የኮምቦልቻ ሪጅዮፖሊታን ከተ/አስ/የቢራሮ ክ/ከተማ ኮምዩኒኬሽን

  • Home
  • Ethiopia
  • Kombolcha
  • የኮምቦልቻ ሪጅዮፖሊታን ከተ/አስ/የቢራሮ ክ/ከተማ ኮምዩኒኬሽን

የኮምቦልቻ ሪጅዮፖሊታን ከተ/አስ/የቢራሮ ክ/ከተማ ኮምዩኒኬሽን This is an official page of kombolcha town biraro sub city communication department.

31/08/2026
በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የቢራሮ  ክፍለ ከተማ ራስአገዝ ቀበሌ የክረምት በጎ ፈቃድ አንዱ አካል የሆነውን የእግረኛ መተላለፊያ መንገድ ቀለም የመቀባት ስራ ተከናውኗል።
30/08/2026

በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የቢራሮ ክፍለ ከተማ ራስአገዝ ቀበሌ የክረምት በጎ ፈቃድ አንዱ አካል የሆነውን የእግረኛ መተላለፊያ መንገድ ቀለም የመቀባት ስራ ተከናውኗል።

30/08/2026
በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የቢራሮ ክፍለ ከተማ ሚኒሻ ፅ/ቤት ከክፍለ ከተማው ለሄዱ  ሰላምን ለሚጠብቁ የደጀን ሃይሎች ለልጆቻቸው ለትምህርት የሚያስፈልጋቸውን ደብተር እና እስኪብርቶ ለ40 ...
30/08/2026

በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የቢራሮ ክፍለ ከተማ ሚኒሻ ፅ/ቤት ከክፍለ ከተማው ለሄዱ ሰላምን ለሚጠብቁ የደጀን ሃይሎች ለልጆቻቸው ለትምህርት የሚያስፈልጋቸውን ደብተር እና እስኪብርቶ ለ40 ልጆች ድጋፍ አድርገዋል፡፡

☞ቢራሮ ክ/ከተማ ኮሚዩኒኬሽን፡ ነሃሴ 24/2018ዓ.ም

የክፍለ ከተማው ሚኒሻ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዱ አበበ እንደገለፁት ጓዶች ግንባር ላይ የሀገርን እና የህዝብን ሰላም ለማስከበር ቢሆኑም የነሡ ቤተሰቦች በትምህርት ቁሳቁስ ምክንያት ልጆቻቸው እቤት እንዳይውሉ በኛ በኩል ደብተርና እስኪብርቶ ድጋፍ አድርገናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የቢራሮ ክፍለ ከተማ ራስ አገዝ ቀበሌ  በክረምት በጎ ፈቃድ ለዝቅተኛ የማህበረሰብ ክፍሎች ለሁለተኛ ጊዜ ማዕድ አጋርተዋል፡፡☞ቢራሮ ክ/ከተማ ኮሚዩኒኬሽን፡ ነሃሴ ...
30/08/2026

በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የቢራሮ ክፍለ ከተማ ራስ አገዝ ቀበሌ በክረምት በጎ ፈቃድ ለዝቅተኛ የማህበረሰብ ክፍሎች ለሁለተኛ ጊዜ ማዕድ አጋርተዋል፡፡

☞ቢራሮ ክ/ከተማ ኮሚዩኒኬሽን፡ ነሃሴ 24/2018 ዓ.ም የቢራሮ ክፍለ ከተማ ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ አሊ ይማም እንደገለፁት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በክፍለ ከተማው የራስ አገዝ ቀበሌ ከክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አንዱ የሆነውን የማዕድ ማጋራት በገብርኤል ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ ለሚገኙ ለ200 አቅመ ደጋሞች የማዕድ ማጋራት ተደርጓል ብለዋል።

የቢራሮ ክፍለ ከተማ ራስ አገዝ ቀበሌ አስተዳዳሪ አቶ አብደልሀፊዝ ጌትነት በበኩላቸው በክረምት በጎ ፈቃድ በርካታ ተግባራትን ለማከናወን የታቀደ ሲሆን ዛሬ ለ ሁለተኛ ጊዜ የማዕድ ማጋራት ማድረጋቸውን እና ለዚህ በጎ ተግባር የቀበሌዉ የክረምት በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን አመስግነዋል፡፡

የማዕድ ማጋራት የተደረገላቸው ወገኖች በበኩላቸው ከወደቅንበት አስታውሳችሁ አለንበት ቦታ ድረስ በመምጣት ባደረጋችሁልን የማዕድ ማጋራት ደስተኛ ነን በማለት ተናግረዋል።

በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የቢራሮ ክፍለ ከተማ የፖሊስ አባላቶች በክፍለ ከተማው ስር ካሉ ከአራቱ ቀበሌዎች ዝቅተኛ ነዋሪ ተብለው ለተለዩ 60 ልጆች ደብተር እና ለ15 ልጆች በተጨማሪ ዩኒፎ...
28/08/2026

በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የቢራሮ ክፍለ ከተማ የፖሊስ አባላቶች በክፍለ ከተማው ስር ካሉ ከአራቱ ቀበሌዎች ዝቅተኛ ነዋሪ ተብለው ለተለዩ 60 ልጆች ደብተር እና ለ15 ልጆች በተጨማሪ ዩኒፎርም እና ደብተር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

☞ቢራሮ ክ/ከተማ ኮሚዩኒኬሽን፡ ነሃሴ 22/2018ዓ.ም
የቢራሮ ክፍለ ከተማ ፖሊስ የሀገርን እና የህዝብን ሰላምና ደህንነት ከመጠበቅ፣ ወንጀልንም ከመከላከል ባሻገር በማህበራዊ የበጎ ፍቃድ ስራዎች ላይም በተደጋጋሚ በመሳተፍ የድርሻቸውን እየተወጡ ያሉ የህዝብ አለኝታና ዋልታዎች መሆናቸውን የቢራሮ ክፍለ ከተማ ምክትል ስራ አስፈፃሚና የማህበራዊ ልማት ዘርፍ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አሊ ይማም ገልፀውልናል፡፡

የቢራሮ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ ኢንስፔክተር መሀመድ ይማም በበኩላቸው ዛሬ የተካሄደውን የተማሪዎች የደብተር መስጠትና እና የዩኒፎርም የማልበስ የበጎ ስራውን የቢራሮ ክፍለ ከተማ ትራፊክ ፖሊሶች ሀብት የማሰባሰብ ትልቁን ድርሻ ተወተዋል፡፡

በተጨማሪም የክረምት በጎ ፍቃድ በየአመቱ የሚሰራ ሲሆን በቁሳቁስ ምክንያት ህፃናት እቤት እንዳይውሉ ሁሉም አካል ርብርብ በማድረግ እንዳለበት ኢንስፔክተሩ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የቢራሮ ክፍለ ከተማ ብልጽግና  ፓርቲ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም እና  የ2019ዓ.ም ዕቅድ ትውውቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተካሂዷል።☞ቢራሮ ክ/ከተማ...
27/08/2026

በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የቢራሮ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም እና የ2019ዓ.ም ዕቅድ ትውውቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተካሂዷል።

☞ቢራሮ ክ/ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ነሃሴ 21/2018ዓ.ም የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ የፓርቲ ስራዎች ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2019 ዓ.ም ዕቅድ ትውውቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ ላይ የቢራሮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ከድር እንድሪስ እንደገለፁት የ2018 አፈፃፀማችንን እንደ መነሻ በመውሰድ ክፍተታችንን በመለየት ጠንካራ ጉኖችን በማስቀጠል ለ2019 ይበልጥ ለስራ መትጋት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል::

በዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረኩ ላይ የክፈለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ከድር እንድሪስና የክፍለ ከተማው የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ዙሪያሽወርቅ ሰይድን ጨምሮ ስራ አስፈፃሚዎችና ጽ/ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተካሂዷል።

Address

Kombolcha

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የኮምቦልቻ ሪጅዮፖሊታን ከተ/አስ/የቢራሮ ክ/ከተማ ኮምዩኒኬሽን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share