Bench Sheko Zone High Court

Bench Sheko Zone High Court Judiciary Organ 0471356701

የታክስ ማጭበርበር ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ የ8 ዓመት ከ4 ወር ጽኑ እስራት እና የ40,000 ብር ቅጣት ተፈረደበት።አርባ ምንጭ፣ ሐምሌ 30/2017 ዓ.ም የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፌ...
06/08/2025

የታክስ ማጭበርበር ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ የ8 ዓመት ከ4 ወር ጽኑ እስራት እና የ40,000 ብር ቅጣት ተፈረደበት።

አርባ ምንጭ፣ ሐምሌ 30/2017 ዓ.ም
የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጆችን በመጣስ የተከሰሰውን አቶ አብደላ እንድሪስን የ8 ዓመት ከ4 ወር ጽኑ እስራት እና የ40,000 ብር የገንዘብ መቀጮ ወሰነ።
በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የቆላ ሸሌ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ አብደላ እንድሪስ በወረዳው በአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ ዘርፍ ተሰማርቶ የነበረ ሲሆን፣ የጋሞ ዞን ታክስ አስተዳደርና ገቢዎች ዐቃቤ ህግ ባቀረበው ክስ መሰረት፣ የተጭበረበሩ የታክስ ሰነዶችን ለገቢ ተቋም በማቅረብ እና ታክስ በመሰወር ወንጀሎች ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል።
በመዝገብ ቁጥር 50216 የተመዘገበው ይህ ክስ፣ ተከሳሹ የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 118/1(ሐ) እና 125/1ን መተላለፉን ያመለክታል።
ፍርድ ቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎት በሰውና በሰነድ ማስረጃዎች የጥፋተኝነት ድርጊቱ መረጋገጡን ተከትሎ በተከሳሽ አቶ አብደላ እንድሪስ ላይ የ8 ዓመት ከ4 ወር ጽኑ እስራት እና የ40,000 ብር የገንዘብ መቀጮ ወስኖበታል።
የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ታክስ መሰወር በህግ የሚያስቀጣ ከባድ ወንጀል መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን፣ ሌሎች ግለሰቦችም ከመሰል ህገ-ወጥ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ መልዕክት ያስተላልፋል።
(አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት)፦

 #ጉቦ የተቀበለ የፍርድ ቤት አስተዳደር ሠራተኛ  #በጽኑ እስራት  #ተቀጣ ወላይታ ሶዶ፣ሐምሌ 30/2017 ዓ.ም የፍትህ ደላላ በመሆን ጉቦ የተቀበሉ የዳሞት ወይዴ ወረዳ ፍርድ ቤት የአስተዳ...
06/08/2025

#ጉቦ የተቀበለ የፍርድ ቤት አስተዳደር ሠራተኛ #በጽኑ እስራት #ተቀጣ

ወላይታ ሶዶ፣ሐምሌ 30/2017 ዓ.ም የፍትህ ደላላ በመሆን ጉቦ የተቀበሉ የዳሞት ወይዴ ወረዳ ፍርድ ቤት የአስተዳደር ሠራተኞች በመጋቢት 21/2017 ዓ.ም በሕግ ቁጥጥር ስር ሆነው የክስ ክርክር ሲካሄድ መቆየቱ ይታወሳል።
በወላይታ ዞን ዳሞት ወይዴ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቋሚ ሠራተኛ ሆነው እየሰሩ በነበሩበት ወቅት በተለያዩ ጊዜያት "ከዳኞች ጋር እናገናኛለን፤ እናንተ ገንዘብ ከሰጣችሁን መዝገቡን ለሚሰራው ዳኛ ገንዘቡን በመስጠት ለእናንተ እናስወስናለን፤ ገንዘቡን ለዳኞች በማድረስ ውሳኔውን እናሻሽላለን፤ እናስቀይራለን፤ የቅጣት መጠኑን እናስቀንሳለን፤ ከክሱ በነጻ እንድትሰናብቱ እናስደርጋለን፣ ወዘተ" በማለት በሐሰት ወሬ ሕብረተሰቡን ሲያወናብዱ እና ገንዘብ ሲቀበሉ የነበሩ የፍትህ ደላሎች ላይ የክስ ሂደቱን ሲከታተል የነበረው የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከሶስቱ ተከሳሾች አንዱ ላይ ጥፋተኛ በማለት 3(ሦስት) ዓመት ጽኑ እስራት እና 1,000 ብር እንዲቀጡ ወስኗል።
በወንጀሉ ተከስሶ ጥፋተኛ ተብሎ የፍርድ ውሳኔና ቅጣት ያገኘው ኢሳያስ ጫማሳ የተባለ የፍርድ ቤቱ የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ሥራ ሂደት አስተባባሪ ሲሆን የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት እና የወረዳው ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ጽ/ቤት ከሕብረተሰቡ ያገኘውን ጥቆማ መሠረት በማድረግ ባደረገው ምርመራ ግለሰቦ የተሰጠውን የሕዝብና የመንግስት ኃላፊነትን ወደ ጎን በመተው በተለያዩ ጊዜያት ከተለያዩ ግለሰቦች ጉቦ መቀበሉን በሰው እና በሰነድ ማስረጃ ማረጋገጥ መቻሉን የወረዳው ፖሊስ አዛዥ መቶ አለቃ ይስሐቅ ቦሻ ጠቁመዋል።
ፍትህ እና ርትህ በገንዘብ እንደሚሸመት ሸቀጥ በማድረግ በሕዝብ ላይ ከፍተኛ ለገንዘብ ብዝበዛ እና የሥነ ልቦና ጉዳት በማድረስ፣ ተገልጋዩ ሕዝብ በፍርድ ቤቶችና ዳኞች ላይ ያለው አመኔታ እንዲሸረሸርና ቅቡልነትን እንዲያጣ በማድረግ፣ ከተላያዩ ባለጉዳዮች የውሸት ተስፋ ቃል በመስጠት እና የፍትህ ደላላ በመሆን የፍርድ ቤቱን እና ዳኞችን መልካም ስም በሚያጎድፉ፣ ፍርድ ቤቱ በህገ መንግስቱ የተጎናጸፈውን ነጻ እና ገለልተኛ ተቋም ሆኖ በህዝቡ ዘንድ እንዳይታይ በማድረግ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ በሚያደርሱ አካላት ላይ የወረዳው አስተዳደር የማያዳግም ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድም የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተክሌ ቶማ ገልጸዋል።
የወረዳው ፖሊስ ሕብረተሰቡ እንደዚህ ዓይነት ሕዝብን የሚያማርሩ፣ መንግስታዊ አገልግሎትን በጉቦ፣ በእጅ መንሻና በምልጃ የሚሰጡ አመራርና ባለሙያዎች ላይ የተለመደውን ጥቆማ በመስጠት የተጀመረውን የፀረ ሙስና ትግል እውን እንዲሆን የሁሉም ዜጋ ግዴታ መሆኑን ገልጿል።

14/07/2025
ከ15 ሚሊየን ብር በላይ ለግል ጥቅም በማዋል የተጠረጠሩ 24 ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሰረተ አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2017 ዓ.ም (ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ) ከ15 ሚሊየን ብር በላይ ለግል ጥቅም በማ...
02/07/2025

ከ15 ሚሊየን ብር በላይ ለግል ጥቅም በማዋል የተጠረጠሩ 24 ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሰረተ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2017 ዓ.ም (ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ) ከ15 ሚሊየን ብር በላይ ለግል ጥቅም በማዋል የተጠረጠሩ የቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምርታማነት ማሻሻያ ልህቀት ማዕከል ዲንን ጨምሮ 24 ግለሰቦች ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው።

ክሱ የተመሰረተው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የሙስና ጉዳዮች ችሎት ነው።

ተከሳሾቹ ፍሬው አመነ በምርታማነት ማሻሻያ ልህቀት ማዕከል ዲን፣ ተፈሪ ፈይሳ የማዕከሉ ምክትል ዲን እና ኢንተርፕርነርሺፕ አሰልጣኝ፣ ሀይማኖት አቡን በማዕከሉ ምክትል ዲን፣ ወ/ሮ አሊማ መሃመድ ፋይናንስ ዳሬክተር፣ ሶስና መሃመድ ግዢ ዳይሬክተር እና እንግዳ ወንድአፍረሽ የኦዲት ዳይሬክተርን ጨምሮ 24 ናቸዉ።

1ኛ ክስ በ1ኛ፣ 3ኛ፣ 4ኛ፣ 5ኛ፣ 8ኛ፣ 9ኛ፣ 10ኛ፣ 11ኛ፣ 12ኛ እና 13ኛ ተከሳሾች ላይ የቀረበ ሲሆን በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 (1) (ሀ) እና የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 9 (1) (ሀ) እና (2) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ የማይገባ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት ወይም ለሌላ ለማስገኘት እና በመንግስት ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ የሚል ነው።

1ኛ፣ 3ኛ፣ 4ኛ እና 8ኛ ተከሳሾች ያለ ክፍያ መሰጠት ያለበት ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የሚሰጥ ስልጠና፤ በተቋሙ የሚሰጡ ስልጠናዎች ያለ ክፍያ መሰጠት ያለበት መሆኑን የሚገልፀውን የአሰራር መመሪያ በመተላለፍ 3ኛ ተከሳሽ አበል ክፍያ እንዲፈፀም በደብዳቤ በመጠየቅ፣ 1ኛ ተከሳሽ ክፍያውን በመፍቀድ በማፅደቅ ከ459 ሺህ ብር በላይ ወደ 11ኛ ተከሳሽ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር በማስተላለፍ ለግል ጥቅማቸዉ ያዋሉ እና ያለአግባብ የስልጠና አበል ክፍያ የከፈሉ በመሆኑ።

1ኛ እና 8ኛ ተከሳሾች የስልጠና አበል 200 ሺህ ብር ወደ 11ኛ ተከሳሽ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ በማስተላለፍ ለግል ጥቅማቸዉ ያዋሉ ሲሆን ያለአግባብ የስልጠና አበል ክፍያ በመክፈል 1ኛ፣ 4ኛ እና 8ኛ ተከሳሾች፣ 8ኛ ተከሳሽ የክፍያ ሂሳብ በማዘጋጀት በመመሪያ መሰረት ሁሉም ቅድመ ሁኔታዎች ባልተሟላበት ሁኔታ እና ሊከፈል የማይገባዉ ክፍያ 300 ሺህ ብር እንዲከፈል በማድረግ፣ በ4ኛ ተከሳሽ የክፍያ ሂሳብ ፈቃጅነትና አረጋገጭነት እንዲሁም በ1ኛ ተከሳሽ ክፍያን በማፅደቅ 143 ሺህ ብር ያለአግባብ የውሎ አበል ክፍያ እንዲፈፀም ያደረጉ በመሆኑ።

በአጠቃላይ ተከሳሾች የተቋሙ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በመሆናቸዉን የተሰጣቸውን ኃላፊነት በግልፅ ተግባር በመተላለፍ ከተቋሙ ባንክ ሂሳብ ቁጥር በድምሩ 2 ሚሊየን 400 ሺህ ብር ወደ ራሳቸዉ እና የተለያዩ አካላት ባንክ ሒሳብ በማስተላለፍ ለግል ጥቅም በማዋል እና በዚሁ ልክ በማዕከሉ ላይ ጉዳት እንዲደርስ ያደረጉ በመሆናቸዉ፤ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈጸሙት ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።

ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል የነገ ስብዕናን ይገነባል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

"ማንኛውም ሰው በገንዘብ እጦት ምክንያት ፍትህን ማጣት የለበትም " ----------------------------------------------------------------------የሚዛን ቴፒ...
24/06/2025

"ማንኛውም ሰው በገንዘብ እጦት ምክንያት ፍትህን ማጣት የለበትም "
----------------------------------------------------------------------
የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ህግ ትምህርት ቤት ነፃ የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል
ለቤን ሸኮ ዞን ፤ ሚዛን ከተማ እና ለአካባቢው ነዋሪዎች በሙሉ !!
የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ነፃ የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል አቅም ለሌላቸው እና የህግ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ማንኛውም ሰው ወይም አካል ፤-
• ነፃ የህግ ምክር አገልግሎት በአካልም ሆነ በስልክ መስጠት
• የነፃ የጥብቅና አገልግሎት መስጠት
• ነፃ የክስ -መልስ -ይግባኝ - ውል -የጋብቻ እና የተለያዩ የህግ ፅሁፎችን አዘጋጅቶ መስጠት
• ከባለጉዳዮች ጋር የእርቅ ስምምነት ማስፈጸም ወዘተ ነፃ የህግ አገልግሎት የሚሰጥ እና አድራሻውም በቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ግቢ ውስጥ መሆኑን አውቃችሁ ነፃ የህግ ድጋፍ አገልግሎቱን እንድትጠቀሙ እናስታውቃለን ፡፡
≠mizan tepi university

07/06/2025

ከ696 ሺህ ብር በላይ የመንግስትን እና የህዝብን ሀብት የመዘበረው አቶ ካሣዬ ዎታሮ በተከሰሰበት የሙስና ወንጀል 18 ዓመት ከ6 ወር እና 20 ሺህ ብር እንዲቀጣ የኮንሶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሣኔ አስተላለፈ፣

ተከሳሽ አቶ ካሣዬ ዎታሮ በካራት ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የወረዳው ሠራተኞች ፔሮል አዘጋጅ ባለሙያ ሆኖ በሚሠራበት ወቅት ተገቢ ያልሆነ ጥቅማ ጥቅም ለማግኘት በርካታ ህገ ወጥ ተግባራት ማከናወኑን ከፍተኛ ፍ/ቤቱ ማረጋገጡን ገልጿል።

ጥፋተኛው አቶ ካሣዬ ዎታሮ የወረዳውን ሠራተኞች ፔሮል እየሠራ ባለበት ከ2012 ዓ/ም ነሐሴ ወር ጀምሮ ለ36 ወራት 52 ሀሰተኛ ስሞችን በፔሮል ላይ በመፃፍና በስሞቹ ፊት ለፊት የራሱን የግል የንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር በማስገባት ማጭበርበሩን ፍርድ ቤቱ አረጋግጧል።

ፍርደኛው አቶ ካሣዬ ዎታሮ ለስራ ግብር የተቀነሰ 142 ሺህ 053 ብር ከ92 ሳንቲም፣ ለጡረታ መዋጮ የተከፈለ 112 ሺህ ብር ከ29 ሳንቲም፣ ለኤች አይ ቪ የተከፈለ መዋጮ 2 ሺህ 205 ብር ከ97 ሳንቲም በድምሩ 696 ሺህ 134 ብር ከ24 ሳንቲም ወደ ግሉ የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ በህዝብና በመንግስት ሀብት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ገልጿል ፍ/ቤቱ።

የሙስና ወንጀልን በተመለከተ የበወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 23(2)ሀ)) በመተላለፍና መንግስታዊ ሰነዶችን አስመስሎ በማዘጋጀት የሙስና ወንጀል በመከሰሱ፣ ፍ/ቤቱ በህግ አግባብ ግራ ቀኙን አከራክሮ ተከሳሹ የቀረበበትን ክስ በአግባቡ ባለመከላከሉና በተከሰሰበት የሙስና ወንጀል አንቀጽ 23(2)ሀ)) መሰረት ግለሰቡ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ውሳኔ አስተላልፏል።

በመቀጠልም ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የተከሳሽና የከሳሽ ዐቃቤ ህግ የቅጣት አስተያየትን ተቀብሎ የመረመረ ሲሆን፣ በዚህም መሠረት በቀን 25/09/2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት በተሻሻለው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ መሠረት ተከሳሹ በፈፀመው የሙስና ወንጀል በ18 ዓመት ከ6 ወር እና በ20 ሺህ ብር መቀጮ እንዲቀጣ ከመወሰኑ በተጨማሪ ለግል ጥቅሙ ያዋላቸውን 696 ሺህ 134 ብር ከ24 ሳንቲም ለመንግስት ገቢ እንዲያደርግ ወስኗል።

የመንግስትን እና የህዝብን ሀብት ለግል ጥቅም ለማዋል በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ መንግስት የጀመረው የህግ በላይነትን የማረጋገጥ ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን እና ማንኛውም ጥፋተኛ ከህግ ማምለጥ እንደማይችል የዛሬው ውሳኔ ማሳያ ነው ያሉት የዞኑ ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ጋደቦ ገዋዶ፤ ህብረተሰቡ ይህንን ተገንዝቦ ወንጀለኛን የማጋለጥና ለህግ አሳልፎ የመስጠት ልምድ በማዳበር የመንግስትና የህዝብ ሀብት ለታለመለት ዓላማ ብቻ እንዲውል በቅንጅት ልንሠራ ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል።

መረጃው
የኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ
ግንቦት 26/2017 ዓ.ም

የቤንች ሸኮ ዞን ከፍ/ፍ/ቤትና 10ሩ ሥር ፍ/ቤቶች በ2017 በጀት ዓመት በ9ወር  አፈፃፀም በመልካም አስተዳደርና በአገልግሎት አሠጣጥ ዙሪያ  ከተገልጋይ ህብረተሰብና ከባለድርሻ አካላት የተ...
26/03/2025

የቤንች ሸኮ ዞን ከፍ/ፍ/ቤትና 10ሩ ሥር ፍ/ቤቶች በ2017 በጀት ዓመት በ9ወር አፈፃፀም በመልካም አስተዳደርና በአገልግሎት አሠጣጥ ዙሪያ ከተገልጋይ ህብረተሰብና ከባለድርሻ አካላት የተሰጡትን አስተያየቶችን ላይ አሰመልክቶ በተደረገው የውይይት መድረክ ፦
1:- ከባለድርሻ አካላትና ተገልጋዮች በእያንዳንዱ ፍ/ቤት ላይ የተሰጡትን አስተያየቶች በዳኝነት አገልግሎት አሰጣጡ ላይ የተነሱት ጉዳዮች ዞናዊ ሪፖርት
2:-የዞኑ ፍ/ቤቶች ላይ የተሰራው የዳሰሳ ጥናት ሪፖርት
3:-በዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለማስተካከልና ለማረም የተወሰዱ ተግባራትና ጉዳዮች ሪፖርት
5-:የመዝገቦች እና የችሎት ኢንስፔክሽንና ሱፐርቪዝን ግኝቾች ሪፖርት እንዲሁም
6:- በ9 ወር የስራ ክንውን የእያንዳንዱ ፍ/ቤት የቀረበለትና የወሰነው መዝገብ እንዲሁም ወደ 4 ሩብ አመት ያስተላለፉት መዝገብና መዝገብ የማስተላለፍ ምጣኔ በፐርሰንት ሪፖርት ቀርቦ በዝርዝር የተገመገመ ሲሆን በእያንዳንዱ ፍ/ቤት ያሉ ፕሬዝዳንትና ዳኞች የስራ ሃላፊዎች ከባለድርሻ አካላት እና ከተገልጋይ የተነሱት ችግሮች እና የአሰራር ግድፈቾች ልክ መሆናቸውን እና በቀረቡተት ሪፖርቶችንም በዝርዝር ግምገማ በመተማመን ለጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቆጭቶ ገ/ማርያም ፤ ለዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቢንያም ባቡ ለዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ም/ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ሻንበል ቦሽ ለተነሱት ጥያቄዎች እና አስተያየቶች በዝርዝር አስረድተዋል በቀጣይ በቁርጠኝነት የተነሱትን ችግሮች በማረም ለመስራትና ለመካስ ቃል በመግባት ባለ 5 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት በሙሉ ድምፅ የፀደቀ ሲሆን ከዞን እና ከክልል ፍ/ቤት ፕሬዝዳንቶች በቀጣይ መሠራት ያለባቸውን የትኩረት አቅጣጫ እና የስራ ስምሪት በመስጠት የውይይት መድረኩ ተጠናቋል

የቤንች ሸኮ ዞን ከፍ/ፍ/ቤትና 10ሩ ሥር ፍ/ቤቶች በ2017 በጀት ዓመት በ9ወር  አፈፃፀም በክልል በዞን በወረዳ እና ከተማ አስተዳደር ከባለድርሻ አካላትእና ከተገልጋይ ማህበረሰብ  በዳኝነ...
26/03/2025

የቤንች ሸኮ ዞን ከፍ/ፍ/ቤትና 10ሩ ሥር ፍ/ቤቶች በ2017 በጀት ዓመት በ9ወር አፈፃፀም በክልል በዞን በወረዳ እና ከተማ አስተዳደር ከባለድርሻ አካላትእና ከተገልጋይ ማህበረሰብ በዳኝነት አገልግሎት እና በመልካም አስተዳደር ላይ የተሰጡትን አስተያየቶችን አሰመልክቶ ውይይት የጋራ ማጠቃለያ መድረክ እየተደረገ ይገኛል።

የቤንች ሸኮ ዞን ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈየቤንች ሸኮ ዞን ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የካቲት 10 ቀን 2017 ዓ/ም ባደረገው 5ተኛ ዓመት 2ተኛ ዙር 9ኛ አስቸኳይ ጉ...
20/02/2025

የቤንች ሸኮ ዞን ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ
የቤንች ሸኮ ዞን ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የካቲት 10 ቀን 2017 ዓ/ም ባደረገው 5ተኛ ዓመት 2ተኛ ዙር 9ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ላይ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ
1. በዳኝነት ነፃነት ተጠያቂት የሥራ ሂደት እና በምድብ ችሎት ዳኛ መሃከል በነበረው የዲሲፕሊን ክስ ተከሳሹ ዳኛ ተካ ግርማ የኢተቃ ምድብ ችሎት ዳኛ ሆነው እየሰሩ 1ኘ ክስ ፤-በመ/ቁጥር 64 በተመሰረተው የፍ/ር ክርክር ጉዳዩን ተመልክተው ብር 155.000 ብር ተከሳሽ እንዲከፍል ወስነው የፍርድ ባለመብት አፈፃፀም ክስ መስርቶ የፍርድ ባለዕዳ ንብረታቸውን በጨረታ በቀበሌ አስተዳዳሪ በኩል ተሽጦ ጠቅላላ 155.000 ብሩን አቅርቦ ለፍርድ አፈፃፀም ከሳሽ ገንዘቡን ሳይሰጡት ፍርዱ ተፈፅሞ እንዳለቀ በማስመሰል ትዕዛዝ ሰጥተው መዝገቡ የዘጉና በዳኝነት ስልጣናቸው በፍርድ ተወስኖ በፍርድ አፈፃጸም የተከፈለን የግል ገንዘብ ከቀን 07-10-2015 ዓ/ም ጀምሮ የግል ተበዳይን የግል ገንዘብ በመጠቀም የዳኝነት ስልጣኑን ባልተገባ መንገድ የተገለገለበት በመሆኑ 2ኛ ከክስ፤- በመ/ቁጥር 256 የውል ይፈፀምልኝ የፍ/ር ክስ ጉዳይ ግራ ቀኙን አከራክረው 52.750 /ሃምሳ ሁለት ሺህ ብር ሰባት መቶ ሃምሳ ብርው) ተከሳሽ እንዲከፍል ወስነው አፈፃፀም ከሳሽ አፈፃፀም አቅርቦ አፈፃፀም ተከሳሽ በመገደዱ ንብረቱ በዋናው ዕዳ 50.000 ብር ተገምቶ በቀበሌ አስተዳደር በኩል ተስማምቶ ለአፈፃፀም ከሳሽ ያስረከበ ሲሆን ቀሪው እዳው እንደውሳኔው 2750 /ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ ብር ሁኖ ሳለ ዳኛው ከውሳኔው ውጪ የፍርድ አፈፃፀም ተከሳሽ ዕዳ 59750 /ሃምሳ ዘጠኝ ሲህ ሰባት መቶ ሃምሳ ብር/ በማድረግ የዲሲፕሊን ተከሳሽ 9750 /ዘጠኝ ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ ብር /በችሎቱ ተቀብሎ ለፍርድ አፈፃጸም ከሳሽ 9750 ብር እንደተቀበለ በመዝገቡ ላይ መዝግቦ መዝገቡን የዘጋ ሲሆን የፍርድ አፈፃፀም ከሳሽ ግን የተቀበለው 2750 /ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ ብር/ ብቻ ሲሆን ቀሪውን 7000/ሰባት ሺህ ብር በመጨመር ያጭበረበረና ለግሉ የተጠቀመ በመሆኑ ክሱን አቅርባል ተከሳሸ ክዶ በመከራከሩ ከሳሽ የዳኝነት ነፃነት ተጠያቂነት አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት የ04 ሰው እና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ ያሰማ ሲሆን ችሎቱም መርምሮ በ2ቱም ክስ ላይ እንዲከላከሉ በማዘዝ ተከሳሽ 2 የሰው መከላከያ ማስረጃዎች አቅርበው ያሰሙ ሲሆን የዲሲፕሊን ችሎቱም መርምሮ ተከሳሽ አልተከላከለም በሚል የጥፋተኝነት ፍርድ ሰጥቷል ::

በመቀጠልም የዲሲፕሊን ችሎቱም ከሳሽ የዳኝነት ነፃነት ተጠያቂነት አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት እና የተከሳሽን የቅጣት ማክበጃ አስተያየት እና የቅጣት ማቅለያ አስተያየት በመቀበል መርምሮ ከየካቲት 10 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ዳኛ ተካ ግርማ ከስራ እንዲሰናበት ወስናል :: በኤግዚቢትነት የቀረበው 40.000 ሺህ ብር በ1ኛ ክስ ላይ ላለው የግል ተበዳይ እንዲመለስ አዟል ፡፡
2. በዞኑ ፍርድ ቤቶች የሚሰሩ ረዳት ዳኞች እና ሬጅስትራሮች በተለያዩ ግዜያት ባቀረቡት የዝውውር ጥያቄዎችን አጀንዳ በማድረግ በቅርቡ በክልሉ ምክር ቤት ወደ ዳኝነት ሹመት የፈፀሙ በርካታ ረዳት ዳኞች እና ሬጅስትራሮች በመኖራቸው የተፈጠረውን ክፍተ ቦታዎች በዝውውር ለማስተካከል የታየ ሲሆን ያቀረቡት የዝውውር ጥያቄ እንደተቋሙ የሰው ሃይል እና ፍሰት በማየት በመደበኛ እና በልዩ ሁኔታ የቀረቡትን በመለየትና በማወዳደር ፤ ከማዕከል ወደ ምድብ ችሎት ፤ከምድብ ችሎት ወደ ማዕከል ፤ከወረዳ ወደ ወረዳ በአጠቃላይ 7 ባለሞያዎች ዝውውር እንዲያገኘኙ ወስኗል ::
በመቀጠልም ከምዕራብ ኦሞ ዞን በስምምነት ዝውውር ወደ ቤንች ሸኮ ዞን ለመምጣት ያመለከቱ 3 ባለሞያዎቸ (ዳኛ እና ረዳት ዳኛ ) የምዕራብ ኦሞ ዞን ዳኞች አስተዳደር በስምምነት የሚለቃቸው መሆን አለመሆኑን አጣርቶ ለመወሰን እንዲቻል ስምምነት እንዲጠየቅላቸው ወስኗል :: በቀሪ ክፍት መደቦች ላይ የሰራተኛ ቅጥር እንዲፈፀም ወስኗል ፡፡
3. በክልሉ ምክር ቤት 12 ዳኞች በሹመት የተመደቡ በመሆኑ ስራ ከመጀመራቸው በፊት የቅድመ-ስራ ኦረንቴሽን እና ውይይት ከ12ቱም ዳኞች ጋር የተደረገ ሲሆን አዳዲስ ዳኞች ስራቸውን በህግ እና በህግ ብቻ እንዲከውኑ ፤በታማኝነትና በትጋት እንዲሰሩ በአጠቃላይ ገለፃ ተደርጎላቸው የሥራ ስምሪት በመስጠት ተጠናቋል ፡፡

የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የሙስና ወንጀል ችሎት እነ ሙሉጌታ መሰረት በተከሰሱበት የሙስና ወንጀል ጥፋተኘነት እና  የቅጣት ውሳኔ ዛሬ ባስቻለው ችሎት ውሳኔ አሳለፈ በዞኑ ፍትህ መምሪያ...
22/01/2025

የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የሙስና ወንጀል ችሎት እነ ሙሉጌታ መሰረት በተከሰሱበት የሙስና ወንጀል ጥፋተኘነት እና የቅጣት ውሳኔ ዛሬ ባስቻለው ችሎት ውሳኔ አሳለፈ
በዞኑ ፍትህ መምሪያ ዐ/ህግ በተከሳሾች ላይ ክስ 1 /ሀ/፤የሙስና አዋጅ ቁጥር 881/07 አንቀፅ 9/1/ሀ/ እና /2/፤የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የመንግስት ሰራተኞች የሀገር ውስጥ የቀን ውሎ አበል ክፍያ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 3/2012 አንቀፅ 5/1/2/ ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ለደቡብ ቤንች ወረዳ ፍ/ቤት ከተመደበው በጀት ውስጥ ለስራ ማስኬጃ ከተመደበው በጀት ከሆነው ለተቋሙ ስራ ለማይገናኝ ዓላማ ለተቋሙ ሰራተኛ ላልሆኑት ነጋዴዎች 2013 እስከ 2016 ዓ/ም ብር 1,361,768 ብር አበል ክፍያ እንዲፈፀም በማድረግ ፤ ክስ 2 የሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/07 አንቀፅ 13/1/ሐ/ እና የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ህዝቦችና ክልል መንግስት ፕብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት የመንግስት ሰራተኞች ምልመላና መረጣ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 20/2011 አንቀፅ 5 እና 6 ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ 3 ግለሰቦች ከመመሪያ ውጭ ቅጥር መፈፀም እና ደመወዝ እንዲያገኙ ማድረግና 20,400 ብር በመንግስት ላይ ጉዳት ድረስ ፤ክስ 3 አዋጅ ቁጥር 881/07 አንቀፅ 9/1/ሀ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ ለግል መኖሪያ ቤቱ ጥቅሙ ዋይፋይ ሞደም ከገዛ በኋላ ከተቋሙ በጀት 16,735 ብር በማዋል እንዲወራረድ በማድረግ በመንግስት ላይ ጉዳት አድርሳል በሚል 1ኛ እና 2ተከሳሽ በተናጥል እና በጋራ ክሱን አቅርባል ተከሳሾች ክደው በመከራከራቸው ዐ/ህግ ሰው እና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ ያሰማ ሲሆን ችሎቱም መርምሮ በ1ኛ ክስ እና በሁለተኛ ክስ ላይ እንዲከላከሉ 3ተኛ ክስ ዐ/ህግ ያላስረዳ በመሆኑ በብይን ነፃ በማድረግ ወስኖ ተከሳችም የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎቻቸውን አቅርበው ያሰሙ ሲሆን ችሎቱም መርምሮ ተከሳሾች አልተከላከሉም በሚል የጥፋተኝነት ፍርድ ሰጥቷል ፡፡
በመቀጠልም ችሎቱ የዐ/ህግ እና የተከሳሾችን የቅጣት አስተያየት እና ቅጣት ማቅለያ ማስረጃዎችን በመቀበል መርምሮ ዛሬ ባስቻለው ችሎት 1ኛ ተከሳሽ ሙሉ ጌታ መሰረት በ6 /ስድስት/ ዓመት ፅኑ እስራት እና በብር 7‚500 /ሰባት ሺህ አምስት መቶ/ መቀጮ ፤ 2ተኛ ተከሳሽ ወ/ሪት ፈጠነች በዛብህ 5 ዓመት ከ6 ወር እና በብር 5‚500 /አምስት ሺህ አምስት መቶ/ የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስናል
በተጨማሪም 1ኛና 2ኛ ተከሳሾች በጋራ ሆነው አላግባብ ከአሰራር ውጪ በመንግስት ላይ ጉዳት እንዲደርስ ያደረጉትን ወይም ሌላ ሰው ያልተገባ ጥቅም እንዲያገኝ በጋራ ያደረጉት ገንዘብ በጠቅላላው ገንዘብ ብር 1,345,320/ አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ አርባ አምስት ሺህ ሶስት መቶ ሃያ/ ብር
እንዲሁም 2ኛ ተከሳሽ በተጨማሪ በኦዲቱ በተረጋገጠው ቀሪው ገንዘብ ብር 16‚448 /አስራ ስድስት ሺህ አራት መቶ አርባ ስምንት ላይ ኃላፊነት ያለባት ናት
ስለሆነም በተሻሻለው የፀረ-ሙስና ስነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 882/07 አንቀፅ 29/1/ለ/ እና 34/1/ መሰረት ይህን ገንዘብ ለመንግስት እንዲተኩ እንዲከፍሉ ወስኗል ፡፡

የቤንች ሸኮ ዞን ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ የወረዳ ፍ/ቤት ዳኞችን ለመቅጠር ባወጣዉ የቅጥር ማስታወቂያ መሰረት ተወዳዳሪዎች መዝግቦ መረጃዎች ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ...
10/01/2025

የቤንች ሸኮ ዞን ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ የወረዳ ፍ/ቤት ዳኞችን ለመቅጠር ባወጣዉ የቅጥር ማስታወቂያ መሰረት ተወዳዳሪዎች መዝግቦ መረጃዎች ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመላክ ከ40% የሰጠዉን የጹሁፍ ፈተና በመፈተን የተወዳዳሪዎችን ዉጤት ካሳወቀን በኃላ ከ40% የተሰጠዉን የጹሁፍ ፈተና ወስደዉ 20 እና ከ20 ነጥብ በላይ ያመጡትን 1ኛ ዙር እና 2ተኛ ዙር ተፈታኝ ተወዳዳሪች ተቀብለን ቀሪ ከ60% የሚሞላዉ ዉጤት በቤንች ሸኮ ዞን ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ዳኞች መልማይ እና መራጭ ኮሚቴ አማካኝነት ሲሰራ ቆይቶ መልማይ ኮሚቴዉ ጥር 01 ቀን 2017 ዓ/ም ስራዉን በማጠናቀቅ አቅርቧል ፡፡
የዞኑ ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጥር 01 ቀን 2017 ዓ/ም ባደረገው በ5ተኛ ዓመት 2ተኛ ዙር 6ተኛ አስቸኳይ ጉባኤ የቀረበዉ ሪፖርት ተመልክቶ ከጠቅላላ 14 ተወዳዳሪዎች መካከል በስር ፍርድ ቤቶች ባለዉ ክፍት መደብ ተወዳዳሪዎች ከመንግስት አካላት ፤ከህዝብ አደረጃጀትና ፤ከህግ ባለሙያዎች ፤ከባልደረባዎች እንዲሁም ጉባኤው በተጨማሪ ባጣራው ማጣራት መሰረት ከቀረቡለት 14 ዕጩ ዳኞች ውስጥ 12 በመቀበል ወስኗል
ቀጣዩ ፎርማሊቲ እንዲሟላ በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ህገ-መንግስት አንቀጽ 89 ንሑስ አንቀጽ 8 መሰረት ለሚመለከተዉ የዞኑ መንግስት አካል ዝርዝራችሁን ያስተላለፍን መሆኑን እየገለፅን ለተወዳዳሪዎች ያገኛችሁት ዉጤት እና ጉባኤዉ ከላይ ያስተላለፈዉ ዉሳኔ በወረዳ ፍርድ ቤት ተሹሞ መስራት ለሚፈልግ አንድ ተወዳዳሪ መጨረሻ እና የተሟላ መስፈርት ያለመሆኑ አዉቃች ሁለ ቀሪ ለመስፈርቶች ብቁ መሆናችሁ ተረጋግጦ በክልሉ ምክር ቤት ፊት ቀርባችሁ ሹመታቸዉ ሲጸድቅ ብቻ የወረዳ ፍርድ ቤት ዳኛ መሆናችሁ የሚረጋገጥ መሆኑ እናሳስባለን፡፡

Address

Bench Shako Zone Administration Office
Mizan Teferi

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bench Sheko Zone High Court posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share