28/08/2026
የኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ ትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዲቭዥን ከኬሌ ከተማ አሰተዳደር ትራፊክ ሥራ ሂደት ጋር ዉይይት ማድረጉን አስታወቀ።
ኬሌ:-ነሐሴ 22/2018 ዓ/ም ኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ
የኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ ትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዲቭዥን ከኬሌ ከተማ አሰተዳደር ትራፊክ ሥራ ሂደት ጋር አንድ ዕቅድና አንድ ሪፖርት ሥርዓቶች እና ተግባር አፈፃፀም ዙርያ ዉይይት ማድረጉን አስታዉቋል።
የኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ ትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዲቭዥን ኃላፊ ኮማንደር አበበ ጣሰዉ በዉይይቱ የ2018 ዓ/ም ተግባር አፈፃፀም ገምግመው በ2019 ዓ,ም ዝርዝር ተግባር ዕቅድ ላይ በሰፊው አወያይተዋል።
ዲቪዥን ኃላፊው ኮማንደር አበበ ጣሰው ለአሽከርካሪዎች የግንዛቤ ትምህርቶችን በየጊዜ አጠናክሮ መስጠትና በኃይማኖት ተቋማት በዕድር በተለያዩ ቦታዎች አደረጃጀቶችን ማጠናከር።
የቴክኒክ ብልሽት ያለባቸውን ተሽከርካሪዎችን በጥብቅ መቆጣጠር፤የታሪፍ ቁጥጥር ላይ በትኩረት መሥራት፤የሥነ-ምግባር ችግር ያለባቸው አሽከርካሪዎችን ማረም፤እና የቁጥጥር ሥራዎችን ከአድሎአዊ አሰራር የፀዳ በማድረግ የተሳለጠ አገልግሎት ለማህበረሰባችን በመስጠት ክብር የሆነውን የሰዉ ህይወት ከሞት ከአደጋ ለመታደግና የንብረት ውድመቶች እንዳይከሰት የመከላከል ሥራዎችን መስራት ከእኛ የሚጠበቅ ነዉ በማለት አስረድተዋል።
አክለውም የሚከሰቱ አደጋዎችን በመከላከል ከመንገድና ትራንስፖርት ልማት ጽ/ቤት ጋር በቅርበት በቅንጅት መሥራት ከመናኸሪያ ከመኪና ወንበር በላይ ትርፍ ጭነው የሚወጡትን መቆጣጠርና በከተማ ዉስጥ ከፍጥነት ወሰን በላይ የሚያሽከረክሩትን የሚረብሽ ድምፅ የሚጠቀሙትን አሽከርካሪዎችን መቆጣጠር ማረም ይጠበቅብናል በማለት ገልጸዋል።
በመጨረሻም ተሳታፊዎች በተነሱ ሀሳቦች ላይ በሰፊው ተወያይተው ቀጣይ ተግባር ላይ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በትኩረት ለመሥራት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ
የነበረዉን ዉይይት አጠናቀዋል።
የኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ ህዝብ ግንኙነት