Waajjira S/Sarvisiifi/Mi/ Q/ Namaa A/D/Harawa

Waajjira S/Sarvisiifi/Mi/ Q/ Namaa A/D/Harawa Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Waajjira S/Sarvisiifi/Mi/ Q/ Namaa A/D/Harawa, Government Official, Dawe Harawa, Kemise.

03/09/2026
ሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ሰባቱ ምሶሶዎችየሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ሰባቱ ምሶሶዎች (Pillars of Civil Service Reform)የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ዓላማ የመንግሥት ተቋማትን ቀልጣፋ፣ ተ...
03/09/2026

ሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ሰባቱ ምሶሶዎች
የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ሰባቱ ምሶሶዎች (Pillars of Civil Service Reform)

የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ዓላማ የመንግሥት ተቋማትን ቀልጣፋ፣ ተጠያቂ፣ ግልጽ፣ ውጤታማ እና ለሕዝብ ተደራሽ እንዲሆኑ ማድረግ ነው። ሪፎርሙ በሰባት ዋና ዋና ምሶሶዎች ላይ የተመሠረተ ሲሆን እያንዳንዱ ምሶሶ የራሱ ጠቀሜታ አለው።
1. ነፃና ገለልተኛ የሲቪል ሰርቪስ ግንባታን ማፋጠን
ይህ ምሶሶ የመንግሥት ሠራተኞች ከፖለቲካዊ ተጽዕኖ፣ ከዘመድነት እና ከግል ፍላጎት ነፃ ሆነው ሕግንና ሙያዊ ሥነ-ምግባርን መሠረት በማድረግ እንዲሠሩ ያስችላል።
👉 ዋና ግቦች
በብቃት ላይ የተመሠረተ ቅጥርና ዕድገት።
ፍትሃዊ የሰው ሀብት አስተዳደር።
የሙያ ሥነ-ምግባርን ማጠናከር።
👉 የሚጠበቀው ውጤት
የሕዝብ እምነት የተገነባ ሲቪል ሰርቪስ።
2. አካታችነትን ያረጋገጠ ሲቪል ሰርቪስ መገንባት
ሲቪል ሰርቪሱ ሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍሎች በእኩልነት የሚያሳትፍ እንዲሆን ይሠራል።
👉ትኩረት የሚሰጣቸው
👉 ሴቶች
👉 ወጣቶች
👉 አካል ጉዳተኞች
👉የተለያዩ ብሔርና ማኅበረሰብ ቡድኖች
👉 የሚጠበቀው ውጤት
👉 ፍትሃዊና ሁሉንም የሚወክል የመንግሥት አገልግሎት።
3. አደረጃጀትና አስተዳደር ሥርዓትን ማሳለጥ
በተቋማት ውስጥ ያሉ የሥራ ሂደቶችን ማቅለል፣ የሥልጣን መደራረብን ማስቀረት እና ተጠያቂነትን ማጠናከር ያለመ ነው።
👉 ዋና ተግባራት
👉የተቋማት መዋቅር ማሻሻል።
👉 የሥራ ሂደት ቀለል ማድረግ።
👉 ተደራራቢ ተግባራትን ማስወገድ።
የሚጠበቀው ውጤት
👉ፈጣንና ውጤታማ የአስተዳደር ሥርዓት።
4. ቀልጣፋና ተደራሽ የመንግሥት አገልግሎት አቅርቦት ሥርዓት መዘርጋት
የመንግሥት አገልግሎቶች ለዜጎች በቀላሉ፣ በፍጥነት እና በጥራት እንዲደርሱ ያደርጋል።
ዋና ተግባራት
👉 የአገልግሎት ደረጃዎች ማስቀመጥ።
👉 የዜጎች ቅሬታ አስተናጋጅ ሥርዓት ማጠናከር።
👉 የአንድ መስኮት (One Stop Service) አገልግሎት ማስፋፋት።
የሚጠበቀው ውጤት
👉 የሕዝብ እርካታ መጨመር።
5. የመንግሥት ሠራተኞች የብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ሥርዓት መገንባትና የማስፈጸም አቅምን ማሳደግ
የመንግሥት ሠራተኞች በሥራቸው ላይ ብቁ መሆናቸውን በመመዘን እና በማረጋገጥ የአገልግሎት ጥራትን ማሻሻል ያለመ ነው።
ዋና ተግባራት
👉የብቃት ምዘና ማካሄድ።
👉 የሙያ ማረጋገጫ ሥርዓት መዘርጋት።
👉 ቀጣይነት ያለው ሥልጠና መስጠት።
የሚጠበቀው ውጤት
👉 ብቁና ተወዳዳሪ የመንግሥት ሠራተኛ።
6. የዲጂታል ሲቪል ሰርቪስ በመገንባት ቅቡልነት ያላቸው አገልግሎቶችንና ውሳኔዎችን ማቀላጠፍ
የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማስፋፋት የመንግሥት ሥራዎችን ፈጣን፣ ግልጽ እና ቀልጣፋ ማድረግ ነው።
ዋና ተግባራት
👉 ኢ-አገልግሎቶች (E-Services) ማስፋፋት።
👉 የዲጂታል መረጃ ቋቶች መገንባት።
👉 የመረጃ ልውውጥን ማዘመን።

የሚጠበቀው ውጤት
👉 የወረቀት ሥራ መቀነስ፣ ፍጥነትና ግልጽነት መጨመር።
7. የሲቪል ሰርቪስ ገቢር-ነበብ አመራር እና ተቋም ግንባታን ማፋጠን
ይህ ምሶሶ ውጤት ተኮር አመራርን፣ ጠንካራ ተቋማትን እና ተጠያቂ የአመራር ሥርዓትን ማጠናከር ያለመ ነው።
ዋና ተግባራት

👉 በውጤት ላይ የተመሠረተ አመራር መገንባት።
👉 የአመራር ብቃት ማሳደግ።
👉 የተቋማትን አቅም ማጠናከር።

29/07/2026

አዲሱ የአማራ ክልል የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ፡ ቁልፍ ለውጦች እና አዳዲስ ድንጋጌዎች

​የአማራ ክልል ምክር ቤት በ6ኛ ዙር፣ 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 11ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ አዲስ የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ማጽደቁ ይታወቃል፡፡

ይህ አዋጅ ነባሩ አዋጅ ቁጥር 253/2010 ሙሉ ባለመኾኑ እና አዲሶቹን የፌዴራል የመንግሥት አገልግሎት እና አሥተዳደር ፖሊሲ እንዲሁም የፌዴራል የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1353/2017 መሠረት በማድረግ የተዘጋጀ መሆኑን ከአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ተጠሪ ዳኛ ስለሽ አብርሐም ተገልጿል፡፡

​አዋጁ 16 ክፍሎች እና 151 አንቀጾች ያሉት ሲኾን፣ ይዞዋቸው የመጣቸው አዳዲስ እና ትኩረትን የሚስቡ ዋና ዋና ጉዳዮች በሚከተለው መልኩ ተዘርዝረዋል፡-

​1. የተፈጻሚነት ወሰን እና መዋቅራዊ አደረጃጀት

📌​​​​የተፈጻሚነት ወሰን: አዲሱ አዋጅ ከነባሩ የመንግሥት ሠራተኛ እና ተቋማት በተጨማሪ በመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ጭምር ተፈጻሚነት ይኖረዋል።

📌​​​​መዋቅራዊ አደረጃጀት: የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች መዋቅር ሲዘረጋ የሕዝብ ብዛት፣ የሚሰበሰብ ገቢ፣ የቆዳ ስፋት፣ ቁጥጥር የሚደረግበት መጠን እና ከፌዴራል ተቋማት ጋር የተናበበ መሆን እንዳለበት በግልጽ ተቀምጧል።

​2. የደመወዝ ስኬል እና የኑሮ ውድነት ማስተካከያ

📌​​​​የደመወዝ ስኬል: በፌዴራል ደረጃ በየአራት ዓመቱ የሚወሰነው የሥራ ደረጃ መነሻ ዝቅተኛ ደመወዝ እና ከፍተኛ ጣሪያ ደመወዝ በክልሉ ተፈጻሚ ይሆናል።

📌​​​​ሜሪት እና የደመወዝ ቦርድ: ሀገራዊ የመክፈል አቅምን መሠረት በማድረግ በየጊዜው የሚከሰተውን የኑሮ ውድነት ለመቋቋም የሚያግዝ የደመወዝ ጭማሪ የሚያደርግ ልዩ ቦርድ ይቋቋማል።

​3. የብቃት ምዘና እና ከሥራ ስንብት ጋር የተያያዙ ውሳኔዎች

📌​​​​የብቃት ምዘና ፈተና: የመንግሥት አገልግሎቱን ውጤታማ ለማድረግ እያንዳንዱ በሥራ ላይ ያለ እና አዲስ ሠራተኛ የብቃት ምዘና ፈተና እንዲወስድ ይደረጋል።

📌​​​​ውጤት ማምጣት ላልቻሉ ሠራተኞች የሚሰጥ ዕድል:

📌​​​​​የሚቋቋመው የብቃት ምዘና ማዕከል ፈተናውን የማያልፉትን የማሟያ ሥልጠና ሰጥቶ እንዲበቁ ያደርጋል።

​ሆኖም ሥልጠና ወስዶ ለተከታታይ ሁለት ጊዜ የማለፊያ ነጥብ ማምጣት ካልቻለ ሠራተኛው ከመንግሥት ሥራ ይሰናበታል፡

📌​​​​ዕድሜያቸው ለጡረታ ያልደረሰ እና ከ25 ዓመት በታች ያገለገሉ: ሁለት ዓመት የተጣራ ደመወዝ በአንድ ጊዜ ተከፍሏቸው ከሥራ ይሰናበታሉ።

📌​​​​25 ዓመት አገልግለው ዕድሜያቸው ከ50 እስከ 55 ለሆኑ: ቀደም ብለው ጡረታ የሚወጡበት ሁኔታ ተመቻችቷል።

​4. የሥራ ሰዓት፣ ጥቅማጥቅሞች እና ልዩ ፈቃዶች

📌​​​​የሥራ ሰዓት: መደበኛ የሥራ ሰዓት በፊት በሳምንት 39 ሰዓት የነበረው፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከ39 ሰዓት ሳያንስ እና ከ48 ሰዓት ሳይበልጥ ሊሆን እንደሚችል ተወስኗል።

📌​​​​የጉዲፈቻ ፈቃድ: አንድ እናት ከሦስት ወር ያልበለጠ ሕጻን ልጅ ለማሳደግ በጉዲፈቻ ከተረከች የሦስት ወር እንደ ወሊድ ፈቃድ እንዲሰጥ ተፈቅዷል።

📌​​​​በሥራ ላይ ለሚደርስ አደጋ: በሥራ ላይ በአደጋ ምክንያት ለሚከሰት ሞት ለቤተሰቦቹ የአንድ ዓመት ደመወዝ ይከፈላል።

📌​​​​የተጠባባቂነት አበል: ሁኔታዎች ሲያስገድዱ ብቃትን መሠረት በማድረግ አንድን ሠራተኛ ከአንድ ዓመት ላልበለጠ ጊዜ ከፍ ያለ የሥራ መደብ ላይ በተጠባባቂነት ማሠራት የሚቻል ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም የነበረውን ክፍተት በመሙላት የተጠባባቂነት አበል እና ተጠያቂነት ጭምር ተቀምጧል።

25/06/2026

የተሻሻለው የመንግሥት ሠራተኞች የሥራ ልብስ እና የሥራ መሣሪያዎች አሰጣጥና አጠቃቀም መመሪያ ጸደቀ፡፡
=========================
ባህርዳር ሰኔ 17/2018 ዓ.ም የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግ ስት መስተዳድር ም/ቤት በአብክመ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ተሻሽሎ የቀረበውን ረቂቅ የመንግሥት ሠራተኞች የሥራ ልብስ እና የሥራ መሣሪያዎች አሰጣጥና አጠቃቀም መመሪያ ላይ ተወያቶ አጸደቀ፡፡
የዚህ መመሪያ መሻሻል አስፈላጊ ካደረጋቸው ዋና ዋና ምክንያቶች በስራ ላይ የነበረው የመንግሥት ሠራተኞች የሥራ ልብስና የሥራ መሣሪያዎች አሰጣጥና አጠቃቀም መመሪያ ቁጥር 15/2013 ከተዘጋጀ በኋላ ብዙ የስራ ልብስና የሥራ መሳሪያ የሚያስፈልጋቸው የስራ መደቦች መፈቀዳቸዉ፤ በየጊዜው ከተደረጉ የተቋማት የአደረጃጀት ለውጥ ጋር ተያይዞ እንደ አዲስ የተፈጠሩ ተቋማት መኖራቸው፤
በስራ ላይ ያለዉ መመሪያ የፈቀዳቸዉ የሥራ ልብሶችና የሥራ መሣሪያዎች የሥራ መደቡን የሥራ ባህሪይ መሰረት ያላደረጉ ከመሆናቸዉ በላይ ተመሳሳይ የሥራ ባህሪ ያላቸው የሥራ መደቦች የተለያያ የሥራ ልብስ ና የሥራ መሣሪያ እንዲጠቀሙ ማድረጉ እንዲሁም ተመሳሳይ የሥራ መደብ መጠሪያ እና ተግባር ያላቸዉ ባለሙያዎችን፣ ቡድን መሪዎችን እና ዳይሬክቶሮችን እኩል ተጠቃሚ የማያደርግ በመሆኑ፤
በስራ ላይ በነበረው መመሪያ የሥራ ልብስና የሥራ መሣሪያዎች ብዛት ፤ አይነት እና የማሰፊያ ዋጋ በትክክል አለመገለጽ፤ ለሥራ ልብሶችና መሣሪያዎች የተቀመጠው የመግዣ እና የማሰፊያ ዋጋ ከወቅቱ የገበያ ሁኔታ ጋር የማይጣጣም በመሆኑ እና በመሳሰሉት መሰረታዊ ጉዳዮችን ነባሩ መመሪያ እንዲሻሻል ተደርጓል፡፡
ስለሆነም የክልሉ መስተዳድር ም/ቤት የቀረበውን ረቂቅ መመሪያ ተቀብሎ የተወሰነ ማሻሻያ ተደርጎበት የጸደቀ መሆኑን የአብክመ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የአደረጃጀትና ስራ ምዘና ክፍያ ጥናት ዳሬክቶሬት ዳሬክተር የሆኑት አቶ አንተነህ ይስማው ገልጸዋል፡፡

23/06/2026

(Pillars of Civil Service Reform)

የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ዓላማ የመንግሥት ተቋማትን ቀልጣፋ፣ ተጠያቂ፣ ግልጽ፣ ውጤታማ እና ለሕዝብ ተደራሽ እንዲሆኑ ማድረግ ነው። ሪፎርሙ በሰባት ዋና ዋና ምሶሶዎች ላይ የተመሠረተ ሲሆን እያንዳንዱ ምሶሶ የራሱ ጠቀሜታ አለው።

1. ነፃና ገለልተኛ የሲቪል ሰርቪስ ግንባታን ማፋጠን
ይህ ምሶሶ የመንግሥት ሠራተኞች ከፖለቲካዊ ተጽዕኖ፣ ከዘመድነት እና ከግል ፍላጎት ነፃ ሆነው ሕግንና ሙያዊ ሥነ-ምግባርን መሠረት በማድረግ እንዲሠሩ ያስችላል።
📌ዋና ግቦች
👉በብቃት ላይ የተመሠረተ ቅጥርና ዕድገት።
👉ፍትሃዊ የሰው ሀብት አስተዳደር።
👉የሙያ ሥነ-ምግባርን ማጠናከር።
👉የሚጠበቀው ውጤት
👉የሕዝብ እምነት የተገነባ ሲቪል ሰርቪስ።
2. አካታችነትን ያረጋገጠ ሲቪል ሰርቪስ መገንባት
ሲቪል ሰርቪሱ ሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍሎች በእኩልነት የሚያሳትፍ እንዲሆን ይሠራል።
ትኩረት የሚሰጣቸው
👉ሴቶች
👉ወጣቶች
👉አካል ጉዳተኞች የተለያዩ ብሔርና ማኅበረሰብ ቡድኖች
የሚጠበቀው ውጤት
👉ፍትሃዊና ሁሉንም የሚወክል የመንግሥት አገልግሎት።
3. አደረጃጀትና አስተዳደር ሥርዓትን ማሳለጥ
በተቋማት ውስጥ ያሉ የሥራ ሂደቶችን ማቅለል፣ የሥልጣን መደራረብን ማስቀረት እና ተጠያቂነትን ማጠናከር ያለመ ነው።
📌ዋና ተግባራት
👉የተቋማት መዋቅር ማሻሻል።
👉የሥራ ሂደት ቀለል ማድረግ።
👉ተደራራቢ ተግባራትን ማስወገድ።
✍️የሚጠበቀው ውጤት
ፈጣንና ውጤታማ የአስተዳደር ሥርዓት።
4. ቀልጣፋና ተደራሽ የመንግሥት አገልግሎት አቅርቦት ሥርዓት መዘርጋት
የመንግሥት አገልግሎቶች ለዜጎች በቀላሉ፣ በፍጥነት እና በጥራት እንዲደርሱ ያደርጋል።
📌ዋና ተግባራት
👉የአገልግሎት ደረጃዎች ማስቀመጥ።
👉የዜጎች ቅሬታ አስተናጋጅ ሥርዓት ማጠናከር።
👉የአንድ መስኮት (One Stop Service)
👉አገልግሎት ማስፋፋት።
👉የሚጠበቀው ውጤት
👉የሕዝብ እርካታ መጨመር።
5. የመንግሥት ሠራተኞች የብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ሥርዓት መገንባትና የማስፈጸም አቅምን ማሳደግ
የመንግሥት ሠራተኞች በሥራቸው ላይ ብቁ መሆናቸውን በመመዘን እና በማረጋገጥ የአገልግሎት ጥራትን ማሻሻል ያለመ ነው።
📌ዋና ተግባራት
የብቃት ምዘና ማካሄድ።
የሙያ ማረጋገጫ ሥርዓት መዘርጋት።
ቀጣይነት ያለው ሥልጠና መስጠት።
የሚጠበቀው ውጤት
👉ብቁና ተወዳዳሪ የመንግሥት ሠራተኛ።
6. የዲጂታል ሲቪል ሰርቪስ በመገንባት ቅቡልነት ያላቸው አገልግሎቶችንና ውሳኔዎችን ማቀላጠፍ
የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማስፋፋት የመንግሥት ሥራዎችን ፈጣን፣ ግልጽ እና ቀልጣፋ ማድረግ ነው።
📌ዋና ተግባራት
ኢ-አገልግሎቶች (E-Services) ማስፋፋት።
የዲጂታል መረጃ ቋቶች መገንባት።
የመረጃ ልውውጥን ማዘመን።
👉የሚጠበቀው ውጤት
የወረቀት ሥራ መቀነስ፣ ፍጥነትና ግልጽነት መጨመር።

7. የሲቪል ሰርቪስ ገቢር-ነበብ አመራር እና ተቋም ግንባታን ማፋጠን
ይህ ምሶሶ ውጤት ተኮር አመራርን፣ ጠንካራ ተቋማትን እና ተጠያቂ የአመራር ሥርዓትን ማጠናከር ያለመ ነው።
📌ዋና ተግባራት
✍️በውጤት ላይ የተመሠረተ አመራር መገንባት።
✍የአመራር ብቃት ማሳደግ
✍️የተቋማትን አቅም ማጠናከር።
✍የሚጠበቀው ውጤት
ለውጥን የሚመራ፣ ተጠያቂ እና ውጤታማ አመራር።

እነዚህ ሰባቱ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ምሶሶዎች በአንድነት ሲተገበሩ ነፃና ገለልተኛ፣ አካታች፣ ዲጂታል፣ ቀልጣፋ፣ ተጠያቂ እና ለሕዝብ የሚሰራ ዘመናዊ የሲቪል ሰርቪስ ሥርዓት ይገነባል። ይህም የመንግሥት አገልግሎትን በማሻሻል ለሀገር ልማት፣ለመልካም አስተዳደር እና ለሕዝብ እርካታ ወሳኝ መሠረት ይሆናል።

Waajjira S/Sarvisiifi M/Q/Hu/Namaa A/D/Harawaatti Qindoomina  Ogeessota waajjirichaafi Ogeessoota Istaatiksiitiin Hojiin...
10/06/2026

Waajjira S/Sarvisiifi M/Q/Hu/Namaa A/D/Harawaatti Qindoomina Ogeessota waajjirichaafi Ogeessoota Istaatiksiitiin Hojiin Galmee Istaatiksii Ragaa persanoolii Hojjetaa mootummaafi Muudamtootaa Haala ho'aa ta'een itti fufee kan jirudha.

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የድምፅ መስጫ ቀንን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም.  የ7ተኛው...
27/05/2026

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የድምፅ መስጫ ቀንን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ እንዲከናወን መወሠኑ ይታወቃል።

በዚህም መሠረት በመራጭነት የተመዘገቡ ዜጎች ሁሉ በዕለቱ ድምፃቸውን ለመስጠት ይችሉ ዘንድ እና የደምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ያለምንም የፀጥታ ችግር ይከናወን ዘንድ ቦርዱ የሚከተሉት ተግባራዊ እንዲሆኑ የምርጫ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና ሥነ-ምግባር ዐዋጅ 1162/ 2011 አንቀጽ 161 የመተባበር ግዴታ መሠረት ለመንግሥታዊ እና ለማንኛውም መንግሥታዊ ላልሆኑ ተቋማት ያሳውቃል።

በዚህም መሠረት:-
- ዜጎች ዕለቱን ለድምፅ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ የፌዴራል እና የክልል መንግሥታዊ ተቋማት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ሥራ ዝግ እንዲያደርጉ፣

- ዜጎች ዕለቱን ለድምፅ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ በፌዴራል እና በክልሎች የሚገኙ ማንኛውም መንግሥታዊ ያልሆኑ እና የግል ተቋማት በተመሳሳይ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ዝግ እንዲያደርጉ እያሳወቀ፤

- የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት፣ ሆስፒታሎች፣ የዕለት ተዕለት አገልግሎት ሰጪዎችም (ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የትራንስፓርት አገልግሎት) በዝግ ቀናት የሚያደርጉትን አገልግሎት በተመሳሳይ የሚያከናውኑ ሲሆን፤ የመተባበር ግዴታው እነዚህን ተቋማት እንቅስቃሴ መዘጋት አያስገድድም።

- የትራንስፓርት አገልግሎት በተለመደው መንገድ የሚቀጥል ቢሆንም፤ ዜጎች ድምፅ ከመስጠት ውጪ ከፍተኛ እንቅስቃሴን የሚፈልጉ ሁነቶችን እና ዕቅዶችን እንዳይይዙ እና እንቅስቃሴያቸውን ድምፅ ለመስጠት ብቻ እንዲያደርጉ ቦርዱ ያበረታታል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም.

Guyyaa 28/8/2018Waajirri Siivil Sarviisii fi Misooma Qabeenya humna Namaa A/D/Harawaatti Galmee hojjattoota mootummaa ee...
06/05/2026

Guyyaa 28/8/2018
Waajirri Siivil Sarviisii fi Misooma Qabeenya humna Namaa A/D/Harawaatti Galmee hojjattoota mootummaa eegaluuf Ogeessoota istaatiksii Biyyoolessaafi gahe qabeessoota ogeessoota waajjiitaa waliin mari'achuun guyyaa har'aa Waajjira Galii fi Waajjira Maallaqaa irratti Haala armaan gadiitiin Lakkaawwiin Ogeessootaa jalqabeera.

Address

Dawe Harawa
Kemise

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Waajjira S/Sarvisiifi/Mi/ Q/ Namaa A/D/Harawa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share