21/08/2026
የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር መሬት መምሪያ ለክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚውል የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
ከሚሴ — ነሀሴ 15/2018 የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር መሬት መምሪያ ህዝብ ግንኙነት
የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር መሬት መምሪያ በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሐ-ግብር ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የማኅበረሰብ ክፍሎች ልጆች የሚውል የደብተርና የእስክሪፕቶ ድጋፍ ለዞኑ ትምህርት መምሪያ አስረክቧል።
ይህ ድጋፍ የተዘጋጀው መጪውን የትምህርት ዘመን ታሳቢ በማድረግ ሲሆን፣ ዓላማውም አቅመ-ደካማና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ የሚያደርጉትን ጥረት በከፊልም ቢሆን ለማገዝ መሆኑ ተገልጿል።