ለህዝቡ ተደራሽ እንዲሆኑ የተጀመሩ ተግባራት እንዲጠናከሩ ወ/ሮ ወርቀሰሙ አሳስበዋል ።

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ እንዳሻው ሽብሩ በበኩላቸው መንግስት አምራችና የበለፀገ ዜጋ ተፈጥሮ የማየትን ራዕይ ለማሳካት በጤና ዘርፍ ልዩ ትኩረት ሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን አስገንዝበዋል ።

የጤና አገልግሎት ተቋማትን ደረጃ ማሻሻል ለዘርፉ ውጤታማነት አስፈላጊ መሆኑን ቢሮ ኃላፊው እንዳሻው ጠቁመዋል ።

በክልሉ ለዜጎች ጤንነትና ደህንነት ጠንቅ የሆኑ ህገወጥ የምግብና የመድኃኒት ምርቶች ገበያ ላይ እንዳይውሉ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን የቢሮ ኃላፊው አስገንዝበዋል

የኢትዮጵያ ምግብ መድኃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ በበኩላቸው የባለፈው በጀት አመት የምግብና የጤና ግብዓት ቁጥጥር ስራዎች ውጤታማ እንደነበሩ ገልጸዋል ።

የምግብና የጤና ግብዓት የቁጥጥር ስራዎች መጠናከራቸዉ የማህበረሰቡን ጤና የተሻለ እንዲሆን ማስቻሉን ዳይሬክሯ ጠቁመዋል ።

በቀጣይም በጤና ዘርፍ የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲቻል አሠራሮችን ዲጂታላይዝ በማድረግ ዜጎች በአንድ ማዕከል አገልግሎት እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና ጤናና ጤና ነክ ጉዳዮች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ሶንቆ፣በክልሉ የጤና ግብዓቶች በተገቢው መንገድ ለውጤታማነቱ እንዲውል እየሰራ ነው ብለዋል።

በመድረኩ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጨምሮ ለሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

የበጎነት ተግባራትን በማስፋፋት አቅመ ደካማ ወገኖችን የመደገፍ ባህል ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ።የክልሉ ጤና ቢሮ ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመተባበር ለሁለት...
03/09/2026

የበጎነት ተግባራትን በማስፋፋት አቅመ ደካማ ወገኖችን የመደገፍ ባህል ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ።

የክልሉ ጤና ቢሮ ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመተባበር ለሁለት አቅሜ ደካማ እናቶች ዘመናዊ መኖሪያ ቤት ግንባታ አስጀምረዋል።

ነሐሴ 28/2018 ጤና ቢሮ ኮሚኒኬሽን | ጂንካ
____________

የክልሉ ጤና ቢሮ ከህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ጋር በመቀናጀት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በደቡብ ኦሞ ዞን በና ጸማይ እና በማሌ ወረዳ ቃቆና በነታ ማዘጋጃ ቤቶች ለሚገኙ ሁለት አቅመ ደካማ እናቶች በብሎኬት ዘመናዊ ቤት የማስገንባት ሥራ በይፋ አስጀምረዋል።

የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና ጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ መና መኩሪያ መንግስት ለዜጎች ክብር የሰጠውን ሰው ተኮር ተግባርን ተግባራዊ እያደረጉ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በማይመች ኑሮ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ወገኖችን በመለየትና በመደገፍ የተጀመረው በጎነት የአከባቢው ማህበረሰብ እንዲያስቀጥል አቶ መና ጠይቀዋል።

የክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አጉኔ አሾሌ በበኩላቸው በመተባበር የክረምቱን የበጎ ፈቃድ ስራዎች በማስፋት ለአቅሜ ደካማ እናቶች እየተደረገ ያለው የቤት ግንባታ እስኪጠናቀቅ ያማይቋረጥ ክትትል እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።

በደቡብ ኦሞ ዞን ማሌና በበና ጸማይ ወረዳዎች ለተመረጡ 2
አቅመ ደካማ እናቶች የተጀመረው ቤት ግንባታ ለዘመናት የነበረባቸውን የመኖሪያ ቤት ችግር እንደሚቀርፍ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

የቤት ግንባታ የተጀመረላቸው አቅመ ደካማ እናቶች ወ/ሮ አርዲ ዶቃ እና ወ/ሮ አባለች ኪቴ ለተደረገላቸው በጎ ተግባር ታላቅ ደስታ እንደተሰማቸው ተናግረዋል።

“ፈጣሪ ተመልክቶናል፤ ከዘመናት መከራችን ታድጎናል ስደገፋችሁን ፈጣሪ ያክብራችሁ” ሲሉ የክልሉን ጤና ቢሮ አመስግነዋል።

በመርሃግብሩ የበና ጸማይ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዮሐንስ ጋርሾ እና የማሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አልጋጋ ባለንሲ የጤና ቢሮና ተጠሪ ተቋማቱ በወረዳው ለተደረገ ታላቅ ተግባር ምስጋና ችረዋል።

አቅመ ደካሞችን በመለየት ቤታቸው እንዲሰራ መደረጉ ለአመታት ከነበረባቸው የቤት ችግር የሚያላቅቅ ታላቅ ወገናዊ ተግባር መሆኑን ዋና አስተዳዳሪዎቹ ገልጸዋል።

ዋና አስተዳዳሪዎቹ ተቋማቱ በመቀናጀት በወረዳዎቹ ያስጀመሩት የበጎነት ተግባር ቁርጠኝነትን አድንቀዋል።

በመርሃ ግብሩ የክልሉ ጤና ቢሮ እና ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት አመራሮችና ማናጅመንት አካላት፣ የማሌና በናፀማይ ወረዳ አስተዳዳሪዎችና የአከባቢ ነዋሪዎች ተግኝተዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ እና ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓል ላይ ለመታደም ከወላይታ ዞን አስተዳደር የተላከላቸውን ጥሪ ተቀበሉ።ክብረ በዓኡን ...
02/09/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ እና ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓል ላይ ለመታደም ከወላይታ ዞን አስተዳደር የተላከላቸውን ጥሪ ተቀበሉ።

ክብረ በዓኡን ለመታደም የተደረገላቸውን ጥሪ የቢሮ አመራሮች ተቀብለዋል።

ጤና ቢሮው ጊፋታ በዩኔስኮ( UNESCO) ተመስግቦ የመጀመሪያውን በዓል "የጊፋታ ብስራቶች ለህዝባችን ከፍታ" በሚል መሪ ቃል በመስከረም 10/2019 ዓ.ም የወላይታ ብሔር ተወላጆች፣ ከሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ እንግዶች ጋር በመገኘት በድምቀት እንዲታደሙ በክብር ተጠርቷል።

የቢሮ አመራሩም የተደረገላቸውን የክብር ጥሪ ተቀብለው እንደሚገኙ ቃል ገብተዋል።

Address

South Ethiopia Region, Near To Jinka Hospital
Jinka

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when South Ethiopia Regional State Health Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share