07/09/2026
ጳጉሜ 2 — የማንሰራራት ቀን
አፋር ክልል በአዲስ የተስፋና የልማት መንፈስ የማንሰራራት ጉዞውን እውን እያደረገ ይገኛል።
በሀገራችን በታላቅ ዝግጅት እየተከበረ ከሚገኘው የጳጉሜን ወር መሸጋገሪያ ቀናት መካከል ሁለተኛው ቀን የሆነው "የማንሰራራት ቀን" በአፋር ክልል በልዩ ልዩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሁነቶች በደመቀ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል።
በዕለቱ ምክንያት በማድረግ የክልሉ ፕሬዚዳንት ባስተላለፉት የደስታና የመልካም ምኞት መልእክት፤ ክልላችን ላለፉት ዓመታት ያጋጠሙትን የተፈጥሮና የሰው ሰራሽ ተደራራቢ ፈተናዎች በጽናት በመጋፈጥ፣ በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መስኮች ዘላቂ ማንሰራራትን ማረጋገጥ መቻሉን ገልጸዋል።
በአፋር ክልል ደረጃ የተረጋገጡ ዋና ዋና የማንሰራራትና የልማት ስኬቶች
የከተሞች የኮሪደር ልማትና የገጽታ ግንባታ ማንሰራራት በክልሉ ዋና ዋና ከተሞችና የንግድ ኮሪደሮች (በተለይም በሰመራ-ሎጊያና አካባቢው) የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎች የከተሞችን ጽዳት፣ ውበትና የመሰረተ ልማት ደረጃ በጥራት አድሰዋል። መንገዶችን ማስፋፋት፣ የጎዳና ላይ መብራቶችን መትከል፣ የእግረኛ መንገዶችን ማዘጋጀትና የአረንጓዴ ስፍራዎችን ማስፋፋት የከተሞቻችንን ገጽታ ከመቀየሩም በላይ ለንግድና ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል።
የግብርናና የምግብ ዋስትና ማንሰራራት በመስኖ ልማትና በበጋ ስንዴ ምርት ረገድ አርብቶ አደሩን ወደ Agro-Pastoralist መስኖ ልማት) የመቀየር እንቅስቃሴ ትልቅ ውጤት አሳይቷል። ሰፊ መሬቶችን ወደ ምርታማነት በመቀየር በክልሉ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ጉዞ አዲስ ምዕራፍ ተክቷል።
የመሠረተ ልማትና የአገልግሎት ድርጅቶች መልሶ መገንባት ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ የትምህርት፣ የጤና እና የንጹህ መጠጥ ውሃ ተቋማት በአጭር ጊዜ ውስጥ መልሰው በመገንባታቸው ማህበረሰቡ ሙሉ በሙሉ ወደ መደበኛ አገልግሎት እንዲመለስ ተደርጓል።
የሰላምና ደህንነት መረጋጋት የክልላችን ህዝብ ከአጎራባች ክልሎች ጋር ያለውን የቆየ ወንድማማችነትና አብሮ የመኖር ባህል በማጠናከር፣ አስተማማኝ ሰላም በመገንባቱ ለልማትና ለንግድ እንቅስቃሴዎች ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል።
የወጣቶችና ሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ በስራ ዕድል ፈጠራና በአነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች በኩል በርካታ ወጣቶችና ሴቶች ወደ ምርታማነት በመሸጋገር የራሳቸውንና የክልሉን ኢኮኖሚ በማንሰራራት ላይ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ።
የአፋር ክልል ፕሬዚዳንት ሀጂ አወል አርባ በመልእክታቸው ጨምረው እንደገለጹት፤ "ማንሰራራት ማለት ያለፈውን ፈተና ወደ ድል በመቀየር፣ ከተሞቻችንን በማስበብና ልማትን በማፋጠን ለነገው ትውልድ የተሻለችና የበለፀገች አፋርን መፈጠር ነው" ያሉ ሲሆን፣ መላው የክልሉ ህዝብና ባለድርሻ አካላት በየዘርፉ የተጀመረውን የማንሰራራት ጉዞ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።