Magaale daqaarak doolat angarawih maktaba/የመጋሌ ዳአር የመንግስት ኮሚንኬሺን ፅ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Logya
  • Magaale daqaarak doolat angarawih maktaba/የመጋሌ ዳአር የመንግስት ኮሚንኬሺን ፅ/ቤት

Magaale daqaarak doolat angarawih maktaba/የመጋሌ ዳአር የመንግስት ኮሚንኬሺን ፅ/ቤት magaale daqaarakdoolat angarawih ayfafih maktaba

03/09/2026
በወቅታዊ ሁኔታዎች እና ወደፊት በሚከናወኑ የጋራ ስራዎች ዙሪያ ከሚዲያ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ​የብልፅግና ፓርቲ የአፋር ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ከአጠቃ...
03/09/2026

በወቅታዊ ሁኔታዎች እና ወደፊት በሚከናወኑ የጋራ ስራዎች ዙሪያ ከሚዲያ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ

​የብልፅግና ፓርቲ የአፋር ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ከአጠቃላይ ሀገራዊ እና ክልላዊ ወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታዎች ጋር ተያይዞ ወደፊት በሚከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮች ዙሪያ ከመንግስት እና ከፓርቲ ሚዲያ አጋዥ አካላት ጋር የምክክር ውይይት አካሂዷል።

​ውይይቱን የመሩት የብልፅግና ፓርቲ የአፋር ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ክቡር አቶ መሀመድ አህመድ አሊ ናቸው። በመድረኩ ወቅታዊ ሀገራዊ እና ክልላዊ ሁነቶችን መነሻ በማድረግ የሚዲያ አካላት የህዝብን ግንዛቤ ለማሳደግ፣ ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ተዳራሽ ለማድረግ እንዲሁም በጋራ ለመስራት በሚችሉባቸው የትብብር መስኮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

​ክቡር አቶ መሐመድ አህመድ አሊ በመልእክታቸው ሚዲያው ህዝብንና መንግስትን በማገናኘት ረገድ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው፣ ወደፊት በሚከናወኑ የፖለቲካ እና የልማት ስራዎች ላይ የተቀናጀ የመረጃ ልውውጥ እና የጋራ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በየሳምንቱ ውጤቶች እየተገመገሙ እንደሚሄዱ አብራርተዋል።

​ የሚዲያ አካላት በበኩላቸው የተሰጣቸውን ሀገራዊ እና ክልላዊ ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት እና ከፓርቲው ጽህፈት ቤት ጋር በቅንጅት ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

Magaalê daqaarak ma/ma/da/k/buxa kee Ityoppiyak Kabxâ Bankik Laqilley Ludda E-Banking ayfaafayih mattacaynoh siitingey f...
31/08/2026

Magaalê daqaarak ma/ma/da/k/buxa kee Ityoppiyak Kabxâ Bankik Laqilley Ludda E-Banking ayfaafayih mattacaynoh siitingey ferma abaanamih taama tekke.

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የጋራ ብልጽግና መሰረት ነዉ!የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የኢትዮጵያ የልማት ታሪክ ድል ብቻ ሳይሆን የአባይ ውሃ በፍትሃዊ፣ በምክንያታዊና በዘላቂ መ...
27/08/2026

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የጋራ ብልጽግና መሰረት ነዉ!

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የኢትዮጵያ የልማት ታሪክ ድል ብቻ ሳይሆን የአባይ ውሃ በፍትሃዊ፣ በምክንያታዊና በዘላቂ መርህ ሲተዳደር ለተፋሰሱ ሀገራት የጋራ ብልፅግና መሠረት ሊሆን እንደሚችል ያሳየ ታሪካዊ ምዕራፍ ነው።

መላዉ ኢትዮጵያዊያን ተደምረን የመቻል ምልክት የሆነዉን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ለምርቃት እንዲበቃ ያደረግነዉ ብዙ ፈተናዎችን በብልሃት በመሻገር ነዉ፡፡ ኢትዮጵያ የአባይ ዉሃ 86 በመቶ ምንጭ ሆና ሳለ በተሳሳተ ትርክት የሀገራችንን እዉነት ቀምተዉ እንደራሳቸዉ አድርገዉ በዲፕሎማሲዉ፣ በሚዲያዉና በሌሎች መድረኮች እያቀረቡ አለምን ጭምር እያሳሳቱ ለዘመናት የኖሩት ገመናቸዉ በአደባባይ እየተገለጠ የአዞ እንባቸዉ ሳይታበስ፤ እነሱ እየዛቱብን ያልተገባ ስም በአለም አደባባይ እየሰጡን እኛ አላማችን ላይ አተኩረን ተፈጥሯዊ የባለቤትነት መብታችንን በፍትሃዊነት ተጠቅመን አሳክተናል፡፡ የያኔዉ ጩሄት የነበረዉ ህዳሴ ግድብ ከፍታ በጨመረና ዉሃ የመያዝ አቅም በጨመረ ቁጥር ወደ ተፋሰሱ ሀገራት የሚፈሰዉ የዉሃ መጠን በእጅጉ ይቀንሳል የሚል ነዉ፡፡ እዉነቱ ግን ኢትዮጵያ አስቀድማ እንዳለችዉ በግድቡ አስተዳደር ሳቢያ የአባይ ዉሃ ተፈጥሯዊ ፍሰት አንዳች አልቀነሰም፤ ይልቁንም ህዳሴ ከመገንባቱ በፊት በተለይም በዝናብ ወቅት በጎርፍና በደለል ምክንያት ይከሰት የነበረዉን ተፈጥሯዉ አደጋዎች በእጅጉ ቀንሰዋል፡፡

ህዳሴ ግድብ በመሠረታዊ ዓላማው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ቢሆንም፣ ግድቡ የአባይን የውሃ ፍሰት በመቆጣጠር በዝናብ ወቅት የሚከሰቱ ከፍተኛ ጎርፎችን ለመቀነስና በበጋ ወቅት የተረጋጋ ፍሰት እንዲኖር ያስችላል። ይህም በተለይ ለሱዳን የጎርፍ አደጋን ለመቀነስና የውሃ አቅርቦትን ይበልጥ ያረጋግጣል። ከኢትዮጵያ ደጋማ አካባቢዎች የሚመነጨውና ወደ ታችኛው ተፋሰስ የሚወርደውን ደለል መጠን በመቀነስ፣ የሱዳንና የግብፅ ግድቦች፣ የመስኖ ቦዮችና የውሃ መሠረተ ልማቶች የጥገናና የደለል ማስወገጃ ወጪን ለመቀነስ ያግዛል።

በተጨማሪም የውሃ ፍሰት መረጋጋቱ በሱዳን ያሉ የውሃ ኃይል ጣቢያዎች የበለጠ በተረጋጋ ሁኔታ እንዲሰሩ፣ ለመስኖና ለግብርና የሚውል ውሃ በተሻለ ሁኔታ እንዲገኝ እድል ይፈጥራል። ሱዳን ከእነዚህ ጥቅሞች ባሻገር የኤልክትሪክ ሀይል በተመጣጣኝ ዋጋ የምታገኝበትን እድል ፈጥሯል፡፡ የህዳሴ ግድብ ዉሃ ሙሌት ከተጠናቀቀ በኋላ ከጎርፍና ከደለል ጋር ተያይዞ ይከሰቱ የነበሩ ተፈጥሯዊ አደጋዎች እየቀነሱ መሆናቸዉ የአደባባይ እዉነት ነዉ፡፡

የህዳሴ ግድብ ገና የመሰረት ድንጋይ ሲጣል የዉሃ መጠን ፍሰት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ይፈጠራል መጠኑም ይቀንሳል፣ ግድቦቻችን ዉሃ ይቀንሳሉ፣ መስኖዎቻችንም ይቆማሉ፣ ህልዉናችንም አደጋ ላይ ይወድቃል፤ የሚሉ ክሶች ህዳሴ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቅቆ በፕሮፖጋንዳቸዉ ልክ መሬት ላይ ያለዉ እዉነት መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ እያቀረቡ ሲሞግቱ አይታዩም፤ አንድ ደጋግመዉ የሚደሰኩሯት ነጥብ የቅኝ ግዛት ዘመን ዉል ነዉ፤ ጊዜ ያለፈበት ዉል፡፡ በሀሰት ትርክት የአባይ ዉሃ ብቸኛ ባለቤት እንደሆኑ አስመስለዉ አለምን ሲያወናብዱ የኖሩበትን ልምድ በመጠቀም ጊዜን ወደኋላ ብቻ ነዉ የሚሰራዉ ይሉናል፡፡ ዛሬ አለም በቅኝ ዘመን ላይ አይደለችም፡፡ ብትመኘዉ እንኳን ልትመልሰዉ አትችልም፡፡ የቅኝ ዘመን ዉል በየትኛዉም መመዘኛ በዚህ ዘመን የአለም አቀፍ ህግ ሊሆን አይችልም፡፡

ግብጽ ሰሞኑን በተፈጥሮ ክስተት-ኤል ኒኖ ምክንያት የቀነሰዉን የናይል ዉሃ መጠን ኢትዮጵያ ግድቡን ያስተዳደረችበት መንገድ የፈጠረዉ ችግር ነዉ በማለት የሀገራችንን

Qunxaaneyti Qasri Ratteema kee Teknoloojit Dooqaysimak rakaakayak numma fooca xisaanam kee yaysexeexegoonuh baar le saam...
25/08/2026

Qunxaaneyti Qasri Ratteema kee Teknoloojit Dooqaysimak rakaakayak numma fooca xisaanam kee yaysexeexegoonuh baar le saami ginnime.

Qafar Rakaakayih Doolatak Angaaraw Biirok Naharsi Saqal
Massakaxxale Mohammed Ali Biedo

የአፋር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ከክልሉ ወጣቶች ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ለወጣቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ። (ነሀሴ 19–2018): የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ከክልሉ...
25/08/2026

የአፋር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ከክልሉ ወጣቶች ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ለወጣቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ።

(ነሀሴ 19–2018): የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ከክልሉ ወጣቶች ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር በሰመራ ከተማ ለወጣቶች ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ።

የአፋር ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ ዓሊ ቢዒዶ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት ወጣቶች ዘመናዊ ሚዲያንና ቴክኖሎጂን በብቃት በመጠቀም የክልሉን እውነተኛ ገጽታ መገንባት እና ማስተዋወቅ እንደሚገባቸው ገልፀዋል።

ውይይቱ ወጣቱ ትውልድ የክልሉን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ነባራዊ ሁኔታዎች በመረዳት የህዝቡን የልማትና የሰላም ጥያቄዎች በዲጂታል ሚዲያ አማካኝነት ማስተጋባት እንደሚችል አቶ መሀመድ ዓሊ ቢዒዶ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

በተጨማሪም የክልሉን ሁለንተናዊ ጥቅም ለማስጠበቅ እና ህብረተሰቡን ከመረጃ እጥረትና ከሐሰተኛ ትርክቶች ለመከላከል ወጣቶች ግንባር ቀደም ሚና መጫወት እንዳለባቸው ተመላክቷል።

በመድረኩ ሰነዶች በኮሙኒኬሽን ቢሮ አመራሮች በኩል ቀርቦ ተሳታፊ ወጣቶች ጥያቄና አስተያየቶችን ሰጥተዋል።

በተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ዙሪያ የቢሮው ምክትል ኃላፊዎች አቶ መሀሙዳ መሀመድ ደነባ እና አቶ ሙሳ መሀመድ ደረሳ ተገቢውን ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

የአፋር ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ ዓሊ ቢዒዶ ወጣቱ የልማትና የብልፅግና መሰረት እንደመሆኑ መጠን ዘርፈ ብዙ ተሳትፎውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

በመጨረሻም የክልሉን ሰላም፣ ደህንነት እና የልማት ጉዞ በዘላቂነት ለማረጋገጥ ከባህላዊ እሴቶችና ከትውልድ ማህደር ጋር የተጣጣመ ጠንካራ የህዝብ ግንኙነት ሥራዎችን ማከናወን እንደሚያስፈልግ በመድረኩ ላይ ተሳታፊዎች ተስማምተዋል።
ምንጭ፡ communication service bureau

የብልፅግና ፓርቲ የአፋር ክልል ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ከቢሮ ክላስተር አስተባባሪ ወጣቶች ጋር በስልጠና ዝግጅት ዙሪያ ተወያየ​የብልፅግና ፓርቲ የአፋር ክልል ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሚዲያና ህዝብ ግንኙነ...
24/08/2026

የብልፅግና ፓርቲ የአፋር ክልል ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ከቢሮ ክላስተር አስተባባሪ ወጣቶች ጋር በስልጠና ዝግጅት ዙሪያ ተወያየ

​የብልፅግና ፓርቲ የአፋር ክልል ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ በቅርብ ቀናት ለማካሄድ እቅድ በያዘው የሚዲያ ስልጠና ዙሪያ ከቢሮ ክላስተር አስተባባሪ ወጣቶች ጋር ውጤታማ የውይይት መድረክ አካሂዷል።

​በመድረኩ ላይ የተገኙት የቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ሀላፊ አቶ መሀመድ አደን ለክላስተር አስተባባሪዎች በእቅዱ የተካተቱ ዋና ዋና የስልጠና ርዕሰ ጉዳዮችንና አቅጣጫዎችን የሚያብራራ መነሻ ስላይድ አቅርበዋል።

የሚዲያና ኮሙኒኬሽን አቅምን ማሳደግ ወጣቶች በዲጂታል ሚዲያና በህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ያላቸውን ክህሎት በማጎልበት የፓርቲውንና የክልሉን ልማታዊ እንቅስቃሴዎች በተሻለ መልኩ ለህብረተሰቡ ማድረስ የሚያስችል ስልጠና ማዘጋጀት።

የመረጃ ጥራትን ማረጋገጥ በየደረጃው ያሉ የክላስተር አስተባባሪዎች ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን ለህዝብ በማቅረብ ረገድ ያላቸውን ሚና ማጠናከር። የወጣቶችን ተሳትፎ ማሳደግ ሚዲያን ለበጎ በጎ ተፅዕኖ፣ ለሰላምና ለልማት ስራዎች ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመጠቀም የሚያስችል ዝግጅት ማድረግ።
​በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የክላስተር አስተባባሪ ወጣቶች በቀረበው መነሻ ስላይድ ላይ ሀሳብና አስተያየት የሰጡ ሲሆን፣ ለማካሄድ የታቀደው ስልጠና በወቅቱ አስፈላጊና የወጣቶችን የሚዲያ ግንዛቤ የሚያጎለብት መሆኑን ገልጸዋል።


Kilbatti Rasih Idoola Luk Wakti Caalat Wagittaamal Walal Gexsak Geytiman (Ximolik 14-2018): Qafar Rakaakayak Saay kee Sa...
20/08/2026

Kilbatti Rasih Idoola Luk Wakti Caalat Wagittaamal Walal Gexsak Geytiman

(Ximolik 14-2018): Qafar Rakaakayak Saay kee Salaam Biiroh Koobaahissol Kilbatti Rasuk Inkih tan Daqoorit kee Magaalâ Xiinisssok Tewqeh tan Rasi Idoolay, Kedoh Abbobtiiy, Qunxaaneyta kee Sayyoh Exxaaxi Luk Wakti Caalat Wagittaamal Walal Gudgud Rasi Inyta Abqaala Magaalal Gexsak Geytiman .

Tama Gudgudul Rakaakayak Ciggiila Prezixentih Bilhadal Madduur Kilasterih Koobaahiseey, Plaan Kee Daddoos Biiroh Saqal Gifta Qali Macammad Macmuud, Rakaakayak Saay kee Salaam Biiroh Saqal Komishineer Acmad Cummad, Rakaakayak Buqre Kee Gino Gaddih Daddoosih Biiroh Saqal Injineer Yaasin Qali, Qafar Poliisik Daga Raaqa Miracsentak Baatil Kalalih Langil Ciggiila Amriseeni C/Komishineer Macammad Siraaj Edde Anuk Rakaakayay Rasu Kee Daqoorit Miraaciini Edde Geytimen .

Gudgudul Geytimeh Yan Rakaakayak Ciggiila Prezixentih Bilhadal Madduur Kilasterih Koobaahiseey, Plaan Kee Daddoos Biiroh Saqal Gifta Qali Macammad Macmuud Iyyeemih Qafar Idoola Isiim hinnay Marin-im Abak Assa Idoola Kinnim Ascassuuk Qafar Taway Geyteh tan Isi-amoh Xin Waaruh Adda Kee Irok Salaam Isinnik Dacrisaanam Faxxintah Tanim Diggoose.

Salaama Yaanam Num Isiik Qimbisak Abbinoosam Kinnim Yescesseh Yan Rakaakayak Saay Kee Salaam Biirok Naharsi Saqal Komishineer Acmad Cummad Qafar Ummatta Xakak Wayti kee Salaam Sinna Fan Culussam Xiqta Caagiidak Kalaloonuh Kulli Num Isik Qambalsintam Abam Faxxintah Tanim Ascassuuk Qafar Ummattah Goona Luk Gacak Baahan Curriyatay Qambaalaana Ane-Waam Ummatta Taaxigem Faxxinta Iyye .

Komishineer Acmad Cummad Taturte Udduurah addat Qafarak Kedoh abbobti Ganeenit kee Ken Qokoltah tan Marittel Gexxam Faxxinta Maaqatta Axcuk Madaqeenih Yanin Madqak addafokoot Maca Ceelam Kee Missos Faxxam Tenek Abeh-Meqem Wagittaamal Baar Luk Xayyoosak Rasi Kasle Fidin Walal Edde Abte .

Kilbatti Rasuk Naharsi-Saqal Gifta Macammad Qali Ascab Is Le Katuk Iyyeemih Qafar Ummattah Salaam Kee Sabahalal Maqarroowuh Doolat Abteh tan Seeco Assakaxxuk Temeeteh tan Rasi Kasle Faatite .

Gudgudul Tengeleh tan Kilbatti Rasuk Inkih tan Daqoorit kee Magaala Xiinisssok Tewqeh tan Rasi Idoola Ganeenit Kee Gargarwa Qafarah Bahtu Wayta Curriyat Anewaam Aaxaguk Ummattah Addah addat Salaam Kee Saay Uguugus Abak Geytimaanam Kassiiseenik Lakal Ganeenit Uxi Kinniih Qafar Naqboytiit Kinnim Ascassuuk Missos Faxxa Ximmoomal Baar Luk Walalak Geytiman .

«የሚሰሩ ስራዎች የክልሉን ገጽታ የሚያጎለብቱ እንጂ የህዝባችንን እምነትና ባህል የሚጻረሩ መሆን የለባቸውም» - አቶ መሀመድ አሊ ቢኢዶ​የአፋር ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ በክልሉ በማህበራዊ ሚዲያ...
17/08/2026

«የሚሰሩ ስራዎች የክልሉን ገጽታ የሚያጎለብቱ እንጂ የህዝባችንን እምነትና ባህል የሚጻረሩ መሆን የለባቸውም» - አቶ መሀመድ አሊ ቢኢዶ

የአፋር ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ በክልሉ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በግልና በ ቡድን በሚንቀሳቀሱ የቲክቶክ ባለሙያዎች እና የሚዲያ አካላት የይዘት ስርጭት፣ የባህል፣ የህግና የሃይማኖት እሴቶችን በተከተለ መልኩ መንቀሳቀስ ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት አካሄደ።

የቢሮው ኃላፊ አቶ መሀመድ አሊ ቢኢዶ እና ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀሞዳ መሀመድ ደነባ ውይይቱን የመሩት ሲሆን፣ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው ይዘት የክልሉን ገጽታ፣ የህብረተሰቡን ሃይማኖት እና ባህል እንዲሁም የህግ ማዕቀፎች የጠበቀ መሆን እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።

​ባለፉት ጊዜያት በማህበራዊ ሚዲያ እና በቲክቶክ ላይ የሚለቀቁ አንዳንድ ይዘቶች የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ፣ ሃይማኖት እና ባህል የማይመጥኑ ስህተቶች እየታዩባቸው መሆኑንና ተገቢ ያልሆኑ ይዘቶችን ከወዲሁ ማስቀረት እንደሚያስፈልግ ተመላክቷል።

አሁን ላይ ዋናው ትኩረት የህዝብ ግንዛቤ መፍጠር መሆኑ ተነግሮ፣ ለወደፊቱ ከኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ጋር በቅርበት በመሥራት የአቅም ግንባታ ሥልጠና መድረኮች እንደሚዘጋጁ ተገልጿል።

​የሚሠሩ ሥራዎች ውጤታማና የሕዝብን እምነትና ባህል የጠበቁ እንዲሆኑ ከሴክተር መሥሪያ ቤቶች ጋር በቅንጅት መሥራት እንደሚገባ ተጠቁሟል።

የሕዝብን እምነትና ባህል የጠበቀ እንዲሁም የክልሉን ገጽታ በግልጽ የሚያጎለብት አሰራር መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑ በማስገንዘብ ውይይቱ ተጠናቋል።

Address

Logya
1470

Telephone

+251914240523

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Magaale daqaarak doolat angarawih maktaba/የመጋሌ ዳአር የመንግስት ኮሚንኬሺን ፅ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Magaale daqaarak doolat angarawih maktaba/የመጋሌ ዳአር የመንግስት ኮሚንኬሺን ፅ/ቤት:

Shortcuts

Share