23/08/2026
የግብር ከፋዮች የውይዮት መድረክ አካሄደ።
ነሐሴ 17/2018 ዓ.ም የመ/ሜዳ ከተማ አሰ/ገቢዎች ጽ/ቤት ከግብር ከፋዩ ጋር ውይይት አደረገ።
የመ/ሜዳ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት በ2019 የሚሰበሰበውን ዕቅድ ትውውቅ እና በተሻሻለው የገቢ ግብር በአዋጅ ቁጥር 301/2018 እና የከተሞች አገልግሎት ግብር ማስከፈያ ደንብ ቁጥር 257/2018 ዓ.ም መሰረት በማድረግ የተዘጋጀውን ሰነድ የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ መለሰ በላይግዛው አቅርበዋል።
አቶ መለሰ እንዳሉት በአዲሱ የቀን ገቢ የግብር ጥናት መሰረት ሁሉም ግብር ከፋይ በስልኩ ሜሴጅ በደረሰው በ30 ቀን ውስጥ መክፈል አለበት። ቅሬታ አለኝ የሚል ግብር ከፋይ ቅሬታ የማቅረብ መብቱ የተጠበቀ በመሆኑ እስከ 21 ቀን ድረስ ማቅረብ ይችላል በማለት አንስተዋል።
ግብሩን በተባለው ጊዜ የማይከፍል ከሆነ ለተጨማሪ ቅጣትና ወለድ ይዳረጋል ብለዋል።
የከተማ አገልግሎት ግብር አከፋፈልን በተመለከተ የተሻሻለው ደንብ ዋና ዋና ነጥቦችን አንስተው ግንዛቤ በማስጨበጥ ሁሉም በደንብ ቁጥር 257/2018 ዓ.ም መሰረት መክፈል አለበት ብለዋል።
በመጨረሻም የቀረበውን ሰነድ መነሻ በማድረግ በርካታ ጥያቄዎች ተነስተው ምላሽ ተሰጥቶባቸው እና መልካም መግባባት ተፈጥሮ የውይይት መድረኩ ተጠናቋል።
https://www.facebook.com/share/14j8LpeCdGf/
telegram : https://bit.ly/4fivr4o