15/08/2026
በካራት ዙሪያ ወረዳ የ2018 የበጀት ዓመት የፓርቲና የመንግስት ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ እና የአመራር ምዘና መድረክ ተጠናቀቀ፦
#ካራት ዙሪያ ወረዳ: ነሐሴ 09/2018 ዓ.ም
(ካዙወመኮአገ/ት)
በኮንሶ ዞን ካራት ዙሪያ ወረዳ "ትጋት ለላቀ ስኬት'' በሚል መሪ ቃል ለ3 ተከታታይ ቀናት ሲያካሄድ የነበረውን የ2018 በጀት አመት የፓርቲና የመንግስት ስራዎች አፈፃፀም እና የአመራር ምዘና መድረክ ተጠናቋል።
በመድረኩም የኮንሶ ዞን ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ አስቴር ኩሲያ እንደገለፁት፤ግምገማው አንድነትና ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር ተቋም ማሻገር ላይ በቀጣይ አመራሩ በግምገማውና በምዘናው መሰረት ጉድለቱን በማረም ጥንካሬውን በማስቀጠል ብሎም በመግባባት ሊሰራ እንደሚገባም አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
አክለውም የትኛውም ስኬታማ ተግባር የጋራ የቅንጅት ስራ ውጤት እንደመሆኑ በቀጣይም የበለጠ ቅንጅታዊ አሰራርን አጠናክሮ በመስራት የማህበረሰቡ ተጠቃሚነት ማስፋት ላይ አቅዶ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ኩሴ ጭሎ በግምገማ ማጠቃለያ መድረኩ ላይ በግምገማው የተለዩ የአመራሩ ችግሮችን አስመልክቶ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ላይ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፤የወረዳው ህዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ አመራሩ ቅንጅታዊ አሠራሮችን አጠናክሮ በማስቀጠልና በምዘናና ግምገማ መድረኩ በጉድለት የታዩ ጉዳዮችን በማረም በፓርቲ እሴት፣ መርህና ዲሲፕሊን ላይ ተመስርቶ ለላቀ ዉጤት በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ እና ለዉጤታማነቱም የጋራ ርብርብ ማድረግ ይጠበቅብናል በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የወረዳ ዋና የመንግስት ተጠሪ እና የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ ግለዴ በበኩላቸው ምዘናው አመራሩ የተጣለበትን የህዝብ አደራ ከመወጣትና ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ የነበሩ ውስንነቶች በማረም ለተሻለ ስራ የሚያዘጋጅ እንደሆነ አብራርተዋል።
አክለውም የመንግስትና የፓርቲ አደረጃጀቶች በማጠናከር እስከታችኛው መዋቅር በመውረድ ከአስተሳሰብ ጀምሮ ስራ መስራት እንደሚገባ ገለፀው፤በተለይም የፓርቲና የመንግስት አደረጃጀቶችን በማጠናከር አደረጃጀትን ተልዕኮ መፈፅም እንዲቻል ሰፊ ስራ መሰራት እንደሚገባ ገልፀዋል።
በተደረገው ጥልቅ የአመራር ግምገማ የወረዳው
አመራር ጉድለቱን በሚገባ ያየበት እና ችግሮችን በመለየት ለቀጣይ ተግባር የሚያነሳሳ የግምገማ መድረክ ሆኖ ተጠናቋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡
የpage
https://www.facebook.com/profile.php?id=100069342064100
whatapp:https://whatsapp.com/channel/0029VbBzfVYCRs1tubeysJ1J
Youtube፡ https://www.youtube.com/
Like and Share በማድረግ ቤተሰብ በመሆን መረጃ ይከታተላሉ!
መረጃው፦
የካራት ዙሪያ ወረዳ መንግስት ኮሚዪኒኬሽን አገልግሎት!!
ነሐሴ 09/2018 ዓ.ም