የሰሜን አሪ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ - North Ari Woreda Prosperity Party

  • Home
  • Ethiopia
  • Jinka
  • የሰሜን አሪ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ - North Ari Woreda Prosperity Party

የሰሜን አሪ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ - North Ari Woreda Prosperity Party ይህ የፌስቡክ ገፃችን በተለያዩ ዘርፍ የተሰሩትንና የፓርቲያችን ዕሰት የሆኑ መልዕክቶችን ለመላው ተከታዮቻችን በታማኝነት የምናደርስበት ገጽ ነው።

የጽናት ቀን
08/09/2026

የጽናት ቀን

ጳጉሜን 3  የጽናት ቀን!
08/09/2026

ጳጉሜን 3 የጽናት ቀን!

“የአመራር ውጤታማነትን በማጠናከር፣ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን በማስፈን የክልሉን እመርታ እናረጋግጣለን” — አቶ ገ/መስቀል ጫላየደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን የልማትና የለውጥ ጉዞ ወደ ተ...
07/09/2026

“የአመራር ውጤታማነትን በማጠናከር፣ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን በማስፈን የክልሉን እመርታ እናረጋግጣለን” — አቶ ገ/መስቀል ጫላ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን የልማትና የለውጥ ጉዞ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር፣ የተጠናከረ አመራር፣ የተደራጀ የፓርቲ አቅምና የተግባር ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገ/መስቀል ጫላ ገለጹ።

በቀጣይ የሚከናወኑ የልማትና የለውጥ ሥራዎች የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አቶ ገ/መስቀል ቁልፍ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል፦

🔹 የፓርቲውን አቅም አሟጦ መጠቀም
🔹 የአመራር ውጤታማነትን ማጠናከር
🔹 የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን ማስፈን
🔹 ሌብነትና ብልሹ አሠራርን ማስወገድ
🔹 ወጪን በመቀነስ ሀብትን በቁጠባና በአግባቡ መጠቀም።

እነዚህን የትኩረት አቅጣጫዎች በተግባር በማዋል፣ ውጤታማ አመራርን፣ የተቀናጀ አፈጻጸምንና የሀብት ቁጠባን በማጠናከር የክልሉን እመርታ ማረጋገጥ ይገባል።

07/09/2026
በሰሜን አሪ ወረዳ በዝፍት ኡፃ ቀበሌ የ2018 ዓ/ም የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የሆነውን የእርስበርስ እግር ኳስ ውድድር እየተካሄደ ይገኛልጳጉሜ 2/2018 ዓ/ም በሰሜን አ...
07/09/2026

በሰሜን አሪ ወረዳ በዝፍት ኡፃ ቀበሌ የ2018 ዓ/ም የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የሆነውን የእርስበርስ እግር ኳስ ውድድር እየተካሄደ ይገኛል

ጳጉሜ 2/2018 ዓ/ም በሰሜን አሪ ወረዳ የ2018 ዓ/ም የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የሆነው የእርስበርስ እግር ኳስ ውድድር እየተካሄደ ይገኛል።

በወረዳው በዝፍት ኡፃ ቀበሌ የ2018 ዓ/ም የክረምት ወራት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በሁሉም ዘርፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በ19ኙ ዘርፍ ውስጥ አንዱ ስፖርት ስሆን በክረምት ወራት ወጣቶች በቡድን ተደራጅተው በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል።

‎ሀገራችን ኢትዮጵያ የጀመራቸውን የማንሰራራት ጉዞው በለውጡ መንግስት እና በጽኑ ትውልድ ተጠናክሮ ይቀጥላል ‎‎ገሊላ፣ጳጉሜ 02/2018 ዓ/ም በኣሪ ዞን በሰሜን ኣሪ ወረዳ የ2018 ዓ/ም የ...
07/09/2026

‎ሀገራችን ኢትዮጵያ የጀመራቸውን የማንሰራራት ጉዞው በለውጡ መንግስት እና በጽኑ ትውልድ ተጠናክሮ ይቀጥላል

‎ገሊላ፣ጳጉሜ 02/2018 ዓ/ም በኣሪ ዞን በሰሜን ኣሪ ወረዳ የ2018 ዓ/ም የአመቱ መሰናበቻ ጳጉሜ ቀናቶች በሙሉ በተለያዩ ስያሜ የሚከበር ስሆን በዛሬው ዕለት ጳጉሜ ሁለት "የማንሰራራት" ቀን አጠቃላይ ፐብሊክ ሰርቫንት በተገኙበት በፓናል ውይይት ተከብሯል።

‎የዘንድሮ 2018 ዓ/ም የዓመቱ መሰናበቻ የሆኑ የጳጉሜ ቀናቶች በተለያዩ መሪ ቃል በሀገራችን ኢትዮጵያ በሁሉም አከባቢ እየተከበረ ይገኛል።

‎ሀገራችን ኢትዮጵያ በያዘችው በጀት ዓመት በማህበራዊ ፣በኢኮኖሚያዊ እና በፖሊትካዊ ዘርፈብዙ ለውጦችን ያስመዘገበውን ታሳቢ በማድረግ የጳጉሜውን ቀን እያከበረች ትገኛለች።

‎በዚህም መሠረት የሰሜን አሪ ወረዳ ዋና አሰተዳደር አቶ ጎሳዬ ጉሳር እንደገለጹት ኢትዮጵያ ሀገራችን ልዩ በሆነ መንገድ የዘመን አቆጣጠር ያለች እና ድንቅ ሀገር ነው ብለዋል።

‎አክለውም አስተዳዳሪው እንዳሉት ሀገራችን ኢትዮጵያ የጀመራቸውን ማንሰራራት በለውጡ መንግስት እና በጽኑ ትውልድ በኩል ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

‎በተጨማሪም የሰሜን ኣሪ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገበየሁ ፍልዳክ በበኩላቸው የዛሬውን ቀን ስናከብር ሀገራችን ኢትዮጵያ በለውጡ መንግስት ሪፎርም ከተደረገ በኃላ ሰው ተኮር በርካታ መሰረተ ልማቶች የተሰሩ ስሆን ቀጣይም በማንሰራራት ተጠናክሮ ለውጦች እንደሚቀጥሉም ገለጸዋል።

‎በመሆኑም ሀገራችን ኢትዮጵያ በ2018 ዓ/ም በርካታ ህዝቡን የሚጠቀሙ መካ ፕሮጀክቶችን ያሳካንበት ዓመት እንደመሆኑ የተጀመሩ የሀገርቱ ዕድገት በማንሰራራት ግቡን ትመታለች ስሉ ተናግረዋል።

‎በበዓሉ አከባበር በአስተዳደር ጽ/ቤት በኩል የመወያያ ሰነድ የቀረበ ሰሆን ከሰርቫንቱ ሀሳብና አስተያቶች በተነሱ ላይ ከመድረክ በበዓሉ አከባበር ዙሪያ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥተው መድረኩ ተጠናቋል።

07/09/2026
ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት ክልላዊ የከፍተኛ አመራሮች መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛልርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት ክልል አቀፍ የከፍተኛ አመራሮች መድረክ በወላይታ ...
07/09/2026

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት ክልላዊ የከፍተኛ አመራሮች መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት ክልል አቀፍ የከፍተኛ አመራሮች መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ በመካሄድ ላይ ሲሆን፤ መድረኩ በዋናነት በክልሉ መንግስት የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ አፈጻጸም፤ በ2019 መሪ ዕቅድ እንዲሁም የቀጣይ 5 ዓመት ጠቋሚ ስትራቴጂክ ዕቅድ ዙሪያ የሚመክር ይሆናል፡፡

የ2018 ዓ.ም ማጠቃለያ የሆነው ይሄው የአመራሮች መድረክ፤ የክልሉ መንግስት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለክልላዊ እና ሀገራዊ የሰላም፤ የልማትና የብልጽግና ራዕይ ስኬት ባከናወናቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት የተመዘገቡ ውጤቶችን በመገምገም፤ ለ2019 የላቀ አፈጻጸም ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

መድረኩ የዞን፤ የረጂዮ ፖሊስ ከተሞች እና የክልል አስፈጻሚ ተቋማት የበጀት ዓመቱን አጠቃላይ የተግባራት አፈጻጸም መሠረት ያደረገ የምዘና ውጤት ዙሪያም የሚወያይ ሲሆን፤ ይህም በክልሉ በየደረጃው ያሉ መዋቅሮችና አስፈጻሚ ተቋማት የማስፈጸም አቅም በማጎልበት ለተሻለ ውጤት ለማብቃት የጎላ ፋይዳ የሚኖረው ይሆናል፡፡

በተጨማሪም መድረኩ የክልሉን የብልጽግና ፍኖቴ ካርታ፤ ሀገራዊ የዘላቂ ልማት ግቦችንና የሁለንተናዊ ብልጽግና ራዕይ ማዕከል አድርጎ በተዘጋጀ የክልሉ መንግስት የቀጣይ 5 ዓመት ጠቋሚ ስትራቴጂክ ዕቅድ ዙሪያም የሚመክር ከመሆኑም በላይ የክልሉ አስፈጻሚ ተቋማት የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ የግብ ስምምነት የሚፈራረሙ ይሆናል፡፡

በመድረኩ የተገኙት ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በተለይ የክልሉ መንግስት የትኩረት አቅጣጫ በሆኑ ቁልፍ የልማት ዘርፎችና ሀገራዊ የልማት ኢኒሼቲቮች የውጤት ዘላቂነትን ከማረጋገጥ ባሻገር በላቀ አፈጻጸም የክልሉን ሕዝብ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ ቀጣይ አቅጣጫዎች በማስቀመጥ ለአመራሩ ስምሪት የሚሰጡ ይሆናል፡፡

በዚህም መድረኩ የአመራሩን የዓላማ፤ የአመለካከትና የተግባር አንድነት በማጠናከር ለቀጣይ የዘላቂ ሰላምና ልማት ተልዕኮ ያዘጋጃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የክልሉ መንግስት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በክልሉ ህዝብ ግንባር ቀደም ተሳትፎ በሁሉም የልማት አውታሮች ዘርፍ ብዙ ውጤታማ የሰላም፤ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን በመስራት አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉ ይታወቃል፡፡

በክልሉ በዚሁ በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት፤ በተሻለ የተግባር አፈጻጸም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ መዋቅሮች እና የክልል አስፈጻሚ ተቋማት መድረኩ ዕውቅና ይሰጣል ተብሎም ይጠበቃል፡፡

በመድረኩ ከክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ በተጨማሪ የክልሉ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ገ/መስቀል ጫላ፤ የክልሉ አስተባባሪ አካላት፤ አፈ ጉባዓዎች፤ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፤ የዞንና የፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ከፍተኛ አመራሮች፤ የረ/ፖ/ከተማ ከንቲቦችን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ አመራሮች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡

የኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን፡ ቃልን በተግባር ያረጋገጠ  ጉዞኢትዮጵያችን ዛሬ ታሪካዊ በሆነ የማንሰራራት ምዕራፍ ላይ ትገኛለች።ዛሬ  ጳጉሜ 2 "የማንሰራራት ቀን" ተብሎ ሲከበር ይህ ጽንሰ-...
07/09/2026

የኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን፡ ቃልን በተግባር ያረጋገጠ ጉዞ

ኢትዮጵያችን ዛሬ ታሪካዊ በሆነ የማንሰራራት ምዕራፍ ላይ ትገኛለች።ዛሬ ጳጉሜ 2 "የማንሰራራት ቀን" ተብሎ ሲከበር ይህ ጽንሰ-ሀሳብ ዝም ብሎ ምኞት ሳይሆን በተጨባጭ መሬት ላይ እየታዩ ያሉ ስኬቶች ማሳያ ነው።

ባለፉት የለዉጥ ዓመታት የነበሩት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የተቋማት ግንባታ እና ሌሎች ሪፎርሞችን የማድረግ ስራዎች ተጠናቀው አሁን የዘላቂ ልማት ትሩፋቶችን ለቀጣዩ ትውልድ የማሸጋገር ጊዜ ላይ ደርሰናል።

በትናንት ለቅሶና እሳቤ ታጥረው ከሚኖሩት ይልቅ ብሩህ የወደፊት ተስፋን ሰንቀው ወደ ሚቀጥለው አዲስ ምዕራፍ የሚሸጋገሩ ዜጎች ለዚህ ሀገራዊ ማንሰራራት ዋነኛ ሞተር ናቸው።

ይህ ሀገራዊ ማንሰራራት በግብርናው ዘርፍ፣ በማዕድንና በቡና ወጪ ንግድ እንዲሁም በተኪ ምርት ታሪክ ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል። በተለይም እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያሉ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን ዳር ማድረስ የጀግንነት፣ የወል ትርክት እና የ"ይቻላል" መንፈስ ህያው ምስክር ሆኗል።

መንግስት ወደ ተግባር ያስገባው የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን በመሳብ፣ የአገልግሎት ዘርፍ ልህቀትን በማረጋገጥ እና ለአምራች ኢንዱስትሪው የፋይናንስ አቅርቦትን በማሳደግ ጥራት ያለው ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እንዲረጋገጥ ትልቅ አቅም ፈጥሯል።

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከግብርና መርነት ተላቆ ብዝሃ ዘርፎችን ማዕከል ወዳደረገ መዋቅራዊ ስርዓት መሸጋገሩ፣ የሀገራችን የኢኮኖሚ መሰረት ይበልጥ አስተማማኝ እያደረገው ይገኛል።

የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ ይበልጥ ወደ ላቀ ከፍታ የሚያሸጋግሩት በጉባ ይፋ የተደረጉት ግዙፍ አዳዲስ ፕሮጀክቶች መከናወን መጀመራቸው የዘመኑ ታላቅ ብስራት ነው።

እነዚህ ግዙፍ ፕሮጀክቶች፤ ሀገር በቀል የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታን፣ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ፕላንትን፣ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ግዙፉን የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያን፣ የ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ቤቶች ግንባታን እና የነዳጅና ጋዝ ልማት ያካተቱ ናቸው። ፕሮጀክቶቹ የኢትዮጵያን የወደፊት እጣ ፈንታ ከመወሰንም ባሻገር የሀገራችንን የፕሮጀክት አፈፃፀም ፍጥነት፣ ጥራትና ብቃት በተግባር የሚያስመሰክሩ ናቸው።

ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ማንሰራራት ቀጠናዊ እና አለም አቀፋዊ ተፅዕኖዋን በሚመጥን መልኩ እያደገ ነው። ሀገራችን የብሪክስ (BRICS) አባል መሆኗን ተከትሎ አሁን የተጀመሩት እንደ ኒውክሌር ፕላንት እና አቪዬሽን ያሉ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ልማት ፕሮጀክቶች ከውጭ ሀገራት ጋር የምናደርገውን የኢኮኖሚ እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ትብብር ይበልጥ ያጠናክሩታል።

ወጣቱ ትውልድ በዲጂታል ኢኮኖሚ፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና በእውቀት ላይ በተመሰረተ የፈጠራ ስራ ላይ መሳተፍ መጀመሩ ይህን ሀገራዊ ማንሰራራት ወደማይቀለበስበት ደረጃ ያደርሰዋል።

የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ማሻሻያው እውነተኛ ትርጉም የሚያገኘውም ይህ የሰው ሃይል ግንባታ ከዘላቂ የሰላም ግንባታ፣ ጠንካራ የጸረ-ሙስና ትግል እና የፍትህ ስርዓት መሻሻል ጋር ተሰናስሎ ሲጓዝ ነው።

ይህ የማንሰራራት እና የማጽናት ጉዞ ዘላቂ እንዲሆን ሁላችንም አሮጌውንና የማይጠቅመውን አስተሳሰብ አውልቀን በመጣል፣ አዲሱን የለውጥና የስራ ባህል መላበስ ይገባናል።

እርስ በእርስ ከመጠላለፍና ጣት ከመቀሳሰር ወጥተን፣ በሌት ተቀን ትጋት፣ በቅንነት፣ እንዲሁም በነቃ ከተሳትፎ፤ ብልጽግናዋ ያረጋገጠች ኢትዮጵያን ለትዉልድ ማቆየት እንችላለን።

አዲሱ ዓመት ሀገራዊ ማንሰራራትን በተግባር የምናረጋግጥበት፣ ጀግንነትንና የወል ትርክትን አጠናክረን የምንቀጥልበት የብሩህ ተስፋ ዘመን ነው!

Address

North Ari Woreda Gelila
Jinka

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሰሜን አሪ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ - North Ari Woreda Prosperity Party posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share