Konso Zone Council Office ኮንሶ ዞን ምክር ቤት

Konso Zone Council Office ኮንሶ ዞን ምክር ቤት ይህ ትክክለኛው የኮንሶ ዞን ምክር ቤት ፌስቡክ ገጽ ነው!

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰንደቅ ዓላማ እና አርማ ከክልሉ ሕገ-መንግስት አንጻር:-          ነሐሴ 05/2018 ዓ/ምበደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕገ-መንግስት አንቀጽ 3 ንዑስ አንቀጽ 1 መሰ...
11/08/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰንደቅ ዓላማ እና አርማ ከክልሉ ሕገ-መንግስት አንጻር:-

ነሐሴ 05/2018 ዓ/ም

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕገ-መንግስት አንቀጽ 3 ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት የክልሉ ሰንደቅ አላማ ላይ ሊኖሩ የሚገባቸውን ቀለማትና የክልሉ አርማ እንደሚኖርበት ይገልጻል፡፡

ይሁን እንጂ በተለያዩ የሕትመት ውጤቶችና የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ላይ አንዳንድ ግለሰቦችና ድርጅቶች በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ትክክለኛ ያልሆነውን የክልሉን ሰንደቅ አላማና አርማ ጥቅም ላይ እያዋሉ ይገኛሉ ፡፡

በዚህም የክልሉ ሰንደቅ ዓላማ ከላይ አረንጓዴ ፤ ከመሃል ውሃ ሰማያዊ ፤ ከታች ቀይ ሆኖ በአግድሚ የተቀመጡ ሲሆን ከአረንጓዴው እና ከቀዩ ቀለም መስቀያ ጠርዝ በመነሳት ሰማያዊው መደብ ላይ የሚያርፍ ሦስት ማዕዘን ቅርጽ ያለው ቢጫ ቀለም ሆኖ በመሃሉ በሚገኘዉ ውሃ ሰማያዊ መደብ ላይ የክልሉ ዓርማ የሚቀመጥ ስሆን እያንዳንዱ ቀለማት በጥቁር መስመሮች ተለያይዘዋል፡፡

በሰንደቅ ዓላማዉ ውሃ ሰማያዊ መደብ መሃል ላይ የሚቀመጠው የክልሉ ዓርማ ላይ የሚገኙት የተሰባጠሩ እያንዳንዱ ምስሎች የሚያስተላልፉት መልዕክት ያላቸው ስሆን መሀል ላይ የሚገኘው የነጭ እርግብ ምስል ክልሉ የሰላም ተምሳሌት መሆኑን ፣ ከምስሉ ጫፍ ላይ በጥቁር መደብ የተቀመጠዉ ምስል አብዛኞቹ በክልሉ ዉስጥ የሚገኙ አከባቢዎች ለማኑፋክቸሪንግ ምቹ መሆናቸዉን በአፅንኦት ይገልጻል።

እንድሁም ደግሞ በእግርጌው ያለዉ ያጎመራ የቡና ምስል ክልሉ የሀገር ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት የሆነዉ የቡና ምርት በስፋት ብሎም በጥራት የሚመረትበት ስለመሆኑ መገለጫ ነዉ ፣ በስተቀኝ ያለዉ ከአንገት በላይ ያለ የበሬ አካል ምስል በቆላማው አከባቢ ያለዉ የማህበረሰብ ክፍል አርብቶ አደር መሆኑን ስገልጽ በስተ ግራ ያለዉ እንሰት በከፍተኛ ሁኔታ ድርቅን በመቋቋም በክልሉ የተለያዩ አከባቢዎች በስፋት የሚመረት ለተለያዩ የምግብ ፍጆታዎች የሚዉል ምርት መገኛ የመሆኗ መገለጫ ነዉ።

ስለሆነም ማንኛውም ተቋም ሆነ ግለሰብ ትክክለኛ የሆነዉን የክልሉን ሰንደቅ ዓላማ እና አርማ በመለየት መጠቀም እንደሚገባው ሲሆን ትክክለኛ ያልሆነውን አርማም ሆነ ሰንደቅ ዓላማ መጠቀም በሕግ የሚያስጠይቅ መሆኑን እንገልፃለን።

መረጃዉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ብሔረሰቦች ምክር ቤት

የኮንሶ ዞን ሽግግር ምክር ቤት የ2019 ዓ.ም በጀትን ከ2.3 ቢሊዮን ብር በላይ በማጽደቅ 13ኛ መደበኛ ጉባዔውን አጠናቀቀ ካራት፡ ነሐሴ 04/2018 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ካራት)የኮንሶ ዞን ...
10/08/2026

የኮንሶ ዞን ሽግግር ምክር ቤት የ2019 ዓ.ም በጀትን ከ2.3 ቢሊዮን ብር በላይ በማጽደቅ 13ኛ መደበኛ ጉባዔውን አጠናቀቀ

ካራት፡ ነሐሴ 04/2018 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ካራት)

የኮንሶ ዞን ሽግግር ምክር ቤት የ2019 ዓ.ም በጀት ከ2.3 ቢሊዮን ብር በላይ በማጽደቅ 13ኛ መደበኛ ጉባዔውን አጠናቋል።
የግግር ምክር ቤቱ 13 መደበኛ ጉባኤ የምክር ቤት፣ የአስፈፃሚ መ/ቤቶች እና የፍርድ ቤት 2018 ዓ.ም አፈፃጸምና 2019 ዕቅድ መርምሮ በሙሉ ድምጽ ያጸደቅ ሲሆን ጉባዔው የኮንሶ ዞን የ2019 በጀት ዓመት በጀት 2,325,296,944 ብር እንዲሆን በሙሉ ድምፅ ጸድቋል።

የ2019 ዓ.ም ረቂቅ በጀትን በዝርዝር ያቀረቡት የዞኑ ምክር ቤት የመንግሥት በጀትና ፋይናንስ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ አያኖ ካውዳይታ ናቸው።

በቀረበው የበጀት ድልድል መሠረት፦

1 :- ከመንግሥት ግምጃ ቤት፡ 1,060,306,272 ብር

2:- መደበኛ ገቢ፡ 1,015,934,305 ብር

3:- የውጭ እርዳታ፡ 5,892,563 ብር

4:- የጤና ተቋማት ገቢ፡ 82,445,211 ብር

5:- የትምህርት ቤቶች ገቢ፡ 33,069,794 ብር

6:- የማዘጋጃ ቤት ገቢ፡ 127,648,799 ብር

በድምሩ 2,325,296,944 ብር (ሁለት ቢሊዮን ሦስት መቶ ሃያ አምስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ዘጠና ስድስት ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ አራት ብር) ሆኖ ፀድቋል።

የተፈቀደው በጀት በ2019 ዓ.ም የዞኑን የልማት፣ የሕዝብ አገልግሎትና ሌሎች የመንግሥት ዕቅዶችን ለማስፈፀም የሚውል ሲሆን፣ በጀቱ በታለመለት ዓላማ ላይ ብቻ በተገቢው መንገድ እንዲውል የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባዔ የተከበሩ አቶ ገልገሎ ኦቶማ አሳስበዋል።

የኮንሶ ዞን ሽግግር ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ጉባኤውን ጀመረካራት፡ ነሐሴ 04/2018 ዓ.ም የኮንሶ ዞን ሽግግር ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ጉባኤውን ጀመረ።በጉባኤው የእንኳን ደህና መጣችሁ መ...
10/08/2026

የኮንሶ ዞን ሽግግር ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ጉባኤውን ጀመረ

ካራት፡ ነሐሴ 04/2018 ዓ.ም

የኮንሶ ዞን ሽግግር ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ጉባኤውን ጀመረ።

በጉባኤው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የኮንሶ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክቡር አቶ ገልገሎ ኦቶማ፣ በዞኑ የተጀመረውን ልማት ለማጠናከርና የሰፈነውን አንጻራዊ ሰላም ለማጽናት ሁሉም የለውጥ ሐዋርያ ሊሆን እንደሚገባ ገልጸዋል።

አቶ ገልገሎ ኦቶማ እንደገለጹት፣ ሰላም የሁሉም ልማት መሠረት በመሆኑ፣ የዞኑ መንግሥት በሰጠው ትኩረት በአካባቢው የሰፈነው አንጻራዊ ሰላም አበረታች ለውጥ ነው። በመሆኑም በኮንሶ ሕዝብ ምክር ቤት ስም ለተደረገው ጥረት አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

ለሕዝቡ የሚታይ ለውጥ ለማምጣት አመራሩም ሆነ ባለሙያው በእውነትና በእውቀት ላይ ተመስርቶ መትጋት እንደሚገባውም አስገንዝበዋል።

በዞኑ ያሉ ጸጋዎችን ወደ ሀብት በመቀየር የሕዝቡን ልማት ለማረጋገጥ፣ አመራሩና ባለሙያው በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ ጠንካራ የሥራ ባህል በመገንባት ለትውልድ የሚተላለፍ አሻራ ማሳረፍ እንደሚጠበቅባቸውም አቶ ገልገሎ ገልጸዋል።

የ13ኛው መደበኛ ጉባኤ ዋና አጀንዳዎች

የኮንሶ ዞን ሽግግር ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ጉባኤ በርካታ አጀንዳዎችን የሚያይ ሲሆን፣ ከእነዚህም፦

የ13ኛ መደበኛ ጉባኤ አጀንዳ ማቅረብና ማጽደቅ፤

የ12ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ-ጉባኤ ማጽደቅ፤

የኮንሶ ዞን ምክር ቤት የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ማጠቃለያ ሪፖርት መመርመርና ማጽደቅ፤

የ2019 በጀት ዓመት የምክር ቤቱን ዕቅድ መመርመርና ማጽደቅ፤

የኮንሶ ዞን አስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ማጠቃለያ ሪፖርት መመርመርና ማጽደቅ፤

የአስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ መመርመርና ማጽደቅ፤

የኮንሶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ማጠቃለያ ሪፖርትና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ መመርመርና ማጽደቅ፤

የ2019 በጀት ዓመት የበጀት ረቂቅን መመርመርና ማጽደቅ

የሚሉት ዋና ዋና አጀንዳዎች ይገኙበታል።

‎የኮንሶ ዞን ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ጉባኤውን እየተሠሩ ባሉ ልማታዊ መስክ ምልከታ በማድረግ  በይፋ አስጀመረ፣‎‎ካራት:ነሐሴ 03/2018 ዓ.ም ‎‎የኮንሶ ዞን ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ጉ...
09/08/2026

‎የኮንሶ ዞን ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ጉባኤውን እየተሠሩ ባሉ ልማታዊ መስክ ምልከታ በማድረግ በይፋ አስጀመረ፣

‎ካራት:ነሐሴ 03/2018 ዓ.ም

‎የኮንሶ ዞን ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ጉባኤውን በልማታዊ መስክ ምልከታ አስጀመረ፣

‎በዞኑ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ገልገሎ ኦቶማ የተመራው የኮንሶ ዞን ምክር ቤት አባላት ልዑክ 13ኛ መደበኛ ጉባኤውን በካራት ከተማ አስተዳደር እየተሰሩ ያሉ የመንገድ መሠረተ ልማቶችን በመስክ ተመለከቱ፣

የዞኑ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበረ አቶ ‎ገልገሎ ኦቶማ በበኩላቸው ህዝብን ካስተባበርን የማይቻል ስራ አይኖርም ያሉት ሲሆን የከተማ አስተዳደር መዋቅር ያሳየው ብርቱ እንቅስቃሴ የሚደነቅ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

‎የካራት ከተማ ከንቲባ አቶ ጋሻሁን ኩሲያ እንደገለጹት ልማት ወዳድ ከመሆኑ የተነሳጨ ከብልጸግና መንግስት ጋር ለመተባበር ባለው ከፍተኛ ፍላጎት የመሠረተ ልማት ስራን በስኬት ማከናወኑን አስገንዝበዋል።

‎የመንገድ መሠረተ ልማት የህዝቡ ከፍተኛ ፍላጎት በመሆኑ መንግስት ከሚያደርገው ድጋፍ ጎን በመሆን ህዝቡ ከፍተኛ ተሳትፎ ያሳየ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ቀሪ ስራዎችን ክትትል እንደሚያደርጉም ገልጸዋል።

‎ከንቲባው አቶ ጋሻሁን የጋራ ልማት እስከሆነ ድረስ ተረባርበን መስራት ይጠበቅብናል ያሉት አቶ ጋሻሁን፤ህዝብን ከተቋማት ጋር ለማገናኘት ወሳኝ የሆኑ የመንገድ ከፈታ ስራዎችን እየተከናወኑ ሲሆን ህዝቡ በራሱ ተነሳሽነትና እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ የሚያስመሰግን መሆኑ አስረድተዋል።

‎የዞኑ ከተማና መሠረተ ልማት ምሪያ ኃላፊ አቶ ኩንዳርታ ኩታዬ በወቅቱ እንደገለጹት ከ9.2 ኪ ሜ በላይ የሆነ የመንገድ ከፈታ እንዲሁም በተያየዥ የውሃ መስመር ዝርጋታ በከተማው እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

‎የመስክ ምልከታው ልዑክ በሰጡት አሰተያየት በቅንጅት እየተሠራ ያለው የመንገድ ስራ ህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ እያደረገ እንደሚገኝ ጠቅሰው፣የተቀናጀ ልማታዊ ስራዎች እየተከናወኑ ስራዎች ባሉበት ወቅት ህዝቡ ያሳየው የነቃ ተሳትፎ እጅግ የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል።

ለምክር ቤቶች ከተሰጡት ስልጣናት መካከል የህዝብን ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ክትትል ማድረግ አንዱ በመሆኑ እየተከናወኑ ያሉ ልማታዊ ስራዎችን ብሎም ደግሞ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራም ተመላክቷል።

‎የዞኑ ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ጉባኤው ከነገ ጀሞሮ የሶስቱ የአስፈጻሚ አካላት የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ፣የ2019 በጀት ማጽደቅ፣የቀጣይ የ2019 ዕቅድ ዙሪያ እንደሚመክር እንደዚሁም የተለያዩ አጀንዳዎች እንደሚኖሩም ምክር ቤቱ አስታውቋል።

‎የኮንሶ ዞን ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ጉባኤውን ነሐሴ 4 እና 5/2018 ዓ.ም እንደሚያካሂድ አስታወቀ፣‎‎ካራት:ነሐሴ 01/2018 ኮንሶ ካራት//የኮንሶ ዞን ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ጉባኤ...
07/08/2026

‎የኮንሶ ዞን ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ጉባኤውን ነሐሴ 4 እና 5/2018 ዓ.ም እንደሚያካሂድ አስታወቀ፣

‎ካራት:ነሐሴ 01/2018 ኮንሶ ካራት//
የኮንሶ ዞን ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ጉባኤውን ነሐሴ 4 እና 5/2018 ዓ.ም ይካሄዳል ከዝህ ቀን ቀደም ብሎ 3/12/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ለምክር ቤት አባላት የስልጠና መድረክ ስለሚኖራቸው ሁሉም የምክር ቤቱ አባላት ሰዓትን በማክበር በዞኑ ምክር ቤት አዳራሽ እንዲገኙም ምክር ቤቱ ጥሪውን ያስተላልፏል።

‎የዞኑ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ገልገሎ ኦቶማ በሰጡት መግለጫ የዞኑ ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ጉባኤውን በመጪው ነሐሴ 4-5/2018 ዓ.ም ለማካሄድ ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጸዋል።

‎ዋና አፈ ጉባኤው የተከበሩ አቶ ገልገሎ አክለውም የምክር ቤቱ አባላት ለወከሉት ህዝብ ክብር ሲሉ ሰዓትን በማክበር በምክር ቤት አዳራሽ እንዲገኙ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ተጋባዥ እንግዶችም በተመሳሳይ በተባለው ሰዓትና ቦታ እንዲገኙ አሳስበዋል።

‎በ13ኛ መደበኛ ጉባኤው የሶስቱ የአስፈጻሚ አካላት የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት፣የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ግምገማ፣የ2019 በጀት ማጽደቅ እንዲሁም ሌሎች አጀንዳዎች ይኖራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ አመላክቷል።

‎በተያያዘም የምክር ቤት አባላት በቀን 03/12/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ ስልጠና ስለሚኖራቸው በምክር ቤት አዳራሽ እንዲገኙ ምክር ቤቱ ጥሪውን አስተላልፏል።

በኮንሶ ዞን ሠገን ዙሪያ ወረዳ የተካሄደው የ«ሁለንተናዊ እርቀ ሰላም ኮንፈረንስ» በሰላም መጠናቀቁን ተከትሎ የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የምስጋና መልዕክት አስተላለፉካራት፣ ሐምሌ 28/201...
04/08/2026

በኮንሶ ዞን ሠገን ዙሪያ ወረዳ የተካሄደው የ«ሁለንተናዊ እርቀ ሰላም ኮንፈረንስ» በሰላም መጠናቀቁን ተከትሎ የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የምስጋና መልዕክት አስተላለፉ

ካራት፣ ሐምሌ 28/2018 ዓ.ም. (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን)

በኮንሶ ዞን ሠገን ዙሪያ ወረዳ "ሁለንተናዊ እርቀ ሰላም ኮንፈረንስ ለወረዳው ሁለንተናዊ ብልጽግና" በሚል መሪ ቃል የተካሄደው ኮንፈረንስ በሰላም መጠናቀቁን ተከትሎ፣ የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ገለቦ ጎልቶሞ ለኮንፈረንሱ ስኬት አስተዋጽኦ ላደረጉ ሁሉ የምስጋና መልዕክት አስተላልፈዋል።

ክቡር አቶ ገለቦ በመልዕክታቸው፣ የእርቀ ሰላም ኮንፈረንሱ ሕዝቡን በጠንካራ የሰላም መሠረት ላይ ለማቆም፣ በማኅበረሰቡ ውስጥ የነበሩ ቂምና በቀልን በይቅርታና በፍቅር በመተካት ዘላቂ አንድነትና አብሮነት ለመገንባት የታለመ መሆኑን ገልጸዋል።

ሕዝቡም የሰላም ጥሪውን በመቀበል ወደ ወንድማማችነትና አንድነት መመለሱ ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየ ታሪካዊ ክንውን መሆኑን ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም ለኮንፈረንሱ ስኬት ከሩቅና ከቅርብ በመገኘት ድጋፍ ላደረጉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የዞን አመራሮች፣ የአጎራባች ዞኖችና ወረዳዎች አመራሮች፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የክልሉ ፀጥታ አካላት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሰላም ኮሚቴዎች፣ የወረዳው አመራሮች፣ ወጣቶች፣ ሚሊሻ አባላት እና መላው ማኅበረሰብ በዞኑ ሕዝብና በራሳቸው ስም ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።

አቶ ገለቦ በቀጣይም የተገኘውን የሰላም አየር በማጠናከር ሁሉም አካላት የየድርሻቸውን በመወጣት ከዚህ ቀደም ያመለጡ የልማት ዕድሎችን በአንድነት በመጠቀም ሕዝቡን በልማት ለመካስና የአካባቢውን ገጽታ በጋራ ጥረት ለመቀየር መስራት እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።

በመጨረሻም ሰላም የሁሉም ነገር መሠረትና የሕይወት ዋስትና መሆኑን በማስታወስ፣ ሁሉም የሰላምን ዋጋ በመገንዘብ ለሰላም ማጽናት በንቃት እንዲሳተፍና የሰላም መልዕክተኛ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።

"ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!" በማለትም የምስጋና መልዕክታቸውን አጠናቀዋል።

መረጃው ፦ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን ነው

‎የኮንሶ ዞን ምክር ቤት የአስፈጻሚ ተቋማት የ2018 በጀት ዓመት ማጠቃለያ  አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ግምገማ ማካሄድ ጀመረ፣‎‎ካራት:ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም ኮንሶ...
03/08/2026

‎የኮንሶ ዞን ምክር ቤት የአስፈጻሚ ተቋማት የ2018 በጀት ዓመት ማጠቃለያ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ግምገማ ማካሄድ ጀመረ፣

‎ካራት:ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም ኮንሶ ካራት

‎ምክር ቤቱ የአስፈጻሚ ተቋማት የ2018 በጀት ዓመት ማጠቃለያ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ግምገማ በዛሬው ዕለት ጀምሯል።

‎የዞኑ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ገልገሎ ኦቶማ በግምገማው ማስጀመሪያ መርሃግብር ወቅት እንደገለጹት የአስፈጻሚ ተቋማት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ዋና አላማው የተቋማት አፈጻጸም አቅምን መለየትና የተቋማቱን ጥንካሬ ለማስቀጠልና ጉድለቶችን እንዲታረሙ በማድረግ ተቋማት በተሻለ በመፈጸም የህዝብን ተጠቃሚነት እንዲያረጋግጡ ለማስቻል መሆኑን ተናግረዋል።

‎የአስፈጻሚ ተቋማት ግምገማ በሶስቱም ዘርፎች በአፈጻጸም ሪፖርትን የታዩ ጉድለቶችን በነጥብ በነጥብ ተለይተው በግብረ መልስ ለተቋማቱ የማድረስ ስራ እንደሚሠራ የገለጹት የተከበሩ አቶ ገልገሎ፤የሶስቱ ዘርፎች የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች አፈጻጸሙን በጥልቀት በመመርመር የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ትኩረት መስጠት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

‎በዛሬ የግምገማ መርሃግብር መሠረት በህግ ፍትህ መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዘርፍ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በዘርፉ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ገረሙ ካይሲሞ ተገምግሟል።

‎በሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ዘርፍ ደግሞ የስራና ክህሎት መምሪያ፣የካራት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዘርፉ ቋሚ ኮሚቴ ተወካይ የተከበሩ አቶ ኤሬኬ ገየቶ ግምገማ ተደርጓል።

‎በበጀት ፋይናንስ መንግስት ሀብት ቁጥጥር ዘርፍ ደግሞ የዞኑ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ፣ገቢዎች መምሪያ በዘርፉ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ አያኖ ካውዳይታ የተገመገሙ ሲሆን በቀጣይ ቀናት ቀሪ አስፈጻሚ ተቋማት ግምገማ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

ግብርን በወቅቱ በመክፈል የህዝቡን የመልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ ሁሉም ግዴታውን ሊወጣ እንደሚገባ የኮንሶ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ገልገሎ ኦቶማ አሳ...
07/07/2026

ግብርን በወቅቱ በመክፈል የህዝቡን የመልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ ሁሉም ግዴታውን ሊወጣ እንደሚገባ የኮንሶ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ገልገሎ ኦቶማ አሳሰቡ፣

‎የዞኑ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ገልገሎ ኦቶማ የ2019 የግብር መክፈያ ጊዜ፣የንግድ ስራ ፍቃድ የሌላቸው ፍቃዱን እንዲያወጡ፣ነባር ንግድ ፍቃድ ያላቸው ደግሞ የማሳደሻ ጊዜ መድረሱን ተከትሎ መግለጫ ሰጥተዋል።

‎የዋና አፈ ጉባኤው መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል።

‎የ2019 በጀት ዓመት የግብር መክፈያ ወቅት ከሐምሌ 01/2018 ዓ.ም በይፋ እንደሚጀምር የገለጹት የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ገልገሎ፤የንግድ ስራ ፍቃድ የሌላቸው አዲስ የንግድ ስራ ፍቃድ እንዲያወጡ እንደዚሁም ነባር የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው ደግሞ የማሳደሻ ጊዜው በመሆኑ ሁሉም የበኩሉን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

‎ታታሪው ህዝባችን በዘንድሮ ምርጫ ያሳየውን ድል በግብር ልደግም ይገባል ያሉት የተከበሩ አቶ ገልገሎ፤ግብር ለሀገር ክብር መሆኑን ተገንዝበን በተያዘልን ጊዜ ገደብ በፊት በነቂስ ወጥተን ግብርን በመክፈል የልማት አርበኝነታችንን ማረጋገጥ ከሁላችንም የሚጠበቅ ግዴታ መሆኑን አስገንዝበዋል።

‎ግብር የልማት ሁሉ መሠረት ነው ያሉት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ገልገሎ፤በየተዋረድ የሚገኙ የወረዳና የቀበሌ ምክር ቤቶች ግብር አሰባሰብ ተግባር ግንባር ቀደም ሚናቸውን በኃላፊነት እንዲወጡ በዞኑ ምክር ቤት ስም አሳስባለሁ።

‎"ግብር ለሀገር ክብር፤ግብርን በወቅቱ መክፈል የልማት አርበኝነት መገለጫም ነው!"

‎ (የተከበሩ አቶ ገልገሎ ኦቶማ)
‎ የኮንሶ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ
‎ሰኔ 29/2019 ዓ.ም

የኮንሶ ዞን ምክር ቤት ሲያካሂድ የቆየው የ2018 በጀት ዓመት የ3ኛ ሩብ ዓመት የአስፈፃሚ ተቋማት ግምገማ ልማታዊ መስክ ምልከታ በማድረግ አጠናቀቀ፣‎‎በኮንሶ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ...
20/05/2026

የኮንሶ ዞን ምክር ቤት ሲያካሂድ የቆየው የ2018 በጀት ዓመት የ3ኛ ሩብ ዓመት የአስፈፃሚ ተቋማት ግምገማ ልማታዊ መስክ ምልከታ በማድረግ አጠናቀቀ፣

‎በኮንሶ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ገልገሎ ኦቶማ የተመሩት የቋሚ ኮሚቴዎች ልዑክ በ2018 በጀት የ3ኛ ሩብ ዓመት የአስፈፃሚ ተቋማት አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ መሠረት በተጨባጭ በመሬት ላይ ያሉ ተግባራትን ለማረጋገጥ በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች ተዘዋውረው ልማታዊ መስክ ምልከታ አደረጉ፣

‎ልዑካኑ በካራት ከተማ አስተዳደር የካይሌ ውሃ ፕሮጀክት ያለበት ደረጃ፣ከካራት-ሠገን ከተማ እየተሠራ ያለው መንገድ፣በሠገን ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ያሉ ተጠርጣሪዎች ሰብዓዊ መብት አያያዝ፣የሠገን መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አጠቃላይ ሁኔታ እንደዚሁም ጥገና የተደረገለት የወረዳው አስተዳደር ህንፃ፣በቤቾ ቀበሌ የጤፍና የማሾ የበልግ አዝመራ ምልከታ አካሂደዋል።

‎ምክር ቤቱ ከመቼውም በላይ የህዝብን ተጠቃሚነት በተግባር ለማረጋገጥ በመስክ ምልከታ የታጀበ የክትትል ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያስገነዘቡት የተከበሩ አቶ ገልገሎ፤አስፈላጊ ልማትን ለማረጋገጥ ሁሉም ለህዝብ ተጠቃሚነት መትጋት እንደሚኖርበት ጨምረው አሳስበዋል።

‎የመስክ ምልከታው ልዑካን በሰጡት አስተያየት እየተሠሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው በመቀጠል የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መረባረብ ይጠበቅብናልም ብለዋል።

‎በካራት ከተማ አስተዳደር የካይሌ ውሃ ስራ የተሻለ አፈፃፀም ላይ እንደሚገኝ የተመለከቱ ሲሆን ከካራት- ሠገን የሚወስድ መንገድ በሚጠበቀው ፍጥነት እንዳይሠራ የነዳጅ እጥረት ችግር ለማስተጓጐል እየዳረገ መሆኑን ተመልክተው የህዝቡ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የአጭር ጊዜ መፍትሄዎችን መፈለግ እንደሚያስፈልግ የምልከታው ልዑኩ አመላክቷል።

‎በአፈፃፀም ግምገማ ሪፖርት ላይ በጉድለትም ሆነ በጥንካሬ የገመገምናቸው ጉዳዮችን በተጨባጭ በምልከታው ማረጋገጥ ችለናል ያሉት ልዑካኑ፤በጉድለት የተገመገሙ ነጥቦችን በማጠናከር ለሚመለከታቸው አካላት በግብረ መልስ በማድረስ የህዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሠሩም አረጋግጠዋል።

‎በመጨረሻም ልዑካኑ ከመለጋና ዱጋያ በተፈጥሮ የጎርፍ አደጋ ምክንያት ለተፈናቀሉ ተፈናቃዮች እየተደረገ ያለው የምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ድጋፍ መርሃግብርንም ተመልክተዋል።




የኮንሶ ዞን ምክር ቤት የ2018 በጀት ዓመት የ3ኛ ሩብ ዓመት የአስፈጻሚ ተቋማት አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀመረ፣‎‎የዞኑ ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ገልገሎ ኦቶማ በግምገማ መ...
20/05/2026

የኮንሶ ዞን ምክር ቤት የ2018 በጀት ዓመት የ3ኛ ሩብ ዓመት የአስፈጻሚ ተቋማት አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀመረ፣

‎የዞኑ ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ገልገሎ ኦቶማ በግምገማ መርሃ ግብር ማስጀመሪያ ወቅት እንደገለፁት ምክር ቤቱ የተጠናከረ የአስፈፃሚ ተቋማት ግምገማ ስርዓትን በመዘርጋት የህዝብን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ስራ ሲሠራ መቆየቱን ገልጸዋል።

‎የተከበሩ አቶ ገልገሎ አክለውም አሁን ያለንበት ወቅት የ7ኛ አገራዊ ምርጫ ተልዕኮዎች የሚፈፀሙበት ወቅት ቢሆንም የተቋማትን የመፈፀም አቅም ለማሳደግና የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሲባል ሌሎች ተግባራት ሳይጉላሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ ግምገማውን ለማጠናቀቅ አጭር የአስፈፃሚ ተቋማት የግምገማ መርሃ ግብር ማውጣታቸውን ጠቅሰው ግገማውም በመስክ ምልከታ የታጀበ እንደሚሆንም ጠቁመዋል።

‎በመርሃ ግብሩ መሠረት በበጀት ፋይናንስ የመንግስት ሀብት ቁጥጥር ዘርፍ የግብርና መምሪያ እና የንግድና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ፣ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ እንደዚሁም የውሃና ኢነርጂ ልማት መምሪያዎች በዘርፉ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በተከበሩ አቶ አያኖ ካውዳይታ አማካኝነት እንደሚገመገሙ ተመላክቷል።

‎በህግ ፍትህ መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዘርፍ ፍትህ መምሪያ፣ሠላምና ፀጥታ መምሪያ፣ፖሊስ መምሪያ፣ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ በዘርፉ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በተከበሩ አቶ ገረመው ካይሲሞ አማካኝነት ግምገማው እንደሚከናወን ተጠቅሷል።

‎በሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ዘርፍ ትምህርት መምሪያ፣ባህልና ስፖርት መምሪያ፣ጤና መምሪያ እንዲሁም ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ በዘርፉ ቋሚ ኮሚቴ ተወካይ በክብርት ወ/ሮ ዝናሽ ቢታማ አማካኝነት እንደሚገመገሙ ከምክር ቤቱ የተገኘ መረጃ አመላክቷል።

‎የግምገማ ሂደት በመስክ ምልከታ መታጀቡ በይበልጥ የአስፈፃሚ ተቋማት ጥንካሬና ጉድለት ለመለየት እንደሚያግዝ የገለፁት የዞኑ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ገረመው አያኖ፤የዘርፉ ቋሚ ኮሚቴዎች በግምገማው ሂደት የአስፈፃሚ ተቋማትን ጥንካሬና ጉድለት በሚገባ በመለየት ጉድለቶች እንዲታረሙና ስኬቶችን ለማስቀጠል ግብረ-መልስ የመስጠት ተግባር እንደሚከናወንም ተገልፃዋል

Address

Konso Arbaminch
Konso

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Konso Zone Council Office ኮንሶ ዞን ምክር ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Konso Zone Council Office ኮንሶ ዞን ምክር ቤት:

Shortcuts

Share