Jinka Town Administration prosperity Party, የጂንካ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ

  • Home
  • Ethiopia
  • Jinka
  • Jinka Town Administration prosperity Party, የጂንካ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ

Jinka Town Administration prosperity Party, የጂንካ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ This is official page of jinka town administration prosperity party public relations page

🌾🤝 በጎነት ለአብሮነት! በጂንካ ከተማ በኩሬ የበቆሎ ሽልቃቆ ተከናወነነሐሴ 8/2018 ዓ.ም | ጂንካበጂንካ ከተማ በኩሬ የበቆሎ ሽልቃቆ በበጎ ተግባር መልክ ተከናወነ። የጂንካ ከተማ ወጣቶች...
14/08/2026

🌾🤝 በጎነት ለአብሮነት! በጂንካ ከተማ በኩሬ የበቆሎ ሽልቃቆ ተከናወነ

ነሐሴ 8/2018 ዓ.ም | ጂንካ

በጂንካ ከተማ በኩሬ የበቆሎ ሽልቃቆ በበጎ ተግባር መልክ ተከናወነ። የጂንካ ከተማ ወጣቶችና የሴቶች አደረጃጀቶች ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ጋር በመተባበር በተግባሩ ተሳትፈዋል።

ከፌዴራል ሰላም ሚኒስቴር ተወክለው የመጡት አቶ ፍለታሞ ፈከና፣ ወጣቶች በእንዲህ ያሉ በጎ ተግባራት በመሳተፍ አብሮነትንና ሰላምን ማጠናከር እንዳለባቸው ገልጸዋል።
የስብዕና ግንባታ ልማት ቡድን መሪ አቶ አረጋ ዳጉማ በበኩላቸው፣ ወጣቶች ለማህበረሰቡ የሚጠቅሙ በጎ ተግባራትን በተከታታይ ማከናወን እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
የጂንካ ከተማ ወጣቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ወጣት አንተነህ ተሾመ፣ ወጣቶች በበጎ ተግባር በመሳተፍ ለማህበረሰቡ ችግር መፍትሄ ከመሆን ባለፈ የአብሮነት ባህልን ማጠናከር እንዳለባቸው ገልጸዋል።
የወጣቶች ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትም ኤፍሬም ጉልላት የወጣቶች አደረጃጀቶች በተቀናጀ መልኩ ሲሰሩ በከተማው የልማትና የበጎ ተግባር ሥራዎች የሚታይ ውጤት እንደሚመጣ ገልጸዋል።
የወጣቶች ማህበር ጸሐፊ ወጣት አንተነህ አለማየሁ በበኩላቸው፣ “የበጎ ተግባር ዋና ዓላማው ለሌላው መድረስና አብሮነትን በተግባር ማሳየት ነው” በማለት፣ ወጣቶችና ሴቶች በጋራ ሲሰሩ ትንሽ የሚመስል ተግባር እንኳን ትልቅ ውጤት እንደሚያመጣ አስገንዝበዋል።
የከተማዉ የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሥራ አስፈጻሚዎችም ባደረግንዉ ማስተባበር የተከናወነው ይህ ተግባር፣ የመረዳዳት፣ የትብብርና የአብሮነት ነዉ በማለት ተገልፆል ።

🌱 በጎነት ለአብሮነት፤ አብሮነት ለልማት!

በአሪ ዞን የጂንካ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲና የመንግስት ስራዎች አፈፃፀም ግምገማና ምዘና መድረክ በጂንካ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።    ነሐሴ 08/2018 ዓ.ም    ...
14/08/2026

በአሪ ዞን የጂንካ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲና የመንግስት ስራዎች አፈፃፀም ግምገማና ምዘና መድረክ በጂንካ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

ነሐሴ 08/2018 ዓ.ም
ጂንካ

በአሪ ዞን የጂንካ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲና የመንግስት ስራዎች አፈፃፀም ግምገማና ምዘና መድረክ በጂንካ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የአሪ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የአደረጃት ዘርፍ ኃላፊና ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ አስፋው ዶሪ : የአሪ ዞን መንግስት ኮምንኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ደምበላሽ አቦነህ; የአሪ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ኢንስፐክሽንና ስነ ምግባር ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ አቶ አብረሃም በዳና; የጂንካ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ደግፌ ጌታቸው ; የጂንካ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ግርማ ገብሬ: የከተማው አስተባባሪ ኮምቴ አባላት የከተማው አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

የጂንካ ከተማ ንግድ ኢንዱስትሪ ጽህፈት ቤት ከተረጅነት ወደ ምርታማነት የድጋፍ ጥሪን አስመልክቶ ከንግዱ ማህበረሰብ የተሰበሰበ  የአደጋ ጊዜ ስጋት መቋቋሚያ የሀብት ማሰባሰብ ተግባር ቀጥሏል።...
14/08/2026

የጂንካ ከተማ ንግድ ኢንዱስትሪ ጽህፈት ቤት ከተረጅነት ወደ ምርታማነት የድጋፍ ጥሪን አስመልክቶ ከንግዱ ማህበረሰብ የተሰበሰበ የአደጋ ጊዜ ስጋት መቋቋሚያ የሀብት ማሰባሰብ ተግባር ቀጥሏል።

የጂንካ ከተማ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ደግፌ ጌታቸው፣ የጂንካ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና ትምህር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ውባለም ገዛህኝ በተገኙበት ድጋፋቸውን የሰጡ አካላትን አመስግነዋል ።

በጂንካ ከተማ አስተዳደር ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ በአቶ ሐብታሙ ሐዝሚ አስተባባሪነት የተመራው ከተረጅነት ወደ ምርታማነት የሀብት ማሰባሰብ ከባለሀብቶችና የከተማዋ የንግድ ማህበረሰብን ያሳተፈ፣ የማሰባሰብ ተግባሩ የቀጠለ መሆኑን ጠቁመው ዋልያ ቢራ እና ለስላሳ መጠጦች ማከፋፈያ እንዲሁም ሐበሻ ቢራ ማከፋፈያን ላደረጉት ድጋፍ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

ከዋልያ ቢራ እና ለስላሳ መጠጦች ማከፋፈያ ባለቤት ከአቶ በላይ አብርሃም 10 ኩንታል የበቆሎ ድጋፍ አድርጓል ።

እንዲሁም ሐበሻ ቢራ ማከፋፈያ በተመሳሳይ 10 ኩንታል ያደረጉ ስሆን በአጠቃላይ 20 ኩንታል አድርገዋል። ጥሪውን ተቀብሎ የተለያዩ ድጋፊ እያደረጉ የሚገኙ ባለሐብቶችን የጂንካ ከተማ ንግድ ኢንዱስትሪ ጽህፈት ቤት ኃላፊው አመስግነዋል የሀብት ማሰባሰብ ስራ ተጠናክሮ የቀጠለ መሆኑንም ጭምር አሳውቀዋል ።

13/08/2026
የጂንካ ከተማ የሥራና ክህሎት ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ የሥራ አጥ ወጣቶች ልየታ ንቅናቄ መድረክ ተካሄደ ።          ነሐሴ 7/2018 ዓ.ም     ...
13/08/2026

የጂንካ ከተማ የሥራና ክህሎት ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ የሥራ አጥ ወጣቶች ልየታ ንቅናቄ መድረክ ተካሄደ ።
ነሐሴ 7/2018 ዓ.ም
ጂንካ ።
የጂንካ ከተማ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸምን እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድን ለመገምገም ፣ የሥራ አጥ ወጣቶችን ልየታ ለማካሄድና በቀጣይ የሚከናወኑ የሥራ ፈጠራና የክህሎት ልማት ተግባራትን በጋራ ለማቀድ የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል ።

በመድረኩ የጂንካ ከተማ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ደግፌ ጌታቸው ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል ። ከንቲባው በንግግራቸው የሥራ አጥ ወጣቶችን በትክክል መለየትና ያላቸውን እውቀት ፣ ክህሎትና ፍላጎት በመለየት ከሚያስፈልጋቸው የሥራ ዕድል ጋር ማገናኘት ለወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማስፋፋት ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል ።

በተጨማሪም የጽ/ቤቱ የ2018 ዓ.ም አፈጻጸም በጥንካሬና በውስንነት እንዲገመገም ፣ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድም በተጨባጭ የሥራ ዕድል ፈጠራን ፣ የክህሎት ልማትን እና ወጣቶችን ወደ ሥራ ዓለም ማስገባትን ያማከለ መሆን እንዳለበት ጠቁመዋል ።

የጂንካ ከተማ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ስድራቅ አልቅሲ በበኩላቸው የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸምን ፣ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድን እና የሥራ አጥ ወጣቶች ልየታ ሥራን አስመልክተው ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል ። የጽ/ቤቱ ቀጣይ ሥራዎች የሥራ አጥ ወጣቶችን በመለየት ፣ በክህሎት በማብቃት እና ከሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎች ጋር በማገናኘት ላይ እንደሚያተኩሩ ገልጸዋል ።

የጂንካ ከተማ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ጽ/ቤት የስራ ዕድል ፈጠራና የኢንተርፕራይዞች ቡድን መሪና ባለሙያ አቶ ሰንበታ ፈይዳኪ የ2018 ዓ.ም አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ እንዲሁም የሥራ አጥ ወጣቶች ልየታ ሥራን በሰፊው ከማብራሪያ ጋር ሪፖርት አቅርበዋል ።

በመድረኩ የቀረበው ሪፖርት ላይ ውይይት በማካሄድ የ2018 ዓ.ም አፈጻጸም የተገኙ ውጤቶችንና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በመለየት ፣ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድን በተጨባጭ ሁኔታ ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል ።

በተለይም የሥራ አጥ ወጣቶች ልየታ ሥራ በተገቢው ሁኔታ በማካሄድ ወጣቶችን ከሥራ ዕድል ፣ ከክህሎት ሥልጠና ፣ ከሥራ ፈጠራና ከሌሎች የልማት ዕድሎች ጋር ለማገናኘት በቅንጅት እንዲሠራ አቅጣጫ ተሰጥቷል ።

መድረኩ የጂንካ ከተማ ወጣቶች በተለያዩ የሥራና የክህሎት ዕድሎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተቀናጀ የሥራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል።

🩸 አንድም እናት በደም እጥረት መሞት የለባትም! በጂንካ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽህፈት ቤት አስተባባሪነት፣ የጂንካ ደም ባንክ በጂንካ ከተማ አስተዳደር ቅጥር ግቢ በመገኘት የክረምት በጎ ተግ...
13/08/2026

🩸 አንድም እናት በደም እጥረት መሞት የለባትም!

በጂንካ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽህፈት ቤት አስተባባሪነት፣ የጂንካ ደም ባንክ በጂንካ ከተማ አስተዳደር ቅጥር ግቢ በመገኘት የክረምት በጎ ተግባር አካል የሆነውን የደም ልገሳ ፕሮግራም ጀምሯል።

የፌዴራል ሰላም ሚኒስቴር ተወካይ አቶ ፈልታሞ ፋካና፣የጂንካ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ፖለቲካ እና ህዝብ ግንኘነት ዘርፍ ኃላፊና ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ በላይ ወልዴ ፣ የጂንካ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አደም ሮራ በጋራ ፕሮግራሙን አስጀምረዋል ።

የደም ልገሳ ማለት ለተቸገሩ ወገኖቻችን የሕይወት ስጦታ መስጠት ነው። በደም ልገሳችን እናቶችን፣ ሕፃናትንና ሌሎች የደም እጥረት ያጋጠማቸውን ወገኖች ለመታደግ እንችላለን። ይህም ስለ ደም ልገሳ ያለንን አመለካከት በማሻሻል የልገሳ ባህልን ለማጎልበት ያግዛል።

ከጤና ባለሙያዎች ጎን በመቆም፣ ደም መለገስን ባህላችን እናድርግ። በተቻለ መጠንም በየ**3 ወሩ አንድ ጊዜ** ደም በመለገስ የሰውን ሕይወት እንታደግ።

❤️ ደም ለግሰን ሕይወት እናድን!🌱 የክረምት በጎ ተግባር — በጎነት ለአብሮነት!**

የጂንካ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት በነገው ዕለት የደም ልገሳ ፕሮግራም በከተማ አስተዳደር ቅጥር ግቢ እንደምደረግ አስታወቀ።               ነሐሴ 6/2018ዓ.ም            ...
12/08/2026

የጂንካ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት በነገው ዕለት የደም ልገሳ ፕሮግራም በከተማ አስተዳደር ቅጥር ግቢ እንደምደረግ አስታወቀ።

ነሐሴ 6/2018ዓ.ም
ጂንካ
በከተማው የደም ልገሳ ፕሮግም ላይ ሁሉም አመራርና ፐብሊክ ሰርባንት በነቅስ ወጥቶ ከጧቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ በከተማው አስተዳደር ቅጥር ግቢ ስለምደረግ ተገኝተው ደም እንድለግሱ የጂንካ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ደግፌ ጌታቸው ጥሪ አስተላልፈዋል።

የጂንካ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ሮራ በበኩሉ ለሚደረገው የደም ልገሳ መሳካት ሁሉም አመራርና ሰርባንት በነቅስ ወጥቶ ፕሮግራሙን ግንባር ቀደም ሆኖ እንድያስጀምር አሳስበዋል።

በደም እጥረት ምክንያት የሚጠፋውን ነፍስ ለመታደግ በሚካሄደው የደም ልገሳ ፕሮግራም ላይ እየተሳተፉ ያሉ ቅን ልቦችን በእጅጉ አመስግነው በነገው ዕለት በሚደረገው የደም ልገሳ መረሃ ግብር ላይ እንድሳተፍ ስልም ጥሪ አቅርበዋል አክለውም በወባ ወረሽኝ ምክንያት በደም ማነስ የሚሞቱ ወገኖቻችን ሕይወት እንታደግ!!

የኣሪ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲና የመንግስት ሥራዎች አፈፃፀም ግምገማ እና ሚዜና ማካሄድ ጀመረ።ነሐሴ 5/2018 ዓ/ም    ኣሪ ዞን/ጂንካበመድረኩ ...
11/08/2026

የኣሪ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲና የመንግስት ሥራዎች አፈፃፀም ግምገማ እና ሚዜና ማካሄድ ጀመረ።

ነሐሴ 5/2018 ዓ/ም
ኣሪ ዞን/ጂንካ

በመድረኩ መክፈቻም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ብዮት ደምሴ እንደተናገሩት ይኸ መድረክ
እዉነትንና እዉቀትን ባማከለ እና በጥቅም አልባ ግንኙነትና በሚዛናዊነትን መርህ ባደረገ መንገድ ትናንትን በማከም ነገን በመተለም ዕሳቤ እንድሁም ከስብራቶቻችንን ልያሻግረን በሚችል ለዉጥ በወለደዉ ቁጭት የሕዝብ ጥቅምንና የተገልጋይ ተጠቃሚነትን ልያረጋግጥ በሚችል ትጋትና ለላቄ ዉጤት ልንታትር እንደሚገባም ተናግረዋል።

አክለዉም ክቡር የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብረሃም አታ አክለዉ እንደተናገሩት የ2018 ዓ/ም የመንግስት እና የፓርቲ አፈፃፀም ግምገማ አስፈላጊነቱ በበጀት ዓመቱ በድክመት ያለፍንባቸዉንና መስተካከል የሚያስፈልጉ ነጥቦችን በመለየት ሕዝብን የማሻገር ተልዕኮ ላይ የጋራ መግባባት መፍጠር የሚያስችል ልዩ ዕድል እንደሆነም ገልፀዉ ለዚህም ስኬት የእያንዳንዱ አመራርና ባለድርሻ አካላት ሚና እና ጤናማ መስተጋብር መኖር አማራጭ የለሌዉ ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል ።

በስተመጨረሻም ከዚህ የመንግስት እና የፓርቲ አፈፃፀም ግምገማና ሚዜና ማግስት ተጨባጭ ለዉጥ ለማምጣትም ቀና የሆነ አመለካከት እና ለለዉጥ የተዘጋጀ ስነ ልቦና ልኖረን እንደሚገባም አስገንዝበዋል ።

🏟️⚽ በጂንካ ከተማ የክረምት በጎ ስፖርታዊ ውድድር በከተማ አቀፍ ደረጃ በጂንካ ሁለገብ ስታዲየም የመክፈቻ ጨዋታ እየተካሄደ ይገኛል              ⚽ ኮብራ ካይ 🆚 ፍቅር ያሸንፋል  ጀ...
09/08/2026

🏟️⚽ በጂንካ ከተማ የክረምት በጎ ስፖርታዊ ውድድር በከተማ አቀፍ ደረጃ በጂንካ ሁለገብ ስታዲየም የመክፈቻ ጨዋታ እየተካሄደ ይገኛል

⚽ ኮብራ ካይ 🆚 ፍቅር ያሸንፋል ጀምረዋል

የመክፈቻ ጨዋታውን የኣሪ ዞን ባህልና ስፖርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ተወካይ አቶ ሳሙኤል ገዛኸኝ ፣ የጂንካ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ኃላፊና ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ በላይ ወልዴ ፣ የጂንካ ከተማ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ዩኒቲ አስተባባሪ አቶ አዘነ ፈንታ በጋራ የዕለቱን ጨዋታ አስጀምረዋል።

የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለአደጋ ስጋት ጊዜ ድጋፍ የሚሆን 5 ኩንታል በቆሎ አበረከተ                                  ነሐሴ 1/2018 ዓ.ም                  ...
07/08/2026

የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለአደጋ ስጋት ጊዜ ድጋፍ የሚሆን 5 ኩንታል በቆሎ አበረከተ

ነሐሴ 1/2018 ዓ.ም
ጂንካ
የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለጂንካ ከተማ አስተዳደር ለአደጋ ስጋት ጊዜ ድጋፍ የሚሆን 5 ኩንታል በቆሎ ያበረከተ ስሆን የኣሪ ዞን ግብርና ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊና የጂንካ ከተማ ደጋፊ አመራር የሆኑት አቶ ኤሊያስ ቃሾ እና የጂንካ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ደግፌ ጌታቸው በጋራ ተረክበዋል ።

በዚህ ወቅት የጂንካ ከተማ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ደግፌ ጌታቸው “ከተረጅነት ወደ ምርታማነት” በሚል መርህ እየተካሄደ ያለውን የሀብት ማሰባሰብ፣ የእርሻ ሥራዎችን እና ሌሎች የልማት ተግባራትን ተዟዙረው ተመልክተዋል።

አክለውም የተቋማት ትብብርና የማህበረሰብ ድጋፍ በአስፈላጊ ጊዜያት የጋራ አቅምን እንደምያጠናክር ጠቁመው የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮለጅን አመስግነዋል።

Address

South Ethiopia, Jinka
Jinka

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Jinka Town Administration prosperity Party, የጂንካ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share