Masha Woreda Communication

Masha Woreda Communication የማሻ ወረዳ እምቅ ሀብቶቻችንን በጋራ እናልማ
https://t.me/Mashawordacom

 !የ2018 ዓ.ም የጳጉሜን ቀናት የኢትዮጵያ መንሠራራት በሚል መሪ ሐሳብ፣ በአምስቱ የጳጉሜን ቀናት ስያሜዎች ይከበራል፡፡የጳጉሜን ቀናት አከባበር ዐቢይ ዓላማ ኢትዮጵያ ከአግድሞሽና ከዝቅታ ...
03/09/2026

!

የ2018 ዓ.ም የጳጉሜን ቀናት የኢትዮጵያ መንሠራራት በሚል መሪ ሐሳብ፣ በአምስቱ የጳጉሜን ቀናት ስያሜዎች ይከበራል፡፡

የጳጉሜን ቀናት አከባበር ዐቢይ ዓላማ ኢትዮጵያ ከአግድሞሽና ከዝቅታ ጉዞ ተላቃ በሁሉም ዘርፎች ወደ ላቀ ከፍታ ማንሠራራት መጀመሯን በማብሰር፣ ለበለጠ ሀገራዊ ውጤት ከፍተኛ መነሳሳትንና የተስፋ መንፈስ መፍጠር ነው።

የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ የፍጆታ እቃዎች በህብረት ስራ ማህበራት በኩል ለህብረተሰቡ እንዲደርስ እየሰራ መሆኑን የሸካ ዞን ንግድ ገበያ ልማት እና ኢንቨስትመንት መም...
03/09/2026

የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ የፍጆታ እቃዎች በህብረት ስራ ማህበራት በኩል ለህብረተሰቡ እንዲደርስ እየሰራ መሆኑን የሸካ ዞን ንግድ ገበያ ልማት እና ኢንቨስትመንት መምሪያ ገለፀ

በዓሉን አስመልክቶ ህገ ወጥ የዋጋ ጭማሪ እንዳይደረግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እየሰራ እንደሚገኝ መምሪያው ገልጿል።

የሸካ ዞን ንግድ ገበያ ልማት እና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ትዕግስት ከበደ በዓሉን አስመልክቶ የንግዱን ዘርፍ መግለጫ የሰጡ ሲሆን አስፈላጊ የሆኑ የፍጆታ ዕቃዎች እንደዘይት፣ ስኳር፣ ፉርኖዱቄት እና ሌሎች ምርቶች በበቂ የቀረቡ መሆኑን ገልጸው በህብረት ስራ ማህበራት በኩል ለህብረተሰቡ የሚደርስ መሆኑን ተናግረዋል።

የመምሪያ ኃላፊዋ አያይዘው እንደገለጹት ማህበረሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶችን እንዲያገኝ ከሌሎች ተቋማት ጋር እየተሰራ የሚገኝ ሲሆን ከጅምላ አከፋፋዮች በበቂ ሁኔታ ምርት ማግኘት እንደሚቻልም ተናግረዋል።

በሌላ በኩል በዓሉን ምክንያት በማድረግ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖር እና ባዕድ ነገሮች እንዳይቀላቀሉ ክትትል እና ቁጥጥር ለማድረግ እንዲሁም ኮሚቴ በማቋቋም እስከታችኛው መዋቅር ድረስ በመውረድ ድጋፍ እና ክትትል እየተደረገ እንደሚገኝ የመምሪያ ኃላፊዋ ገልጸዋል።

ህብረተሰቡ ባዕድ ነገሮችን አቀላቅለው በሚሸጡ አካላት እንዳይጭበረበር እና ጥንቃቄ እንዲያደርግ የመምሪያ ኃላፊዋ አሳስበው ይህ የማጭበርበር ሁኔታ ሲያጋጥም ጥቆማ በመስጠት ወንጀልን ለመከላከል ህብረተሰቡ እንዲተባበር ጠይቀዋል።

በንግድ እንቅስቃሴው ዙሪያ በአሁኑ ሰዓት የናፍጣ አቅርቦትም በበቂ መኖሩን የመምሪያ ኃላፊዋ ወ/ሮ ትዕግስት ገልፀው ከነጋዴ ማህበረሰብ ጋርም ውይይት እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።

በመጨረሻም ወ/ሮ ትዕግስት ከበደት የሸካ ዞን ንግድ ገበያ ልማት እና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ መልካም የዘመን መለወጫ በዓል እንዲሆን እና ህብረተሰቡ በሰላም፣በፍቅር እና በመተሳሰብ እንዲያከብር መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችል ታሪካዊ የትብብር ስምምነት መፈረሙን ገለጹ  በ...
03/09/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችል ታሪካዊ የትብብር ስምምነት መፈረሙን ገለጹ

በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችል ታሪካዊ የትብብር ማዕቀፍ፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) መካከል ዛሬ መፈረሙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት እንዳስታወቁት፣ ይህ አዲስ የሚቋቋመው ኩባንያ በ100 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር ካፒታል የተቋቋመ ሲሆን፣ ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) ደግሞ ለተቋሙ እስከ 200 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ የፋይናንስ አስተዋፅኦ ያደርግበታል።

ይህ ተቋም ወደ ሥራ ሲገባ በባንክ ዘርፉ ውስጥ የሚታየውን የጥሬ ገንዘብ ፍሰት አለመመጣጠን ችግር የሚቀርፍ ከመሆኑም በላይ፣ በመላው ኢትዮጵያ ተደራሽ የሚሆን የቤት መግዣ ብድር ፋይናንስ አቅርቦትን እንደሚያስገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አብራርተዋል።

በተጨማሪም ይህ አጋርነት መንግሥት በተመጣጣኝ ዋጋ የኢትዮጵያውያንን ክብር የጠበቁ 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለማቅረብ ያስቀመጠውን ግብ ለማሳካት፣ እንዲሁም በሀገራችን የፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ የግል ዘርፉን ተሳትፎ ይበልጥ ለማስፋት የሚያስችል ወሳኝ እርምጃ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ ፈጣን፣ ጠንካራ እና ሁሉንም ያካተተ ኢኮኖሚ የመገንባት ጥረቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አረጋግጠዋል።

በአውሮፓ ገበያ ተመራጭ ቡና ለማምረት በቴክኖሎጂ የታገዘ የመረጃ ስርዓት ውስጥ መግባት እንደሚገባ ተገለጸ በNABU ኢትዮጵያ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት በቡና መ...
02/09/2026

በአውሮፓ ገበያ ተመራጭ ቡና ለማምረት በቴክኖሎጂ የታገዘ የመረጃ ስርዓት ውስጥ መግባት እንደሚገባ ተገለጸ

በNABU ኢትዮጵያ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት በቡና መረጃ መሰብሰቢያ መተግበሪያ (Ethiopian Coffee Traceability Management System) ላይ የአሰልጣኞች ስልጠና በቦንጋ ከተማ እየሰጠ ይገኛል።

ስልጠናው ከንድፈ ሀሳብ ገለፃ ቀጥለው በተግባር የተደገፈ ማሳ ላይ መተግበሪያ ላይ የደረሰ ሲሆን ሰልጣኞችም በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን በተዘጋጀው ECTMS መረጃ የማቅረብ ሂደቶችን እየተለማመዱ ነው።

በወቅቱ አስተያየታቸውን የሰጡን ሰልጣኞች እንደገለፁት በክልሉ የቡና ተረካቢ ሀገራት መስፈርቶችን ለሟሟላት ላለፉት ዓመታት የተቀናጀ ተግባራት ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው በአሁኑ ወቅት የነበሩንን ከፍተቶች በማሻሻል ወደ ተሟላ ደረጃ የሚያደርስ መተግበሪያ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም SW በሚባል በተግበሪያ በክልሉ ቡና በስፋት የሚመርትባቸው ማሳዎችን የማስተሳሰር ስራ መስራታቸውን የተናገሩት ሰልጣኞች አሁን የመጣው መተግበሪያ የአውሮፓ ገበያ ፍላጎትን የሚያሟላና በብሔራዊ ደረጃ ጠንካራ የመረጃ ቋት መሆኑን አክለው ገልጿል።

ስርዓቱ ቡና አምራች አካላትን በእጅጉ ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ያሉት አስተያየት ሰጪዎች፤ ወደ ታች ወርደው ፈፃሚዎችን ለማሰልጠንና ለመተግበር በከፍተኛ ኃላፊነት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

የኢ.ፈ.ዴ.ሪ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ICT ዳይሬክተርና ECTMS ፎካል ወ/ሮ ሃዊ አቶምሳ፤ ባለስልጣኑ ለአውሮፓ ገበያ ከሚቀርቡ ቡና ምርቶች የሚገኘውን ከፍተኛ ገቢ ላለማጣት የመረጃ ስርዓቱን በቴክኖሎጂ ለማዘመንና የገበያ ሰንሰለቱን በወጣው እስታንዳርድ ለማዘጋጀት ECTMS መተግበሪያ አዘጋጅተው ስልጠና እየሰጠ መሆኑን ገልጿል።

ኢትዮጵያ ከደን ጭፍጨፋ ነፃ ለመሆን ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ ስራና ቀድሞ የነበራት የደን ሽፋን ጠቃሚ ማሳያ ነው ያሉት ዳይሬክተሯ በተለይ ከለቀማ ጀምሮ ያሉት የምርት ሂደቶችና ግብይቶች በብሔራዊ መረጃ ቋት ውስጥ እንዲገባ ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

እንደ ሀገር 5.2 ሚልዮን በላይ አነስተኛ ማሳ ያላቸው ቡና አምራች አርሶ አደሮችን በዋናነት ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ሌሎች ማህበራት፣ዩኒዬኖች፣ ኢንቨስትመንቶችና አቅራቢ ድርጅቶች ወደ ስርዓቱ በመግባት ራሳቸውንና ሀገሪቱን ከዓለም ገበያው እንዲጠቀሙ ያደርጋል ብለዋል።

የቦንጋ ዩኒቨርስቲ ቡና ሳይንስ ተመራማሪና አሰልጣኝ ዶ/ር ክፍሌ በላቸው እንደገለፁት የቡና አምራች ሀገራት መካከል ብርቱ ፉክክር መኖሩን ጠቅሰው ይኸን ለማሸነፍና ገበያውን ለመምራት የምርት ሂደት ጥራት ላይ ጠንካራ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ከአምራቾች ባሻገር አቅራቢዎችና ላኪዎች እንደ ቀድሞ ዱካው ያልተመዘገበ ቡና ለአውሮፓ ገበያ ማቅረብ እንደማይችሉ ተገንዘበው ወደ ስርዓቱ በመግባት በዓለም ደረጃ ውዱ ገበያ ላይ ምርቱን በማቅረብ ከግለሰብ እስከ ሀገር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዶ/ር ክፍሌ አሳስበዋል።

እነዚህን ተግባራት ማሳ ድረስ ለማውረድ የኢንተርኔት አቅርቦትን ጨምሮ የተለያዩ መሠረተ ልማቶች ያስፈልጋል ያሉት አስተያየት ሰጪዎች በሀገር ደረጃ የሚንታወቅበትን ቡና ምርት በጥራቱ ተመራጭ ብራንድ እንዲሆን ከወትሮም በላይ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል ሲል የክልሉ መንግስት ኮምኒኬሽን ዘግቧል ።

‎በሸካ ዞን ማሻ ወረደ የአመራሮች የስራ አፈፃፀም ምዘና መካሄድ ተጀመረ‎‎ማሻ ወረዳ ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም በማሻ ወረዳ  የ2018 ዓ.ም የፓርቲና የመንግስት ስራዎች አፈፃፀም መነሻ በማድ...
02/09/2026

‎በሸካ ዞን ማሻ ወረደ የአመራሮች የስራ አፈፃፀም ምዘና መካሄድ ተጀመረ

‎ማሻ ወረዳ ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም በማሻ ወረዳ የ2018 ዓ.ም የፓርቲና የመንግስት ስራዎች አፈፃፀም መነሻ በማድረግ የአመራር ምዘና መካሄድ ተጀምሯል።

‎መድረኩን የመሩት የሸካ ዞን ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፍ አቶ ዋስሁን አውሎ እንደገለጹት የምዘናው ዋና ዓላማ ጠንካራ የፓርቲና የመንግስት ተቋም በመፍጠር የህዝብ ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ አንጻር በጥንካሬ የሚታዩ ጉዳዮችን በማጎልበት ድክመቶችን ለማረም ዓላማ ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

‎አክለውም ይህ የምዘና መድረክ የአመራሩን አሁናዊ ነባራዊ ሁኔታ በመፈተሽ፣በቀጣይ የሚከናወኑ የፓርቲና የመንግስት ተግባራትን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግና አመራሩን ለቀጣይ ተልዕኮዎች ብቁ ለማድረግ ያለመ የአመራር ግንባታ አካል መሆኑንም ገልፀዋል።

‎የሸካ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፍ አቶ በላቸው በቀለ በበኩላቸው ​ይህ የምዘና እና የግምገማ መድረክ አመራሩ የህዝብን ጥያቄዎችና ልማታዊ እቅዶችን በፍጥነትና በጥራት እንዲፈጽም አቅም እንደሚፈጥር እንዲሁም ለቀጣዩ የስራ ዘመን የተሻለ ዝግጅት ለማድረግ እንደሚረዳ ተገልጿል።

‎በመድረኩ ባለፈው በጀት ዓመት በፓርቲው መሪነት የተከናወኑ ዋና ዋና የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ስራዎች አፈጻጸም በዝርዝር ይገመገማሉም ተብሎ ይጠበቃል።

‎​በመድረኩም አጠቃላይ የወረዳ አመራሮች እየተሳተፉና ምዘናውም ለተከታታይ ሁለተ ቀናት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ከመረሃ ግብሩ ለማወቅ ተችሏል።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

‎↪️በቴሌግራም https://t.me/Mashawordacom
‎↪️ፈስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100065002861326
‎↪️ቲክቶክ https://vm.tiktok.com/ZS9JC9jDNrd8S-1XYDP/
‎↪️ዋቲስአፒ https://chat.whatsapp.com/Hw5eZF6lr3j3Ylz29czbrP?mode=gi_t

 ፡ “ #ሀገር” ሀገር በድንጋይና በኮንክሪት የምትቆም ሳትሆን፣ በሕዝቦቿ የጋራ ሕልምና አስተሳሰብ የምትገነባ ረቂቅ ተቋም ናት። የሀገር ግንባታ የትዕግስት፣ የጋራ ራዕይ እና የዜጎች ዕለት ...
01/09/2026

፡ “ #ሀገር”

ሀገር በድንጋይና በኮንክሪት የምትቆም ሳትሆን፣ በሕዝቦቿ የጋራ ሕልምና አስተሳሰብ የምትገነባ ረቂቅ ተቋም ናት። የሀገር ግንባታ የትዕግስት፣ የጋራ ራዕይ እና የዜጎች ዕለት ተዕለት አስተዋጽኦ ድምር ውጤት የሆነ የረጅም ጊዜ ጉዞ ነው።

ሀገራት ከውድቀትና ከድህነት ወጥተው ወደ ተከበሩና የበለጸጉ ሀገራትነት የተሸጋገሩት ልዩነትን በጠረጴዛ ዙሪያ መነጋገርን በማስቀደማቸውና ተቋማዊ መሰረቶችን በመጣላቸው ነው።

በፖለቲካ ሳይንስ ሊቃውንት ዘንድ ሀገራት የሚበለጽጉበትና የሚወድቁበት ዋና ምክንያት የተቋማት ጥራት ነው። በዳሮን አሴሞግሉ እና በጄምስ ሮቢንሰን የተጻፈው “Why Nations Fail” የጋራ መጽሐፋቸው እንደሚያስረዱን÷ የሀገራት እድገት ምስጢር የተፈጥሮ ሀብት ብዛት ሳይሆን አሳታፊ እና ነፃ የሆኑ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተቋማት መኖራቸው ነው።

ከግለሰቦች ፍላጎት ነፃ የሆኑ፣ ሕግና ሥርዓትን የሚያስከብሩ ገለልተኛ የፍትሕ፣ የህግ አስከባሪ እና የፋይናንስ ተቋማት ሲገነቡ የሀገር መረጋጋት ይረጋገጣል።

በተጨማሪም የሀገር ግንባታ መሰረቱ ያልተግባቡባቸውን ጉዳዮች በውይይት መፈታት መቻሉ ነው። ልዩነቶችን በጠረጴዛ ዙሪያ መፍታት፣ በጋራ እሴቶች ላይ መስማማት እና ማንም ሰው ከሕግ በላይ እንዳይሆን ማድረግ ለጋራ እድገት መንገድ ይጠርጋል።

ከዚህ አንጻር የሲንጋፖርን ተሞክሮ እንመልከት፦

የእስያ አህጉር ተአምር የምትባለው ሲንጋፖር ከተፈጥሮ ሀብት እጥረትና ከከፍተኛ ድህነት ተነስታ ዛሬ ላይ የደረሰችው በጠንካራ አመራርና በተቋማዊ መዋቅር ነው። በተለይም የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት ሊ ኳን ዩ ሙስናን በማጥፋት ሹመት በብቃት ብቻ እንዲሆንና ብቃት ላይ የተመሰረተ አመራር እንዲፈጠር ስራ ሰርተዋል።

በትምህርትና በክህሎት ላይ ከፍተኛ በጀት በመመደብ የሰለጠነ የሰው ሀብት መፍጠር ችለዋል። ለዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ምቹ ሁኔታ በመፍጠርና የወደብ መሰረተ ልማትን በማስፋፋት የዓለም ንግድና የፋይናንስ ማዕከል ለመሆን ስልታዊ የኢኮኖሚ ፖሊሲን በመዘርጋት ሃገራቸው ዛሬ ላይ እንድትደርስ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል።

ወደ ኢትዮጵያ ስንመጣ፣ ሀገሪቱ ረጅም ታሪክ ያላት ቢሆንም ውስብስብ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ፈተናዎችን ስታልፍ ቆይታለች። አሁን ላይ እነዚህን ችግሮች ለመፍታትና ዘላቂ ሀገር ለመገንባት ሰፊ የለውጥ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “መደመር” በተሰኘው መጽሐፋቸው ውስጥ እንደገለጹት፦"ጠንካራ ሀገር የሚገነባው በጠንካራ ግለሰቦች ብቻ ሳይሆን፣ ነጻ፣ ገለልተኛና በሙያዊ ብቃት የተገነቡ ጠንካራ ተቋማትን በመፍጠር ነው። ተቋማት የሀገር ሕልውና አስከባሪ፣ የግለሰቦችን ፍላጎት አስተካካይና የታሪክ መሸጋገሪያ ድልድዮች ናቸው።"

በዚህም ባለፉት አምስት ዓመታት መንግሥት በዚህ ላይ ትኩረት አድርጎ ሰርቷል። ከዚህ ውስጥ አንዱ የፍትህ እና የሰብዓዊ መብት ማሻሻያ ነው። የፍትሕ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ፍኖተ ካርታ በመቅረጽ፣ ፍርድ ቤቶች ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ነጻ እንዲሆኑና በህግና በማስረጃ ብቻ እንዲሰሩ ተደርጓል። ያለፉ ቁስሎችን ለመፈወስ የሽግግር ፍትህ ስርዓት መዘርጋቱ የፍትህ አካላትን አመኔታ ጨምሮታል።

ሌላው በኢኮኖሚው ላይ የተደረገው ጥልቅ ማሻሻያ ሲሆን፤ ኢኮኖሚው ከቀደመው የተወሰኑ ዘርፎች ላይ ብቻ ከተንጠለጠለ አሰራር ወጥቶ ወደ ብዝሃ ዘርፍ ማለትም ግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝምና ቴክኖሎጂ እንዲሸጋገር የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ በመደረጉ ውጤት ማምጣት ተችሏል።

የመሰረተ ልማት እና የሰው ሀብት ልማት ላይም የተሰራው ስራ ለጠንካራ ሀገር ግንባታ መሰረት የሚጥል ነው። በትራንስፖርት፣ በኃይል፣ በኮሙኒኬሽን እና በጤና አውታሮች ላይ የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች ከሀገር በቀል የትምህርት ፖሊሲ ጋር ተጣጥመው የነገውን ትውልድ ለማንጽ እየሰራ ይገኛል።

ከምንም በላይ ደግሞ ለጠንካራ ሀገር ግንባታ የተግባባ እና አንድነቱ የተጠናከረ ማህበረሰብ መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ፤ ለዚህም መንግስት ታሪካዊ ስብራቶችን ለመጠገንና በዋና ዋና ብሄራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ያስችል ዘንድ የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን በማቋቋም ወደ ስራ በማስገባት ማህበረሰቡ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መግባባት እንዲፈጥሩ ተደርጓል። ይህም የሰላምና የአንድነት መሰረት እየጣለ ይገኛል።

ብዙ ጸሐፊያን እንደሚያምኑት የሀገር ግንባታ የሒደት ውጤት ነው። በውይይት የሚፈቱ ልዩነቶች፣ ነፃና ገለልተኛ ተቋማት፣ ጥራት ያለው ትምህርት እና የዜጎች የጋራ ጥረት ሲቀናጁ የጸናችና የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ይቻላል።

"የ21ኛው ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ኅብረ-ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር ለዘላቂ ሰላም እና ለኢኮኖሚ ዕድገታችን ጉልህ አበርክቶ ይኖረዋል" — አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገርየኢ...
01/09/2026

"የ21ኛው ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ኅብረ-ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር ለዘላቂ ሰላም እና ለኢኮኖሚ ዕድገታችን ጉልህ አበርክቶ ይኖረዋል" — አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር

የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤና የበዓሉ አስተባባሪ ዐቢይ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አገኘሁ ተሻገር በ21ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ላቅ ያለ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ውጤት እንዲመዘገብ ከወዲሁ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ገለጹ።

አፈ ጉባኤው እንዳመለከቱት በዓሉ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ባህልና ልምዳቸውን በመለዋወጥ ኅብረ-ብሔራዊና ዲሞክራሲያዊ አንድነታቸውን እንዲያጠናክሩ እንዲሁም ለሀገራችን ዘላቂ ሰላምና ዘርፈ-ብዙ የኢኮኖሚ እድገት በጋራ እንዲቆሙ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።

በዓሉ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ እና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ተጠናቅቆ አዲስ መንግሥት በተመሰረተበት፣ ሀገራዊ ችግሮችን በምክክር ለመፍታት መሠረት በተጣለበት እንዲሁም የዲሞክራሲ ባህልን የሚያጎለብቱ በርካታ አገራዊ ሁነቶች በተከናወኑበት ማግሥት የሚከበር በመሆኑ የተለየ ትርጉምና ገጽታ ይኖረዋል።

የገዳ ሥርዓትን ጨምሮ የበርካታ ታሪካዊና ባህላዊ ሀብቶች ባለቤት በሆነችው ታሪካዊቷ የጅማ ከተማ በሚካሄደው በዚህ በዓል፣ የሕዝቦች ወንድማማችነትና አብሮነት ከፍ ብሎ እንደሚንፀባረቅ ተጠቅሷል።

በዚሁ የምክክር መድረክ በፌዴሬሽን ምክር ቤት የመንግሥታት ግንኙነት፣ የዲሞክራሲያዊ አንድነትና የሕገመንግሥት አስተምህሮ ቋሚ ኮሚቴ ጸሐፊ ወ/ሮ ባንቺይርጋ መለሰ የበዓሉን ረቂቅ መሪ ዕቅድ አቅርበው ጥልቅ ውይይት እንደተደረገበት ከምክር ቤቴ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የሸካ ዞን የ2018 የአመራር ግምገማና ምዘና መድረክ እየተካሄደ ነውየሸካ ዞን የ2018 በጀት ዓመት የአፈጻጸም ማጠቃለያ የአመራር ግምገማና ምዘና መድረክ በቴፒ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። በ...
29/08/2026

የሸካ ዞን የ2018 የአመራር ግምገማና ምዘና መድረክ እየተካሄደ ነው

የሸካ ዞን የ2018 በጀት ዓመት የአፈጻጸም ማጠቃለያ የአመራር ግምገማና ምዘና መድረክ በቴፒ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ መክፈቻ ላይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ የሺዋስ አለሙ፤ በበጀት ዓመቱ የመንግሥትና የፓርቲ ተልዕኮዎችን በተሻለ አቅም በማስኬድ የሕዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ አበረታች ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።

አያይዘውም፣ አመራሩ በብልፅግና ፓርቲ መርሆዎችና ዕሴቶች ላይ የተመሠረተ፣ ተልዕኮውን በጥልቀት የተረዳ እና ጠንካራ ትግል ማድረግ እንደሚገባው አሳስበዋል።

​የዚህ የግምገማና ምዘና መድረክ ዋና ዓላማዎች ያሳካናቸውን ተግባራት ጥራትና ውጤታማነት በአግባቡ መገምገም፣ የውስጠ-ፓርቲ ጤንነትንና የዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት መርህን በማክበር ጠንካራ የአመራር ሥርዓት መዘርጋት እንዲሁም በሂደቱ ላጋጠሙ ችግሮች ቆራጥ መፍትሔ መስጠት ለመስጠት መሆኑን ገልጸዋል ።

ይህ የምዘና መድረክ የበጀት ዓመቱን አፈጻጸም በመፈተሽ ጥንካሬዎችን ለማጠናከር፣ ድክመቶችን ለማረም እና አመራሩ ለቀጣይ ተልዕኮዎች በብቃት ዝግጁ እንዲሆን ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን አመላክተዋል ።

​የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ የሺዋስ አለሙ እና የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ጫናቸው ወንድሙ በጋራ እየመሩት በሚገኘው በዚህ መድረክ ላይ የሸካ ዞን አጠቃላይ አመራርና የወረዳ/ከተማ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

ይህ የግምገማና ምዘና መድረክ ለተከታታይ ሦስት ቀናት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተመላክቷል።

በየቦታው "አፈሳ አለ" በሚል ህብረተሰቡ እንዳይረጋጋ የሚያደርጉ አካላት ከድርግታቸው መቆጠብ እንደሚገባ የማሻ ወረዳ ሠላም ፀጥታና ሚልሻ ጽ/ቤት አስታወቀ‎‎በ​ማሻ ወረዳ ውስጥ ወጣቶች ያለፍ...
28/08/2026

በየቦታው "አፈሳ አለ" በሚል ህብረተሰቡ እንዳይረጋጋ የሚያደርጉ አካላት ከድርግታቸው መቆጠብ እንደሚገባ የማሻ ወረዳ ሠላም ፀጥታና ሚልሻ ጽ/ቤት አስታወቀ

‎በ​ማሻ ወረዳ ውስጥ ወጣቶች ያለፍቃዳቸው በግዴታ እየተወሰዱ ነው በማለት የምናፈሰውን መረጃን አስመልክቶ የማሻ ወረዳ ሠላም ፀጥታና ምልሻ ጽ/ቤት መግለጫ ሰጠ ።

‎የማሻ ወረዳ ሠላም ፀጥታና ሚልሻ ጽ/ቤት ኃላፍ አቶ ትግሉ ታደሰ እንደገጹት ሰሞኑን በወረዳው ባሉት ቀበሌዎች እና በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ በወረዳው አፈሳ አለ በሚል የሚናፈሱ ሃሰተኛ መረጃዎች ህብረተሰቡን ለማስደንገጥ ሆን ተብለው የተፈጠሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

‎ይህ የሃሰት መረጃ የህዝብን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ለማስተጓጎልና በነዋሪው መካከል አላስፈላጊ ስጋት ለመፍጠር የታለመ እና በወረዳው ምንም አይነት መደበኛ ያልሆነ ህገወጥ አፈሳ እንዳልተካሄደ የጸጥታ ሁኔታው ሙሉ በሙሉ ሰላማዊ እንደሆነ ኃላፍው አመላክተዋል ።

‎ከዚህ እውነት ውጪ በግዳጅ የተፈጠረ ነገር የለም፥ነገም አይፈጠርም ያሉት ኃላፊው ህብረተሰቡ ያልተረጋገጡ መረጃዎችን በማጋራት ለተጨማሪ ወንጀል ራሱን አሳልፎ መስጠት እንደሌለበትም አክለዋል።

‎የማሻ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ደበበ ደቁሾ በበኩላቸው በወረዳውም ፍላጎት ያላቸው ወጣቶች የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባል በመሆን ሀገራቸውን እንዲጠብቁና በዘርፉ ሰልጥነው የሙያ ባለቤት እንዲሆኑ እንደ ሀገር በወረደው አቅጣጫ መሰረት ምዝገባ ሲካሄድ እንደነበር እና ይህ ምዝገባ በፍላጎትና በሰላማዊ መንገድ እንጂ በወረዳው ምንም አይነት መደበኛ ያልሆነ ህገወጥ አፈሳ እንዳልተካሄደ የጸጥታ ሁኔታው ሙሉ በሙሉ ሰላማዊ እንደሆነ ገልጸዋል ።

‎የሃገር መከላከያ ምልመላ ወጣቶች በፍላጎታቸው የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበርና ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የሚሰለጥኑበትና የሙያ ባለቤት የሚሆኑበት ተቋም እንጂ ያላግባብ ከህግ ውጭ ሰው ታፍሶ የሚወሰድበት ቦታ አይደለም ብለዋል ።

‎በወረዳው ህብረተሰቡ የሃሰት ፕሮፓጋንዳዎችንና ወሬዎችን በንቃት በመከላከልና ባለመቀበል ለወረዳው ዘላቂ መረጋጋት የድርሻውን እንዲወጣ ከእውነታው በራቁ መሰል ወሬዎች ሳይደናገጥ የተለመደውን የዕለት ተዕለት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴውን በሰላም እንዲቀጥል ጠቁመዋል ።

‎በመጨረሻም የሃሰት መረጃዎችን በሚያሰራጩ እና በህዝብ መካከል አላስፈላጊ ፍርሃትና ስጋት በሚፈጥሩ አካላት ላይ ጥብቅ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ የገለጹት የፖሊስ አዛዡ የሀሰት መረጃዎችን የሚያሰራጩ አካላት አጀንዳን አለመጋራትና ለሚመለከተው አካል ማጋለጥ የእያንዳንዱ ነዋሪ ኃላፊነት ሊሆን እንደሚገባም አሳስበዋል ።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

‎↪️በቴሌግራም https://t.me/Mashawordacom
‎↪️ፈስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100065002861326
‎↪️ቲክቶክ https://vm.tiktok.com/ZS9JC9jDNrd8S-1XYDP/
‎↪️ዋቲስአፒ https://chat.whatsapp.com/Hw5eZF6lr3j3Ylz29czbrP?mode=gi_t


በMMA Adwa  fight በደቡብ ምዕራብ የቡና መገኛ ምድር ካፋ ፍሬ ንቃተ ህሊና  ከሮቤል ጋር ያደረገውን ፊልሚያ በአሸናፊነት አጠናቋል::             ድል ለጫካው አንበሳ
27/08/2026

በMMA Adwa fight በደቡብ ምዕራብ የቡና መገኛ ምድር ካፋ ፍሬ ንቃተ ህሊና ከሮቤል ጋር ያደረገውን ፊልሚያ በአሸናፊነት አጠናቋል::
ድል ለጫካው አንበሳ

Address

Sheka Zone Masha Woreda Govt. Dep. T
Masha

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Masha Woreda Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share