Fogera woreda communication affairs office

Fogera woreda communication affairs office ወቅታዊ መረጃ ለህብረተሰቡ ማድረስ

በደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ ወረዳ በቁሃር ሚካኤል ቀበሌ የሚገኘው ሞዴል የችግኝ ጣቢያ ለ2019 በጀት አመት ለሰፋፊ ክላስተር ተከላ የሚውሉ የተለያዩ ችግኞች ማለትም የአቦካዶ፣ የማንጎ እና የ...
05/09/2026

በደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ ወረዳ በቁሃር ሚካኤል ቀበሌ የሚገኘው ሞዴል የችግኝ ጣቢያ ለ2019 በጀት አመት ለሰፋፊ ክላስተር ተከላ የሚውሉ የተለያዩ ችግኞች ማለትም የአቦካዶ፣ የማንጎ እና የሌሎች ዝግጅት ከፊል ገፅታ በምስል !

ለተጨማሪ ወቅታዊና ፈጣን መረጃ ገፆቻችን ይወዳጁ!
Facebook: https://facebook.com/fogeraworedacommunicationoffice
Telegram: https://t.me/fogeracomm
Twitter: https://x.com/fogeraworeda
YouTube: www.youtube.com/

ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም
ፎገራ ኮሙዩኒኬሽን

በደቡብ ጎንደር ዞን የፎገራ ወረዳ አስተዳደር የጳጉሜን  ቀናት በሚከናወኑ የመንግስት እና የፓርቲ ስራዎች ዙሪያ ከወረዳው አመራሮች ጋር ተወያይተዋል። ‎ በደቡብ ጎንደር ዞን የፎገራ ወረዳ የ...
05/09/2026

በደቡብ ጎንደር ዞን የፎገራ ወረዳ አስተዳደር የጳጉሜን ቀናት በሚከናወኑ የመንግስት እና የፓርቲ ስራዎች ዙሪያ ከወረዳው አመራሮች ጋር ተወያይተዋል። ‎

በደቡብ ጎንደር ዞን የፎገራ ወረዳ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በቀጣይ ቀናት የሚከበረውን አምስቱን የጳጉሜ ቀናት ስያሜና አከባበር መሰረት ያደረገ የውይይት መድረክ እያካሄዱ ነው።

በውይይቱም !
ጳጉሜ 1 የእምርታ ቀን
ጳጉሜ 2 የማንሰራራት ቀን፣
ጳጉሜ 3 የፅናት ቀን፣
ጳጉሜ 4 የህብር ቀን፣
ጳጉሜ 5 የነገ ቀን በሚል መሰየማቸውን በመድረኩ ተመላክቷል።
ጳጉሜን ለስራ፣ ጳጉሜን ለበጎ አድራጎት፣ ጳጉሜን ለንቅናቄ፣ ጳጉሜን ለተሻለ እቅድ ማዘጋጃ መጠቀም ተገቢ እንደሆነም ተገልጿል።

ለተጨማሪ ወቅታዊና ፈጣን መረጃ ገፆቻችን ይወዳጁ!
Facebook: https://facebook.com/fogeraworedacommunicationoffice
Telegram: https://t.me/fogeracomm
Twitter: https://x.com/fogeraworeda
YouTube: www.youtube.com/
ነሀሴ 30/2018 ዓ.ም
የፎገራ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን

የጳጉሜን ቀናት በአግባቡ መከበር ለመጭው ዘመን ስኬታማ እና ውጤታማ ስራዎች መሰረት ጥለው እንደሚያልፉ ተጠቆመየደቡብ ጎንደር ዞን በቀጣይ ቀናት በሚከናወኑ የመንግስት እና የፓርቲ ስራዎች ዙሪ...
04/09/2026

የጳጉሜን ቀናት በአግባቡ መከበር ለመጭው ዘመን ስኬታማ እና ውጤታማ ስራዎች መሰረት ጥለው እንደሚያልፉ ተጠቆመ

የደቡብ ጎንደር ዞን በቀጣይ ቀናት በሚከናወኑ የመንግስት እና የፓርቲ ስራዎች ዙሪያ ከመምሪያ ኃላፊዎችና ከወረዳ አስተባባሪዎች ጋር ተወያይቷል።

"በመተጋገዝ ላይ የተመሰረተ የአመራር ሰጭነት ሚናን ለመወጣት የሚያስችል አሰራር ውስጥ መግባት እንደሚገባ ያስገነዘቡት"የደቡብ ጎንደር ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መንበር ክፈተው "በተደራጀ አመራርና ህዝባዊ ንቅናቄ ፅንፈኝነትን ከመሰረቱ ማምከን ለነገ የማይባል የህልውና አጀንዳ ነው" ብለዋል።

በታሪካዊ አመጣጥ ደረጃ ፀጋና የተባረኩ መሆናቸው የሚወሳላቸው የጳጉሜን ቀናት ለመጭው የስራ ዘመን ሁለንተናዊ እድገት ለማስመዝገብ ሙሉ ዝግጅት የምናደርግባቸው ቀናት ናቸው ያሉት አቶ መንበር የትምህርት ምዝገባ እና አጀማመር አስመልክቶ በአጭር ቀን ለማጠናቀቅ የሚያስችል ዝግጅት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

የጳጉሜን ቀናት አከባበር አስመልክተው ማብራሪያ የሰጡት የደቡብ ጎንደር ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሰረት በላይ ተግባራት የሚከወኑበት የራሳቸው ጊዜ አላቸው ብለዋል።

ጳጉሜን የተለየች የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያውያን ልዩ ስጦታ መሆኗን የተናገሩት ኃላፊው ከጳጉሜን አንድ እስከ ጳጉሜ አምስት ድረስ የሚከበሩበትን ምክንያቶች አስገንዝበው ሁሉም ተቋማት የድርሻቸውን በመወጣት የጳጉሜን ቀናት በተያዘላቸው የዕቅድ ዓላማዎች ናክበር እንደሚገባ አሳስበዋል።

ጳጉሜን ለስራ፣ ጳጉሜን ለበጎ አድራጎት፣ ጳጉሜን ለንቅናቄ፣ ጳጉሜን ለተሻለ እቅድ ማዘጋጃ ልንጠቀም ይገባል ብለዋል።
መረጃ:- ደቡብ ጎንደር ኮሙዩኒኬሽን

በደቡብ ጎንደር ዞን ሰላምን ሲያውኩ የነበሩ ጽንፈኞች ተደመሰሱ።በደቡብ ጎንደር ዞን የተሰማራው የምሥራቅ ዕዝ ኮር አንድ መቶ ሰባት ፅንፈኞችን ተከታትሎ ደምስሷል። ኮሩ ከነሐሴ 01 አስከ ነሐ...
04/09/2026

በደቡብ ጎንደር ዞን ሰላምን ሲያውኩ የነበሩ ጽንፈኞች ተደመሰሱ።

በደቡብ ጎንደር ዞን የተሰማራው የምሥራቅ ዕዝ ኮር አንድ መቶ ሰባት ፅንፈኞችን ተከታትሎ ደምስሷል። ኮሩ ከነሐሴ 01 አስከ ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም ባካሄደው የተቀናጀ የፀረ ሽምቅ ኦፕሬሽን 51 ፅንፈኞች ሲደመሰሱ፣ 24 ቆስለዋል፣ 32 በተለያየ መንገድ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ኮሩ ባካሄደው ሕግ የማስከበር እርምጃ የተለያዩ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች፣ የነፍስ ወከፍ እና የቡድን መሳሪያ ተተኳሾች፣ የመገናኛ ሬድዮዎች እና ከኅብረተሰቡ ዘርፎ ሲገለገልባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል።

ከተደመሰሱት መካከል፣ ግዜ ግርማ የተባለ የፅንፈኛዉ ቡድን የአንዳቤቴ ብርጌድ የነሱ መዋቅር ፍርድ ቤት ኀላፊ፣ ሙጨ ታምር የአንበሳዉ ጋይንት ክፍለ ጦር አደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ፣ ሽሻነዉ ጠጋ የአንበሳዉ ጋይንት ሻለቃ አዛዥ ይገኙበታል።

የፅንፈኛዉን የጥፋት ዓላማ የተረዱ 12 አመራርና አባላት የሰላምን አማራጭ ተቀብለዉ የገቡ ሲኾን ከነዚህም ውስጥ ቻሌ አለባቸዉ የእስቴ ዴንሳ በነሱ አጠራር ኮር ዘመቻ የነበረ እና አማረ ደሴ ሞላ ሻለቃ መሪ የነበረ ይገኙበታል። ታጣቂዎቹ እንደተናገሩት፣ በፊት የፅንፈኛውን የሀሰት ፕሮፓጋንዳ በመከተል እና በመደናገር ገብተው ነበር። አሁን ላይ ግን እውነታውን በየዕለት ሥራዎቹ ስለተረዱና ቡድኑ የሚሠራውን ግፍ በቅርበት ስላዩ፣ ለአማራ ሕዝብ ነፃነት እንዋጋለን እያለ ግን ሕዝብን ሰላም እያሳጡ እንደኾነም ስለተረዱ የጽንፈኞችን ሥራ ሙሉ በሙሉ ጠልተነዋል ብለዋል። ሰላም ይሻላል በማለትም የሰላምን አማራጭ ተቀብለው መግባታቸውን ገልጸዋል።

የሀገር መከላከያ ሠራዊት ባካሄደው ፀረ-ሽምቅ ስምሪት የደቡብ ጎንደር የፀጥታ ኃይል፣ መሪዎች እና ሰላም ወዳዱ ሕዝብ ከፍተኛ ሚና መጫዎታቸውም ተገልጿል።
መረጃው የምሥራቅ ዕዝ ነው።
መረጃ:- ደቡብ ጎንደር ዞን ኮሙዩኒኬሽን

በደባርቅ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን መቀበል ቀጥለዋል። በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን መቀበል ቀጥለዋል...
03/09/2026

በደባርቅ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን መቀበል ቀጥለዋል።

በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን መቀበል ቀጥለዋል።

በወረዳው ከአሁን በፊትም በርካታ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለው መግባታቸው ይታወሳል። ዛሬም ተጨማሪ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል።

የሰላም አማራጭ የተቀበሉትን ታጣቂዎች የደባርቅ ወረዳ የሥራ ኀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የሰላም አማራጭን የተቀበሉት ታጣቂዎች ሲጓዙበት የነበረው መንገድ የተሳሳተ መኾኑን መገንዘባቸውን ገልጸዋል።

ከደባርቅ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የነበሩበትን የጥፋት መንገድ በመተው ወደ ኅብረተሰቡ እና ሰላማዊ ሕይወት ለመመለስ መወሰናቸውንም አስታውቀዋል።
መረጃ:- አሚኮ

የደቡብ ጎንደር ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የሀብት አስተዳደር ዘርፍ በ2018 በጀት ዓመት በክልሉ ካሉ ዞኖች ጋር ተወዳድሮ 1ኛ ደረጃ በመውጣቱ የምስጋና ምስክር ወረቀት ተሰጥቶታል።መረጃ...
02/09/2026

የደቡብ ጎንደር ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የሀብት አስተዳደር ዘርፍ በ2018 በጀት ዓመት በክልሉ ካሉ ዞኖች ጋር ተወዳድሮ 1ኛ ደረጃ በመውጣቱ የምስጋና ምስክር ወረቀት ተሰጥቶታል።
መረጃ:- ደቡብ ጎንደር ዞን ኮሙዩኒኬሽን

የደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ባስመዘገበው የላቀ ውጤት 1ኛ ደረጃ በመውጣቱ የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበረከተለት፣መረጃ:- የደቡብ ጎንደር ዞን ኮሙዩኒኬሽን
02/09/2026

የደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ባስመዘገበው የላቀ ውጤት 1ኛ ደረጃ በመውጣቱ የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበረከተለት፣
መረጃ:- የደቡብ ጎንደር ዞን ኮሙዩኒኬሽን

የደቡብ ጎንደር ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት የላቀ ውጤት በማስመዝገቡ ሽልማት ተበረከተለት፤የአማራ ክልል በ2018 በጀት ዐመት እቅድ ግምገማና የ2019 በጀት ...
02/09/2026

የደቡብ ጎንደር ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት የላቀ ውጤት በማስመዝገቡ ሽልማት ተበረከተለት፤

የአማራ ክልል በ2018 በጀት ዐመት እቅድ ግምገማና የ2019 በጀት እመት እቅድ ትውውቅ በባህርዳር እያካሄደ ነው።

በመሆኑም የደቡብ ጎንደር ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ በበጀት ዓመቱ ከሌሎች ዞኖች ጋር ሲወዳደር 3ኛ ደረጃ በመውጣት ዴስክቶፕ፣ ኮምፒውተርና ዋንጫ ተሸልሟል።
መረጃ:- ደቡብ ጎንደር ዞን ኮሙዩኒኬሽን

የደቡብ ጎንደር ዞን ስራና ክህሎት መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት የላቀ ውጤት በማስመዝገቡ እውቅና እና ምስጋና ተሰጠው፤የአማራ ክልል በ2018 በጀት ዓመት እቅድ ግምገማና የ2019 በጀት እመ...
02/09/2026

የደቡብ ጎንደር ዞን ስራና ክህሎት መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት የላቀ ውጤት በማስመዝገቡ እውቅና እና ምስጋና ተሰጠው፤

የአማራ ክልል በ2018 በጀት ዓመት እቅድ ግምገማና የ2019 በጀት እመት እቅድ ትውውቅ በባህርዳር እያካሄደ ነው።

በመሆኑም የደቡብ ጎንደር ዞን ስራና ክህሎት መምሪያ በበጀት ዓመቱ ከሌሎች ዞኖች ጋር ሲወዳደር 3ኛ ደረጃ በመውጣቱ የምስጋና ምስክርወረቀት ተሰጥቶታል።
መረጃ:- ደቡብ ጎንደር ዞን ኮሙዩኒኬሽን

"የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ በክልሉ ሰላምና ልማት እንዲረጋገጥ የድርሻውን እየተወጣ ነው" -አቶ አባይ መንግሥቴ​የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላ...
02/09/2026

"የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ በክልሉ ሰላምና ልማት እንዲረጋገጥ የድርሻውን እየተወጣ ነው" -አቶ አባይ መንግሥቴ

​የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም፣ የተመዘገቡ ስኬቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን የሚገመግም መድረክ እያካሄደ ነው።

​በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግርና የሥራ መመሪያ ያስተላለፉት የቢሮው ሃላፊ አቶ አባይ መንግሥቴ፤ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን መረጃ ለሕዝብ ከማድረስ ባሻገር በክልሉ ሰላም፣ መረጋጋትና ልማት እንዲሰፍን ታሪካዊ ሚና እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል። አክለውም በክልሉ ለተገኘው የሰላም አየርና ለሕዝቡ አብሮነት መጎልበት ዘርፉ ከፍተኛ ድርሻ ማበርከቱን አብራርተዋል።

​በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተግባራት የዘርፉን ኃያልነት በተግባር ያረጋገጡ እንደነበሩ የጠቆሙት ሃላፊው፤ እነዚህ ሥራዎች የሕዝቡን የልማት እንቅስቃሴ የሚያፋጥኑ፣ እውነትን የሚያጎሉና የክልሉን መልካም ገጽታ በመገንባት ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል።

​በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ የተካሄደው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዲሞክራሲያዊ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ የተወጣው ሚና በታሪክ የሚዘከር መሆኑን ጠቅሰዋል።

​ዘርፉ የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ የልማት ፍላጎት በማንጸባረቅ ረገድ የተጫወተው ሚና ለልማት ሥራዎች መፋጠን ትልቅ አቅም መሆኑንም አቶ አባይ አብራርተዋል።

​በመድረኩ ያለፉትን ስኬቶችና ያጋጠሙ ማነቆዎችን በመፈተሽ፤ በቀጣይ የበጀት ዓመት የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ለክልሉ ዘላቂ ሰላም፣ ወንድማማችነትና ሁለንተናዊ እድገት በላቀ ኃላፊነት እንዲሠራ መንገድ የሚጠርግ መሆኑ ተመላክቷል።
መረጃ:- አማራ ኮሙዩኒኬሽን

Address

Fogera
Lalibela
30

Opening Hours

Monday 02:30 - 23:00
Tuesday 02:30 - 23:00
Wednesday 02:30 - 23:00
Thursday 02:30 - 23:00
Friday 02:30 - 23:00

Telephone

+251584460904

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fogera woreda communication affairs office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Fogera woreda communication affairs office:

Shortcuts

Share