02/01/2026
መንግስት ደመውዝ ስጨምርልን ምንም ዓይነት የዋጋ ንረት እንዳይኖር ይደረጋል ብሎ ነበር። ነገር ግን ቀድሞ ዋጋ መጨመር ያሳያው #የመንግስት #ባንክ(የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ከዛም በኋላ #ኢትዮ #ቴሌኮም ጨመረ። አሁንም ቢሆን በመንግስት ሠራተኞች ጫናው በርትቷል።
#የደሞወዝ ጭማረዉን ምክንያት በማድረግ ኢትዮ-ቴሌኮም 25% የታርፍ ጭማሪ አደረገ። ይገርማል!!!! መንግስት እንደቀላል ሊታዘበው እና ዝም ሊለው የሚገባ ጉዳይ አይደለም። ምክኒያቱም ነጋዴዎች ይሄን ተከትለው በሁሉም ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ ቢያደርጉ ምንም አይገርመኝም። ምክኒያም አሁን በምንመለከታቸው ሁኔታዎች በኢትዮጵያ ውስጥ /ድሃ / ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ የማህበረሰብ ከፍሎች ያማራቸውን ምግብ መብላት እና ስልክ መያዝ፣ መጠቀም የተፈቀደላቸው አይመስለኝም። ኧረ በጣም ይገርማል። መንግስት መጀመሪያ እንደዚህ አይነት ጭማሪዎችን ከመፍቀዱ በፊት ወደ ማህበረሰቤ ያለው በምን ደረጃ ነው።ብሎ ወደ ታች ቢወርድ እና የማህበራሰቡን ሁኔታ በመለከት ምን አለበት። ይሄ ሲጨንቃቸው በጦስ ላይ ጦስ አሉ ያገሬ ሠዎች እንግዲህ የአባይ ግድብ ተመርቋል። መብራ በነፃ መጠቀም እንጀምራለን ።ለሌሎች ሀገሮችም እናከራያለን የሚባሎው ነገር ቅዠት ነው።እስሚባል ድረስ የመብራት ኪሎ ዋት /KWT/ መጨመሩ ያስገርመናል። ለዚህ ሁሉ ጦስ ተጠያቂ እና ድሃን በማፈናቀል የበሠ ወንጀል እየሠራ መሆኑ ያልታወቀው መንግስት ሀገር ወዳድ ትውልድን እየፈራ እንዳልሆነ እና ከሀገሩ ይልቅ ስደትን የሚመርጥ ትውልድን እያፈራ መሆኑን ልገልፅላቹህ አወዳሎህ ። እናንተስ ምን ሀሳብ አላቹህ????
ለሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች እንዲደርስ link በማድረግ ለመጪው ትውልድ በጎ ሰራዎችን እንስራ። አመሰግናሎሁ !!!!