23/09/2025
🏆🏆🏆እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ፡፡🏆🏆🏆
የመ/ጌ/ም/ወ/ም/ቤት /ቤት በ2017 በጀት አፈፃፀም በተደረገ የስራ አፈጻፀም ግምገማ ሁለተኛ ደረጃ መውጣቱ ይታወቃል፡፡
የሰ/ሽዋ ዞን የተዋረድ ም/ቤቶች ፎረም በደብረብርሀን ከተማ በደማቅ ሁኔታ ተካሄዷል፡፡ በፎረሙ ላይ የከተማ የወረዳ ም/ቤት አፈ-ጉባኤዎች፣ ም/አፈ-ጉባኤዎችና የቋሚ ኮሚቴዎች ሰብሳቢዎች ተሳትፈዋል፡፡
ፎረሙ የተዋረድ ም/ቤት የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማና የቀጣይ የ2018 ዓ.ም እቅድ ትውውቅ መርሀ-ግብር አድርጓል፡፡
በበጀት አመቱ የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ም/ቤት የላቀ ተግባር በመፈፀም ከ22 ወረዳ ም/ቤቶች ጋር ተወዳድሮ 2ኛ ደረጃን አግኝተናል፡፡
ለዚህ ውጤት መምጣት የቀበሌ ም/ቤቶቻችን ፣የወረዳ ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች፣ የወረዳ ም/ቤት አባላት እና ባለድርሻ አካላት ለነበራቸው አስተዋጽኦ በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ም/ቤት ስም አመሰግናለሁ ፡፡
የመ/ጌ/ም/ወ/አፈ-ጉባኤ አቶ መከተ ጌታቸው፤