Konso Zone Karat Town Adiminstration Revenue office -ኮ/ዞ/ካ/ከ/አስ/ር ገቢዎች ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Konso
  • Konso Zone Karat Town Adiminstration Revenue office -ኮ/ዞ/ካ/ከ/አስ/ር ገቢዎች ጽ/ቤት

Konso Zone Karat Town Adiminstration Revenue office -ኮ/ዞ/ካ/ከ/አስ/ር ገቢዎች ጽ/ቤት ይህ ትክክለኛ የኮንሶ ዞን ካራት ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት ገጽ ስለሆነ ግብርን በተመለከተ መረጃ ለማግኘት ገጹን ይከተሉት. >

በኢ-ክሊራንስ መተግበሪያ የሚሰጡ አገልግሎቶች ግንቦት 22/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)"ኢ-ታክስ" ታክስን ለማሳወቅ፣ ክፍያን ለማከናወን፣ ከዕዳ ነጻ ማረጋገጫ (Tax Clearance)...
04/06/2026

በኢ-ክሊራንስ መተግበሪያ የሚሰጡ አገልግሎቶች

ግንቦት 22/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

"ኢ-ታክስ" ታክስን ለማሳወቅ፣ ክፍያን ለማከናወን፣ ከዕዳ ነጻ ማረጋገጫ (Tax Clearance) ፣ የተለያዩ ታክስ ነክ ማብራሪያዎች እና ግብር ከፋዮች የራሳቸውን የታክስ መረጃ ለማየት እንዲሁም ሌሎች ተጨማሪ አገልግሎቶችን በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ለማግኘት የሚያስችል ሥርዓት ነው፡፡

በዚህ ሥርዓት ከሚሰጡ አገልግሎቶች ውስጥ ግብር ከፋዩ በየትኛውም ቦታና በማንኛውም ጊዜ (ሰዓት) የኢ-ክሊራንስ አገልግሎትን ማግኘት ይችላል፡፡

እቤትዎ ሆነው የፋይዳ መለያ ቁጥሮዎን ከግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ጋር ለማስተሳሰር ከዚህ በታች ያለውን ልንክ ይጠቀሙ !! https://mor-migration.fayda.et
25/02/2026

እቤትዎ ሆነው የፋይዳ መለያ ቁጥሮዎን ከግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ጋር ለማስተሳሰር ከዚህ በታች ያለውን ልንክ ይጠቀሙ !! https://mor-migration.fayda.et

አስቸኳይ ማስታወቂያ በመሆኑ ለግብር ከፋዮቻች ቶሎ እንድደርስ መልዕክቱን ለማስተላለፍ ይተባበሩን !!
25/02/2026

አስቸኳይ ማስታወቂያ በመሆኑ ለግብር ከፋዮቻች ቶሎ እንድደርስ መልዕክቱን ለማስተላለፍ ይተባበሩን !!

‎የካራት ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት የአልጋ ክፍል ይዞታ ክፊያ ዙሪያ ከሆቴልና አልጋ ቤት ባለቤቶች ጋር ውይይት አድርጓል። ‎‎የካራት ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ንጋቱ...
24/02/2026

‎የካራት ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት የአልጋ ክፍል ይዞታ ክፊያ ዙሪያ ከሆቴልና አልጋ ቤት ባለቤቶች ጋር ውይይት አድርጓል።

‎የካራት ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ንጋቱ በሪሶ የሆቴል ቱሪዝም ዘርፍ የከተማው ዋነኛ የገቢ ምንጭ በመሆኑ እንደ ኮንሶ ያለው የተፈጥሮ ፀጋዎችና የቱሪስት መስህቦችን ተከትሎ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን የቱሪስት ፍሰት የሚመጥን ገቢ ማግኘት አለበት ሲሉ ገልጸዋል።

‎በከተማው ያለውን የገቢ አማራጮችን በመለየትና ለመሰብሰብ ይረዳ ዘንድ የአልጋ ክፍል ይዞታ ክፊያ ጥናት ተካሂዶ በከተማው ም/ቤት ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ ወደ ሥራ እንደምገባ ተናግረዋል።

‎የአልጋ ክፍል ይዞታ ክፊያ ዓላማው እያደገ ከመጣው የቱሪዝም መስፋፋት ጋር ተያይዞ የቱሪስት መዳረሻዎችን ይበልጥ ለማልማት ፣ ከተማው በራሱ ገቢ ወጪውን እንዲሸፍን ለማስቻል እንደሆነ ተገልጿል።

‎በጽ/ቤቱ የታክስ ሞዴርናይዜሽንና ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ዳይሮክቶሬት አስተባባሪ በአቶ ኩናሌ ኩርሻይቴ ኮንሴ የአልጋ ክፍል ይዞታ ክፊያ ዙሪያ የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።

‎የአልጋ ክፍል ይዞታ ክፊያ ለማስከፈል የአልጋ ቤቶቹ ተለይተው የአልጋ ኪራያቸው ከ500 ብር በላይ የሆነው ድርጅቶች የመሰብሰብ ግደታ እንዳለባቸውና የክፊያ መጣኔውም 2.5% (ሁለት በመቶ) እንደሚሆን በሰነዱ ተጠቅሷል።

‎አንድ የማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ የሚሰበሰብ የሆቴል ክፍል አከራይ ድርጅት/ግለሰብ በየወሩ የሰበሰበውን ገቢ በቀጣዩ ወር ባሉት 30 ቀናት ውስጥ ገቢውን ማሳወቅ እንደሚኖርበት ተገልጿል።

‎ለከተማው ዕድገት ገቢ ወሳኝ መሆኑን ተሳታፊዎች ተናግረው በከተማው ለእንግዶች የሚሆን የውሃ እጥረት ፣ የመብራት መቆራረጥ ፣ ሽንት ቤቶች በየጊዜው እና በየቦታው ሞልተው እየፈሰሰ በመሆኑ ፣ እና መሰል ችግሮች እንግዶችቻችን በከተማዋ አልጋ ይዘው ከማደር አልፈው ወደ ሌላ ከተማ እየሄዱ ገቢያችን እያጣን በመሆኑ የሚመለከተው የመንግሥት አካል ኃላፊነቱን እንዲወጣ ገልጸዋል።

‎ከደረሰኝ አቆራረጡ በሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ እንድሆን እና በሌሎች የተነሱ ችግሮችንና ጥያቄዎች ለመፍታት ጽ/ቤቱ ከኮንሶ ዞን ገቢዎች መምሪያ ጋር በቅንጅት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል።

‎ኮንሶ ካራት ፡ የካቲት 17/2018 ዓ.ም

‎የኮንሶ ዞን ካራት ከተማ አስ/ር ገቢዎች ጽ/ቤት በአዲሱ ተቋማዊ የሪፎርም ሥራ ማለቁን ተከትሎ ውይይት አካሂዷል። ‎‎የጽ/ቤቱ ኃላፊ የሆኑት አቶ: ንጋቱ በርሶ ተቋዋሚ ሪፎርም  የገቢ አሰባ...
31/01/2026

‎የኮንሶ ዞን ካራት ከተማ አስ/ር ገቢዎች ጽ/ቤት በአዲሱ ተቋማዊ የሪፎርም ሥራ ማለቁን ተከትሎ ውይይት አካሂዷል።

‎የጽ/ቤቱ ኃላፊ የሆኑት አቶ: ንጋቱ በርሶ ተቋዋሚ ሪፎርም የገቢ አሰባሰብ ተልኮውን የበለጠ ውጤታማ የሚያደርግ እና በጥናት ላይ የተመሠረተ መሆኑን ገልጸዋል።

‎በሪፎርሙ መሠረት በጽ/ቤቱ የሰዉ ሀብት በኩል ለሁሉም ሠራተኞች ደብዳቤ የተሰጠ ሲሆን በተቋማዊ ሪፎርም እና የአፈጻጸም መመሪያ መሠረት በተሰጠው የሥራ መደብ ላይ ገለጻና ማብራሪያ ተሰጥቷል።

‎በተቋማዊ ሪፎረም መሠረት የተደረገው የሰራተኛ ድልድል ግልጽ እና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ የተሠራ በመሆኑ ሠራተኛው በተመደበበት ሥራ ሂደት እና ሥራ መደብ በትጋት ሥራውን መሥራት እንዳለበት ተገልጿል።

‎በመጨረሻም በአዲሱ ተቋሟዊ ሪፎርም መሠረት ከሰኞ ማለትም ከቀን 25/05/2018 ዓ.ም ጀምሮ ሠራተኞቹ በመደባቸው መሥራት እንደሚጀምሩ መግባባት ላይ ተደርሶ ውይይቱ ተጠናቋል።

‎ ጥር 23/05/2018 ዓ.ም

‎‎የኮንሶ ዞን ካራት ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት የአድሱ ገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል የወጣ አዋጅ ቁጥር 1395/2017  ዙርያ ለደረጃ ''ለ'' በቀድሞ የደረጃ ''ሐ'' ግብር ከፋዮች...
21/01/2026

‎‎የኮንሶ ዞን ካራት ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት የአድሱ ገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል የወጣ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ዙርያ ለደረጃ ''ለ'' በቀድሞ የደረጃ ''ሐ'' ግብር ከፋዮች ሥልጠና ሰጥቷል ።

‎የኮንሶ ዞን ካራት ከተማ አስ/ር ገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ንጋቱ በርሶ በመክፈቻ ንግግራቸው አድሱ የገቢ ግብር አዋጅ መንግሥት ጥናት በማድረግ ያወጣ በመሆኑ ሁሉም ግብር ከፋይ በፍትሀዊነት የሚያስከፍል መሆኑን በመግለፅ ሥልጠናው በይፋ አስጀምረዋል ።

‎ለሥልጠናው የተዘጋጀው ሠነድ በምጣኔ ጥናት የታክስ ትምህርት እና ቅሬታ አጣሪ ዳይሬክቶረት ባለሙያ በሆኑት አቶ ካሣቦ ካሣዬ ከቀረበው በኃላ ሰፊ ማብራሪያ እና አስተያየቶች ከግብር ከፋዮች ተነስቷል።

‎ለሥልጠናው የተዘጋጀው ሠነድ በዋናነት የዳሰሰው በየሩብ ዓመት በደረጃ ''ለ'' ግብር ከፋዮች የሚከፈለው 25% ወይም 1/4 አከፋፈል እና የመክፊያ ጊዜ ሠለዳ መሆኑ ተገልጿል።

‎የሥልጠናው ዓላማው በደረጃ ለ ግብር ከፋዮች በየሩብ ዓመት የሚከፈለው 1/4 ግብር ያልከፈሉትን ግብር ከፋዮች በመለየት ልዩ ትኩረት በመስጠት እንድከፍሉ ለማድረግ እና ቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ እንደሆነ ተገልጿል ።

‎በማጠቃለያ ንግግራቸው የጽ/ቤቱ ኃላፊ የሆኑት አቶ ንጋቱ በሪሶ እንደገለፁት በየሩብ ዓመት የሚከፈለውን 25 % ያልከፈሉት በተጨማሪ በተሰጠው ጊዜ ገደብ እንድከፍሉ በመግለፅ እስከ ጥር 30/2018 ዓ.ም ሥራው መጠናቀቅ እንዳለበት አስገንዝበዋል።

‎ ጥር 13/2018 ዓ.ም
‎ ካራት





18/01/2026
አስቸኳይ ማስታወቂያ እና የሥልጠና ጥሪ ለካራት ከተማ አስተዳደር በቀድሞው የደረጃ ''ሐ'' በአሁኑ የደረጃ ''ለ'' ግብር ከፋዮች:-
15/01/2026

አስቸኳይ ማስታወቂያ እና የሥልጠና ጥሪ ለካራት ከተማ አስተዳደር በቀድሞው የደረጃ ''ሐ'' በአሁኑ የደረጃ ''ለ'' ግብር ከፋዮች:-

‎የካራት ከተማ አስ/ር ገቢዎች ጽ/ቤት በዞኑ ገቢዎች መምሪያ የድጋፍ እና ክትትል ቲም የተሰጠለት ግብረ መልስ ላይ ከሚመለከተው የጽ/ቤቱ ሠራተኞች ጋር ውይይት አካሂዷል።‎‎የኮንሶ ዞን ገቢዎ...
13/01/2026

‎የካራት ከተማ አስ/ር ገቢዎች ጽ/ቤት በዞኑ ገቢዎች መምሪያ የድጋፍ እና ክትትል ቲም የተሰጠለት ግብረ መልስ ላይ ከሚመለከተው የጽ/ቤቱ ሠራተኞች ጋር ውይይት አካሂዷል።

‎የኮንሶ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ የሆኑት አቶ ካሣሁን ገረሙ በውይይቱ ላይ በመገኘት የገቢ ተቋሙን ለመደገፍ የተመደቡ ባለሙያዎች የሠሩትን ሥራ በመግለጽ የተቋሙ እቅድ ክንውን ያለበት ደረጃ እና የባለሙያዎች የሥራ ተነሳሽነት ጋር ተያይዘው ከጽ/ቤቱ አመራር እና ሥራተኞች በተገኙበት ውይይት ተደርጓል።

‎በውይይቱ ከሠራተኞች የተለያየ ሀሳቦች የተነሱ ስሆን ለሥራ ትኩረት የማይሰጡ ፣ የሥራ ሰዓት የማያከብሩ ሠራተኞች ላይ አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ እንደሚወስድ የጽ/ቤቱ ኃላፊ በሆኑት አቶ ንጋቱ በርሶ ሰፊ አስተያየት እና ማብራሪያ ተስጥቷል።

‎ የውይይቱ ዓላማ ያልተሠሩ ሥራዎች ላይ ትኩረት በመስጠት ተጨማሪ የሥራ ስምሪት ለመስጠት እና ቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ እንደሆነ ተገልጿል ።

‎ ወደ ጽ/ቤቱ ለድጋፍ እና ክትትል የተመደቡት ባለሙያዎች እንደገለፁት የገቢ ጉዳይ በአንዳንድ አካላት ብቻ የሚተገበር ሳይሆን የሁሉም ባለሙያዎች ትኩርት የሚጠይቅ በመሆኑ በጽ/ቤቱ በተደጋጋሚ የሚታየው ክፍተት መፍትሔው የተቋሙ ባለሙያዎች እንደሆነ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

‎አቶ ካሳሁን ገረሙ በማጠቃለያ ንግግራቸው እንደገለፁት የዛሬው ውይይት የመጀመሪያ ስሆን ቀጣይነት እንዳለው በመግለፅ ሁሉም ባለሙያ ለተመደበበት ሥራ በአግባቡ የማይሠራ ከሆነ ጽ/ቤቱ ወደ ማስጠየቅ ሥራ እንደሚሸጋገር አሳስቧል።

‎ ጥር 05/2018 ዓ.ም
‎ ኮንሶ-ካራት

Address

Konso

Opening Hours

Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00

Telephone

+251945305132

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Konso Zone Karat Town Adiminstration Revenue office -ኮ/ዞ/ካ/ከ/አስ/ር ገቢዎች ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share